2010–2019 (እ.አ.አ)
በጋን ከወላጄ አክስት ከሮዝ ጋር
ኦክተውበር 2015


21:4

በጋን ከወላጄ አክስት ከሮዝ ጋር

በራሳችሁ የብሩህ ደቀመዛሙርትነት መንገድ ላይ በምትጓዙ ግዜ፣ በመንገዳቹ ላይ እያንዳንዱ እርምጃችሁን እምነት እንዲያጠነክረው እፀልያለሁ።

የተወደዳችሁ እህቶቼ እና ጓደኞቼ፣ ከእናንተ ጋር በመሆኔ ደስታ ይሰማኛል። በሶስቱ ውድ ጓደኞቻችን እና የጌታ እውነተኛ ሐዋሪያት መጥፋት በጣም አዝነናል። ፕሬዘደንት ፓከርን፣ሽማግሌ ፔሪ፣ እና ሽማግሌ ስኮት ይናፍቁናል፣ እናፈቅራቸዋለንም። ለቤተሰብቻቸውን ለጓደኝፕቻቸው እንጸልያለን።

ይሄኛውን የጉባዔ ክፍለ ጊዜ ሁሌም በጉጉት ነው ምጠብቀው -- የሚያምረው መዝሙር እና ከተነሳሱ እህቶቻችን የሚመጣው ምክር መንፈስ በትልቁ ያመጣል። ከእናንተ አብሮነት በኋላ እኔ የተሻልኩ ሰው ነኝ።

ዛሬ ለእናንተ ምን ማለት እንዳለብኝ በማሰላስልበት ግዜ፣ ሀሳቦቼ አዳኝ ወዳሰባቸው መንገድ ዞሩ። ቀላል ታሪኮችን በመጠቀም በጣም ያልታሰቡ ነገሮችን እንዴት ለማሰተማር መቻሉ አስደናቂ ነው። የእሱ ምሳሌዎች እውነቶችን የእሱን ደቀ መዛሙርት በአእምሮዋቸው ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በልቦቻቸውም እንዲቀበሉ እናም ከቀን ተቀን ህይወታቸው ጋር ዘላለማዊ መርሆዎችን እንዲያገናኙ ጋብዟቸዋል።1 የኛ ውድ ፕሬዘዳንት ሞንሰንም እራሳቸው በግል ልምዶች በማስተማር ጠቢብ ናቸው።2

ዛሬ፣ እኔም የማካፍለው ታሪክ አለኝ። በመንፈስ እንድታዳምጡት እጋብዛችኋለሁ። በዚህ ምሳሌ ውስጥ ለእናንተ መንፈስ ቅዱስ መልእክትን እንድታገኙ ይረዳችኋል።

የወላጄ አክስት ሮዝ

ታሪኩ ኤቫ ስለምትባል ሴት ልጅ ነው። ስለ ኤቫ ማወቅ ያለባችሁ ሁለት ጠቃሚ ነገሮች አሉ። አንዱ በዚህ ታሪክ ውስጥ የ11 አመት ልጅ ነበረች። ሌላኛው ደግሞ በፍፁም፣ በእርግጠኝነት ከወላጇአክርስ ሮስ ጋር ሄዳ መኖር አትፈልግም ። በጭራሽ። በምንም መንገድ አይሆንም።፡

ነገር ግን የኤቫ እናት ለመዳን ረጅም ጊዜን የሚጠይቅ ቀዶ ጥገና ልታደርግ ነበር። ስለዚህ የኢቫ ወላጆች በጋን ከአክስት ሮስ ጋር እንድታሳልፍ ይልኳት ነበር።

በኤቫ አእምሮ ውስጥ፣ ይህ ሀሳብ ለምን መጥፎ እንደነበር ሺ ምክንያቶች ነበሩ። አንዱ፣ ከእናትዋ ልትለይ መሆንዋ ማለት ነው። ጓደኖቿን እና ቤተሰቦቿብ ጥላ መሄዷ ማለትም ነው።እናም ከዛ ሌላ፣ የእናትዋን አክስት ሮስንም አታውቃትም። በጣም አመሰግናለሁ በነበረችበት ቦታ ምቾት ላይ ነበረች።

