የወንጌል ብርሀንን ወደቤቴ አመጣለሁ
በሌሎች ውስጥ ቀና ነገር በመፈለግ እና በመካፈል የወንጌሉን ብርሀን ወደ ቤታችን፣ ትምህርት ቤት እና ስራ ቦታችን ማምጣት እንችላለንማምጣት እንችላለን።
በእህት ሊንዳ ኬ. በርተን በሚያዚያ በነበረው ጠቅላላ ጉባኤ1 ለተደረገው ግብዣ መልስ በመስጠት በአካባቢያችሁ ያሉ የስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ብዙዎቻችሁ በቅን እና በደግነት የልግስና ስራ ውስጥ ተሳትፋችኃል። ከቀላል ወደ አንድ ለ አንድ ጥረቶች ከዛ ወደ ማህበረሰብን ያከሉ ፕሮግራሞች የፍቅር ነፀብራቅ ናቸው። ግዚያችሁን፣ መክሊታችሁን እና ሀብታችሁን ስትካፈሉ የእንተ— እና— የስደተኞችን ልብ ታበራላችሁ። በሰጪና በተቀባይ መሀል ተስፋ እና እምነት እንዲሁም ትልቅ ፍቅር መገንባ የልግስና ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው።
ነብዩ ሞረናይ ልግስና በሰሌስቻል መንግስት ከሰማይ አባት ጋር ለሚኖሩ አስፈላጊ በሀሪ እንደ ሆነ ይነግረናል። “ልግስና ከሌላችሁ በስተቀር በምንም አትድኑም”2 ሲል ፅፏል።
እርግጥ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ የልግስና ፍፁም አርአያ ነው። እሱ በቅድመ አለም ለእኛ አዳኝ ለመሆን መስጠቱ፣ በሟች አለም ሳለ ያሳደረው ተፅእኖ፣ የእሱ መለኮታዊ የሀጢያት ክፍያ ስጦታው፣ እናም እኛን ወደ ሰማይ አባት እኛን ለመመለስ ቀጣይነት ያለው ጥረቱ የመጨረሻው የልግስና ደረጃ ነው። እሱ የሚሰራው በነጠላ አተኩሮት፤ ለአባቱ ያለውን ፍቅር ለእያንዳንዳችን ባለው ፍቅር የተገለፀ ነው። ስለታላቂቷ ትዕዛዝ ሲጠየቅ፤ ኢየሱስ እዲህ ሲል መለሰ፣
“እግዚአብሔር አምላክህን ብሙሉ ልብ በመሉ ነፍስ በሙሉ አእምሮ ውደድ።
“ይህ የመጀመሪያዋ እና ታላቂቷ ትዕዛዝ ነች።
“ሁለተኛውም እንደ መጀመሪያቱ ነች፤ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ።”3
ለባልንጀሮቻችን ፍቅር ማዳበር እና ማሳየት የምንችልበት አንዱ እና ታላቅ የሆነው መንገድ በአስተሳሰባችን እና በቃላችን ደግ በመሆን ነው። ከጥቂት አመታት በፊት የተወደደችው ጓደኛዬ “የልግስና አንደኛው ክፍል ፍርዳችንን ማቆም ነው” ስትል አሳሰበች።4 ዛሬም ይህ እውነት ነው።
በቅርቡ የሶስት አመቷ አሊሳ ከእህት አና ወንድሞቿ ጋር ፊልም ስታይ በመገረም ሁኔታ “እማዬ ያዶሮ ወጣያለ ነው” ብላ ገለፀች።
እናቷ እስክሪኑ አየች እና በፈገግታ “ማሬ ያ ፒኮክ ነው ብላ መለሰችላት።”
ልክ እንደማታውቀው የሶስታ አመቷ ልጅ፤ እኛም ሌሎችን ባልተሟላ ወይም ትክክል ባልሆነ አረዳድ ልናያቸው እንችላለን። የእኛ የሰማይ አባታችን በእሱ አምሳል የፈጠራቸውን ልጆቹን እፁብ ድንቅ የሆነ አቅም እዳላቸው ሲያያቸው እኛ በአካባቢያች ባሉ ላይ ባላቸው ልዩነት ላይ እና በሚታይ ድክመታቸው ላይ ልናተኩር እንችላለን።
ፕሬዘደንት ጄምስ ኢ. ፏስት “እድሜ በጨመረ ቁጥር ፈራጅነቴን እየቀነሰ አመጣለሁ”5 በሚለው አባባል ይታወሳል። ይህም የጳውሎስ አመለካከትን ያስታውሰኛል፥
ልጅ ሳለሁ እንደልጅ እናገር ነበር እንደ ልጅም አስብ ነበር ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትትን ጠባይ ሽሬያለሁ።
“ዛሬስ በመስታወት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን ዛሬ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።”6
የራሳችንን ፍፁም አለመሆን በግልፅ ስንመለከት ሌሎችን “በጨለመ መስታወት” ማየታችን ይቀንሳል። ሌሎችን አዳኙ በሚያቸው እኛ እንድናያቸው የወንጌሉን ብርሀን መጠቀም አለብን—በፍቅር በርህራሔ በተስፋ እና በልግስና። ስሌሎቸች ልብ ሙሉ የሆነ መረዳት የሚኖረን ቀን ይመጣል እንዲሁም ምህረት ሲሰጠን አመስጋኝ እንሆናለን—ልክ በዚህ ህይወት እኛ ለሌሎች በልግስና የተሞላ ሀሳብ እና ቃላቶች እንደምንሰጠው።
ከጥቂት አመታት በፊት ከወጣት ሴቶች ቡድን ጋር ታንኳ ቀዘፋ ሄድኩኝ። ሰማያዊ ጥልቁ ሀይቅ በአረጓንዴ ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነ ኮረብታ እና ድጋያማ ዳገት የተከበበ ሲሆን ትንፋሽ የሚወስድ ውበት አለው። መቅዘፊያውን ወደ ንፁህ ውሀ ሰደን ስንቀዝፍ ውሃው ያንፀባርቅ ነበር እናም ቀስብለን መውሀው ላይ ስንንሳፈፍ ፀሀይዋ በሙቀት ታበራለች።
ሆኖም ግን፣ ደመና ሰማዩን አጨለመው፣ እናም ጠንካራ ንፋስ መንፈስ ጀመረ። ለውጥ ለማምጣጥ ውሀውን በጥልቀት ያለማቋረጥ ቀዘፍን። ከተወሰነ ጀርባ ከሚሰብር ስራ በኃላ በሀይቁ ጥግ በስተመጨረሻ ስንዞር በሚያስደንቅ እና ደስበሚል ሁኔታ ንፋሱ እኛ መሄድ ወደ ምንፈልግበት መሆኑን አወቅን ።
በፍጥነት የዚን እድል ስጦታ ተጠቀምንበት። ትንሽ ጨርቅ በማውጣት ሁለቱን ጫፍ ከመቅዘፊያው ጋር አሰርነው ሌላኛውን ደግሞ ከባለቤቴ እግር ላይ አሰር ነው እሱን በታንኳው ጫፍ ላይ ዘረጋው። በአስፈላጊነቱ የተሰራው ጊዜአዊ የመርከብ ሸራ በንፋስ ተነፋ፣ እናም መሄድ ጀመርን!
በሌላ ታንካ የነበሩት ወጣት ሴቶቹ በውሃው ላይ በቀላሉ መጓዛችንን ሲያዩ ፈጠን ብለው የራሳቸውን የመርከብ ሸራ አዘጋጁ። ልባችን በሳቅ እና በእረፍት ቀልሎልን ነበር ከቀኑ መከራ ስላረፍን አመሰገንን።
ልክ እንደዛ ጠንካራ ንፋስ ሁሉ እውነተኛ ማድነቅ ይሆናል ለጓደኛችን የወላጅ የደስታ ሰላምታ፣ የእህት ወንድም ማረጋገጫ ወይም የስራ ባልደረባ ወይም የክፍል ጓደኛ የእርዳታ ፈገግታ ምን ያህል የሆናልምን ያህል የሆናል እነዚህ ሁሉ በህይወታችን ያሉ ችግሮች ስንጋፈጥ አዲስ ንፋስ ወደ መርከባችን ሸራ ያመጡልናል። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ስለዚህ እንዲህ ብለዋል፥ “የንፋሱን አቅጣጫ ማስተካከል አንችልም ነገር ግን ሸራውን ማስተካከል እንችላለን። ለፍጹም ደስታ፣ ሰላም፣ እና እርካታ መልካም አስተያየትን እንምረጥ።”7
ቃላቶች የሚያስገርሙ ሀይል፣ የሚገነብ እና የሚያፈርሱ ሀይል አላቸው። ሁላችንም መልካም ያልሆኑ እኛን ዝቅ ያደረጉን እና በፍቅር የተነገሩን መንፈሳችንን ያቆሰሉን ቃላትን እናስታውሳለን። ለሌሎች ስሌሎች በእኛ አካባቢ ለሚገኙ ከፍ ለማድረግ እና ለማጠናከር መምረጥ ሌሎች የአዳኙን መንገድ እንዲከተሉ ይረዳቸዋል።
