የታላቅ ዋጋ ዕንቁ የርዕስ ገፅ መግቢያየታላቅ ዋጋ ዕንቁ መፅሐፍ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እምነትና ትምህርትን የሚዳስሱ ተመራጭ መረጃዎችን የያዘ ነው። እነዚህ መረጃዎች በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ተተርጉመውና ተሰርተው፣ እናም አብዛኛዎቹ በጊዜው በቤተክርስቲያኗ ጋዜጣዎች ታትመው ነበር። ሙሴ ሙሴ ፩እግዚአብሔር እራሱን ለሙሴ ገለጠ—ሙሴ ተለወጠ—እርሱም ከሰይጣን ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጠ—ሙሴ ብዙ ሰው የሚኖርባቸው አለማትን አየ—ቁጥራቸው ታላቅ የሆኑ አለማት በወልድ ተፈጥረው ነበር—የእግዚአብሔር ስራና ክብር የሰውን ህያውነትና ዘለአለማዊ ህይወትን ማምጣት ነው። ሙሴ ፪እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ—የተለያዩ አይነት ፍጥረታት ተፈጠሩ—እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ እና በሁሉም ነገሮች ላይ ግዛትን ሰጠው። ሙሴ ፫እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች በፍጥረታዊ አካል ከመፍጠሩ በፊት መንፈሳዊ አካል ፈጥሯቸዋል—በመጀመሪያ ሰውን፣ መጀመሪያ ስጋን፣ ፈጠረ—ሴትም ለወንድ ረዳት ነች። ሙሴ ፬እንዴት ሰይጣን ዲያብሎስ እንደሆነ—ሰይጣን ሔዋንን ፈተነ—አዳምና ሔዋን ወደቁ፣ እናም ሞት ወደ ምድር መጣ። ሙሴ ፭አዳምና ሔዋን ልጆችን ወለዱ—አዳም መሥዋዕት አቀረበ፣ እግዚአብሔርንም አገለገለ—ቃየንና አቤል ተወለዱ—ቃየን አመጸ፣ ሰይጣንንም ከእግዚአብሔር በላይ ወደደ፣ እናም የጥፋት ልጅ ሆነ—ገዳይነትና ክፉነት ተስፋፋ—ወንጌሉም ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ የተሰበከ ነው። ሙሴ ፮የአዳም ዘር የመታሰቢያ መፅሐፍን ጻፉ—ጻድቅ ዝርያዎቹ ንስሐን ሰበኩ—እግዚአብሔር ለሔኖክ ራሱን ገለጠ—ሔኖክ ወንጌሉን ሰበከ—የደህንነት እቅድም ለአዳም ተገልጦ ነበር—ጥምቀትንና ክህነትን ተቀበለ። ሙሴ ፯ሔኖክ ሕዝብን አስተማረ፣ መራ፣ እና ተራሮችንም አንቀሳቀሰ—የጽዮን ከተማም ተቋቋመ—ሔኖክ የሰው ልጅ መምጣትን፣ የኃጢአት ክፍያ መስዋዕቱን፣ እና የቅዱሳንን ትንሳኤን አስቀድሞ አየ—ዳግሞ መመለስን፣ መሰብሰብን፣ የክርስቶስን ዳግም ምፅዓት፣ እና የፅዮንን መመለስ አስቀድሞ አየ። ሙሴ ፰ማቱሳላ ተነበየ—ኖህና ልጆቹ ወንጌልን ሰበኩ—ታላቅ ጥፋት በዛ—ወደ ንስሀ መጠራትም አልተሰማም—እግዚአብሔርም ሰጋዎችን በሙሉ በጥፋት ውሀ ለማጥፋት አወጀ። አብርሐም አብርሐም ፩አብርሐም የፔትሪያርካዊ ስርዓት በረከትን ፈለገ—በከላውዴዎ ውስጥ በሐሰት ቀሳውስት ተንገላታ—ያህዌህ አዳነው—የግብፅ ጅማሬ መንግስትም ተከለሰ። አብርሐም ፪አብርሐም ከዑር ወጥቶ ወደ ከነዓን ሄደ—ሀራን ውስጥም ያህዌህ ተገለጠለት—የወንጌል በረከቶችም ሁሉ ለዘሮቹና በዘሩም በኩል ለሁሉም ቃል ተገብተዋል—ወደከነዓንና ወደ ግብፅ ሄደ። አብርሐም ፫አብርሐም ስለጸሀይ ጨረቃና ከዋክብት በኡሪምና ቱሚሙን መሰረት ተማረ—ስለመንፈሶች ዘለአለማዊነት ጌታ ገለጠለት—ከምድር በፊት ስለነበረው ህይወት፣ ስለቀድሞ መመረጥ፣ ስለፍጥረት፣ ስለአዳኝ ምርጫ፣ እና ስለሰው ዳግመኛ ሁኔታ ተማረ። አብርሐም ፬አማልክት ምድርንና በዚያም ህይወቶችን በሙሉ ለመፍጠር አቀዱ—በስድስት ቀን የመፍጠሪያ እቅዳቸው ተዘርዝረዋል። አብርሐም ፭አማልክቱ ሁሉንም ነገሮች ለመፍጠር እቅዳቸውን ጨረሱ—እንደ እቅዳቸውም ፍጥረታቸውን አከናወኑ—አዳም ሁሉንም ህያዋን ፍጡራንን ስም ሰጠ። ቅርፅ ፩ ቅርፅ ፪ ቅርፅ ፫ ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ ፩ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት አስቀድሞ ነገራቸው—ስለሰው ልጅ ስለክፉው መጥፊያ ዳግም ምፅዓት፣ እና ስለክፉዎች ጥፋት አስተማረ። የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ ፩ጆሴፍ ስለትውልዱ፣ ስለቤተሰብ አባላቱ፣ እና ከጊዜው ቅድሚያ መኖሪያቸው ተናገረ—በምዕራብ ኒው ዮርክ ውስጥ ልዩ በሀይማኖት መነሳሳት ተሰራጨ—በያዕቆብ እንደተመራው ጥበብን ለመፈለግ ወሰነ—አብና ወልድ ታዩት፣ እና ጆሴፍ ወደነብያዊ አገልግሎቱ ተጠራ። (አንቀፅ ፩–፳።) የእምነት አንቀጾች የእምነት አንቀጾች ፩በዘለአለማዊ አባት እግዚአብሔር፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን።