2010–2019 (እ.አ.አ)
አገልግሉ
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


10:58

አገልግሉ

እያንዳንዱ አባል የሚፈለግ ነው፣ እናም እያንዳንዱ አባል ለማገልገል እድል ያስፈልገዋል።

በልጅነቴ ከአጎቴ ላይማን እና ከአክስቴ ዶርቲ ጋር በእርሻ ስፍራቸው አብሬ መስራት እደሰትበት ነበር። አጎቴ ላይማን በአብዛኛው ስራችንን ይመራል፣ እናም አክስቴ ዶርቲ ትረዳ እና አሮጌውን የዶች መኪና ትነዳ ነበር። በጭቃ ውስጥ መኪናውን ስንነዳ ወይም በኮረብታ ላይ ስንወጣ ያስደስተኝ እንደ ነበር አስታውሳለሁ። አጎቴ ላይማንም፣ “ወደ ኮምፖውንድ አስገቢያት፣ ዶርቲ!” ብሎ ይጮህ ነበር። በዚያም ጊዜ ነበር መጸለይየምጀምረው። እንደምንም፣ በጌታ እርዳታ እና የማርሹ ጥርሶች ከተፋጩ በኋላ፣ አክስቴ ዶርቲ ኮምፓውንዱን ታገኘዋለች። የመኪና ጎማዎቹ እየዞሩ እና እየገፉ፣ መኪናው ወደፊት ዘልሎ ይሄዳል እናም ስራችንን እንቀጥላለን።

“ወደ ኮምፓውንድ ማስገባት” ማለት የመኪና ማርሹን በልዩ ሁኔታ ቀይሮ የተለያዩ የማርሽ ጥርሶች አብረው በመስራት ለመኪናው ከፍተኛ ሀይል እንዲሰጡት የሚያደርግበት ነው።1 የኮምፓውንድ ማርሽ፣ ከአራት ጎማዎች በአንድነት ከሚሰሩበት ጋር፣ ወደታችኛው ማርሽ ለማስገባት፣ ሀይልን ለመጨመር እና ወደፊት ለመሄድ የሚፈቅድላችሁ ነው።

የኮምፓውንድ ማርሽ

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ—በዎርዳችን እና በቅርንጫፎቻችን፣ በቡድኖቻችን እና በደጋፊ ድርጅቶቻችን ውስጥ ስናገለግል እያንዳንዶቻችንን እንደ ኮምፓውንድ ማርሽ ለማሰብ እወዳለሁ። ማርሾቹ አንድ ላይ ታላቅ ሀይል እንደሚሰጡ፣ እኛም አንድ ላይ ስንቀናጅ ታላቅ ሀይል አለን። ለማገልገል አንድ ስንተባበር፣ በብቻችን ለማድረግ ከምንችለው በላይ አብረን ብዙ ለማከናወን እንችላለን። በምናገለግልበት ነገጣጠም እና መተባበር እና በጌታ ስራ መርዳት የሚያስደስት ነው።

ማገልገል በረከት ነው

የማገልገል እድል በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከሚገኙት ታላቅ በረከቶች መካከል አንዱ ነው።2 ጌት እንዳለው፣ “ብትወዱኝ ታገለግሉኛላችሁ፣”3 እናም የምናገለግለው ሌሎችን በማገልገል ነው።4

ስናገለግል ወደ እግዚአብሔር እንቀርባለን።5 ካላደረግን ለማወቅ በማንችልበት መንገድም እርሱን ለማወቅ እንችላለን። በእርሱ ያለን እምነትም ይጨምራል። ችግሮቻችንንም በልዩ እይታ እንመለከታቸዋለን። ህይወትም በተጨማሪ የሚያረካ ይሆናል። ለሌሎች ያለን ፍቅር፣ እንዲሁም ሌሎችን የማገልገል ፍላጎት ይጨምራል። በዚህ በተባረከ ሂደት በኩል፣ እንደ እግዚአብሔር እንሆናለን፣ እናም ወደ እርሱ ለመመለስም በደንብ የተዘጋጀን እንሆናለን።6

ፕሬዘደንት ሜሪዮን ጂ. ሮምኒ እንዳስተማሩት፥ “አገልግሎት በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ለመኖር መብት ለማግኘት በዚህ ምድር ላይ የምንጸናበት አይደለም። አገልግሎት በሰለስቲያል መንግስጥ ውስጥ ከፍ ያለ ህይወት የሚሰራበት የደም ስር ነው።”7

ማገልገል አስቸጋሪ ሊሆንም ይችላል

ነገር ግን፣ የሚያስፈራ ነገር እንድናደርግ ከተጠየቅን፣ በማገልገል ከደከምን፣ ወይም መጀመሪያ አስደሳች የማይመስለንን ነግረ ለማድረግ ከተጠራል፣ በቤተክርስቲያኗ ማገልገል አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

በቅርብ አዲስ ሀላፊነትን ተቀበልኩኝ። በአፍሪካ ደቡብ ምስራቅ ክልል ውስጥ አገለግል ነበር። ቤተክርስቲያኗ አዲስ በሆነችበት እና እየተመሰረተች ባለችበት ማገልገሉ በጣም የሚያስደስት ነበር፣ እናም ቅዱሳንን እንወድ ነበር። ከዚያም ወደ ቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ መምሪያ እንድመለስ ተጠራሁ፣ እና በእውነትም፣ የተደሰትኩኝ አልነበርኩም። ሀላፊነት መቀየር አንዳንድ የማይታወቁትን አመጣ።

አንድ ምሽት የሚመጣውን ለውጥ ካሰብኩበት በኋላ፣ ስለቅድመ አያቴ አያት ጆሴፍ ስክን ህልም አየሁ። እርሱ እና ባለቤቱ፣ ማሪያ፣ ወደ ናቩ ሲሄዱ ለማገልገል ፍላጎት እንደነበረው፣ ስለዚህ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን እንደፈለገና እንዴት ለመርዳት እነሚችል እንደጠየቀ ከማስታወሻ መጽሀፉ በማንበብ አውቅ ነበር። ነቢዩም ከከተማው በስተምስራቅ በኩል ትንሽ ኪሎ ሜትር በራቀ በስሚዝ የእርሻ ቦታ ውስጥ እንዲያገለግል እና የሚችለውን ያህል እንዲያደርግ ጠየቀም፣ እርሱም እንዲህ አደረገ። በስሚዝ እርሻ ላይ መስራት ጀመረ።8

ጆሴፍ ስኪን ሀላፊነቱን በዚህ መንገድ ለመቀበል ስላለው ልዩ እድል አሰላሰልኩኝ። በድንገትም እኔ እንዲህ አይነት ልዩ እድል እንዳለኝ፣ ሁላችንም እንዳለን፣ ተረዳሁ።የቤየክርስቲያን ጥሪ የሚመጣም በእግዚአብሔር—በተመደቡት አገልጋዮቹ በኩል ነው።9

አዲሱ ሀላፊነቴ በመንፈስ የተነሳሳ እንደሆነ ልይ የመንፈስ ማረጋገጫ አገኘሁ። እንደዚያ አይነት ግንኙነት፣ እንዲሁም ጥሪዎቻችን የሚመጡት በክህነት መሪዎች በኩል ከእግዚአብሔር እንደሆነ፣ ማወቁ አስፈላጊ ነው። ከዚህ አጋጣሚ በኋላ፣ አስተያየቴ ተቀየረ፣ እናም ለማገልገል ጥልቅ የሆነ ፍላጎት ሞላኝ። ለንስሀ መግባት በረከት እና ለተቀየረው ልቤ ምስጋና አለኝ። አዲሱን ሀላፊነቴ እወደዋለሁ።

ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ጥሪአችን የክህነት መሪያችን ሀሳብ እንደሆነ፣ ወይም ይህም ለእኛ የተሰጠው ማንም ሊቀበለው ስለማይፈልግ ነው ብለን ብናስብበትም፣ ስናገለግል እንባረካለን። ነገር ግን የእግዚአብሔርን እጅ በጥሪአቸን ስንገነዘብ እና በሙሉ ልባችን ስናገለግል፣ ለአገልግሎታችን ተጨማሪ ሀይል ይመጣል፣ እናም የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አገልጋይ እንሆናለን።

አገልግሎች እምነት ያስፈልገዋል

ጥሪን ማሟላት እምነት ያስፈልገዋል። ጆሴፍ በእርሻ ቦታው ላይ መስራት ከጀመረ በትንሽ ጊዜ በኋላ፣ እርሱ እና መሪያ በጣም ታመሙ። ምንም ገንዘብ አልነበራቸውም እናም ከእንግዳዎች መካከል ነበሩ። ለእነርሱም ይህ የሚያስቸግር ጊዘ ነበር። በማስታወሻው ውስጥም፣ ጆሴፍ እንዲህ ጻፈ፣ “ምንም እንኳን ዲያብሎስ ሊያጠፋን እና ሊያዞረን ቦሞክርም፣ ባለን ትንሽ እምነተም በመስራት ቀጠለን [እናም] ቤተክርስቲያኗን በጥብቅ ያዝን።”10

እኔ፣ ለብዙ መቶ ሌሎች ትውልዶ ጋር፣ ጆሴፍ እና መሪያ በመዞር ስላለተመለሱ ዘለአለማዊ ምስጋና አለኝ። በጥሪዎቻችን እና በሀላፊነቶቻችን ስንጸና እና ባለን እምነት በሙሉ አጥብቀን ስንይዝ በረከቶች ይመጣሉ።

ስታትስተምር የክፍ አባላትን ከፍ የምታደረግ አስድናቂ የወንጌል ትምህርት አስተማሪን አውቃለሁ፣ ነገር ግን ይህ ሁልጊዜ እንደዚህ አለነበረም። በቤተክርስቲያኗ አባል ከሆነች በኋላ፣ የመጀመሪያ ክፍል እንድታስተምር ጥሪ ተሰጣት። የማስተማር ችሎታ እንዳልነበራት ይሰማት ነበር፣ ነገር ግን የማገልገል አስፈላጊነትን ስላወቀች፣ ተቀበለችው። ወዲያው ፍርሀት አጥለቀለቃት፣ እናም እንዳታስተምን ለማድረግም ተሳታፊነቷን አቆመች። በምስጋናም የቤት ለቤት አስተማሪይዋ እንደማትመጣ ተመለከተ፣ ጎበኛት፣ እና እንድትመለስ ግብዣ ሰጣት። ኤጲስ ቆጶሱ እና የዎርድ አባላት እርዳታ ሰጧት። በመጨረሻም፣ እምነቷ እያደገ፣ ልጆችን ማስተማር ጀመረች። እርሷም Teaching in the Savior’s Way ውስጥ ያለውን መሰረታዊ መርሆች ስትጠቀም፣ ጌታ ጥረቷን ባረከው፣ እናም ጥሩ ስጦታ ያላት አስተማሪ ሆነች።11

በሁላችንም ውስጥ ያለው የፍጥረት ሰው “ለማገልገል የተዘጋጀሁ አይደለሁም፣ ተጨማሪ መማር ያስፈልገኛን፣” “ደክሞኛል እና እረፍት ያስፈልገኛል፣” “እድሜዬ ገፍቷል፣ የሌላ ሰው ተራ ነው፣” ወይም “በስራ የተጠመድኩኝ ነኝ” በሚሉ ምክንያቶች ላለማገልገል ዝንባሌ ይኖረናል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ጥሪን መቀበል እና ማከናወን የእምነት ስራ ነው። ቢያችን ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በተደጋጋሚ ያስተማሩትን ለማመን እንችላለን፥ “ጌታ ሲጠራ፣ ጌታ ለዚህ ብቁ ያደርጋል፣” እናም “እኛ በጌታ ስራ ላይ እያለን፣ ለጌታ እርዳታ መብት አለን።”12 የተጥለቀለምን ብንሆንም ባንሆንም፣ በጣም የፈራን ወይም የተሰላቸን ብንሆንም፣ ጌታ ምርሽን እንድቀይር፣ ሀይል እንድናገኝ፣ እና እንድናገለግል ይፈልገናል።

ፕሬዘደንት ሞንሰን እና አብረራቸው የሚያገለግሉት የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለት ሐዋሪያት በስራ የተጠመዱበትን ወይም በጣም የደከሙበትን ምንም ምልክት አላይም። እምነትን ስንለማመድ፣ ሀላፊነትን ስንቀበል፣ እና በልብ ውሳኔ እና በተቀደሰ አላማ ይህን ስናከናውን ስለሚመጣው ሀይል በሚያነሳሳ ምሳሌ ያሳዩናል። እነርሱም “[ትከሻቸውን] ባጋሪው ላይ ያደረጉት”13 ከብዙ አመት በፊት ነው፣ እናም ወደፊት ወደላይም በመግፋት እየቀጠሉም ናቸው።

አዎን፣ በአስፈላጊ ጥሪዎችን እያገለገሉ ናቸው፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ጥሩ አስፈላጊ ነው። የድሮው የቤተክርስቲያኗ ነቢይ እና ፕሬዘደንት የነበሩት ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ እንዳሉት፣ “በዚህ ታላቅ ስራ ሁላችን አምድ ላይ ነን። … በሀላፊነት ክባችሁ እንደ እኔ ሀላፊነት ክብ ግዴታችሁ ኮስታራ ነው። በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ትንሽ ጠቅም ያለው ምንም ጥሪ የለም።”14 እያንዳንዱ ጥሩ አስፈላጊ ነው።15

እናገልግል

በእምነት እንነሳ፣ “[ትከሻዎቻችንን] በጋሪው ላይ እናድርግ፣” እናም ይህን “ብቁ ስራ” እንግፋ።16 እኛም ከታማኝ አክስት ዶርቲ ጋር “ወደ ኮምፓውንድ እናስገባውን” እናም እናገልገል። እንደ ወንድሞች እና እህቶች፣ እናገልግል።

ኤጲስ ቆጶሳችሁን ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዘደንታችሁን ለማስደሰት ከፈለጋችሁ፣ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፣ “እንዴት ለመርዳት እችላለሁ?” “ጌታ የት እንዳገለግል ይፈልገኛል?” እርሱም ሲጸልይ እና የግል፣ የቤተሰብ፣ እና የስራ ሀላፊነታችሁን ሲያስብበት፣ ትክክለኛ የሆነ ጥሪ ለእናንተ ለመስጠት በመንፈስ ይነሳሳል። በጥሪያችሁ ስትለዩም፣ ውጤታማ እንድትሆኑ የክህነት በረከቶችን ትቀበላላችሁ። እናንተምትባረካላችሁ! እያንዳንዱ አባል የሚፈለግ ነው፣ እናም እያንዳንዱ አባል ለማገልገል እድል ያስፈልገዋል።17

ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌአችን ነው

ምሳሌአችን ኢየሱስ ህይወቱን ለአባቱ ስራ አሳልፎ ሰጥቷል። አለም ከመደራጀቷ በፊት በነበረው ታላቅ ሸንጎ፣ ከመጀመሪያ ጀምሮ የተመረጠው እና የተቀባው ኢየሱስ “በዚህ አለሁ፣ እኔን ላከኝ”18 በማለት ፈቃደኛ ሆነ። ይህን በማድረግ፣ ለሁላችንም አገልጋይ ሆነ። በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው በኩል በምንቀበለው ሀይል በኩል፣ እኛም ለማገልገል እንችላለን። እርሱም ይረዳናል።19

በግል ጉዳዮች ምክንያት በቤተክርስቲያኗ በልምድ ሁኔታ አሁን ለማገልገል ለማትችሉት ግን ህይወታችሁን በአገልግሎት መንፈስ ለምትኖሩት፣ በልቤ የሚሰማን ፍቅሬን አቀርብላችኋለሁ። ለጥረታችሁ እንድትባረኩም እጸልያለሁ። በየሳምንቱ ጥሪያቸውን ለሚያጎሉ፣ እንዲሁም በቅርብ ጥሪን ለሚቀበሉ እና ለሚያገለግሉም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የምታደርጉት እና መስዋእቶቻችሁ በሙሉ፣ በልዩም ለምታገለግሏቸው፣ ዋጋ ያላቸው ናቸው። የሚያገለግሉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ጸጋ ይቀበላሉ።20

እድሜአችን ወይም ጉዳያችን ምንም ቢሆን፣ አገልግሎት “መንቀሳቀሻሽን”21 ይሁን። በጥሪአችሁ አገልግሉ። በሚስዮን አገልግሉ። አናታችሁን አገልግሉ። እንግዳን አገልግሉ። ጎረቤታችሁን አገልግሉ። በምንም አገልግሉ።

ለማገልገል እና የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ለመሆን በምንጥርበት ጐታ ይባርከን።22 ህያው እንደሆነ እና ስራውን እንደሚመራ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. See “Compound Gears,” technologystudent.com/gears1/gears3.htm; “Compound Gear Reduction,” curriculum.vexrobotics.com.

  2. Preach My Gospel: A Guide to Missionary Service (2004)፣ 3187 ተመልከቱ።

  3. ትምህርተ እና ቃልኪዳኖች 42፥29፤ እንዲሁም ትምህርተ እና ቃልኪዳኖች 59፥5 ተመልከቱ።

  4. ማትዎስ 25፥40ሞዛያ 2፥17 ተመልከቱ።

  5. ዮሀነስ 15፣26 ተመልከቱ።

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥4–6 ተመልከቱ።

  7. ሩሴል ኤም ኔልሰን፣ “The Spirit of Elijah፣” Ensign፣ ህዳር 1982 (እ.አ.አ.)፣ 93።

  8. See Joseph Skeen, reminiscences and diary, 7, Church History Library, Salt Lake City; see also Journal and History of Joseph Skeen (1996), 23.

  9. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥38የእምነት አንቀጾች 1፥5ተመልከቱ።

  10. Skeen, reminiscences and diary, 8, spelling and punctuation standardized; see also Journal and History of Joseph Skeen, 23; Luke 22:31; 2 Nephi 28:19–24; Alma 30:60; Doctrine and Covenants 10:22–27.

  11. Teaching in the Savior’s Way (2016), 37–38; Handbook 2: Administering the Church (2010), 5.3, 5.5.4 ተመልከቱ።

  12. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Duty Calls፣” Ensign፣ ግንቦት 1996 (እ.አ.አ)፣ 44።

  13. “Put Your Shoulder to the Wheel,” Hymns, no. 252.

  14. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “The Empty Tomb Bore Testimony፣” Ensign፣ ግንቦት 1995 (እ.አ.አ)፣ 71።

    ፕሬዘደንት ሒንክሊም በተጨማሪ እንዲህ አሉ፥ “እናንተ በሀላፊነታችሁ መከናወን ለመርካት እኔ እንዳለኝ እድል አላችሁ። የዚህ ስራ ወደፊት መግፋት በጋራ ጥረታችን የሚወሰን ነው። ጥሪአችሁ ምንም ቢሆን፣ መልካምን ለማከናወን ባለው አንድ እድል እንደ እኔ የተሞላ ነው። አስፈላጊ የሚሆነው ያም የመምህር ስራ መሆኑ ነው። ስራችን እርሱ እንዳደረገው መልካም ለመስራት መሄድ ነው” (“This Is the Work of the Master,” 71)።

    ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳሉት፥ “ስው ጥሪውን እንዴት ለማጉላት ይችላል? ከዚህ ጋር የተገናኘውን አገልግሎት በማከናወን ነው” (“Duty Calls,” 43)።

  15. አልማ 37፥6 ተመልከቱ።

  16. “Put Your Shoulder to the Wheel,” Hymns, no. 252.

  17. Handbook 2, 3.3.1, 3.3.3, 19.1.1, 19.4 ተመልከቱ። “በወንዶች እና ሴትች … በወንድ ልጆች እና በልጃገረዶች አገልግሎት በኩል ነው የእግዚአብሔር ስራ ተሚከናወነው” (Gospel Principles [2009], 163)።

  18. አብርሐም 3፥27

  19. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥5 ተመልከቱ።

  20. ሞዛያ 18፥26ተመልከቱ።

  21. “They, the Builders of the Nation,” Hymns, no. 36.

  22. ሞሮኒ 7፥48 ተመልከቱ።