ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፷፮


ክፍል ፷፮

ጥቅምት ፳፱፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሂራም ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ውልያም ኢ መክለለን ለነበሩት አምስት ጥያቄዎች መልስ በነቢዩ በኩል በሚስጥር እንዲመልስለት ጌታን ጠይቆ ነበር፣ እነዚህም ለጆሴፍ ስሚዝ የታወቁ አልነበሩም። በመክለለን ጥያቄ፣ ነቢዩ ጌታን ጠየቀ እና ይህን ራዕይ ተቀበለ።

፩–፬፣ የወንጌሉ ሙሉነት ዘለአለማዊው ቃል ኪዳን ነው፤ ፭–፰፣ ሽማግሌዎች ይስበኩ፣ ይመስክሩ፣ እናም ከህዝብም ጋር ይወያዩ፤ ፱–፲፫፣ ታማኝ የወንጌል አገልግሎትም የዘለአለም ህይወትን ውርስ ያረጋግጣል።

እነሆ፣ ጌታ ለአገልጋዬ ውልያም መክለለን እንዲህ ይላል—ከኃጢአቶችህ ዞር እስካልህ ድረስ፣ እና እውነቴን እስከተቀበልህ ድረስ የተባርክ ነህ፣ እንዲሁም በስሜ የሚያምኑት ሁሉ፣ ይላል ጌታ ቤዛህ፣ የአለም አዳኝ።

እውነት እልሀለሁ፣ ዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን፣ እንዲሁም በነቢያት እና ሐዋርያት በቀደሙት ቀናት እንደተጻፈው፣ ህይወት እንዲኖራቸው እና በመጨረሻዎቹም ቀናት የሚገለጡትን ክብሮች ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ፣ ወደሰው ልጆች የተላከውን የወንጌሌን ሙሉነት በመቀበልህ የተባረክህ ነህ።

በእውነትም እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ውልያም ሆይ፣ አንተ፣ በሁሉም ባይሆን፣ ንጹህ ነህ፤ ስለዚህ በፊቴ ለማያስደስቱኝ ነገሮች ንስሀ ግባ፣ ጌታ እነዚህን ያሳይሀልና

እናም አሁን፣ በእውነትም፣ እኔ ጌታ ስለአንተ በመመልከት ያለኝን ፈቃዴን፣ ወይም አንተን በተመልከተ ፈቃዴን አሳይህ ዘንድ እሻለሁ።

እነሆ፣ በእውነትም እልሀለሁ፣ ከስፍራ ወደ ስፍራ፣ እና ከከተማ ወደ ከተማ፣ አዎን፣ ባልታወጁበት አካባቢዎች ውስጥ ሁሉ ወንጌሌን ታውጅ ዘንድ ፍቃዴ ነው።

በዚህ ስፍራ ለብዙ ቀናት አትቆይ፤ ወደ ፅዮን አገርም ገና አትሂድ፣ ነገር ግን፣ ለመላክ የምትችለውን ላክ፤ አለበለዚያም፣ ስለ ንብረቶችህ አታስብ።

ወደ ምስራቅ ባሉ ምድሮችም ተጓዝ፣ በእያንዳንዱም ስፍራዎች፣ ለእያንዳንዱም ሰው እናም በየምኩራቦቻቸው፣ ከህዝብ ጋር እየተወያየህ፣ ምስክርነትህን ስጥ።

አገልጋዬ ሳሙኤል ኤች ስሚዝም አብሮህ ይሂድ፣ እናም አትተወው፣ እናም አስተምረውም፤ እናም ታማኝ የሆነውም እርሱ በሁሉም ስፍራ ጠንካራ ይሆናል፤ እና እኔ ጌታም ከአንተ ጋር እሄዳለሁ።

በታመሙትም ላይ እጆችህን ጫን፣ ይድኑማል። እኔ ጌታ እስከምልክህ ድረስም አትመለስ። በስቃይህም ትእግስተኛ ሁን። ለምን፣ እናም ይሰጥሀል፤ አንኳኳ፣ ይከፈትልህማል።

ብኩንነትን አትሻ። ከፅድቅ ያልሆኑውን ሁሉ ተው። የተፈተንህበትን አመንዝራትን አትፈጽም።

፲፩ እነዚህ ያዘዝኩህን ጠብቅ፣ እውነት እና ታማኝ ናቸውና፤ እናም ሀላፊነትህን ታጎላለህ፣ እናም የዘለአለም ደስታ መዝሙሮች በራሳቸው ላይ ሆኖ ብዙ ህዝብን ወደ ፅዮን ትገፋለህ።

፲፪ እስከመጨረሻውም በእነዚህ ነገሮች ፅና፣ እናም በጸጋ እና በእውነት በተሞላው በአባቴም ቀኝ በኩልም የዘለአለም ህይወት አክሊል ይኖርሀል።

፲፫ በእውነትም፣ እንዲህ ይላል ጌታ እግዚአብሔርህ፣ ቤዛህ፣ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ። አሜን።