እንደ ህጻን የመጀመሪያ ክፍል ሴት ልጅ የአንድ አባባል ዘይቤን ለማወቅ በጣም ጥሬ ነበር ይህም “የወንጌሉን ብርሀን ወደ ቤቴ አመጣለሁ” ተብሎ ይነበባል። በአንዱ የሳምንት ቀን ከሰዓት እኛ ልጃገረዶች መርፊያችንን በጨርቅ ላይ ስንከት እና ስናወጣ አስተማሪያችን በአንድ ሸለቆ ጎን በኮረብታ ላይ ስለ ምትኖር አንድ ሴት ልጅ ታሪክ ነገረችን። ሁልጊዜ ከሰዓት በኮረብታው ላይ ሆና በሸለቆው በወዲያኛው በኩል መስኮቶቹ ወርቅማ ብርሀን ያላቸው አንድ ቤት ትመለከታለች። የራሷ ቤት ትንሽ እና አርጀት ያለ ነው እና ልጅቷ ወረቃማ መስኮቶች ባለው ቤት መኖርን ታልም ነበር።
አንድ ቀን ልጅቷ ሸለቆውን በባይስክሏ አቋርጣ እንድትሔድ ተፈቀደላት። ለረጅም ጊዜ ስታደንቀው የነበረው ያወርቅማ መስኮቶች ያሉት ቤት ለመድረስ በጉጉት ጋለበች። ነገር ግን ከ ባይስክሏ ስትወርድ ቤቱ ብቻውን የተተወ እና ለመታደስ እንኳ በማይችልበት ሁኔታ ላይ መሆኑን አየች በአትክልት ስፍራው ላይ ረጃጅም አረሞች እና መስኮቶቹ ቆሻሻ ናቸው። በማዘን ልጅቷ ቤቷ ወዳለበት ዞር አለች። ለእሷ ግርምት በሸለቆው በወዲያኛው በኩል በኮረብታ ላይ መስኮቶቹ ወርቅማ ብርሀን ያላቸው አንድ ቤት ትመለከታለች እናም የእራሷ ቤት እንደሆነ ወዲያው ተረዳች!8
አንዳንዴ ልክ እንደዚች ልጅ ሌሎች ያሏቸውን ወይም የሆኑትን በመመልከት ከነሱ ለመወዳደር እንደምናንስ ሊሰማን ይችላል። በፒንተረስት ወይም በኢንስትግራም አይነት ህይወት ወይም በትምህርት ቤታችን ወይም በስራ ቦታችን ባለ አይት ህይወት በማተኮር አእምሮአችን በመወዳደር ሀሳብ ይሞላል። ሆኖም ግን ጊዜ ወሰድ አድርገን “ብዙ በረከቶቻችንን ስንቆር”9 በእውነተኛ እይታ እና በማስተዋ እግዚአብሔር ለሁሉም ልጆቹ ያለውን ደግነትን እናያለን።
ስምንትም ሆነ መቶ ስምንት አመት ብንሆን፤ በማንኛውም ቢሆን በማንሀንታን በቆመ ትልቅ አፓርትመንት ሆነ ሁለት ቋሚ ላይ ባለ የማሌዢያ ቤት ወይም በሞንጓሊ በሚገኝ ጎጆ የወንጌሉን ብርሀን ወደ አካባቢያችን ማምጣት እንችላለን። በለንበት ሁኔታውስጥ ሆነን በሌሎች ውስጥ መልካምነትን ለማየት መወሰን እንችላለን። ወጣት እና በጣም ወጣት ያልሆኑ ሴቶች በራስ መተማመንን እና የሌሎችን እምነት የሚገነቡ ቃላትን ለመጠቀም በመምረጥ በማንኛውም ቦታ ልግስናን ማሳየት ይችላሉ።
ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ ስለ አንድ ከጓደኞቹ በላይ በትምህርት ቤት ይሾፍበት ስለነበረ ልጅ ተናገረ። ጥቂት አመት በኃላ ቦታ በመቀየር ውትድርናን ተቀላቀለ ትምህርትን ተቀበለ እናም በቤተክርስቲያኑ ተሳታፊ ሆነ። የህይወቱ ጊዜ ሁሉ በውጤታማ ተሞኦክር የተሞላ ነበር።
ከብዙ አመታት በኃላ ወደ ትውልድ ቦታው ተመለሰ። ገር ግን ህዝቡ የእሱን መሻሻል እና ማደጉን ሊቀበሉ አልቻሉም። ለእነሱ ያረጀ እና ሌላም ሌላም ነገር ነበር እና በዛ አይነት ሁኔታ ነበር ያጎሳቆሉት። እያደር ይህ መልካም ሰው ባዳበረው ችሎታው ሌሎችን ያልተቀበሉትን እና ያፌዙበትና ለማባረክ ሳይችል ወደ ቀድሞው ስኬታማ ማንነቱ ተመለስ።10 ምን አይነት ክስተት ነበር ለሱም ሆነ ለማህበረሰቡ።
ሀዋሪያው ጴጥሮስ “ከሁሉም በላይ በራሳችሁ መሀከል ልግስና ይኑራችሁ፤ ፍቅር የኃጢያትን ብዛት ይሸፍናልና” 11 ልዩ ልግስና ማለትም በሙሉ ልብ የሌሎችን ቂምን ደብቆ ከመያዝና ወይም ሉሎች ትዝ እንዲላቸው እና የነሱን ያለፈውን ድክመታቸውን ከማየት ይልቅ ስህተት እና መደናቀፍን በመርሳት ማሳየት እንችላለን።
ልክ እንደ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን በምናደርገው የእኛ ግዴታ እና በረከት ጥረት የሁሉንም ሰዎች መሻሻልን መቀበል ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን የሀጢያ ክፍያ ተረድቶ ትክክለኛ ለውጥ በህይወቱ ወይም በህይወቷ ለውጥ ሲያመጡ ማየት ምን ያህል ደስ የሚያሰኝ ስሜት ነው። ሌሎች ሰዎች ሲቀየሩ እና ወደ ጥምቀት ውሃ ውስጥ የሚገቡ እና በቤተመቅደስ በር ውስጥ ሲገቡ ያዩ ሚሺነሪዎች የተሰማቸው ደስታ ተሞክሮ— ሌሎች እንዲቀየሩና ማበረታት— እና መፍቀድ ትልቅ በረከት እንዳለው ምስክሮች ናቸው። የመንግስቱ አጠራጣሪ ተወዳዳ ተብለው የሚወሰዱት ሰዎች ሲቀበሏቸው እና የጌታ ፍቅር እንዲሰማቸው ሲረዷቸው አባላቶች ትልቅ እርካታ ይኖራቸዋል። የኢየሱስ ክርስቶስ ታላቁ ውበት ዘላለማዊ እድገት ነው—ለተሸለ ለመቀየር ብቻ አይደለም የተፈቀደልን ነገር ግን ለማበረታት እንዲሁ ደግሞም ለማዘዝ በመሻሻል ክትትል ላይ መቀጠል ታዘናል እና ወደ መጨረሻው ፍፅምና መድረስ ነው።
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንደመከሩት፥ “በመቶ ትትንሽ መንገዶች፣ ሁላችሁም የልግስና ሀላፊነት ለብሳችኋል። …እርስ በእርሳችን ፈራጅ ከመሆን ይልቅ በዚህ ህይወት አብረውን ለሚጓዙት የክርስተስ ፍቅር ይኑረን። እያንዳንዱ ወይም እያንዳንዷ የህይወትን ችግር ለመጋፈጥ [የራሱን ወይም የራሷን] ጥረት እያደረጉ እንደሆነ እናስተውል እናም እኛ ለመርዳት የራሳችንን ጥረት እናድርግ”።”12
ልግስና ቀና ቃላት ታጋሽ ነው፣ ደግ ነው እና የተሟላ ነው። ልግስና ሌሎችን ያስቀድማል፣ ትሁት ነው፣ እራሱን ይቆጣጠራል፣ በሌሎች ውስጥ ጥሩን ያያል እናም ሌላው ጥሩ ሲሰራ ደስ ይለዋል።13
በፅዮን እንደ እህት እና ወንድሞች “በአዳኙ ስም ለማባረክ እና ለማስደሰት ለሌሎች ሰብአዊ የሆነ ነገር ለማድረግ አንድ ላይ ሁላችንም ልንሰራ ቃል እንገባለን?”14 ሌሎችን እንዲሻሻሉ በመፍቀድ እና በማበረታት በፍቅር እና በታላቅ ተስፋ በሌሎች ያለውን ውበት ለመፈለግ እና ለመቀበል እንችላለን? ራሳችንን ለማሻሻል ለመስራት በምቀጠል ስለሌሎች ውጤታማነት ለመደሰት እንችላለን?
አዎን፣ እኛም በሌሎች ውስጥ ቀና ነገር በመፈለግ እና በመካፈል እንዲሁም የነሱን ትንሽ ፍፁም አለመሆን እንዲጠፋ በማድረግ የወንጌሉን ብርሀን ወደ ቤታችን፣ ትምህርት ቤት እና ስራ ቦታችን ማምጣት እንችላለን ። በዚህ አንዳንዴ በሚከብድ እና ፍፁም ባልሆነ አለም ውስጥ ዝም ብለን ሀጢያት ስንሳራ ንሰሀ አንድን ገባ ስላስቻለው አደኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ሳስብ ልቤን ምን ያህል ደስታን ይሞላዋል!
የእርሱን ፍጹም ምሳሌ ስንከተል፣ በዚህ ህይወት ታላቅ ደስታ እና ከሰማይ አባታችን ጋር የዘለአለም ህይወት የተስፋ ቅል የሚያመጣውን የልግስና ስጦታ ለመቀበል እንደምንችል እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።