2010–2019 (እ.አ.አ)
ግልፅ እና ውድ እውነቶች
ኦክተውበር 2015


7:10

ግልፅ እና ውድ እውነቶች

በሚያስቸግሩ ዘመናት ውስጥ ለመኖራችን የሰማይ አባት የሚከፍለን በዘመን ሙላት ጊዜ በመኖራችን ነው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ. ፓከር እና ሽማግሌዎች ኤል. ቶም ፔሪ እና ሪቻርድ ጂ. ስኮት ከመድረኩ በኋላ ያልተቀመጡበት እና በእነዚህ ስብሰባዎች በአንዱ ያልተናገሩበት አጠቃላይ ጉባዬ ከነበረ ብዙ አስር አመቶች አልፈው ነበር። ስለእነርሱ ያሉን ትዝታዎች የሚያሳዝኑ ነበሩ፣ እናም እነርሱን ከሚያከብሩ ምስጋና አድንቆች ጋር የእኔንም እጨምራለሁ፣ እያንዳንዱ ልዩ ቢሆኑም ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለኃጢያት ክፍያው ባላቸው ምስክር እና በምስክርነታቸው አንድ ነበሩ።

በተጨማሪም፣ እንደ እናንተም፣ እኔ ጥንካሬ አገኛለሁ እናም ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰንን እንደ ነቢይ፣ ባለራዕይ፣ እና ገላጭ እደግፋለሁ፣ እናም በታማኝነታቸው እና በሐዋሪያነት ከ50 አመት በላይ በሆነ አገልግሎት ባሳለፉት ሀላፊነታቸውም እደነቃለሁ።

እና በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ጠዋት፣ ከጠዋት 3 ሰዓት በኋላ፣ የኤጲስ ቆጶስ አመራር በዚህ ጉባኤ ውስጥ ከሚገኙት ከኢስያ ክልል አመራር ጋር ስብሰባ እየጀመርን እያለን ነበር ከፕሬዘደንት ሞንሰን እና ከአማካሪያቸው ጋር እንድንገናኝ የተጠራሁት። ከጊዜ በኋላ፣ ከቢሮአቸው አጠገብ ከሚገኘው በአመራር መሰብሰቢያ ውስጥ ስገባ፣ ከጠረቤዛው ባሻገር ስቀመጥ የተረበሽኩ እመስል ነበር፣ እና እኔን ለማረጋጋት በደግነት ሲያናግረኝ ነበር። ስለእድሜዬ በመናገር፣ ወጣት እንደምመስል እና ከእድሜዬ ይልቅ ወጣት እንደምመስል ተናገሩ።

ከዚያም፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን በጌታ ፍላጎት መሰረት በአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ ጥሪ እንደሚያቀርቡልኝ ገለጹ። ይህን ጥሪ እቀበል እንደሆነ ጠየቁኝ፣ እናም በመደንገጥ ክብር የሌለው በሚሰማ ማቃተት በኋላ፣ አዎን ብዬ መስል ሰጠሁ። ከዚያም፣ አብዛኛዎቹ ብቁ ያለመሆን ስሜት የሆኑ፣ በብዛት የነበሩትን ስሜት በድምጽ ለመግለጽ ከመቻሌ በፊት ፕሬዘደንት ሞንሰን እንደ ሐዋርያ ከብዙ አመት በፊት በፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ. ማኬይ እንዴት እንደተጠሩ፣ እና እንዴት ብቁ እንዳልሆኑ እንደተሰማቸው በመግለጽ አነጋገሩኝ። በተረጋጋ ሁኔታ እንዲህ አስተማሩኝ፣ “ኤጲስ ቆጶስ ስቲቨንሰን፣ ጌታ የሚጠራቸውን ብቁ ያደርጋል።” እነዚህ የሚያረጋጉ የነቢይ ቃላት የሰላም ምንጭ፣ ራስን በሚፈተሽበት አውሎ ንፋስ ውስጥ የሚያረጋጋ እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በቀን እና በምሽት ያልፉ በነበሩ በስቃይ ሰዓቶች ለስላሳ ስሜት ነበሩ።

ለእናንተ የነገርኳችሁን ለውድ ባለቤቴ፣ ሌሳ፣ በዚያ ቀን በኋላ፣ ቤተመቅደስ እና እና ታሪካዊ ታበርናክል በፊታችን በሚታይበት፣ በቤተመቅደስ አደባባይ ጎን በኩል ተቀምጠን እያለን ነገርኳት። የቀኑን ድርጊት ለመረዳት እና በማሰላሰል እየሞከርን እያለን፣ መልህቃችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት እና ስለታላቅ የደስታ እቅድ ያለን እውቀት እንደሆነ አወቅን። ይህን ለሌሳ ያለኝ ፍቅር ወደ መግለጽ መራኝ። በህይወቴ ውስጥ የጸሐይ ብርሐን እና አስደናቂ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ነች። ህይወቷ ስለራሷ ባለማሰብ የምታገለግልበት እና ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር የምትሰጥ ነች። ለዘለአለማዊ አንድነታችን በረከት ብቁ ለመሆን እጥራለሁ።

ሶስቱ ለስድስቱ የልጅ ልጆቻችን እናት ከሆኑት ከቆንጆ ባለቤቶቻቸው ጋር በዚህ ለሚገኙት፣ ለአራት ወንድ ልጆቻችን እና ለቤተሰቦቻቸው ያለኝን ታላቅ ፍቅር እገልጻለሁ፤ ሚስዮን የሆነው አራተኛውም በሚስዮን የተመደበውን የመኝታ ጊዜ አሳልፎ በመቆየት ከሚስዮን ፕሬዘደንቱ እና ከሚስዮን ፕሬዘደንቱ ባለቤት ጋር በታይዋን ካለው የሚስዮን ቤት እነዚህን መተላለፊያዎች ለማየት ፈቃድ አግኝቶ ነበር። እያንዳንዱን እወዳቸዋለሁ እናም አዳኝን እና ወንጌልን እንዴት እንደሚያፈቅሩም እውዳለሁ።

ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባሎችም ፍቅሬን እገልጻለሁ፥ እንዲሁም ከማስታውሳቸው መጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ በውስጤ እንደሚኖር የሚመስለውን ምስክርነቴን እንዳሳድግ ያደረጉትን ባለፈው አመት የሞቱትን ውድ እናቴን እና አባቴን። ይህን ምስጋናዬን የማቀርበው ለወንድሜ፣ ለእህቶቼ፣ እና ለታማኝ ባለቤቶቻቸው፣ እናም አብዛኛዎቹ በዚህ ለሚገኙት ለሌሳ ቤተሰቦችም ነው። የምስጋና መረብንም የምወረውረው በህይወት መንገዴ ላይ ለነበሩት ለቤተሰብ አባላቴ፣ ለጓደኞቼ፣ ለሚስዮኖች፣ ለመሪዎች፣ እና አስተማሪዎች ነው።

ከቀዳሚ አመራር ፣ ከአስራ ሁለት፣ ከሰባ፣ እና ከአጠቃላይ ደጋፊ አመራሮች ጋር ግንኙነት ለማግኘት ተባርኬ ነበርኩኝ። ለእያንዳንዳችሁ እህቶች እና ወንድሞች ያለኝን ፍቅር እና ክድር እገልጻለሁ እናም ለሚቀጥለው ግንኙነታችን ብቁ ለመሆን በመጣር እቀጥላለሁ። የኤጲስ ቆጶስ አመራር እንደ ሰማያዊ የሆነ አንድነትን ይደሰትበታል። በየቀኑ ከኤጲስ ቆጶስ ጄራድር ኮሴ፣ ከኤጲስ ቆጶስ ዲን ኤም. ዴቪስ፣ እና ከደጋፊዎቻቸው ጋር የነበረኝን ግንኙነት እናፍቃለሁ።

ጌታ በመጀመሪያው የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል ውስጥ በመዘገባቸው ቃላት መረጃ በመሆን በፊታችሁ ቆሜአለሁ። “የወንጌሌ ሙላት በደካሞች እና በተራ ሰዎች አማካይነት በነገስታት እና በገዢዎች ፊት እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ይታወጅ ዘንድ ተሰጥቷቸዋል።”1 እነዚህ ቃላት አብ ለልጆቹ ያለውን ፍቅር በሚያሳዮ ቃላት ተከትለዋል፥ “ስለዚህም እኔ ጌታ በምድር ነዋሪዎች ላይ የሚመጣውን መቅሰፍት በማወቄ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን ጠራሁት እናም ከሰማይም ተናገርኩት እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጠሁት”2

ወዳጅ የሰማይ አባታችን እና ልጁ፣ ያህዌ፣ መጨረሻው እስከ መጀመሪያው እውቀት ያላቸው፣3 ሰማያትን ከፈቱ እናም እንደሚመጡ የሚያውቁትን መቅሰፍት ለማመዛዘን አዲስ ዘመንን ከፈቱ። ሐዋርያው ጳውሎስ የሚመጡትን መቅሰፍት እንደ “የሚያስጨንቅ ዘመን” ገልጿቸው ነበር።4 ለእኔ፣ ይህ የሰማይ አባት በሚያስጨቅን ዘመል ለሚኖሩት ያለው ደግ ክፍያ በዘመን ሙላት ውስጥ እንድንኖር ማድረጉ መሆኑን ሀሳብ ያቀርብልኛል።

በዚህ ሳምንት ብቁ ስላለመሆኔ በማሰብ በምሰቃይበት ጊዜ፣ የሚገስጸኝ እና የሚያፅናናኝ ልዩ ስሜት ተቀበልኩኝ፥ ይህም ለማድረግ በማልችለው ላይ ሳይሆን፣ ግን በምችለው ላይ እንዳተኩር ነው። ስለወንጌል ግልፅ እና ውድ እውነቶች ለመመስከር እችላለሁ።

እነዚህም ለብዙ መቶ ጊዜዎች በቤተክርስቲያኗ አባል ከሆኑት እና አባል ካልሆኑት ጋር ያካፈልኳቸው ቃላት ናቸው፥ “እግዚአብሔር [አፍቃሪ] የሰማይ አባታችን ነው። እኛ ልጆቹ ነን።… ስንሰቃይ አብሮን ያለቅሳል እናም ትክክል የሆነውን ስናደርግም ይደሰታል። ከእኛ ጋር ይነጋገራል፣ እናም እኛም ከእርሱ ጋር በልባዊ ጸሎት ለመነጋገር እንችላለን። …

“የሰማይ አባት ለእኛ፣ ለልጆቹ፣ … ወደእርሱ የምንመለስበት መንገድ ሰጥቶናል።… በ[ሰማይ] አባታችን አላማ ዋናውም የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ነው።”5

የሰማይ አባት ለሰው ዘር ሁሉ ኃጢያቶች ለመክፈል ልጁን ወደ ምድር ልኳል። ስለእነዚህ ግልፅ እና ውድ እውነቶች እመሰክራለሁ፣ እናም ይህን የማደርገውም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።