2010–2019 (እ.አ.አ)
አራተኛ ፎቅ፣ የመጨረሻው በር
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


21:33

አራተኛ ፎቅ፣ የመጨረሻው በር

እግዚአብሔር “ከልባቸው ለሚሹት ዋጋ ይሰጣል፣” ስለዚህ በማንኳኳት መቀጠል ይገባናል። እህቶች፣ ተስፋ አትቁረጡ። በሙሉ ልባችሁ እግዚአብሔርን እሹ።

በውዱ ነብያችን እና ፕሬዝዳንታችን፣ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ምሬት ስር በዚህ አለም አቀፍ ጉባኤ እንደገና በመሰብሰባችን በጣም ተባርከናል። ፕሬዝዳንት፣ እንወዶታለን እናም እንደግፍዋታለን። የቤተክርስቲያኗን እህቶች እንደምትወዱ እናውቃለን።

ለቤተክርስቲያን ሴቶች በተሰጠው በዚህ በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ ይህን ድንቅ ክፍለ-ጊዜ መካፈል በጣም ያስደስተኛል።

እህቶች፣ እናንተን ሳይ፣ በህይወቴ በጣም ተፅእኖ ፈጣሪ የነበሩትን ሴቶች ሳላስብ መቅረት አልችልም፤ ቤተክርስቲያኑ ምን እንደሆነ መጥተው እንዲያዩ የቀረበላቸውን ግብዣ በመቀበል የመጀመሪያ የነበሩት አያቴን እና እናቴ።1 ለመጀመሪያ ጊዜ ሳያት በፍቅር የወደኩላት ውዷ ሚስቴ፣ ሀሪየትም አለች። በካንሰር ምክንያት ባሏን አጥታ ብዙም ሳትቆይ ቤተክርስትያኑን የተቀላቀለችው የሀርየት እናት አለች። ከዛም እህቴ፣ ሴት ልጄ፣ የልጅ ልጄ፣ የልጅ ልጅ ልጄ—ሁሉም እነዚህ ግለሰቦች ቀራጭ አነሳሾቼ ነበሩ። በእውነትም በህይወቴ የፀሀይ ብርሀንን ያመጣሉ። የተሻለ ሰው እና የበለጠ የሚሰማው የቤተክርስቲያን መሪ እንድሆን አነሳስተውኛል። ህይወቴ ያለነሱ ምን ያህል የተለየ ይሆን ነበር!

ሆኖም የበለጠ ትሁት የሚያደርገኝ እንደ እነርሱ የሆነ ተፅእኖ እንደ እናንተ ባሉ የእምነት ሴቶች ብቃቶች፣ ተሰጥኦዎች፣ እውቀት፣ እና ምስክርነት አማካኝነት በቤተክርስቲያኑ በሞላ በሚሊዪኖች ጊዜ መሰራጨቱን ማወቄ ነው።

አሁን፣ አንዳንዶቻችሁ ለእንደዚህ አይነት ሙገሳ ብቁ ያለመሆን ሊሰማችሁ ይችላል። በሌሎች ላይ ትርጉም ያለው ተፅእኖ ለማኖር ብዙም የማትጠቅሙ እንደሆናችሁ ሊሰማችሁ ይችላል። ስለሆነም አንዳንድ ጊዜ ከጥርጣሬ ወይም ፍራቻ ጋር ትግል ስለምታደርጉ እራሳችሁን እንደ “የእምነት ሴት” አድርጋችሁም አታስቡ ይሆናል።

ዛሬ፣ በዚህ መንገድ ተሰምቶት ለሚውቅ ሁሉ ለመናገር እፈልጋለሁ—እናም ያ ደግሞ በአንድ ወይም በሌላ ጊዜ ሁላችንንም የሚያካትት ሊሆን ይችላል። ስለ እምነት መናገር እፈለጋለሁ—ምን እደሆነ፣ ምን ማድረግ እንደሚችል እና እንደማይችል፣ እናም የእምነትን ሀይል በህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ምን ማድረግ እንዳለብን።

