ቅዱሳት መጻህፍት
የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነት


የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነት

የመፅሐፈ ሞርሞንን መምጣት በተመለከተ የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የራሱ ቃላት የሚከተሉት ናቸው፥

“በመስከረም [፲፰፻፳፫] (እ.አ.አ.) ምሽት ላይ … በትህትና ሁሉን ለሚገዛው እግዚአብሔር መፀለይ እና መማጸን ጀመርኩ። …

“እግዚአብሔርን በመጥራት ላይ ባለሁበት ጊዜ፣ ብርሃን በክፍሌ ውስጥ ሲመጣ ተመለከትኩ፣ ብርሃኑም ከቀትር ፀሐይ እስኪበልጥ ድረስ መጨመሩን ቀጠለ፣ ወዲያውኑም አንድ ሰው በአልጋዬ አጠገብ እግሩ መሬት ሳይነካ በአየር ላይ ቆሞ ተገለጠልኝ።

“በጣም ያሸበረቀ ነጭ ካባ ለብሶ ነበር። ንጣቱም ምድራዊ ከሆኑ ካየኋቸው ነገሮች በሙሉ የበለጠ ነበር፤ ማንኛውም ምድራዊ ነገር እንደዚህ እጅግ ነጭና ደማቅ መሆን ይችላል ብዬም አላምንም። እጆቹ፣ እናም ደግሞ ክንዶቹ፣ ከፍንጁ ትንሽ ከፍ ብሎ፣ በልብስ አልተሸፈኑም ነበር፤ እግሮቹም ደግሞ እንዲሁ ከቁርጭምጭሚቱ በላይ በልብስ አልተሸፈኑም ነበር። ራሱና አንገቱም የተገለጡ ነበሩ። ካባው ተከፍቶ ደረቱን ማየት እችል ስለነበር፣ ከካባው በቀር ሌላ ልብስ እንዳልነበረው ለማወቅ እችል ነበር።

“እጅግም የነጣው ካባው ብቻ አልነበረም፣ ነገር ግን መላ ሰውነቱ መግለፅ ከሚቻለው በላይ ብሩህ ነበር፣ እንዲሁም ፊቱ በእውነት ልክ እንደ መብረቅ ነበር። ክፍሉ እጅግ ብርሃን ነበር፣ ነገር ግን ልክ በእርሱ ዙሪያ እንደነበረው በጣም የደመቀ አልነበረም። በመጀመሪያም ወደ እርሱ በተመለከትኩ ጊዜ ፈርቼ ነበር፣ ነገር ግን ፍርሃቱ ወዲያው ለቀቀኝ።

“በስሜ ጠራኝ፣ እናም እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እኔ የተላከ መልዕክተኛ እንደሆነና ስሙም ሞሮኒ እንደሆነ፣ እግዚአብሔርም ለእኔ የምሰራው ስራ እንደነበረው፤ እናም ስሜም በሁሉም ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ህዝብ መካከል በጥሩና በመጥፎ እንደሚነሳ፣ ወይም በሁሉም ህዝብ መካከል ጥሩና መጥፎ እንደሚባልልኝ ነገረኝ።

“እርሱ በዚህ አህጉር ቀድመው ነዋሪ ስለነበሩት ታሪክ እና እነርሱ የመጡበትን ምንጭ ከየት እንደሆነ የሚናገር በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ ተፅፎ የተቀበረ መፅሐፍ እንዳለ ተናገረ። ለጥንት ነዋሪዎች በአዳኙ የተሰጠውን የዘለዓለማዊውን ወንጌል ሙሉነትም በውስጡ እንደያዘ ደግሞ ተናገረ፤

“ደግሞ ከሰሌዳዎቹም ጋር የተቀበሩ ሁለት ድንጋዮች በብር ቅስት ውስጥ ነበሩ፣ እናም እነዚህ ድንጋዮች፣ በደረት ኪስ ታስረው፣ ኡሪምና ቱሚም የሚባለውን ይሰራሉ፤ እናም የእነዚህ ድንጋዮች ባለቤትና ተጠቃሚ በጥንት ወይም በድሮ ጊዜ ‘ባለራዕይ’ የሚባሉት ናቸው፤ እናም እግዚአብሔር መጽሐፉን ለመተርጎም ዓላማ እነርሱን አዘጋጅቶ ነበር።…

