ከመፅሐፈ አብርሐም ቅርፅ ቁጥር ፪ መግለጫ ስዕል ፩ ይህ የመጀመሪያውን ፍጥረትና ከሰለስቲያል ወይም ከእግዚአብሔር መኖሪያ አጠገብ ያለው ቆሎብ ነው። የመጀመሪያው በመንግስት ውስጥ፣ የመጨረሻውም ከሰአት መለኪያ ጋር ግንኙነት ያለው ነው። በሰለስቲያል ሰአትም አንድ ቀንን ከክንድ ጋር ያመዛዝናቸው፣ በሰለስቲያል ጊዜ መሰረት መለኪያ። አንድ ቀን በቆሎብ በዚህ አለም አቆጣጠር መሰረት፣ በግብጻውያን ጃሆህኸ እንደሚባለው፣ አንድ ሺህ አመታት ጋር እኩል ነው። ስዕል ፪ ለጌታ በሰራው በመሰዊያ ላይ መስዋዕት ሲያደርግ ለአብርሐም ከእግዚአብሔር የተገለጠለት፣ በግብጻውያን ኦሊብሊሽ ተብሎ የሚጠራው፣ በሰለስቲያል ወይም እግዚአብሔር በሚኖርበት ስፍራ አጠገብ የሚገኘው የሚቀጥለው ታላቅ ፍጥረት፤ ከሌሎች አለማት ጋር በመገናኘት፣ ደግሞም የሀይል ቁልፍን የያዘ። ስዕል ፫ የዘለአለማዊ ብርሃን ዘውድ በራሱ ላይም ተደርጎ፣ እግዚአብሔር በሀይልና በስልጣን ተሸፍኖ በዙፉን ላይ ተቀምጦ ለማሳየት ነው፤ በዔድን ገነት ውስጥ ለአዳም፣ ደግሞም ለሴት፣ ለኖህ፣ ለመልከ ጼዴቅ፣ ለአብርሐም ክህነት ተገልጦላቸው ለነበሩት ሁሉ የተገለጠውን የቅዱሱ ክህነት ታላቁ ቁልፍ ቃላትን የሚወክል ነው። ስዕል ፬ ጠፈርን፣ ወይም የሰማያት ጠፈርን በማስመልከት ራኡኪያንግ ለእብራውያን ቃል መልስ የሚሰጥ፤ ደግሞም በግብጻዊ አንድ ሺ የሚል ቁጥር ስዕል፤ በቆሎብ መዞሪያና ከሰአት መለኪያ ጋር አንድ የሆነው፣ ኦሊብሊሽ ለሚባለው ሰአት መለኪያ መልስ የሚሰጥ ነው። ስዕል ፭ በግብጻዊ ቋንቋ እኒሽ-ጎ-ኦን-ዶሽ ተብሎ ይጠራል፤ ይህ ደግሞም ከመሪ አለማት አንዱ ነው፣ በግብጻውያን ጸሀይ፣ እና ከቆሎብ ታላቅ ቁልፍ በሆነው ወይም በሌላ ቃላትም አስራ አምስት ሌሎች የማይነቃነቁ አለማትን ወይም ከዋክብትን፣ ደግሞም እንደ ፍሎኢስ ወይም ጨረቃ፣ ምድርና ጸሃይን በአመታዊ መዘዋወራቸው የሚመራ ገዢ ሀይል በኬ-ር-ቫንራሽ በኩል ብርሃኑን የሚዋስ ነው። ይህ አለም ሃይሉን የሚያገኘው በክሊ-ፎሎስ-ኢስ-እስ፣ ወይም በሀ-ኮ-ኮ-ቢም በኩል ነው፣ በቁጥር ሀያ ሁለትና ሀያ ሶስት የሚወከሉት ከዋክብት ብርሃንን የሚቀበሉት በቆሎብ መዘዋወሪያዎች ነው። ስዕል ፮ ይህም ምድርን በአራት የምድር መዓዘናት ይወክላል። ስዕል ፯ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ በሰማይ የክህነት ታላቅ ቁልፍ-ቃላት በኩል መገለጥን ይወክላል፤ ደግሞም፣ በርግብ አምሳል ለአብርሐም የተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ምልክት። ስዕል ፰ ለአለም ሊገለጽ የማይቻል ጽህፈት ያለበት፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ቅዱስ ቤተመቅደስ የሚገኝ ነው። ስዕል ፱ በዚህ ጊዜ መገለጥ የለበትም። ስዕል ፲ ይህኛውም። ስዕል ፲፩ ይህኛውም። አለም እነዚህ ቁጥሮችን ለማግኘት ከቻሉ፣ እንዲህም ይሁን። አሜን። ሰእሎች ፲፪፣ ፲፫፣ ፲፬፣ ፲፭፣ ፲፮፣ ፲፯፣ ፲፰፣ ፲፱፣ ፳፣ ፳፩ እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ ይሰጣሉ። ከዚህ በላይ ያሉትን ትርጉሞች በዚህ ጊዜ ለመስጠት ባለን መብት ነው የሰጠነው።