የእምነት ምንነት

እምነት ስለምናምነው ነገር ያለን የፀና እምነት ነው—የፀና እምነትቱ በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ እኛ በማንኛውም መንገድ የማናደርጋቸውን ነገሮች እንድርግ የሚገፋፋን ነው። “እምነት ተስፋ ስለምናደርገው እና ስለማናየው ነገር እርግጠኛ መሆን ነው።”2

ይሄ ለሚያምኑ ክርስቲያኖች ትርጉም ሲሰጥ፣ ለማያምኑት ደግሞ በብዛት ግራ የሚያጋባ ነው። እራሳቸውን ይነቀንቁና ይጠይቃሉ፣ “ስለማያዩት ነገር እርግጠኛ መሆን የሚችሉት እንዴት ነው?” ለእነርሱ፣ ይሄ የእምነት ምክንያታዊ አለመሆን ማስረጃ ነው።

እነርሱ ለመረዳት ያልቻሉት ከአይኖቻችን ሌላ የመመልከቻ ብዙ መንገዶች እንዳሉ ነው። ከእጆቻችን ሌላ የመዳሰሻ ተጨማሪ መንገዶች አሉ፣ ከጆሮዎቻችን ሌላ የማዳመጪያ መንገዶች አሉ።

በይበልጥም ከሴት አያትዋ ጋር በእግር እየሄደች የነበረች አንድ ወጣት ሴት ተሞክሮ አይነት ነው። የወፎቹ ዝማሬ ልትንሽዋ ልጅ ታላቅ ነበር፣ እናም እያንዳንዱን ድምፅ ለአያቷ ጠቀሰች።

“ያንን ሰማሽው?” እያለች ትንሽዋ ልጅ ደጋግማ ጠየቀች። ነገር ግን አያቷ መስማት ስለሚከብዳቸው ድምፆቹን ማግኘት አልቻሉም ነበር።

በስተመጨረሻ፣ አያትየው ተንበረከኩ እና እንዲህ አሉ፣ “አዝናለሁ፣ ውዴ። አያትሽ በደምብ አትሰማም።”

በመበሳጨት፣ ትንሽዋ ልጅ የአያቷን ፊት በእጆችዋ ይዛ፣ ወደ አይናቸው በአጥኖት ተመለከተች እና እንዲህ አለች፣ “አያቴ፣ የበለጠ በደምብ ስሚ!”

በዚህ ታሪክ ውስጥ ለማያምን እና ለሚያምን ለሁለቱም ትምህርቶች አሉ። መስማት ስለማንችል ብቻ የሚሰማ ነገር የለም ማለት አይደለም። ሁለት ሰዎች አንድ አይነት መልእክት ሊሰሙ ወይም ተመሳሳይ የቅዱስ መፃፍ ጥቅስ ሊያነቡ ይችላሉ፣ እናም አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ሊሰማው ይችላል፣ ሌላኛው ሳይሰማው።

በሌላ ወገነን፣ የምንወዳቸው ሰዎች የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ እና ጥልቁ፣ ዘለአለማዊው፣ እና ጥልቅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውብነት ተሞክሮ እንዲኖራቸው ለመርዳት ባለን ጥረት ውስጥ፣ “የበለጠ በደምብ እንዲሰሙ” መናገር ይበልጥ የሚረዳ መንገድ ላይሆን ይችላል።

በእርግጥ እምነትን ለማጠንከር ለሚፈልግ ሰው የተሻለ የሚሆነው—በተለየ መልኩ እንዲሰሙ መምከር ነው። ለጆሮዋችን ብቻ ሳይሆን ለመንፈሳችን የሚናገር ድምፅን እንድንሻ ሐዋርያው ጳውሎስ ያበረታታናል። እንዲህ አስተማረ፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ የሌው ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚመጡትን ነገሮች መቀበል አይችልም ነገር ግን ሞኝነት ብሎ ያስበዋል፤ በመንፈስም የሚመረመር ሰለ ሆነ ሊረዳውም አይችልም።”3 ወይም ምናልባት እንዲህ ያለውን ሴይንት ኤክሱፕሪ በትንሽ ልኡል ምስጥ የጻፈውን ቃላት ማሰብ ያስፈልገናል፥ “ሰው በጥራት የሚያየው በልቡ ብቻ ነው። ወሳኝ የሆነ ነገር ሁሉ ለአይን አይታይም።”4

የእምነት ሀይል እና ውስንነቶች

አንዳንዴ፣ በአካላዊ አለም ውስጥ እየኖሩ በመንፈሳዊ ነገሮች እምነትን ማሳደግ ቀላል አይደለም። ነገር ግን ጥረት ማድረጉ ዋጋ አለው፣ ምክንያቱም በህይወታችን የእምነት ሀይል ሊገለፅ ይችላል። በእምነት ምክንያት አለማት ተቀርፀዋል፣ ውሀዎች ተከፍለዋል፣ የሞቱት ተነስተዋል፣ ወንዞች እና ተራሮች ከቦታቸው ተነስተዋል። 5

ግን አንዳንዶች እንዲህ ሊጠይቁ ይችላሉ፣ “እምነት በጣም ሀይል ያለው ከሆነ፣ ከልብ ለመነጨ ፀሎት ምላሽ ለምን አላገኝም? ባህርን መክፈል ወይም ተራራን ማንቀሳቀስ አያስፈልገኝም። ህመመሜ ብቻ እንዲወገድ ወይም ወላጆቼ እርስ በእርስ ይቅር እንዲባባሉ ወይም ዘለአለማዊ የትዳር አጋር በበሬ መግቢያ እቅፍ አበቦች በአንድ እጁ እና በሌላው ደግሞ የቃልኪዳን ቀለበት ይዞ እንዲከሰት ብቻ ነው የምፈልገው። ታዲያ እምነቴ ያንን ለምን አያሳካም?”

እምነት ሀያል ነው ፣ እና በአብዘኘው በተአምራት ውስጥ ይመጣል። ነገር ግን የቱንም ያህል እምነት ቢኖረን፣ እምነት ማድረግ የማይችላቸው ሁለት ነገሮች አሉ። አንዱ፣ የሌላን ሰው ነፃ ምርጫ አይጣረስም።

አንድ እናት አስቸጋሪ ሴት ልጇ ወደ ክርስቶስ እቅፍ እንድትመለስ ፀለየች እናም ፀሎቷ ሳይመለስ የቀረ መስሏት መሰላቸት ተሰማት። ከመንገዶቻቸው ንስሀ የገቡ ሌሎች የጠፉ ልጆችን ታሪኮች ስትሰማ በተለየ ሁኔታ የሚያም ሆነባት።

ችግሩ ያለመፀለይ ወይም የእምነት ማነስ አልነበረም። መረዳት የነበረባት ነገር፣ ምንም ያህል ለሰማይ አባት አሳዛኝ ቢሆንም፣ የፅድቅን መንገድ እንዲመርጥ ማንንም ሰው አያስገድድም። እግዚአብሔር በቅድመ ህይወት አለም ውስጥ እንዲከተሉት የራሱን ልጆች አላስገደደም። አሁን በዚህ ምድራዊ ህይወት ውስጥ ስንጓዝ የእርሱ የማስገደድ መጠኑ ምን ያህል ያነሰ ነው የሚሆነው?

እግዚአብሔር ይጋብዛል እናም ያበረታታል። እግዚአብሔር በፍቅር እና መነሳሳት እናም በማበረታታት ሳይደክም ይረዳል። ነገር ግን እግዚአብሔር በፍፁም አያስገድድም—ያ ለዘለአለማዊ እድገታችን ያለውን ታላቅ እቅድ ያቀለው ነበር።

ሁለተኛው እምነት ማድረግ የማይችለው ነገር በእኛ ፍላጎት እግዚአብሔርን ማስገደድ ነው። የቱንም ያህል ትክክል ነን ብለን ብናስብም ወይም ከልብ ብንፀልይም—እግዚአብሔር የእኛን ፍላጎት እንዲፈፅም ልናስገድደው አንችልም። የጳውሎስን ተሞክሮ አስታውሱ “የስጋ እሾህ” ብሎ ከጠራው—የግል ፈተናው ለመገላገል ብዙ ጊዜ ጌታን የተማፀነው። ነገር ግን ያ የእግዚአብሔር ፍላገጎት አልነበረም። ከጊዜ በኋላ የእርሱ ፈተና በረከት እንደነበር ጳውሎስ አስተዋለ፣ እና እርሱ ተስፋ ባደረገው መንገድ ፀሎቱን ስለመለሰለት እግዚአብሔርን አመሰገነው።6

ማመን እና እምነት

የእምነት አላማ የእግዚአብሔርን ፍላጎት መቀየር አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር ፍቃድ ላይ እንድንተገብር ሀይል ለእኛ መስጠት ነው። እመነት ማመን ነው—እኛ የማናየውን እግዚአብሔር እንደሚያይ እና እኛ የማናውቀውን እርሱ እንደሚያውቅ ማመን ነው።7 አንዳንዴ፣ የእራሳችንን ራእይ እና ፍርድ ማመን በቂ አይደለም።

ይህንን እንደ የአየር መንገድ አብራሪነቴ የፊቱን በጣም ጥቂት እርቀት ብቻ በማይበት ጉም ወይም ደመናዎች ውስጥ ማብረር በነበረብኝ ቀናት ተምሬያለሁ። የት እንደነበርኩ እና ወዴት እንደምሄድ በሚነግሩኝ መሳሪያዎች ላይ መመርኮዝ ነበረብኝ። የአየር ትራፊክ ቁጥጥርን ድምፅ መስማት ነበረብኝ። እኔ ከነበረኝ የተሸለ መረጃ ከነበራቸው ምንጮች የሚመጣ ምሬትን ማመን ነበረብኝ። የማላየውን ነገር ግን እንዳምነው የተማርኩትን ሰው። እኔ ማየት የማልችለውን የሚያይ ሰውን። ወደ መዳረሻዬ በደህንነት እንድደርስ ማመን እና መተግበር ነበረብኝ።

እምነት ማለት በእግዚአብሔር ጥበብ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በእርሱ ፍቅርም መተማመን ነው። እግዚአብሔር ፍፁም በሆነ መልኩ እንደሚወደን፣ የሚያደርገው ነገር ሁሉ—የሚሰጠው እያንዳንዱ በረከት እና ለጊዜው የማይሰጠው በረከሮች ሁሉ—ለእኛ ዘለአለማዊ ደስታ እንደሆነ ማመን ማለት ነው።8

በዚህ አይነት እምነት፣ አንዳንድ ነገሮች ለምን እንደሚሆኑ ወይም አንዳንድ ፀሎቶች ለምን ሳይመለሱ እንደሚቀሩ ባናውቅም እንኳን፣ ከጊዜ በኋላ ሁሉም ነገር ትርጉም እንደሚሰጥ ማወቅ እንችላለን። “እግዚአብሔርን ለሚወዱት ነገር ሁሉ ለበጎ ይደረጋል።”9

ሁሉም ነገሮች ትክክል ይደረጋሉ። ሁሉም መልካም ይሆናል።

መልሶች እደሚመጡ እርግጠኛ መሆን እንችላለን፣ እና በመልሶቹ ይዘት መደሰት ብቻ ሳይሆን፣ለእኛ ለልጆቹ የሰማይ አባት ባለው ፀጋ፣ ምህረት፣ ደግነት፣ እና ፍቅር በጣም እንደምንደነቅ እርግጠኛ እንሆናለን።

ማንኳኳታችሁን ቀጥሉ

እስከዛ፣ ባለን እምነት እንጓዛለን፣10 ሁሌም እምነታችንን ለማጠንከር በመሻት። አንዳንዴ፣ ይሄ ቀላል ተልእኮ አይደለም። በቀላሉ የሚደክሙ፣ ትእግስት የሌላቸው፣ ያልተሰጡ፣ ወይም ግድ የለሽ ለሆኑት እምነት የማይጨበጥ ነገር ነው። ቶሎ ብርታት የሚያጡ ወይም ትኩረት የሚስቱ እነሱ ተሞክሮው ሊኖራቸው ከባድ ነው። እምነት የሚመጣው ለትሁት፣ ለትጉህ፣ ለፅኑዎች ነው።

