ምዕራፍ ፪
ኢየሱስም ኔፋውያን ደቀመዛሙርት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንዲሰጡ ስልጣንን ሰጣቸው። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።
፩ ክርስቶስ ለመረጣቸው አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት እጁን በመጫን የተናገራቸው ቃላት—
፪ እናም በስማቸውም በመጥራት እንዲህ አላቸው፥ በብርቱ ፀሎት አብን በስሜ ጥሩት፤ እናም ይህንንም ካደረጋችሁ በኋላ እጃችሁን በምትጭኑበት ላይ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ስልጣን ይኖራችኋል፤ እናም በስሜም ትሰጡታላችሁ፤ ይህንንም ሐዋሪያቶቼ ያደርጉታልና።
፫ እንግዲህ ክርስቶስ በመጀመሪያም እራሱን ለእነርሱ ሲገልፅ እነዚህን ቃላት ተናግሯል፤ እናም ህዝቡም አላዳመጡም፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ አዳምጠውታል፤ እናም እጃቸውን በጫኑባቸው በሙሉ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው።