ከመፅሐፈ አብርሐም ቅርፅ ቁጥር ፫ መግለጫ ስዕል ፩ በንጉሱ ትሁትነት፣ አብርሐም የሰማይ ታላቅ አመራር አርማ የሆነውን ክህነት የሚወክለውን ዘውድ በራሱ ላይ ተደርጎለት፣ የፍርድና የፍትሕ በትረ መንግስት በእጁ ይዞ፣ በፈርዖን ዙፋን ላይ ተቀምጦ። ስዕል ፪ ስሙ በፊደል ከራሱ በላይ የተጻፈለት ንጉስ ፈርዖን። ስዕል ፫ በስዕል ፲ ላይ እንደተሰጠው አብርሐም በግብፅ ውስጥ የሚያስመለክት። ስዕል ፬ ከእጅ በላይ እንደተጻፈው፣ የግብፅ ንጉስ ፈርዖን ልዑል። ስዕል ፭ ከእጁ በላይ በፊደል በተጻፈው እንደሚወከለው፣ የንጉሱ ዋና አስተናጋጅ ሹለም። ስዕል ፮ የልዑሉ ንብረት ባሪያ ኦሊምላኽ። አብርሐም በንጉሱ አደባባይ ውስጥ ስለ ስነ ፈለክ ጥናት መሰረታዊ መርሆች ሲሟገት።