ቅዱሳት መጻህፍት
የስምንቱ ምስክሮች ምስክርነት


የስምንቱ ምስክሮች ምስክርነት

ይህ ስራ ለሚደርሳቸው ሀገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ህዝቦች በሙሉ፥ ወርቅ የሚመስሉትን ሰሌዳዎች የእዚህ ስራ ተርጓሚ፣ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እንዳሳየን፣ እናም የተባለው ስሚዝ የተረጎማቸውን ብዙዎቹን ገጾች በእጆቻችን እንደዳሰስናቸ የታወቀ ይሁን፤ እናም ደግሞ በዚያም ላይ የተቀረፁትን ተመልክተናል፣ ሁሉም የጥንት ስራ፣ እና በብልሃት የመሰራት ገፅታ አላቸው። እናም የተባለው ስሚዝ ለእኛ እንዳሳየን፣ እናም አይተን እንዳነሳን እናም የተባለው ስሚዝ ያልናቸውን ሰሌዳዎች እንዳለው በእርግጥ ማወቃችንን በጥሞና ቃላት ምስክርነት እንሰጣለን። ያየነውም ለዓለም ሁሉ ምስክር ይሆን ዘንድ ስማችንን ለዓለም እንሰጣለን። እናም አልዋሸንም፣ እግዚአብሔርም ስለዚህ ይመሰክራል።

ክርስቲያን ዊትመር

ጄከብ ዊትመር

ፒተር ዊትመር፣ ዳግማዊ

ጆን ዊትመር

ሀይረም ፔጅ

ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ

ሀይረም ስሚዝ

ሳሙኤል ሔሪሰን ስሚዝ