2010–2019 (እ.አ.አ)
በመንገዳችሁ ላይ ጽኑ
ኦክተውበር 2015


10:43

በመንገዳችሁ ላይ ጽኑ

ምንም አይነት ፈተናዎች ቢያጋጥማችሁም እንኳን፣ እግዚአብሔርን አስቀድሙ። እግዚአብሔርን ውደዱ። በክርስቶስ እምነት አድርጉ እንዲሁም በሁሉም ነገሮች እራሳችሁን አሳልፋችሁ ለእርሱ ስጡ።

በመጋቢት 11፣ 2011 (እ.አ.አ) ጃፓን ኮቤ ሚስዮንን ለመጎብኘት በቶኪዮ ሺናጋዋ ባቡር ፌርማታ ላይ ቆሜ ነበር። በግምት ከሰአት ላይ በ8፡46 ሰዓት፣ 9.0 መለኪያ ያለው ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። በኃይለኛ መንቀጥቀጡ የተነሳ መቆም አልቻልኩኝም ነበር እናም የደረጃውን ዘንግ አጥብቄ ያዝኩኝ። በአቅራቢያ ያሉት የኮርኒስ መብራቶች መሬት ላይ መውደቅ ጀመሩ። መላ ቶኪዮ ድንጋጤ ውስጥ ነበረች።

እንደ እድል ሆኖ፣ አልተጎዳሁም ነበር፣ እና ከአራት ሰዓታት በኋላ መላ ቤተሰቤ ደህና መሆናቸውን ሳውቅ እፎይታ ተሰምቶኝ ነበር።

በቴሌቪዥን ላይ ቀጣይነት ያላቸው አስፈሪ፣ አስደንጋጭ ምስሎች እየታዩ ነበር። እጅግ ግዙፍ የሆነ ሱናሚ በመንገዱ ላይ ያለውን ነገርሁሉ ማለትም መኪናዎችን፣ ቤቶችን፣ ፋብሪካዎችንና እርሻዎችን እየጠራረገ ወደ ሰንዲ ሚስዮን አካባቢ ገባ። በአሳዛኝ ምስሎች በጣም ተገርሜ አነባሁ። እናም የሰማይ አባት ጥበቃና እርዳታ ሁሌም ከልብ በምወደው በዚህ ክልል ውስጥ ያሉት ሰዎች ላይ እንዲሆን አጥብቄ ፀለይኩኝ።

ከዛ በኋላ ሁሉም ሚስዮኖችና የቤተክርስቲያን አባሎች ደህና እንደነበሩ ተረጋገጠ። ይሁን እንጂ፣ ብዙ አባሎች የቤተሰብ አባሎችን፣ ቤቶችንና የቤት ንብረቶችን በማጣት ተጠቅተው ነበር። ከ20000 ህዝቦች በላይ የሚጠጉ ሰዎች ጠፉ፣ ማህበረሰቦች ፈራረሱ፣ እናም በኒውክሌር ኃይል ጣቢያው አደጋ ምክንያት ብዙ ህዝቦች ቤቶቻቸውን ትተው እንዲሄዱ ተገፍተው ነበር።

እንደዚህ አይነቱ አስከፊ ድንገተኛ አደጋ ብዙ የሕይወት መጥፋትን እያስከተለ ሀቮክን ወደ ብዙ የአለም ክፍሎች እያፈራረሳት ነው ዛሬ። አስከፊ ክስተቶች፣ ጦርነቶችና እጅግ ብዙ የሆኑ ችግሮች በአለም ውስጥ እንደሚከሰቱ እየተስጠነቀቅን ነው።

እንደዚህ አይነት ችግሮች በድንገት በእኛ ላይ ሲመጡ “እነዚህ ነገሮች ለምንድን ነው በእኔ ላይ የሚከሰቱት?” ወይም “ለምንድን ነው መሰቃየት ያለብኝ?”ብለን እንጠይቅ ይሆናል።

ወደ ወንጌል ከተለወጥኩኝ በኋላ ለእረጅም ጊዜ፣ “ለምንድን ነው ፈተናዎች የሚሰጡኝ?” ለሚለው ጥያቄ ግልፅ መልስ አልነበረኝም ነበር። መፈተን አለብን የሚለውን የደህንንት ዕቅድ ክፍል ተረድቼው ነበር። ይሁን እንጂ፣ በእውን ወደዚህ ጥያቄ ሲመጣ ሙሉ በሙሉ መልስ ለመስጠት ኃይለኝ የሆነ አቋም አልነበረኝም ነበር። ነገር ግን እኔም በሕይወቴ ውስጥ ታላቅ ፈተናን ያየሁበት ጊዜ መጣ።

የ30 አመት እድሜ እያለሁ፣ እንደ ስራዬ አንዱ አካል፣ ናጎያ ሚስዮንን እየጎበኘው ነበር። ከስብሰባው በኋላ፣ የሚስዮኑ ፕሬዘዳንት ወደ አየር ማረፊያ ይወስዱኝ ዘንድ ለሚስዮኖቹ ሁኔታን አመቻቸላቸው። ይሁን እንጂ፣ ከእረጅም ኮረብታ እግር ስር ያለ መስቀለኛ መንገድ ላይ ስንደርስ፣ አንድ ተሳቢ መኪና በከፍተና ፍጥነት ላይ እንዳለ ከኋላቸን እየተመዘገዘገ መጣ። ከመኪናችን የኋለኛ ክፍል ጋር በመላተም ከ20 ሜትሮች በላይ እየገፋት ወሰዳት። የዚህ ነገር ሁሉ አስደንጋጭ ነገር ሾፌር የሚባል ነገር አለመኖሩ ነበር። የመኪናችን የኋለኛ ክፍል መጀመሪያ ከነበረው በግማሽ ተጨራምቶ ነበር። እድለኛ ሆነን፣ ሚስዮኖቹም እኔም ተረፍን።

ይሁን እንጂ፣ በሚቀጥለው ቀን፣ በአንገቴ ውስጥና ትከሻዎቼ ላይ ህመም ይሰማኝ ጀመር እንዲሁም ከባድ እራስ ምታት አጋጠመኝ። ከዛ ቀን ጀምሮ መተኛት አልቻልኩኝም ነበር እናም እያንዳንዱን ቀን በአካላዊና አእምሮአዊ ህምም ለመኖር ተገድጄ ነበር። ወደ እግዚአብሔር ህመሜን እንዲፈውሰኝ በትህትና ፀለይኩኝ፣ ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ለ10 አመታት ቀጠሉ።

በዚህ ጊዜ የጥርጣሬ ስሜቶች ወደ አእምሮዬ መምጣት ጀመሩና “ይህን ያህል የህመም ስቃይ ለምን እሰቃያለሁ?” ብዬ ተገረምኩኝ። ይሁን እንጂ፣ እሻው የነበረው አይነት ፈውስ ባይሰጠኝም፣ የእግዚአብሔር ትዕዛዛትን በመጠበቅ አማኝ ለመሆን ተጣጣርኩኝ። ስለ ፈተናዎቼ ያሉኝን ጥያቄዎች መቅረፍ እችል ዘንድ መፀለዬን ቀጠልኩኝ።

ከተጨማሪ ግላዊ ጉዳይ ጋር እራሴን ያገኘሁበት ጊዜ መጣ፣ እና ከዚህ አዲስ ፈተና ጋር እራሴን እንዴት ማላመድ እንዳለብኝ ባለማወቄ ተረብሼ ነበር። መልስ ለማግኘት እየፀለይኩኝ ነበር። ነገር ግን ወዲያውኑ መልስ አላገኘሁም ነበር። ስለሆነም ወደ ማምነው የቤተክርስቲያን መሪ ሄጄ ተነጋገርኩኝ።

ስንነጋገር ፍቅር በተሞላበት ድምፁ እንዲህ አለ፣ “ወንድም አዮአጊ፣ እዚህ ምድር ላይ ያለህበት አላማ ይሄንን ፈተና ለመለማመድ አይደለምን? የዚህን ሕይወት ፈተናዎች ሁሉ እንዳሉ መቀበል እና ቀሪውን ለጌታ መተው በቂ አይደለምን? ትንሳኤ ስናደርግ ይህ ችግር እንደሚቀረፍ አታስብምን? ”

እነዚህን ቃሎች ስሰማ፣ የጌታ መንፈስ በጣም በጠነከረ ሁኔታተሰማኝ። ይህንን ትምህርት ለብዙ ጊዜ ሰምቼው ነበር፣ ነገር ግን የመረዳቴ አይኖች አሁን ከነበሩት በአንፃሩ ተከፍተው አልነበሩም። በፀሎቴ ውስጥ ከጌታ እሻው የነበረው መልስ ይህ እንደነበር ተረዳሁ። የሰማይ አባታችንን የደህንነት ዕቅድ በግልፅነት ለመረዳትና ችዬ ነበር፣ እንዲሁም የዚህን ጠቃሚ መርህ አዲስ የሆነ መረዳትን አገኘሁ።

በአብረሐም ውስጥጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣“እናም የእነሱ ጌታ እግዚአብሔር የሚያዛቸውን ማንኛውንም ነገሮች ያደርጉ ዘንድ ለማየት በእዚህ ነገሮች እንፈትናቸዋለን።”1

ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ያ እግዚአብሔር የዚህን ምድር ታላቅ ምህንድስና ያውቃል፣ በሰማያትና በምድር ላይ ባሉትን ነገሮች በሙሉ የበላይነት አለው፣ የደህንነት ዕቅዱን ለማሳካት በዚህ ምድር ላይ እስካለን ድረስ ብዙ ልምዶችን ማለትም ፈተናዎችን ሰጠን።

ጌታ ለዮሴፍ ስሚዝ እንዲህ ሲል ነገረው፥

ልጄ እነዚህ ሁሉ መከራዎች ልምድ እንደሚሰጡህና ለመልካም እንደሆኑናእወቅ… .

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ለዘለአለም ይሆናል2እየተከተልከው ባለው መንገድ ላይ ጽና።

የዚህ ምድር ፈተናዎች ህመምንና ሞትን ጨምሮ፣ የደህንነት ዕቅዱ አካል ናቸው እንዲሁም መወገድ አይችሉም። መንገዳችንን እንደያዝን መጽናትና ፈተናዎቻችን በእምነት መቀበል ለኛ ወሳኝ ነው።

ይሁን እንጂ፣ የሕይወቶቻችን አላማ ዝም ብሎ ፈተናዎችን መቋቋም አይደለም። የሰማይ አባት ውድ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ በዚህ ምድር ላይ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ማሸነፍ እንድንችል፣ አዳኛችንና ቤዛችን ይሆን ዘንድ ላከው፤ በሌላ አባባል፣ ደካማ ነገራችንን ጠንካራ እንዲሆኑ ያደርጋል።3 ለሃጢያቶቻችንና ኢፍፁምነታችን መሰዋት ሆነ፣ እንዲሁም አለሟችነትንና ዘላለማዊ ሕይወትን ማግኘት እንድንችል አስቻለን።

ፕሬዘዳንት ሔነሪ ቢ አይሪንግ እንዲህ ሲሉ አስቀመጡ፥ “ነገር ግን አፍቃሪ እግዚአብሔር ከፊታችን ያስቀመጠው ፈተና ችግሮችን መቋቋም እንደምንችል ለማየት ብሎ አይደለም። በጥሩ ሁኔታ መቋቋም እንደምንችል ለማየት ነው። እርሱንና የሰጠንን ትዕዛዛት እንዳስታወስን በማሳየት ፈተናውን እናልፋለን።”4

በፈተና ጊዜዎች “በመንገዳችን ላይ መጽናት” ቁልፍ ምርጫ ነው። ልባችንን ወደ እግዚአብሔር ማዞር አለብን፣ በተለይ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በትህትና ታዘዙ። ምኞታችሁን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በማስታረቅ እምነት አሳዩ።

እስቲ አሁን በናጎያ የነበረውን የመኪናውን ኋላ ክፍል ግጭት እናስብ። በዛ አደጋ ውስጥ ሞቼ ነበር። ይሁን እንጂ፣ በጌታ ፀጋ ታምራታዊ በሆነ ሁኔታ ተረፍኩኝ። መከራዎቼ ለእውቀቴና ለእድገቴ እንደነበሩ አውቃለሁ። s የሰማይ አባት ትዕግስት እንዲኖረኝ፣ የሌሎችን ስሜት መረዳት እንዳዳብርና በስቃይ ላይ ያሉ ሰዎችን እንዳፅናና አስተማረኝ5 ። ይህንን በመገንዘብ፣ ልቤ ለዚህ ፈተና ለሰማይ አባቴ በምስጋና ስሜት ተሞልቶ ነበር።

ምንም አይነት ፈተናዎች ቢያጋጥማችሁም እንኳን፣ እግዚአብሔርን አስቀድሙ። እግዚአብሔርን ውደዱ። በክርስቶስ እምነት አድርጉ እንዲሁም በሁሉም ነገሮች እራሳችሁን አሳልፋችሁ ለእርሱ ስጡ። ለእንደዚ አይነት ሰዎች ሞሮኒ የሚቀጥለውን ቃል ገባ፥ “እናም ለራሳችሁ ኃጢአተኝነትን በሙሉ ከካዳችሁ፣ በሙሉ ኃይላችሁ እና አእምሮአችሁ እና ጉልበታችሁ እግዚአብሔርን ከወደዳችሁ፣ ፀጋው ለእናንተ ይበቃችኋል፣ በፀጋው በክርስቶስ ፍፁም ትሆናላችሁ።”6

አባት እግዚአብሔርና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው እንደሆኑና በፈተናዎች ውስጥ እያሉም እንኳን “በመንገዳቸው ላይ ለሚጸኑ” እና እርሱን ለሚወዱት ሰዎች የእግዚአብሔር ቃል-ኪዳኖች እንደሚያሟሉ በቅንነት እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።