2010–2019 (እ.አ.አ)
እመኑ እንጂ፣ አትፍሩ
ኦክተውበር 2015


19:29

እመኑ እንጂ፣ አትፍሩ

ለማመን ስንመርጥ፣ በንሰሀ፣ እና አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል፣ እምነትን ስንለማመድ፣ መንፈሳዊ አይኖቻችንን ብዙም ልናስባቸው ወደ ማንችላቸው ውበቶች እንከፍታለን።

ባቢሎን እና ዳንኤል

ከሁለት ሺህ ስድሰት መቶ አመታት በፊት፣ ባቢሎን የአለማችን ታላቅ ሀይል ነበረ። ከተማዋን የከበቡት ግንቦች 300 ፊት(90 ሜ) ከፍታ እና 80 ፊት (25 ሜ) ስፋት እንዳላቸው አንድ የጥንት የታሪክ ሰው ገልጹዋል። “በግዝፈቱ፣ከእሱ ጋር የሚስተካከል ሌላ ከተማ የለም ” በማለት ጽፏል።1

በጊዜው፣ ባቢሎን የአለም የትምህርት፣ የህግ፣ እና ፍልስፍና ማእከል ነበር። የጦሩ ሀይል አቻ አልነበረውም። የግብፅን ሀይል ሰባብሯል። የሶሪያ ዋና ከተማ፣ ነነዌን፣ ወሯል፣ አቃጥሏል እናም ማርኳል። እየሩሳሌምን በቀላሉ ተቆጣጥሯል እና ምርጥ እና ብሩህ የነበሩትን የእስራኤል ልጆች ንጉስ ነቡከደነዖርን እንዲያገለግሉ ወደ ባቢሎን ምልሷል።

ከምርኮኞቹ መካከል አንዱ ዳንኤል የሚባል ወጣት ነበር። በዚያ ጊዜ ዳንኤል ከ12 እስከ 17 አመት እድሜ እንደሚሆነው ብዙ ምሁራን ያምናሉ። ተወዳጅ ወጣት የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች ሆይ፣ ይህን አስቡት፣ በአለማዊው ባቢሎን ቋንቋ፣ ህግ፣ ሀይማኖት፣ እና ሳይንስ እንዲማር ወደ ንጉሱ ግቢ ሲወሰድ ዳንኤል በእናንተ እድሜ ነበር።

ከቤታችሁ እንድትለቁ፣ 500ማይል (800 ኪ.ሜ) ወደ አዲስ ከተማ መጓዝ፣ እና በጠላቶቻችሁ ሀይማኖት መሰበክ ምን አይነት ስሜት እንደሚኖረው መገመት ትችላላችሁን?

ዳንኤል ያደገው እንደ ህዋዌ ተከታይ ነበር። በአብረሀም፣ በይስሀቅ፣ እና በያእቆብ እግዚአብሔር ያምናል እናም ያመልካል። የነብያትን ቃላት አጥንቷል፣ እና እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያለውን ግንኙነት ያውቃል።

አሁን ግን፣ በጣም በወጣት እድሜው፣ በባቢሎን ውስጥ የእስር-ተማሪ ነበር። የድሮ እምነቱን ለማስተው እና የባቢሎኑን እንዲቀበል የነበረው ግፊት ጥልቅ ነበር። ነገር ግን ለእምነቱ እውነተኛ ሆኖ ቆየ---በቃል እናም በድርጊት።

ብዙም ያልታወቀ እውነትን መጠበቅ ምን አይነት ስሜት እንዳለው አብዛኞቻችሁ ታውቃላችሁ። በዛሬው የኢንተርኔት አባባል፣ ከእኛ በሚቃረኑ ሰዎች ስለ “መቃጠል” እናወራለን። ነገር ግን ዳንኤል በህዝብ የመሳለቅ አደጋ ውስጥ ብቻ አልነበረም። በባቢሎን ውስጥ፣ የሀይማኖት አባቶችን የሚቃወም--በምሳሌያዊ እና የእውነትም “መቃጠል” እንዳለባቸው ነው የሚረዱት። የዳንኤል ጓደኞች ሲድራቅን፣ ሚሳቅን፣ እና አብደናጎምን ጠይቋቸው።2

በዚያ አከባቢ አማኝ መሆን ለዳንኤል ቀሎት እንደነበር አላቅም። እንዳን ሰዎች በሚያምን ልብ ተባርከዋል--ለእነርሱ፣ እምነት ከሰማይ እንደመጣ ስጦታ ይመስላል። ነገር ግን ዳንኤል እንደ አብዛኞቻችን ለምስክርነቱ ጠንክሮ የሰራ ይመስለኛል። ተንበርክኮ በመፀለይ፣ በእመነት መሰዊያ ላይ ጥያቄዎቹን እና ፍራቻዎቹን በማድረግ፣ ለመረዳት እና ለጥበብ ጌታን በመጠበቅ ብዙ ሰኣታትን እንዳሳለፈ እተማመናለሁ።

እና ጌታ ዳንኤልን ባረከው። እምነቱ ተቃርኖ እና መሳለቅ ቢያጋጥመውም፣ በእራሱ ተሞክሮ ትክክል መሆኑን ላወቀው እውነተኛ ሆኖ ቆየ።

ዳንኤል አምኗል። ዳንኤል አልተጠራጠረም።

እና ከዛም በአንድ ምሽት፣ ንጉስ ነቡከነድዖር አእምሮውን የረበሸ ህልም አይቶ ነበር። ህልሙን እንዲያብራሩ እና ትርጉሙን እንዲገልፁ የምሁራን እና የአማካሪዎቹን ቡድኖች ሰበሰበ እናም ጠየቃቸው።

እርግጥ ነው፣ አልቻሉም። “የጠየከውን ማንም ሊያደርገው አይችልም፣” ብለው ተማፀኑ። ነገር ግን ይሄ ነቡከነድዖርን ይበልጥ አናደደው፣ እና ሁሉም ጠቢብ ሰዎች፣ አስማተኞች፣ ጠፈርተኞች፣ እና አማካሪዎች--ዳንኤልንም ጨምሮ እንዲቆራረጡ አዘዘ።

ለዳንኤል መፅሀፍ አዲስ ያልሆናችሁ ከዛ ምን እንደተከሰተ ታውቃላችሁ። ዳንኤል ነቡከነድኦርን ተጨማሪ ጊዜ እንዲኖር ጠየቀ፣ እና እሱ እንዲሁም ታማኝ አጋሮቹ ወደ እምነት አቸው እና ሰብአዊ ጥንካሬ ምንጭ አመሩ። ለእግዚአብሔር ጸለዩ እና በዚህ ወሳኝ ወቅት መለኮታዊ እርዳታን ጠየቁ። እና “ከዛ ለዳንኤል ሚስጥሩ በራእይ ተገለፀለጠት።”3

ከተማረከ ህዝብ የሆነው ወጣት--እንግዳ በሆነ እምነት በማመኑ ሲተች እና ሲሰቃይ የነበረው--ዳንኤል፣ ወደ ንጉሱሰ ዘንድ ሄደ እና ህልሙን እና ትርጉሙን ገለጸለት።

ከዚያ ቀን ወዲያ፣ በእግዚአብሔር በነበረው ቀጥተኛ እምነት የተነሳ፣ ዳንኤል በባቢሎን ሁሉ ዝነኛ የሆነ፣ የንጉሱ ታማኝ አማካሪ ሆነ።

ያመነው እና በእምነቱም የኖረው ወጣት የእግዚአብሔር ሰው ሆነ። ነብይ ሆነ። የጽድቅ ልኡል ሆነ።4

እኛ እንደ ዳንኤል ነን?

የእግዚአብሔርን ቅዱስ ክህነት ለተሸከምን ሁሉ እኔ እጠይቃለሁ፣ እኛ እንደ ዳንኤል ነን?

ለእግዚአብሔር ታምነን እንቆማለን?

የምንሰብከውን እንተገብራለን፣ ወይስ የእሁድ ቀን ክርስቲያኖች ብቻ ነን?

የየቀን ድርጊቶቻችን እናምናለን የምንለውን በግልፅ ያንፀባርቃሉን?

“ድሆችን እና የተቸገሩትን፣ የታመሙ እና የተሰቃዩትን” እንረዳለን?5

በንግግር ብቻ ነን፣ ወይስ በጉጉት መንገዱን እንጓዛለን?

ወንድሞች፣ ብዙ ተሰጥቶናል። የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መለኮታዊ እውነት ተምረናል። ወገኖቻችንን ለመርዳት እና በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መንግስት በመገንባቱ እንድናግዝ ታምነን የክህነት ስልጣን ተሰቶናል። የመንፈሳዊ ሀይል ታላቅ ስጦታ ባለበት ጊዜ ነው የምንኖረው። የእውነት ሙሉነት አለን። በምድር እና በሰማይ ለማተም የክህነት ቁልፎች አሉን። ቅዱስ መጽሐፍቶች እና የህያው ነብያት እና ሐዋርያት ትምህርቶች ከየትኛው ጊዜ በበለጠ ሁኔታ አሁን ይገኛሉ።

ውድ ጓደኞቼ፣ እነዚህን ነገሮች አቅልለን አንውሰድ። በእነዚህ በረከቶች እና እድሎች ታላቅ ሀላፊነቶች እና ግዴታዎች ይመጣሉ። ወደ እነርሱ ከፍ እንበል።

ጥንታዊቷ የባቢሎን ከተማ በመፈራረስ ውስጥ ነች። ድምቀቷ ከጠፋ ቆይቷል። ነገር ግን የባቢሎን አለማዊነት እና ሀጢአተኛነት አሁንም ይኖራል። አሁን በእምነት አልባ አለም ውስጥ አማኞች ሆነን መኖሩ የእኛ ውሳኔ ነው። የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መርሆዎች በየቀኑ መተግበር እና ለእግዚአብሔር ትእዛዛት በእውነት ለመኖር ድረሻው የእኛ ነው። በእኩዮቻችን ግፊት ውስጥ በዝግታ መቆየት፣ በታወቁ ዝንባሌዎች እና ሀሰተኛ ነብያት አለመነሳሳት፣ መለኮታዊ ያልሆኑ ትችቶችን ንቆ ማለፍ፣ የክፉውን ፈተናዎች መቋቋም፣ እና የእራሳችንን ስንፍና ማሸነፍ ይኖርብናል።

ስለዚያ አስቡበት። በባቢሎን መንገድ ዝም ብሎ ለመጉዋዝ ለዳንኤል ምን ያህል ቀላል ነበር? እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች የሰጠውን የድርጊት መመሪያ ወደ ኋላ መተው ይችል ነበር። በንጉሱ የሚቀርቡትን አሪፍ ምግቦች መመገብ እና በተፈጥሮአዊው ሰው አለማዊ ደስታ ውስጥ መገዛት ይችል ነበር። ትችቶችን ማስወገድ ይችል ነበር።

ታዋቂ መሆን ይችል ነበር።

ከሌሎች ጋር መመቻቸት ይችል ነበር።

የመንገዱ ውስብስብነት በጣም ይቀንስ ነበር።

ያም፣ በእርግጥ፣ ንጉሱ ለህልሙ ትርጉም እስከጠየቀበት ቀን ነው። ከዛም ዳንኤል ልክ እንደ ሌሎቹ የባቢሎን “ጠቢብ ሰዎች፣” የብርሀን እና ጥበብ እውነተኛው ምንጭ ጠፍቶበት ይገኝ ነበር።

ዳንኤል ፈተናውን አልፏል። የእኛ ግን አሁንም ይቀጥላል።

ለማመን ብርታት

ሰይጣን፣ እኛ ጠላት፣ እኛ እንድንወድቅ ይፈልጋል። እምነታችንን ለማውደም ባለወው የጥረት ክፍል ውሸቶችን ያሰራጫል። ተጠራጣሪ ሰው የተማረ እና እውቀት ያለው እንደሆነ እና በእግዚአብሔር እና በተአምራቶቹ ላይ እምነት ያለቸው ደግሞ እንደ ገራገር፣ እውር፣ ወይም የተሳሳቱ መሆናቸውን በስውር ይጠቁማል። መንፈሳዊ ስጦታዎችን እና የእውነተኛ ነብያትን ትምህርቶች መጠራጠር አሪፍ እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል።

የዚህ አንድ ቀላል እውነታ ለሁሉም በማስራደት መርዳት ብችል ምኞቴ ነው፤ በእግዚአብሔር ላይ የምናምነው በልባችን እና አእምሮአችን በምናውቃቸው ነገሮች ነው እንጂ፣ በማናውቃቸው ነገሮች ምክንያት አይደለም። መንፈሳዊ ተሞክሮዎቻችን አንዳነዴ በአለማዊ ቃላት ለማብራረት ከሚቻለው በላይ ቅዱስ ናቸው፣ ነገር ግን እውነት አይደሉም ማለት አይደለም።

የሰማይ አባት ለልጆቹ መንፈሳዊ ድግስ አዘጋጅቷል፣ ሊታሰብ የሚችል እያንዳንዱ አይነት ምግብ የቀረበበት---እና አሁንም--- በእነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች ከመደሰት ይልቅ፣ ተጠራጣሪዎች ከሩቅ በሚያዩት እራሳቸውን ያዝናናሉ፣ ከጥርጣሬአቸው እና ክበር-አልባ ሲኒያቸው ውስጥ ይጎነጫሉ።

ወደሰማይ አባታችን በመምጣት፣ አእምሮአቸውን በጥበብ የሚያሰፋውን እና ነብሳቸውን በደስታ የሚሞላውን የመንፈሳዊ እውቀት ደማቅ ጸሀይ ማግኘት እየቻሉ፣ ማንስ ሰው በእራሳቸው መረዳት የሻማ ብርሀን መርካት ለምን በህይወት ውስጥ ይጓዛሉ?

እናንተ እና እኔ ስለ እምነት ሰዎችን ስናወራ፣ “እንዳንተ ማመን ብችል እመኛለሁ” ሲሉ በአብዛኛው ሰምተን አናውቅምን?

በዚህ አይነት አርፈተ ነገር ውስጥ የሚያመላክተው ሌላ የሰይጣን ማሳሳቻ ነው፤ እምነት ለአንዳንድ ሰዎች እንዳለ እና ለሌሎች እንደሌለ ማድረግ። የማመን አስማት የለም። ነገር ግን ለማመን መፈለግ የመጀመሪያው ደረጃ ነው! እግዚአብሔር ሰዎችን አይለይም።6 አባታችሁ ነው። እናንተን ማናገር ይፈልጋል። ቢሆንም፣ ጥቂት ሳይንሳዊ ጉጉትን---በእግዚአብሔር ቃላት ላይ ተሞክሮ ማድረግን-- እና “ቅንጣት እምነት”ን መለማመድን ይጠይቃል።7 ትንሽ ትህትናንም ይጠይቃል። ክፍት ልብ እና ክፍት አእምሮንም ይጠይቃል። መሻትን፣ በሙሉ የቃሉ ትርጉም፣ ይጠይቃል። እናም፣ ከሁሉም የሚከብደው፣ ታጋሽ መሆንን እና ጌታን መጠበቅን ይጠይቃል።

ለማመን ጥረት ካላደረግን፣ የባትሪውን ሶኬት ነቅሎ እና ባትሪው ምንም አይነት ብርሀን ለምን የለውም ብለን እንደምንከስ አይነት ሰው እንሆናለን።

በቅርቡ እራሱን ከእግዚአብሔር በማራቁ እውነታ ላይ ስለተኩራራ አንድ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ ሰምቼ ተገረምኩ እናም አዘንኩ። እንዲህ አለ፣ “እግዚአብሔር እራሱን ለእኔ ከገለጠ፣ ከዛ አምናለሁ። እስከዛ ድረስ፣ በእራሴ መረዳት እና መንገዱን እንዲያበራልኝ በእራሴ እውቀት በመደገፍ፣ እውነቱን አገኛለሁ።”

የዚህን ወጣት ልብ አላውቅም፣ ነገር ግን ለእርሱ በጣም ከማዘን ውጪ ምንም ማድረግ አልችልም። ጌታ ያቀረበለትን ስጦታዎች በቀላሉ ተቃወመ። ይህ ወጣት የባትሪውን ሶኬት ነቅሎ እና ማብራት እንደሌለ በጎበዝ ምልከታው ውስጥ እራሱን ያረካ ይመስላል።

መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ፣ ዛሬ ይሄ ታዋቂ ባህሪ የሆነ ይመስላል። የማረጋገጥ ሸክምን በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ ከቻልን፣ የእግዚአብሔር ትእዛዛትን በአተኩሮ ከመውሰድ እና ከሰማይ አባት ጋር ላለን ግንኙነት ሀላፊነትን ከመውሰድ እራሳችንን መቆጠብ እንደምንችል እናስባለን።

ወንድሞች፣ ግልፅ ላድረገው፤ ተጠራጣሪ በመሆን የሚያስከብር ወይም የሚያስደንቅ ነገር ምንም የለም። ተጠራጣሪነት ቀላል ነው---ማንም ሊያደርገው ይችላል። የእምነት ህይወት ነው ሰብአዊ ጥንካሬ፣ መሰጠትን፣ እና ብርታትን የሚጠይቀው።

ነገር ግን እምነት በማህበረሰብ ዋጋ ማጣቱ ሊያስገርመን አይገባም። አለም የማይረዳውን ነገር የመቃወም የቆየ ታሪክ አለው። እና ማየት የማይችለውን ነገር ለመረዳት ይቸገራል። ነገር ግን አንድን ነገር በአካላዊ አይኖቻችን ማየት ስላልቻልን ያ ነገር የለም ማለት አይደለም። በእርግጥ፣ በትምህርት መጽሐፍቶቻችን፣ የሳይንስ ፅሁፎች፣ እና አለማዊ ፍልስፍናዎች ውስጥ “ከታለሙት በላይ ብዙ ነገሮች በሰማይ እና በምድር ውስጥ አሉ።”8 አለም በመንፈሳዊ አይኖች ብቻ በሚስተዋሉ አስገራሚ፣ ጥልቅ እና አስደናቂ ነገሮች የተሞላ ነው።

የማመን ቃልኪዳን

ለማመን፣ ንሰሀ እስከመግባት እምነታችንን ስንለማመድ፣ እና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመከተል ስንመረጥ፣ ከምንገምተው በላይ ወደሆኑት ድምቀቶች መንፈሳዊ አይኖቻችንን እንከፍታለን።9

ወንድሞች፣ በጣም በአስቸጋሪ ጊዜያትም እንኳን፣ በገሊላ መንገድ ላይ ለጓጓው አባት አዳኝ ያለውን ነገር ለእናንተም ይላችኋል፣ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ።”10

ለማመን መምረጥ እንችላለን።

በማመን ውስጥ፣ የብርሀንን መውጣት እናገኛለን።

እውነትን እናገኛለን።11

ሰላምን እናገኛለን።12

በእምነታችን ምክንያት፣ በፍፁም አንራብም፣ በፍፁም አንጠማም።13 የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታዎች ለእምነታችን እውነተኞች እንድንሆን ያስችሉናል እናም ነብሳችንን “መቼም በማያልቅ የውሀ ምንጭ” ይሞላሉ።14 እውነተኛ እና የማያልቅ የደስታ ተሞክሮ ይኖረናል።15

ስለዚህ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ በእግዚአብሔር ክህነት ውስጥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፤

ለማመን ብርታት ይኑራችሁ።

እመኑ ብቻ እንጂ፣ አትፍሩ።

ከዳንኤል ጋር ቁሙ።

እያንዳንዳችን--ወጣት ወይም በእድሜ የገፋን---የታደሰ ጥንካሬ፣ ብርታት፣ እና ለማመን ፍላጎት እንድናገኝ እፀልያለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።