ለአማኝነት ዋጋ ለሚከፍሉት ይመጣል።

ይሄ እውነት ጥቂት የተቀየሩ ሰዎች ጥምቀት ባለበት በአውሮፓ፣ በሚያገለግሉ ሁለት ወጣት ሚስኦናውያን ተሞክሮ ውስጥ ታይቷል። እነርሱ ያደረጉት ብዙም ለውጥ እንደማያመጣ ቢያስቡ የማይገርም እንደሚሆን አስባለሁ።

ነገር ግን እነዚህ ሁለት ሚስኦኖች እምነት ነበራቸው፣ እናም ቆራጥ ነበሩ። ማንም ሰው መልእክታቸውን ባይሰማ፣ ምክንያቱ ጥረታቸው የተሻለ ስላልነበረ እንደማይሆን ነበር ያሰቡት።

አንድ ቀን፣ በደምብ የተያዘ የአራት ፎቅ መኖሪያ ህንፃ ላይ ነዋሪዎችን ለማናገር ተነሳሱ። ከመጀመሪያው ፎቅ ጀመሩ እና እያንዳንዱን በር አንኳኩ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን አዳኝ መልእክታቸውን እና ስለተመለሰው የእርሱ ቤተክርስቲያን አካፈሉ።

የእህት ኡክዶርፍ የልጅነት መኖሪያ ህንጻ

ከመጀመሪያው ፎቅ ማንም ሰው አላዳመጠቸውም።

ለማለት ምን ያህል ቀላል ነበረ፣“ሞክረናል። አሁን ይብቃን። እንሂድ እና ሌላ ህንጻ እንሞክር።”

ነገር ግን እነዚህ ሚስኦናውያን እምነት ነበራቸው እና ለመስራት፣ ፍቃደኛ ነበሩ፣ እናም ሁሉንም የሁለተኛውን ፎቅ በሮች አንኳኩ።

በድጋሜ፣ ማንም አላዳመጣቸውም።

ሶስተኛውም ፎቅ ላይም እንደዛው ነበር። እናም አራተኛውም እንደዛው—ያም የሆነው የአራተኛውን ፎቅ የመጨረሻ በር እስኪያንኳኩ ነበር።

ያ በር ሲከፈት፣ ወደ እነርሱ ትንሽ ሴት ልጅ ፈገግ አለች እናም እናቷን እስክታናግር ድረስ እንዲጠብቁ ጠየቀቻቸው።

እናታቸው 36 አመቷ የነበረ፣ ባለቤቷን በቅርብ ጊዜ ያጣች፣ እና ከሞርሞን ሚስዮኖች ጋር ለመነጋገር ያልፈለገች ነበረች። ስለዚህ ሴት ልጇን እንድትልካቸው ነገረቻት።

ነገር ግን ሴት ልጇ ተማፀነቻት። እነዚህ ወጣት ወንዶች በጣም ጥሩ ናቸው፣ አለች። እናም ጥቂት ደቂቃ ብቻ ነው የሚፈጀው።

በቸልተኝነት፣ እናትየው ተስማማች። ሚስኦኖቹ መልእክታቸውን አቀረቡ እና እናትየው እንድታነብ መፅሀፍ ሰጧት—መጽሐፈ ሞርሞን ነበር።

ከሄዱ በኋላ፣ እናትየው ጥቂት ገልፆች እንኳን ለማንበብ ወሰነች።

በጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ መጽሐፉን ጨረሰች።

የእህት ኡክዶርፍ ቤተሰብ ከሚስዮኖች ጋር

ብዙ ሳይቆይ፣ እርስዋ እና ሁለት ሴት ልጆቿ ወደ ጥምቀት ውሃ ገቡ።

ትንሹ ቤተሰባቸው በፍራንክፈርት፣ ጀርመን የሚገኘውን የአከባቢው አጥቢያ ሲካፈሉ፣ አንድ ወጣት ዲያቆን ከሴት ልጆቿ የአንዷን ውበት አስተዋለ እና ለእራሱ እንዲህ አሰበ፣ “እነዚህ ሚስኦናውያን ታላቅ ስራ እየሰሩ ነው!”

