ቅዱሳት መጻህፍት
የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገፅ


መፅሐፈ ሞርሞን

ከኔፊ ሰሌዳዎች ተወስዶ
በሞርሞን እጅ
በሰሌዳዎች
ላይ የተፃፈ መዝገብ

ስለዚህ፣ ይህ የኔፊ ህዝብ፣ እናም ደግሞ የላማናውያን አጭር ታሪክ ነው—የእስራኤል ቤት ቅሪት ለሆኑት ለላማናውያን፣ እናም ደግሞ ለአይሁድና ለአህዛብ የተፃፈ—በትዕዛዝ መሰረት፣ እናም ደግሞ በትንቢት መንፈስና በመገለጥ የተፃፈ—እንዳይጠፉ ሲባል ተፅፈውና ታሽገው በጌታ የተደበቁ—ለነበረው ትርጉም በእግዚአብሔር ኃይልና ስጦታ ይመጡ ዘንድ—በአህዛብ በኩል በትክክለኛው ጊዜ ይመጡ ዘንድ፣ በሞሮኒ እጅ ታሸጉ፣ እናም ለጌታ የተደበቁ—ትርጉሙም በእግዚአብሔር ስጦታ ነው።

ጌታ ወደ ሰማይ ለመድረስ ግንብ ሲገነቡ ቋንቋቸውን በደባለቀባቸው ጊዜ የተበተኑት የያሬድ ህዝቦችን ታሪክ ከያዘው ከመፅሐፈ ኤተር የተወሰደ አጭር ታሪክ—ይህም ጌታ ለእስራኤል ቤቶች ቅሪት ለአባቶቻቸው ምን ያህል ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገ ለማሳየት ነው፤ እናም የጌታን ኪዳን ያውቁ ዘንድ፣ ለዘለዓለምም እንደማይጣሉ ያውቁ ዘንድ—እናም ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ ዘለዓለማዊ አምላክ እንደሆነ፣ እራሱንም ለሁሉም ሀገሮች እንደገለፀ፣ ለአይሁድና ለአህዛብ እስከማሳመን—እና አሁን፣ ስህተቶች ካሉ ስህተቶቹ የሰዎች ስህተቶች ናቸው፣ ስለዚህ፣ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ያለ እንከን ትሆኑ ዘንድ የእግዚአብሔር የሆኑትን አትኮንኑ።

ከሰሌዳዎቹ የመጀመሪያው የእንግሊዝኛ ትርጉም
በጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ።