ቅዱሳት መጻህፍት
ሞሮኒ ፭


ምዕራፍ ፭

የቅዱስ ቁርባኑን ወይን የሚባረክበት ስርዓት እንደሚከተለው ተገልጿል። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ወይኑን የሚባረክበትም ስርዓት—እነሆ ዋንጫውን ወስደው እንዲህ ይላሉ፥

አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ወይን የሚጠጡት ነፍሳት ሁሉ ለእነርሱ የፈሰሰውን የልጅህን ደም በማስታወስ ያደርጉት ዘንድ፣ ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱ ለአንተም፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ እንዲኖራቸው፣ ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን።