ስለመፅሐፈ ሞርሞን አጭር መግለጫ
መፅሐፈ ሞርሞን በብረት ሰሌዳዎች ላይ የተቀረጸ እና በጥንታዊት አሜሪካ የነበሩ ህዝቦች ቅዱስ ታሪክ ነው። ይህ መዝገብ የተጠረዘበት ምንጮቹ የሚከተሉት ናቸው፥
-
ሁለት ዓይነት የነበሩት የኔፊ ሠሌዳዎች፥ ትንንሾቹ ሠሌዳዎች እና ትልልቆቹ ሠሌዳዎች። የመጀመሪያው በተለይ በብዛት የተፃፈበት ስለመንፈሳዊ ነገሮችና ስለነቢያት አገልግሎትና ትምህርቶች ሲሆን፣ የኋለኞቹ በአብዛኛው በ(፩ ኔፊ ፱፥፪–፬) ያሉትን ህዝቦች አለማዊ ታሪክ በተመለከተ የተፃፈ ነበር። ሆኖም፣ ከሞዛያ ጊዜ ጀምሮ ትልቁ ሰሌዳ ዋናውን መንፈሳዊ ጠቃሚ ዝርዝሮችን አጠቃሏል።
-
የሞርሞን ሠሌዳዎች፣ ከብዙ ሀተታዎች ጋር ከትልቁ ከኔፊ ሰሌዳዎች ላይ በሞርሞን በማሳጠር የተፃፉትን ይዘዋል። እነዚህ ሰሌዳዎች ደግሞ የሞርሞን ታሪክ ቅጥያ እና የወንድ ልጁ የሞሮኒን ተጨማሪዎችን ይዘዋል።
-
የኤተር ሠሌዳዎች፣ የያሬዳውያንን ታሪክ ያቀርባል። ይህ ታሪክ ያጠረው የራሱን አስተያየት ጨምሮ ከጠቅላላው “መፅሐፈ ኤተር” ከሚባለው ታሪክ ጋር ባቀላቀለው በሞሮኒ ነው።
-
የነሀስ ሠሌዳዎች በሌሂ ህዝቦች በ፮፻ ም.ዓ. ከኢየሩሳሌም የመጡ ናቸው። እነዚህም “አምስቱን የሙሴ መፅሐፍ፣… እናም ደግሞ የአይሁዶችን ታሪክ ከመጀመሪያው ጀምሮ … እስከ የይሁዳ ንጉስ ሰዴቅያስ የመጀመሪያ ንግስ ድረስ፤ እናም ደግሞ የቅዱሳን ነቢያትን ትንቢቶችን” ይይዛሉ (፩ ኔፊ ፭፥፲፩–፲፫)። ከእነዚህ ሰሌዳዎች ብዙ ጥቅሶች፣ ኢሳይያስንና ሌሎች የመፅሐፍ ቅዱስ፣ እና ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆኑ ነቢያትን፣ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ሲጠቅሱ ይታያሉ።
መፅሐፈ ሞርሞን፣ ከአንዱ በስተቀር በልምድም በዋናው ፀሐፊያቸው ስም የሚጠሩ መፅሐፍ ተብለው የሚታወቁ፣ አስራ አምስት ዋና ዋና ክፍሎችን ይዟል። የመጀመሪያው ክፍል (በኦምኒ የሚያልቁ የመጀመሪያዎቹ ስድስቱ መፅሐፍቶች) ከትንሹ የኔፊ ሰሌዳዎች የተተረጎመ ነው። በኦምኒና በሞዛያ መፅሐፍቶች መካከል የሞርሞን ቃላት የተባለ ገብቷል። ይህ በመሀል የገባው በትንሹ ሰሌዳዎች ላይ የተቀረፁትን ታሪኮች ከትልቁ የሞርሞን ታሪክ ጋር ያያይዛል።
ከሞዛያ እስከ ሞርሞን ምዕራፍ ሰባት ያሉት ትልቁ ክፍል፣ ከትልቁ የኔፊ ሰሌዳዎች ላይ ሞርሞን ካጠረው የተተረጎመ ነው። ማጠቃለያው ክፍል፣ ከሞርሞን ምዕራፍ ፰ እስከ መጽሐፉ መጨረሻ፣ በሞርሞን ልጅ በሞሮኒ የተቀረፁ ነበሩ፣ እርሱም የአባቱን ህይወት ከመዘገበ በኋላ የያሬዳውያንን ታሪክ አሳጥሮ (እንደ መፅሐፈ ኤተር) ፃፈ፣ እናም በኋላ መፅሐፈ ሞሮኒ የተባለውን ክፍል ጨመረበት።
በ፬፻፳፩ ዓ.ም. ወይም ገደማ፣ የመጨረሻው የኔፊ ባለታሪክ እና ነቢይ ሞሮኒ፣ በጥንታዊ ነቢያት አማካኝነት እንደተተነበየው በእግዚአብሔር ድምፅ በኋለኛው ቀን እንዲመጣ ቅዱሱን መዝገብ አተመው እናም በጌታ እንዲጠበቅ ደበቀው። በ፲፰፻፳፫ (እ.አ.አ.) የቀድሞው ሞሮኒ፣ ከሞት የተነሳው ሰው፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን ጎበኘው፣ እናም በመጨረሻ ተቀርጾባቸው የተቀበሩትን ሰሌዳዎች ሰጠው።
ስለዚህ ቅጂ፥ የመጀመሪያው የርዕስ ገፅ ወዲያው የሚከተለው የማውጫውን ገፅ ከሰሌዳው የተወሰደ ነው እናም የተቀደሰ ፅሁፍ ክፍል ነው። እንደ ፩ ኔፊ እና ከሞዛያ ምዕራፍ ፱ ወዲያው ተከትለው እንዳሉት አይነት ጠመም ባለ የፊደል አጣጣል የተጻፉ መግቢያዎችም የተቀደሰ ፅሁፍ ክፍል ናቸው። እንደ ምዕራፍ ርዕስ አይነቶቹ ጠመም ባለ የፊደል አጣጣል የተጻፉት መግቢያዎች በፅሁፉ በመጀመሪያ ይገኙ የነበሩ አይደሉም ነገር ግን በጥናት እርዳታ ለምንባብ ምቾት እንዲሆኑ የተጨመሩ ናቸው።
በእንግሊዝኛ በታተሙት በመፅሐፈ ሞርሞን የድሮ ቅጂዎች ውስጥ በጽሁፍ አንዳንድ ቀላል ስህተቶች ተቀታትለው የመጡ ነበሩ። ይህ ቅጂ ይህን ጽሁፍ ከመታመቱ በፊት ከነበረው ጽሁፍ እና በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ከተስተካከሉት ከመጀመሪያ ቅጂዎች ጋር ለማስማማት አስፈላጊ የሆኑትን ያስተካክላል።