ፈዋሹ መምህር
በኃጢያት ምክንያት የሚመጣውን ሀዘን፣ በሌሎች ስራዎች የሚጣውን ስቃይ፣ ወይም የሟች ህይወት እውነቶችን—በብቻ መጋፈጥ የለብንም።
ሽልማት የሚሰጠኝ አንዱ እድሌ መጓዝ ነው–ይህም በአለም አቀፍ ውስጥ ካሉት እህቶቼ እንድማር ይረዳኛል። ከእናንተ ጋር ከንድ በክንድ፣ ፊት ለፊት፣ እና ልብ በልብ ከመሆን የሚሻል ምንም የለም።
በዚህ አይነት አጋጣሚ አንድ ጊዜ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር መሪ እንዲህ ጠየቀች፣ “ሴቶች ማተኮር የሚገባቸው አንድ ልዩ ነገር አለን?”
የፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ለእህቶቼ ልመና” የሚለው ንግግር በአዕምሮዬ ሲመጣም፣ “አዎን!” ብዬ መለስኩኝ። ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “የክርስቶስ ትምህርት መረዳት ጠንካራ መሰረት ያላቸው ሴቶች ያስፈልጉናል።”1
ኔፊ የክርስቶስን ትምህር እንዲህ ገልጾታል፥
“የምትገቡበትም በር ንስሀ እና የውሀ ጥምቀት ነው፤ ከዚያም የኃጢአታችሁ ስርየት በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ይመጣሉ። …
“እናም አሁን ... ሁሉ ተደርጓልን? ብዬ እጠይቃችኋለሁ። እነሆ፣ አይደለም፣ እላችኋለሁ፤ በማይናወጥ እምነትና ለማዳን ኃያል በሆነው በክርስቶስ ቃል ባይሆን በምህረቱ ሙሉ በሙሉ በመተማመን እስከዚህ አትመጡም ነበር።
“ስለሆነም በክርስቶስ ባላችሁ ጠንካራ እምነት መቀጠል አለባችሁ፣ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር ይኖራችኋል። ስለሆነም አብም የምትቀጥሉ ከሆነ፣ የክርስቶስን ቃል ብትመገቡ፣ እናም እስከመጨረሻው ብትፀኑ፣ እነሆ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል ይላል።
“… ንገዱ ይህ ነው፤ ሰው በእግዚአብሔር መንግስት መዳን የሚችልበት ከሰማይ በታች የተሰጠ ሌላ መንገድም ሆነ ስም የለምና። አሁንም እነሆ፣ ይህ የክርስቶስ ትምህርት ነው።”2
እነዚህን መሰረታዊ መርሆች የመረዳት ጠንካራ መሰረት ለምን ያስፈልገናል።
እርዳታ በጣም የሚያስፈልጋቸው፣ ግን የዘለአለም እርዳታ ወደሚያቀርበው የማይዞሩ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች ጋር በብዙ ጊዜ ተገናኝቻለሁ። በብዙ ጊዜ “ታላቅ እና ሰፊ ህንጻን” በመፈተሽ መረዳጃን ይፈልጋሉ።3
መልስ ስንሰጥ እና የክርስቶስ ትምህርት የምንረዳበትን ስናሳድግ፣ “ታላቅ የደስታ እቅድ” ዝልቅ መረጃ እንዳለን ወዲያው እናገኛለን።4 ደግሞም አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የዚህ እቅድ ዋና ክፍል እንደሆነም እናውቃለን።
የክርስቶስ ትምህርትን በግል ጉዳዮቻችን ላይ ለመጠቀም ስንማር፣ ለአዳኝ ያለን ፍቅር ያድጋል። እናም “የሚመስለው ልዩነት ምንም ቢሆን፣ ሁላችንም ዘለአለማዊ የሆነው የኃጢያት ክፍያ ሁላችንም እንደሚያስፈልጉን” እንረዳለን።5 እርሱ የእኛ መሰረት —“የቤዛችን አለት፣ … እርግጠኛ መሰረት፣ [ከገነባንበት] [የማንወድቅበት] መሰረት” እንደሆነ እንረዳለን።6
ሰላም እና መረዳትን ስንፈልግ እና ልዩ በሆነው በስጋዊ ጉዞአችን በደስታ ስንጸና፣ ይህ ትምህርት እንዴት ሊባርከን ይችላል?
ኔፊ እንዳለው፣ “በማይናወጥ እምነትና ለማዳን ኃያል በሆነው በክርስቶስ ... በምህረቱ ሙሉ በሙሉ በመተማመን”7 እንድንጀምር ሀሳቤን አቀርባለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት ማንኛውንም ፈተና እንድንቋቋም ያስችለናል።
እኛ፣ በእርግጥም፣ እምነታችን ዝልቅ እና ከሰማይ አባታችን እና ከልጁ ጋር ያለን ግንኙነት በፈተና እንደሚነጠእት በአብዛኛው ሆኖ እናገኘዋለን። ሶስት ምሳሌዎች ላካፍል።
መጀመሪያ፣ አዳኝ፣ ፈዋሽ መምህር፣ ልባችንን ለመቀየር እና በራሳችን ኃጢያት ምክንያት ከሚመጣው ሀዘን እረፍት ለመስጠት ሀይል አለው። የሰማርያን ሴት በውሀ ጉድጓድ አጠገብ ባስተማራት ጊዜ፣ ስለከባዱ ኃጢያቷ ያውቅ ነበር። ነገር ግን፣ “እግዚአብሔር ልብን ያያል፣”8 እናም ለመማር የሚችል ልብ እንዳላትም አውቋል።
ሴቷ እንደ ህያው ውሀ ምሳሌ ወደሆነው ወደ ውሀ ጉድጓድ በመጣችበት ጊዜ፣ ኢየሱስ በቀላል እንዲህ አላት፣ “ውሀ አጠጪኝ።” አዳኛችን እንደዚህም እና ወደ እርሱ ስንመጣ ለእኛ በምናውቀው ድምጽ ነው የሚያናግረን–ያውቀናልና: ባለንበር ይገናኘናል። ማን በመሆኑ እና ለእኛ ባደረገው ምክንያትም፣ ስለእኛ ይረዳል። ስቃያችን አጋጥሞት ስለነበር፣ ስንፈልገውም ህያው ውሀ ይሰጠናል። ለሰማርያ ሴትም ይህን እንዲህ በማለት አስተማራት፣ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር።” በመጨረሻም በመረዳት፣ ሴቷ በእምነት መለሰች እናም ጠየቀች፣ “ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ... ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው።”
የሰማርያ ሴት ይህን አጋጣሚ ገጌታ ጋር ከነበራት በኋላ፣ እርሷም “እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም፣
“ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? አልች።”
ምስክርነት ተቀበለች—የህይወት ውሀን መቀበል ጀመረች—እናም የእርሱን መለኮታዊነት ለሌሎች ለመመስከር ፈለገች።9
ቱሁት እና የሚማር ልብ ኖሮን ወደ እርሱ ስንመጣ—ምንም እንኳን ልባችን በስህተቶች፣ በኃጢያቶች፣ እና በመተላለፍ ይከበዱ ቢሆኑም—እርሱ ሊቀይረን ይችላል፣ “እርሱ ለማዳን ሀያል ነውና።”10 ልቦች ተቀይረው፣ እኛም፣ እንደ ሰማርያ ሴት፣ ስለእርሱ ለመመስከር ወደ ከተማዎቻችን፣ ወደ ቤቶቻችን፣ ወደ ትምህርት ቤቶቻችን፣ እና ወደ ስራ ቦታዎቻችን ለመሄድ እንችላለን።
ሁለተኛ፣ የሚፈውስ መምህር በሌሎች ጻድቅ ባልሆኑ ስራዎች ስቃይ ሲያጋጥመን እኛን ለማፅናናት እና ለማጠናከር ይችላል። በከባድ ሸከም ዝቅ ካሉ ሴቶች ጋር ብዙ ንግግሮች ነበረኝ። ከቤተመቅደስ የሚጀምረው የቃል ኪዳን መንገድ የሚያስቸግር የመፈወስ ጉዞ ሆናል። ከተሰበረ ቃል ኪዳን፣ በተሰበረ ልብ፣ እና እምነት በማጣት ይሰቃያሉ። አብዛኛዎችም፣ በሌሎች ሰዎች ሱስ ምክንያት የምንዝርና የቃላት ሰለባ፣ እናም በፍትወተ ስጋዊና በስሜት ተጎሳቋዮች ናቸው።
እነዚህ አጋጣሚዎች፣ ምንም እንኳን የእነርሱ ጥፋት ባይሆኑም፣ ብዙዎች ጥፋተኘት እና እፍረት ይሰማቸዋል። የሚያጋጥማቸውን ሀይለኛ ስሜት እንዲት መቆጣጠር እንደሚችሉ ባለመረዳት፣ ብዙዎች እነዚህን ለመቅበር፣ ወደ ውስጣቸውም በዝልቅ ለመግፋት ይሞክራሉ።
ተስፋ እና መፈወስ በምስጢር በጨለመ ጥልቁ ውስጥ ሳይሆን በአዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ብርሀን እና ፍቅር ውስጥ ነው የሚገኙት።11 ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት እንደመሰከሩት፥ “ከከፍተኛ ኃጢያት ራሳችሁ ንጹህ ከሆናችሁ፣ አስፈላጊ ባልሆነ ሁኔታ በሌሎች ኃጢያቶች ምክንያት አትሰቃዩ። … ርህራሄ ሊሰማችሁ ትችላላችሁ።. … ግን የሀላፊነት ስሜትን በራሳችሁ ላይ አታድርጉት። … የምታፈቅሯቸውን ለመርዳት የምትችሉትን ካደረጋችሁ፣ ሸከሙን በአዳኝ እግር ስር ጣሉት። … ስታደርጉም፣ ሰላም ማገኘት ብቻ ሳይሆን፣ በንስሀ እና በታዛዥነት በኩል የምናፈቅራቸውን ኃጢያት ሸከም ለማንሳት አዳኝ ሀይል እንዳለው ያላችሁን እምነትንታሳያላችሁ።”
እንዲህም ቀጠሉ፥ ““ሙሉ መፈወስ የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እና ፍትህ ያልሆነ እና የማይገባ ቁስልን በኃጢያት ክፍያው ለመፈወስ ሀይል እና ችሎታ እንዳለው ባላችሁ እምነት በኩል ነው።”12
ራሳችሁን በዚህ አይነት ጉዳይ ካገኛችሁ፣ እህቶች፣ መፈወስ የረጅም ጊዜ ሂደት ሊሆን ይችልል። ይህም በጽሎት መመሪያን እና ትክክለኛ የሆነ እርዳታን መፈለግ፣ በተጨማሪ በትክክል ሹመት ከተሰጣቸው የክህነት ተሸካሚዎች ጋር መማከር ያስፈልገዋል። በግፅ ለመነጋገር ስትማሩ፣ ትክክለኛ ገደብን መስርቱ እና ምናልባትም የሙያ ምክርንም ፈልጉ። መንፈሳዊ ጤንነትን በዚህ ሂደት መጠበቅም አስፈላጊ ነው። መለኮታዊ ማንነታችሁን አስታውሱ፥ እናንተ የሰማይ ወላጆች ሴት ልጆች ናችሁ። የአባታችሁን ዘለአለማዊ እቅድን እመኑ። የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት መሰረት የምትረዱበትን በየቀኑ መገንባትን ቀጥሉ። ከአዳኝ ህያው ውሀ ጉድጓዳ ለመጠጣት እምነትን በየቀኑ ተለማመዱ። ለእኛ በስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ብኩል እንድናገኛቸው የሚቻሉትን እያንዳንዱን መንፈሳዊ በረከት ሀይል ላይ እንመካ። እናም የአዳኝ እና የኃጢያት ክፍያን ፈዋሽ ሀይል በህይወታችሁ ውስጥ እንዲገቡ ፍቀዱ።
ሶስተኛ፣ እንደ መዓት፣ የኧእምሮ በሽታ፣ ህመም፣ሂልጊዜ የሚሰማ ህመም፣ እና ሞት አይነት የሚያሰቃዩ “የሟችነት እውነቶች፣”13 ሲያጋጥሙን ፈዋሽ መምህርት ሊያፅናናን እና ሊደግፈን ይችላል። የአይምሮ በሽታ ካላት ጆዚ ከምትባል ወጣት ሴት ጋር በቅርብ በዋውቄ ነበር። ከእኔ ጋር እንዳካፈለች ወደ መፈወስ የተጓዘችው ጉዞ ትንሹ ይህ ነበር።
“ከጭለማው ይበልጥ የሚደርሰው ቤተሰቤ እና እኔ ‘የመሬት ቀናት’ ብለን በምንጠራበት ነው። ይህም የሚጀምረው የስሜት ጫን እና ለድምፅ፣ ለመነካት፣ ወይም ለብርሀን ከፍተኛ ስሜት የሚሰማበት ሲደርስ ነው። ይህም የአዕምሮ ስሻይ ከፍተኛ ቦታ ነው። ልረሳው የማልችል ልዩ የነበረ አንድ ቀን ነበር።
“ይህም በጎዞው መጀመሪያ ላይ ስለነበር፣ አጋጣሚውን በጣም የሚያስፈራ አደረገው። ሳለቅስ፣ እምባም በፊቴ እየሮጠ አየር ለማግኘት በሀይል ስተነፍስ አስታውሳለሁ። ነገር ግን ያም ስቃይ፣ እኔን ለመርዳት በጣም ፈልጋ፣ ድንጋጤ እናቴን ሲያጥለቀልቃት ስመለከት ከነበረ በላይ አይነት ከፍተኛ አልነበረም።
“ከተሰበረው አዕሮዬ ጋር የተሰበረ ልብ መጣ። ነገር ግን ጭለማ ጥልቅ ቢሆንም፣ ታላቅ ታዕምርን ከማግኘት ትንሽ ብቻ የቀረን እንደነበርን አላወቅንም ነበር።
“ረጅሙ ሰዓት ሲቀጥልም፣ እናቴደጋግማ እንዲህ አሾከሾከችልኝ፣ ‘ካንቺ ይህን ለመውሰድ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ።’
“ይህም እያለ፣ ጭለማው ተስፋፋ፣ እናም ምንም ተጨማሪ ለማድረግ እንደማልችል ባመንኩበት ጊዜ፣ አንድ ታእምራት የሆነ ነገር ደረሰ።
“ከፍተኛ እና አስደናቂ የሆነ ሀይል በድንገት ሰውነቴን ሞላው። ከዚያም፣ ‘በራሴ በላይ በሆነ ሀይል፣’14 የእኔን ስቃይ ለመሸከም ያላትን ፍላጎት በተደጋጋሚ ለገለጸችበት መልስ በታላቅ እምነት ህይወትን የሚቀይሩ ቃላትን ለእናቴ አወጅኩኝ። እንዲህ አልኩኝ፣ ‘የለብሽም፣ ሌላ ይህን አድርጓልና።’”
ለመነቃነቅ ካማያስችል ከአዕምሮ በሽታ የጭለማ ጥልቁ፣ ጆዚ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለኃጢያት ክፍያው ለመመስከር ጥንካሬን ሳበች።
በዚያ ቀን በሙሉ አልተፈወሰችም፣ ነገር ግን በጥልቅ ጭለማ ጊዜ የተስፋ ብርሀን ተቀበለች። እናም ዛሬ፣ የክርስቶስ ትምህርትን በመረዳት ጠንካራ መሰረት እና በየቀኑ በአዳኝ ህያው ውሀ በመታደስ፣ ጆዚ ወደ መፈወስ እና በፈዋሽ መምህር የማይነቃነቅ እምነት ጉዞዋን ቀጠለች። ሌሎችን በመንገድም ትረዳለች። እንዲህም አለች፣ “ጭለማው እንደማይቋረጥ ስሜት ሲመጣም፣ በደግ ምህረቱ ትዝታ ላይ እመካለሁ። በአስቸጋሪ ጊዜዎች ስጓዝም እንደ መሪ መብራቶች ያገለግላሉ።”15
እህቶች፣ እንዲህም እመሰክራለሁ—
በኃጢያት የመጡትን የሀዘን ሸከሞችን በብቻችሁ መሸከም የለባችሁም።
በሌሎች ጻድቅ ባልሆነ ስራ ምክንያት የሚመጡትን ስቃዮች በብቻችሁ መሸከም የለባችሁም።
የሟች ህይወት እውነቶችን የሚያሰቃዩ አጋጣሚዎችን በብቻችሁ መጋፈጥ የለባችሁም።
አዳኝ እንደሚማጸነው፥
“እፈውሳችሁ ዘንድ ንስሃ ገብታችሁ እናም ተለውጣችሁ አሁን ወደ እኔ አትመለሱምን??
“… በእውነት ወደ እኔ ከመጣችሁ ዘለዓለማዊ ህይወትን ታገኛላችሁ። እነሆ የምህረት ክንዴ ወደ እናንተ ተዘርግታለች፣ እናም ማንም ቢመጣ እቀበለዋለሁ ...።”16
“[እርሱም] ይህን ከእናንተ ለመውሰድ ማንኛውንም ነገር ያደርጋል።” በእርግጥም፣ “[እርሱ] ይህን አሁንም አድርጎታል።” በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በፈዋሹ መምህር፣ ስም አሜን።