ቅዱሳት መጻህፍት
ሞሮኒ ፫


ምዕራፍ ፫

ሽማግሌዎች እጃቸውን በካህናት እናም በመምህራን ላይ በመጫን ሾሙአቸው። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ተብለው የሚጠሩት ደቀመዛሙርት ካህናትን እና መምህራንን የሚሾሙበት ስርዓት—

ወደ አብ በክርስቶስ ስም ከፀለዩ በኋላ፣ እጃቸውን ጭነውባቸው እንዲህ አሉ፥

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ካህን እንድትሆን (መምህር ከሆነ መምህር እንድትሆን)፣ ንሰሃን እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢአታቸው ስርየትን በስሙ እስከመጨረሻው በእምነት በመፅናት እንደሚያገኙ እንድትሰብክ እሾምሃለሁ። አሜን።

እናም በዚህ ስርዓት ለሰዎች በእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ መሰረት ካህናትን እናም መምህራንን ይሾሙ ነበር፤ እናም በውስጣቸው ባለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይልም ሾሙአቸው።