ምዕራፍ ፫
[ሰኔ–ጥቅምት ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)]
እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች በፍጥረታዊ አካል ከመፍጠሩ በፊት መንፈሳዊ አካል ፈጥሯቸዋል—በመጀመሪያ ሰውን፣ መጀመሪያ ስጋን፣ ፈጠረ—ሴትም ለወንድ ረዳት ነች።
፩ እንደዚህም ሰማይና ምድር፤ በውስጣቸውም ያሉት ሰራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።
፪ እና እኔ እግዚአብሔር ስራዬን፣ እና ያደረግኳቸውን ነገሮች ሁሉ፣ በሰባተኛው ቀን ፈጸምኩኝ፣ እና ከምሰራው ስራ ሁሉ በሰባተኛው ቀን አረፍኩኝ፣ እና ሁሉም ያደረኳቸው ተፈጸሙ፣ እና እኔ እግዚአብሔር እነርሱ መልካም እንደሆኑም አየሁ፤
፫ እና እኔ እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረኩት፣ ቀደስኩትም፤ እኔ እግዚአብሔርም ካደረግኳቸው እና ከመፍጠር ስራዬ ሁሉ ያረፍኩት በሰባተኛው ቀን ነውና።
፬ አሁንም እነሆ እንዲህ እልሀለሁ፣ በተፈጠሩበት፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በሰራሁበት በዚያ ቀን፣ እነዚህም የሰማይና የምድር ትውልዶች ናቸው።
፭ እናም የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመተከሉ በፊት፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ በምድር ላይ ከመብቀሉ በፊት የተፈጠሩ ናቸው። እኔ እግዚአብሔር አምላክም የተናገርኩባቸውን ነገሮች ሁሉ ከምድር ፊት በፍጥረታዊ አካል ከመፈጠራቸው በፊት በመንፈሳዊ አካል ፈጥሬአቸዋለሁና። እኔ እግዚአብሔር አምላክም በምድር ላይ ገና ዝናብ አላዛነብኩምና። እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም የሰውን ልጆችን ሁሉ ፈጥሬአለሁ፤ እና ምድርን የሚያለማ ሰው ግን አልነበረም፣ በሰማይ ውስጥ ፈጥሬአቸዋለሁና፤ እና በምድር ላይ ምንም ስጋ፣ ወይም ውሀ፣ ወይም አየር አልነበረም።
፮ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላክም ተናገርኩኝ፣ ጉም ከምድር ወጣ፣ የምድርንም ፊት ሁሉ አጠጣ።
፯ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር ዐፈር አበጀሁኝ፣ በአፍጫውም የህይወትን አስተንፋስ እፍ አልኩበት፤ እና ሰውም ህያው ነፍስ፣ በምድረም ላይ የመጀመሪያ ስጋ፣ ደግሞም የመጀመሪያም ሰው ሆነ፤ ይህም ቢሆን፣ ሁሉም ነገሮች በፊት ነበር የተፈጠሩት፤ ነገር ግን በቃላቴ በኩል እንደመንፈሳዊነት ነበር የተደረጉትና የተፈጠሩት።
፰ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም በዔድን ውስጥ በምስራቅ ገነትን ተከልኩኝ፤ የፈጠርኩትንም ሰው በዚያ አኖርኩት።
፱ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን ዛፍ በተፍጥሮ አበቀልኩኝ፤ እና ሰውም ሊያየው ይችላል። እናም ይህም ህያው ነፍስም ሆነ። ይህን በፈጠርኩበት ጊዜ መንፈሳዊ ነበር፤ እኔ እግዚአብሔር በመላው ግዛቴ በፈጠርኩት፣ አዎን፣ ሁሉንም ነገሮች ሰው እንዲጠቀምባቸው ባዘጋጀኋቸው፣ ውስጥ ቀርተዋልና፤ እና ሰው ይህም ለምግብ ጥሩ እንደሆኑ አየ። እኔ እግዚአብሔር አምላክም በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፣ እና ደግሞም መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ ተከልኩኝ።
፲ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክ፣ ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ዘንድ አደረግሁኝ፤ እናም በአራት ክፍል ይከፈል ነበር።
፲፩ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክ የመጀመሪያውን ፊሶን ብዬ ጠራሁት፣ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክ ብዙ ወርቅ በፈጠርኩበት የኤውላጥን ምድር የሚከብብ ነበር፤
፲፪ እና የዚያም ምድር ወርቅም ጥሩ ነበር፣ እና ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኝ ነበር።
፲፫ እና የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነበር፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብብ ነበር።
፲፬ እና የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነበር፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነበር። እና አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነበር።
፲፭ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስጄ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አስቀመጥኩት።
፲፮ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ በማለት አዘዝኩት፥ ከገነት ዛፍ ሁሉ ለመብላት ነጻ ነህ፤
፲፯ ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቅህ ዛፍ አትብላ፤ ቢሆንም ለአንተ ሰለተሰጠህ ለራስህ መምረጥ አለብህ፣ ለአንተ ተሰጥቶሀልና፤ ነገር ግን፣ እንደከለከልኩህ አስታውስ፣ ምክንያቱም ከእርሱም በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህና።
፲፰ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም አንድያ ልጄ እንዲህ አልኩት፣ ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም፤ ስለዚህ ረዳት እንፍጠርለት።
፲፱ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሰራሁ፣ እናም ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንዲያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም እንዲሄዱ አዘዝኩኝ፤ እናም እነርሱም ሕያው ነፍስ ነበሩ፤ እኔ እግዚአብሔር የህይወት አስተንፋስ እፍ ብዬላቸዋለሁና፣ እና አዳምም ሕያው ነፍስ ያለውን ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ እንዲሆንም አዘዝኩኝ።
፳ እና አዳም ለእንስሳት፣ ለሰማይ ወፎች፣ እና ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር።
፳፩ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍን ጣልኩበት፣ አንቀላፋም፣ እና ከጎኑ አንዲት አጥንት ወሰድኩና ስፍራውንም በስጋ ዘጋሁ።
፳፪ እና እኔ እግዚአብሔር አምላክም ከወንዱ የወሰድኩትን ዐጥንት ሴት አድርጌ ሰራኋት፣ እናም ወደ አዳምም አመጣኋት።
፳፫ አዳምም እንዲህ አለ፥ ይህች አጥንት ከአጥንቴ፣ ስጋዋም ከስጋዬ ናት፣ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።
፳፬ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፣ ከሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ።
፳፭ አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፤ እና አይተፋፈሩም ነበር።