ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፹፭


ክፍል ፹፭

በህዳር ፳፯፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ክፍል በእንድፐንደንስ ሚዙሪ ውስጥ ለሚኖረው ዊልያም ደብሊው. ፌልፕስ ነቢዩ ከጻፈው ደብዳቤ ውስጥ የተውጣጣ ምንባብ ነው። ይህም የተሰጠው ወደፅዮን ቢሄዱም፣ ንብረቶቻቸውን እንዲቀድሱ የሚያዘውን ትዝዛዝ ያልተከተሉና በዚህም ምክንያት በተመሰረተው በቤተክርስቲያኗ ህግጋት መረሰት ውርሳቸውን ያልተቀበሉት ቅዱሳንን ጥያቄ ለመመለስ ነበር።

፩–፭፣ በፅዮን ውስጥ ውርሶች የሚገኙት በቅድስና በኩል ነው፤ ፮–፲፪፣ ኃያል እና ብርቱ የሆነው ብቻ ለቅዱሳኑ ውርስን በፅዮን ውስጥ ይሰጣል።

እርሱ የመደበው የጌታ ሂሳብ ሰራተኛ ሀላፊነትም፣ ታሪክን ለመጠበቅ፣ እና በፅዮን የሚደረጉትን ሁሉንም ነገሮች፣ እና ንብረቶቻቸውን የቀደሱትን ሁሉ፣ እና ከኤጲስ ቆጶሱ ውርስን በህግ የሚቀበሉትን የአጠቃላይ የቤተክርስቲያኗን መዝገብ ለመጠበቅ ነው።

ደግሞም አኗኗራቸውን፣ እምነታቸውን፣ እና ስራቸውን፤ እና ደግሞም ውርሶቻቸውን ከተቀበሉ በኋላ የሚያምጹትን ከሀዲዎችን መዝገብ ለመጠበቅ ነው።

ህዝቦቹን አስራት በማስከፈል፣ እነርሱን ለበቀል እና ለመቃጠል ቀን ለማዘጋጀት፣ በሰጣቸው ህጉ ተስማሚ በሆነው፣ ውርሶቻቸውን በቅድስና የማይቀበሉት ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር ስማቸው መመዝገቡ ከእግዚአብሔር ፈቃድ እና ትእዛዝ ጋር የሚቃረን ነው።

የትውልድ ሐረጋቸውም አይጠበቅ፣ ወይም በቤተክርስቲያኗ መዝገብ ወይም ታሪክ ውስጥ የሚገኝ አይሁን።

ስሞቻቸውም ወይም የአባቶቻቸው ስሞች፣ ወይም የልጆቻቸው ስሞች በእግዚአብሔር ህግጋት መፅሐፍ ውስጥ ተፅፈው አይገኙም፣ ይላል የሰራዊት ጌታ።

አዎን፣ በሁሉም ነገሮች በለሆሳስ የሚናገር እና ሰንጥቆ የሚገባው፣ እናም ይህን ሲገልፅም አጥንቶቼን የሚያንቀጠቅጥ፣ አነስተኛ ለስላሳ ድምፅም እንዲህ ይላል፥

እናም እንዲህ ይሆናል፣ እኔ ጌታ አምላክ የሀይልን በትር በእጁ የያዘ፣ ብርሀንን እንደልብስ የለበሰ፣ አንደበቱም ቃላትን፣ እንዲሁም ዘለአለማዊ ቃላትን፣ የሚናገር፣ ኃያል እና ብርቱ እልካለሁ፤ አንጀቱም፣ የእግዚአብሔርን ቤት ለማስተካከል፣ እና ስማቸው እና የአባቶቻቸው እና የልጆቻቸውም ስም በእግዚአብሔር ህግ መፅሐፍ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙትን ቅዱሳን ውርሶቻቸውን በእጣ ለማደራጀት የእውነት ምንጭ ይሆንላቸዋል፤

በእግዚአብሔር ተጠርቶ የተመደበው፣ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት የያዘ ሰው፣ በመብረቅ እንደተመታ ዛፍ፣ በፍላጻ ሞት ይወድቃል።

እናም በመታሰቢያ መጽሐፍ ውስጥ ተፅፈው የማይገኙት ሁሉ በዚያ ቀን ምንም ውርስ አያገኙም፣ ነገር ግን ለሁለትም ይሰነጥቃቸዋል፣ ውርሶቻቸውም ከማያምኑት ጋር ያደርግባቸዋል፣ በዚያም ዋይታና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

የምላቸው እነዚህ ነገሮች ከእኔ አይደለም፤ ስለዚህ፣ ጌታ እንደተናገረው እንዲሁ ደግሞ ይፈጽመዋል።

፲፩ እናም፣ በህግ መፅሐፍ ውስጥ ስሞቻቸው ተፅፎ የማይገኙት ወይም በአመጻ የሚገኙት፣ ወይም ከቤተክርስቲያኗ የተቆረጡት የታላቅ ክህነት ክፍል የነበሩት፣ እና የአነስተኛው ክህነት፣ ወይም አባላት፣ በዚያ ቀን በልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን መካከል ውርሳቸውን አያገኙም፤

፲፪ ስለዚህ፣ በዕዝራ በምዕራፍ ሁለት በስልሳ አንደኛ እና ሁለተኛ አንቀጾች ውስጥ እንደሚገኘው፣ ለእነርሱም ለካህናት ልጆች እንደተደረገው ይደረግባቸዋል።