የዛ ወጣት ዲያቆን ስም ዲይተር ኡክዶርፍ ነበር። እና ቆንጆዋ ወጣት ሴት—ሚስኦናውያኑን እንድታዳምጥ እናቷን የተማፀነችው—ሀርየት የሚባል ድንቅ ስም አላት። ከእኔ ጋር ተጓዥ ሆና በሁሉም የተወደደች ነች። ባላት የወንጌል ፍቅር እና ጉልህ ባህሪዋ ምክንያት የብዙ ሰው ህይወት ባርካለች። በእውነትም የህይወቴ ብርሀን ነች።

እህት ኡክዶርፍ በኖርዌይ ንግግር ሲያቀርቡ

በመጀመሪያው በር ላይ ላላቆሙት ለሁለቱ ሚስዮኖች ልቤ በምስጋና ከፍ ይላል። ለእነርሱ እምነት እና ስራ ምን ያህል ጊዜ በምስጋና ልቤ የሚሞላው። እስከ አራተኛው ፎቅ፣ የመጨረሻ በር ድረስ ቀጥለው በመሄዳቸው ምን ያህል ጊዜ ምስጋና ሰጠኋቸው።

የከፈትላችሁማል

ለሚፀና እምነት ባለን ፍለጋ፣ ማለቂያ ከሌለው ጋር አንድ ለመሆን ባለን ተልእኮ፣ የጌታን ቃልኪዳን እናስታውስ፤ “አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል።”11

አንድ ወይም ሁለት ጊዜ አንኳኩተን ተስፋ እንቆርጣለን? አንድ ወይም ሁለት ፎቅስ?

ወይም አራተኘው ፎቅ፣ የመጨረሻ በር እስክንደርስ ድረስ መፈለጋችንን እንቀጥላለን?

እግዚአብሔርን “ለሚፈልጉት ወጋ ይሰጣል”12 ነገር ግን ያ ዋጋ ያለው በአብዛኛው ከመጀመሪያው በር ጀርባ አይደለም። ስለዚህ በማንኳኳት መቀጠል አለብን። እህቶች፣ ተስፋ አትቁረጡ። በሙሉ ልባችሁ እግዚአብሔርን እሹ። እምነትን ተለማመዱ። በቅድስና ተጓዙ።

ይህንን ካደረጋችሁ—እስከ አራተኛው ፎቅ፣ አራተኛ በር ድረስ—የምትፈልጉትን እውቀት እንደምታገኙ ቃል እገባለሁ። እምነትን ታገኛላችሁ። እናም አንድ ቀን “እስከፍፁሙ ቀን ድረስ ደጋግሞ በሚያበራ” ብርሀን ትሞላላችሁ።13

የተወደዳችሁ በክርስቶስ እህቶቼ፣ እግዚአብሔር እውነት ነው።

ህያው ነው።

ይወዳችኋል።

ያውቃችኋል።

ይረዳችኋል።

የልባችሁን ፀጥተኛ ተማፅኖ ያውቃል። አልተዋችሁም። አይረሳችሁም።

ይህ ልብ የሚማርክ እውነት በራሳችሁ ልብ እና አእምሮ ውስጥ እንዲሰማችሁ ለእያንዳንዳችሁ ይህ የእኔ ምስክርነት እና ሐዋርያዊ በረከት ነው። በእምነት ኑሩ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ ውድ እህቶቼ፣ እናም “[አምላካችን] እግዚአብሔር በዚህ ቁጥር ላይ እልፍ አእላፋት ይጨምር፥ እንደ ተናገራችሁም ይባርከናል!”14

ይህ የእግዚአብሔር ስራ እንደሆነ እምነቴን፣ ቁርጠኝነቴን፣ እናም እርግጠኛ እና የማይወላውል ምስክርነቴን እተውላችኋለሁ። በተወዳጁ አዳኛችን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።