ክፍል ፶፫
በሰኔ ፰፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለአልጀርኖን ስድኒ ጊልበርት የተሰጠ ራዕይ። በስድኒ ጊልበርት ጥያቄ ምክንያት፣ ነቢዩ ስለወንድም ጊልበርት የቤተክርስቲያን ስራና ሀላፊነት ጌታን ጠየቀ።
፩–፫፣ የስድኒ ጊልበርት የቤተክርስቲያን ጥሪ እና ምርጫ እንደ ሽማግሌ እንዲሾም ነው፤ ፬–፯፣ እርሱም እንደ ኤጲስ ቆጶስ ወኪል እንዲያገለግልም ነው።
፩ እነሆ፣ አገልጋዬ ስድኒ ጊልበርት፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ ጸሎቶችህን ሰምቼአለሁ፤ እኔ ጌታ በኋለኛው ቀናት ባነሳኋት በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለህን ጥሪና ምርጫ እውቀት ይሰጥህ ዘንድ እኔ፣ ጌታ አምላክህን፣ ጠይቀሀል።
፪ እነሆ፣ ለአለም ኃጢአት የተሰቀልኩ እኔ ጌታ አለምን እንድትተው ትእዛዝን እሰጥሀለሁ።
፫ በቃሌ በኩል፣ እምነትን እና ንስሀ መግባትን እና ለኃጢአቶች ስርየት እና እጆችን በመጫን መንፈስ ቅዱስን መቀበልን ለመስበክ፣ የሽማግሌነት ሹመቴን በራስህ ላይ ተቀበል፤
፬ እናም ከዚህ በኋላ በሚሰጠው ትእዛዝ፣ ኤጲስ ቆጶሱ በሚመድብበት ስፍራም ለዚህች ቤተክርስቲያን ወኪል እንድትሆንም ነው።
፭ እና ደግሞም፣ በእውነት እልሀለሁ፣ ከአገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እና ከስድኒ ሪግደን ጋር ተጓዝ።
፮ እነሆ፣ እነዚህም የምትቀበላቸው የመጀመሪያ ስነ ስርዓቶች ናቸው፤ እና በወይን ስፍራዬ ውስጥ ባገለገልክ መጠን፣ ቅሪቶቹም በሚመጣው ጊዜ ይገለጣሉ።
፯ እና ደግሞም፣ እስከ ፍጻሜው የሚጸና እርሱ ብቻ እንደሚድን እንድትማርም እፈልጋለሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።