ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵


ክፍል ፵

ጥር ፮፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለሲድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። ይህ እራይ ከመመዝገቡ ቀደም ብሎ፣ የነቢዩ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ “ጄምስ [ኮቪል] የጌታን ቃል ስላልተቀበለ እና ወደ ቀድሞው መሰረታዊ መርሆችና ሰዎች ስለተመለሰ፣ ጌታ ለእኔ እና ለስድኒ ሪግደን ተከታዩን ራዕይ ሰጠን” (ክፍል ፴፱ን ተመልከቱ)።

፩–፫፣ የስደት ፍራቻ እና ለአለም መጨነቅ ወንጌልን አለመቀበልን ያመጣል።

እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን ለመታዘዝ ቃል ኪዳንን ስለገባ፣ የአገልጋዬ የጄምስ ኮቪል ልብ በፊቴ መልካም ነበር።

እናም ቃሉን በደስታ ተቀበለ፣ ነገር ግን ወዲያውኑ ሰይጣን ፈተነው፤ እናም የስደት ፍራቻና ለአለም መጨነቅ ቃሉን እንዳይቀበል አደረገው።

ስለዚህም ቃል ኪዳኔን አፈረሰ፣ እናም መልካም የመሰለኝን በእርሱ ላይ አደርግ ዘንድ ፍቃዴ ነው። አሜን።