“እንደገናም፣ እርሱ የተናገረኝን ሰሌዳዎች ሳገኝ—እነርሱን የምወስድበት ትክክለኛው ጊዜ ገና እንዳልተሟላና—እኔ ማሳየት እንዳለብኝ ከምታዘዘው በቀር እነዚህን ወይም የደረት ኪሱን ከኡሪምና ቱሚም ጋር ለማንም ሰው ማሳየት እንደሌለብኝ፤ ይህን ካደረግሁ ግን መጥፋት እንዳለብኝ ነገረኝ። እርሱ ከእኔ ጋር ስለሰሌዳዎቹ በሚነጋገርበት ጊዜ ሰሌዳዎቹ የተቀበሩበትን ቦታ ማየት እንድችል ራዕይ ለአዕምሮዬ ተገለፀ፣ እናም ይህም በጣም ግልጽ እና ጉልህ ሆኖ ታይቶኝ ቦታውን በጎበኘሁበት ጊዜ እንደገና አውቄው ነበር።

“ይህን ሁሉ ከሰማሁ በኋላ ብርሃን በክፍሉ ውስጥ ባናገረኝ ሰው ዙሪያ በፍጥነት መሰብሰብ ሲጀምር አየሁ፣ እናም ከእርሱ ዙሪያ በቀር ክፍሉ እንደገና እስኪጨልም ሲቀጥል፣ ወዲያውም መተላለፊያ ቀጥታ ወደ ሰማይ ሲከፈት የተመለከትኩኝ መሰለኝ፣ እናም እርሱ እስኪጠፋ ድረስ አረገ፣ እናም ክፍሉ ይህ ሰማያዊ ብርሃን ከመታየቱ በፊት እንደነበረው ሆነ።

“እኔ ተኝቼ በዚህ እንግዳ ዕይታ በጥንቃቄ አሰብኩ፣ እናም ይህ እንግዳው መልዕክተኛ በነገረኝ ታላቅ አስደናቂ ነገር፤ በሃሳቤ ሳወጣና ሳወርድ ክፍሌ እንደገና እየደመቀ መምጣቱን በድንገት ተመለከትኩ፣ እናም ወዲያው ያው የሰማይ መልዕክተኛ በድጋሚ አልጋዬ አጠገብ መሆኑን ተመለከትኩ።

“እርሱም መናገር ጀመረ፣ እናም እንደገና በመጀመሪያ ጉብኝቱ ያደረጋቸውን አንድ አይነት ነገሮች ምንም ሳይለውጥ ተናገረ፤ ይህንን ካደረገ በኋላ፣ ከታላቅ ጥፋት ጋር በረሃብ፣ በሰይፍ፣ እና በቸነፈር፣ ታላቅ ፍርድ በምድር እንደሚመጣ፤ እናም እነዚህ አሳዛኝ ፍርዶች በምድር ላይ በዚህ ትውልድ እንደሚመጡ ገለፀልኝ። እነዚህን ነገሮች ከነገረኝ በኋላ ልክ እንደ በፊቱ በድጋሚ አረገ።

“በዚህ ጊዜ በአዕምሮዬ የተቀረፁት በጣም ጥልቅ ነገሮች ስለነበሩ፣ እንቅልፍ ከዐይኖቼ ጠፋ፣ እናም ባየሁትና በሰማሁት በመደነቅ ተሸንፌ ተኛሁ። ነገር ግን ይገርመኝ የነበረው ነገር በድጋሚ ያንን መልዕክተኛ በአልጋዬ በኩል ሳየው፣ እናም ያንኑ የበፊቱን ነገሮች እንደገና ሲደግመው ስሰማ፣ እናም ሰይጣን ሰሌዳዎቹን ሳገኝ (የአባቴ ቤተሰቦች ድሃ በመሆናቸው ምክንያት) ሀብታም እንድሆንባቸው ሊፈትነኝ እንደሚሞክር ማስጠንቀቂያ ሲጨምርልኝ ነበር። እርሱም፣ ጌታን ከማሞገስ በስተቀር፣ ይኸውም ሰሌዳዎቹን በማግኘቴ ሌላ አእምሮዬን የማያነሳሳ ነገር መኖር እንደሌለበት እንዲህ በማለት ከለከለኝ፣ እናም የእርሱን መንግስት ከመገንባት በማንኛውም ሌላ ነገር ተፅዕኖ ሊደርስብኝ እንደማይገባ አለበለዚያ እነርሱን ማግኘት እንደማልችል ተናገረኝ።

“ከዚህ ከሦስተኛው ጉብኝት በኋላ፣ ልክ እንደበፊቱ በድጋሚ ወደ ሰማይ አረገ፣ እናም አሁን ስለአየሁት እንግዳ ነገር በድጋሚ ማሰላሰሌን ቀጠልኩ፤ ልክ የሰማዩ መልዕክተኛ ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ሰማይ ሲያርግ፣ ዶሮ ጮኸ፣ እናም እየነጋ መሆኑን ተገነዘብኩ፣ ስለዚህ ንግግራችንም ያን ምሽት በሙሉ የያዘ እንደነበር ተረዳሁ።

“ከትንሽ ጊዜም በኋላ ከመኝታዬ ተነሳሁ፤ እናም እንደተለመደው፣ ለቀኑ አስፈላጊ ወደ ሆነው ስራ ሄድኩ፤ ነገር ግን በሌላ ጊዜ እንደምሰራው ስሞክር፣ ኃይልን በማጣቴ ያም ለመስራት ፍፁም አላስቻለኝም። አባቴ ከእኔ ጋር ሲሰራ በእኔ በኩል አንድ ችግር እንዳለ አየ፣ እናም ወደ ቤት እንድሄድ ተናገረኝ። ወደ ቤት ለመሄድ ጀመርኩ፤ ነገር ግን እኛ የነበርንበትን የሜዳ አጥር ለማቋረጥ ስሞክር ብርታቴን በሙሉ አጣሁ፣ እናም አቅቶኝ በመሬት ላይ ወደቅሁ፣ እናም ለተወሰነ ጊዜ አዕምሮዬን ስቼ ነበር።

“የመጀመሪያው የማስታውሰው ነገር አንድ ድምፅ በስሜም እየጠራኝ ሲያናግረኝ ነበር። ተመለከትኩ፣ እናም የፊተኛው መልዕክተኛ ልክ እንደበፊቱ በብርሃን ተከቦ በጭንቅላቴ በኩል ቆሞ አየሁ። እናም እርሱ ባለፈው ምሽት ለእኔ የተናገረውን ሁሉ እንደገና ተናገረ፣ እናም ወደ አባቴ በመሄድ ስለራዕዩና ስለተቀበልኩት ትዕዛዛት እንድናገር አዘዘኝ።

“እኔም ተቀበልኩ፤ በሜዳው ወደአለው አባቴም ተመለስኩ፣ እናም ሁሉንም ነገር ለእርሱ ነገርኩት። እርሱም ከእግዚአብሔር ነው ብሎ መለሰልኝ፣ እናም በመልዕክተኛው የታዘዝኩትን እንድሄድና እንዳደርግ ነገረኝ። ከሜዳውን ወጣሁ፣ እናም መልዕክተኛው ሰሌዳዎቹ ተቀብረዋል ብሎ ወደነገረኝ ቦታ ሄድኩ፤ ያንን በተመለከተ ግልፅ ራዕይ ስለነበረኝ፣ ስፍራው እንደደረስኩ ወዲያው አወቅሁት።

“በኒው ዮርክ፣ በማንቸስተር መንደር፣ በኦንታሪዮ የግዛት ክፍል አጠገብ አንድ ትልቅ፣ እናም ከማንኛውም በአቅራቢያው ካሉት ሁሉ የበለጠ ኮረብታ ቆሟል። በኮረብታው በስተምዕራብ በኩል ከጫፉ ራቅ ሳይል፣ በትልቅ ድንጋይ ስር ሰሌዳዎቹ በድንጋይ ሳጥን ውስጥ ተቀብረዋል። ትልቁ ድንጋይ በላይ በኩል ከመሀሉ ወፍራምና ክብ፣ እንዲሁም ወደጠርዙም በኩል ቀጭን ነበር፣ ስለዚህ የመካከለኛው ክፍሉ ከመሬት በላይ ከፍ ብሎ ይታይ ነበር፤ ነገር ግን ጠርዞቹ በሙሉ በመሬቱ ተሸፍነው ነበር።

“አፈሩን ከቆፈርኩኝ በኋላ፣ ሰቅስቆ ማንሻ አገኘሁ፣ ይህንንም ከድንጋዩ ጠርዝ ላይ ተከልኩኝ፣ እናም በትንሽ ጉልበት አነሳሁት። ወደ ውስጥ ተመለከትኩ፣ እና በእዚያም መልዕክተኛው እንደገለፀው በእርግጥ ሰሌዳዎቹን፣ ኡሪምና ቱሚም፣ እናም የደረት ኪሱን ተመለከትኩ። በውስጡ የተቀመጡበት ሳጥን ሲሚንቶ በሚመስል በተነባበሩ ድንጋዮች የተሰራ ነበር። ከሳጥኑ በታች በኩል ሁለት ድንጋዮች ተቀምጠዋል፣ እናም በእነዚህ ድንጋዮች ላይ ሰሌዳዎችና ከእነርሱ ጋር ሌሎች ነገሮች ነበሩ።

“እኔ እነርሱን ለማውጣት ሞከርኩ፣ ነገር ግን በመልዕክተኛው ተከለከልኩ፣ እናም እንደገና የእነርሱ ማውጫ ጊዜ ገና እንዳልደረሰ፣ ከእዚህም ጊዜ ከአራት አመት በኋላ ድረስ እንደማይደርስም አስታወቀኝ፤ ነገር ግን እርሱ ልክ ከእዚያ ጊዜ በአንድ አመት ወደ እዚያው ቦታ መምጣት እንዳለብኝ፣ እናም እርሱ እዚያ እንደሚያገኘኝ፣ እናም ሰሌዳዎቹ የምወስድበት ጊዜ እስከሚመጣ ይህን ማድረግ መቀጠል እንዳለብኝ ተናገረኝ።

“በታዘዝኩት መሰረት፣ በየአመቱ መጨረሻ እሄድ ነበር፣ እናም በእያንዳንዱ ጊዜም ያንኑ መልዕክተኛ በእዚያ አገኘሁት፣ እናም በእያንዳንዱ ንግግራችን ጌታ እንደሚያደርግ በተመለከተ፣ እናም እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ የእርሱ መንግስት በመጨረሻው ቀን እንደሚመራ መመሪያና እውቀት ከእርሱ እቀበል ነበር።…

“በመጨረሻም ሰሌዳዎቹን፣ ኡሪምና ቱሚም፣ እና የደረት ኪስን የማገኝበት ጊዜ ደረሰ። መስከረም ሃያ ሁለት በአንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃያ ሰባት (እ.አ.አ.)፣ ልክ እንደተለመደው በሌላኛው አመት መጨረሻ ወደ ተቀበሩበት ቦታ ስሄድ፣ ያው የሰማይ መልዕክተኛ እነዚህን ከዚህ ትዕዛዝ ጋር ለእኔ ሰጠኝ፤ ይኸውም ለእነሱ ሀላፊ መሆን እንዳለብኝ፣ በቀላሉ ወይንም በራሴ ንዝህላልነት እንዲሄዱ ካደረግሁ እንደምገለል፤ ነገር ግን ራሱ መልዕክተኛው እንድመልስለት እስከሚጠይቀኝ ደረስ ያለኝን ጥረቴን ሁሉ እነሱን ለመጠበቅ ከተጠቀምኩ፣ እነርሱ እንደሚጠበቁ ነበር።

“እኔ እነርሱን በጥንቃቄ እንዳስቀምጥ ለምን ጥብቅ መመሪያ የተቀበልኩትን፣ እናም ከእኔ የተፈለገውን ባደረግሁ ጊዜ እነርሱን እንድመልስለት የሚጠይቅበትን ምክንያት በፍጥነት አገኘሁት። እነርሱ እንዳሉኝ እንደታወቀ፣ ወዲያውኑ ከእኔ እነርሱን ለመውሰድ ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነ ጥረት ተደረጉ። ይህንንም ዓላማ ለማሳካት የተለያዩ ሥልቶች ጥቅም ላይ ውለዋል። ስደቱም ከበፊቱ የበለጠ አሰቃቂና መራራ ሆነ፣ እናም ብዙ ህዝብም የሚቻል ከሆነ እነርሱን ከእኔ ለመውሰድ በማድፈጥ መጠበቅ ቀጥለው ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ከእኔ የሚፈለገውን እስከማከናውን ድረስ በጥንቃቄ በእጄ ውስጥ ተቀመጡ። በዕቅዱ መሠረት መልዕክተኛው ሊወስዳቸው ሲመጣ፣ እኔም ለእርሱ ሰጠኋቸው፤ እናም እስከዚያ ቀን፣ ግንቦት ሁለተኛው ቀን አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ስምንት (እ.አ.አ.)፣ ድረስም በእርሱ ቁጥጥር ስር።”

ለተሟላ ዘገባ፣ በታላቅ ዕንቁ ዋጋ ውስጥ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክን ተመልከቱ።

ከተቀበረበት የወጣው ጥንታዊው ታሪክ ልክ ህዝቦች ከመሬት እንደሚናገሩት ድምፅ እናም በእግዚአብሔር ኃይልና ስጦታ በአምላክ እውነትነቱ ተረጋግጦ ወደ ዘመናዊው ቋንቋ የተተረጎመው፣ በመጀመሪያ በ፲፰፻፴ ዓመተ ምህረት (እ.አ.አ.) ለዓለም በእንግሊዝኛ The Book of Mormon ተብሎ ታተመ።