ነገር ግን የክርክር መጠን ወይም የአይን እንቅስቃሴ ውሳኔውን ሊያስለውጥ አይችልም። ስለዚህ ኤቫ ሻንጣዋን አሸገች እና ከአባትዋ ጋር ወደ የወላጅ አክስቷ ሮስ ቤት ረጅም የመኪና ጉዞ አረገች።

ኤቫ ገና ቤት ውስጥ ከረገጠችበት ሰአት ጀምሮ፣ ጠላችው።

ሁሉም ነገር በጣም አሮጌ ነበር! እያንዳንዱ የኢንች ርቀት በአሮጌ መፅሃፍ፣ እንግዳ በሚመስል የተዛቡ ጠርሙሶች፣ እና በዶቃዎች ሞለቶ በተደፉ ፌስታሎች፣ በሾረባ ሳህኖች፣ እና በልብስ ቁልፎች የተጨናነቀ ነበር።

የወላጅ አክስቷ ሮስ እዛ ብቻዋን ትኖር ነበር፤ አግብታ አታውቅም። ብቸኛ ኑዋሪ የነበረው በየክፍሉ ከፍታ ቦታዎችን ፈልጎና እዛ መስፈር የሚወደው፤ ልክ እንደተራበ ነብር ወደ ታች ሁሉ ነገር ላይ የሚያፈጠው ግራጫ ድመት ነበር።

ቤቱ ራሱ ብቸኛ ነው ሚመስለው። ራቅ ወዳለ፤ አንዱ ቤት ከአንዱ በጣም የሚራራቅበት ገጠር ውስጥ ነበር። በኤቫ እድሜ ያለ ማንም እሷ ከምትኖርበት በግማሽ ማይል ርቀት ውስጥ የሚኖር ሰው የለም። ያ ደግሞ ኤቫንም ብቸኝነት እንዲሰማት አድርጓታል።

መጀመሪያ ለወላጅ አክስቷ ሮስ ትኩረት አልሰጠችም ነበር። በአብዛኛው ስለ እናቷ ነበር ያሰበችው። አንዳንዴ፤ እናትዋ እንዲሻላት በሙሉ ነፍሷ በመፀለይ ማታ ሳትተኛ ታሳልፋለች። እናም ወዲያው እንዲሆንላት ታስባለች፣ ኤቫ እግዚያብሄር እናትዋን እየተመለከታት እንደነበር ይሰማት ጀመር።

በስተመጨረሻ ቀዶ ጥገናው ውጤታማ እንደነበር የሚናገር ቃል መጣ፣ እናም ለኤቫ ማድረግ የቀረው ነገር ቢኖር በጋው እስኪያልቅ ድረስ መፅናት ነበር። ነገር ግን ኦህ፣ እስከመጨረሻው መፅናትን እንዴት እንደጠላችው!

ስለ እናቷ ምቾት በአእምሮዋ ውስጥ እያለ፤ አሁን ኤቫ የወላጇን አክስት ሮስን ትንሽ በተሻለ ትኩረት ሰጠቻት። ግዙፍ ሴትዮ ነበረች— ሁሉ ነገሯ ግዙፍ ነበር፤ ድምፅዋ፣ ፈገግታዋ፣ ማንነትዋ። መንቀሳቀስ ለእሷ ቀላል አልነበረም፣ ነገር ግን በምትራመድበት ወቅት ሁሌም ትዘምር እና ትስቅ ነበር፣ እናም የሳቋ ድምፅ ቤቱን ይሞላዋል። ሁሌም ምሽት ላይ ምቼት ያለው ሶፋዋ ላይ ትቀመጣለች፣ ቅዱሳን መጽሀፍቶቿን በማውጣት ፣ ጮክ ብላ ታነባለች። እናም በምታነብበት ጊዜ፣ ልክ እንደዚህ በማለት “ኦህ፣ ያንን ማረግ የለበትም ነበር!” ወይም “ እዛ ለመሆን ምን የማልሰጠው ነገር ነበር!” ወይም “ እስከ ዛሬ ከሰማችኋቸው ነገሮች ሁሉ ያ በጣም የሚያምረው አይደለምን!” ብላ አንዳንዴ አስተያየቷን ትሰጣለች፣ እናም በየምሽቱ ሁለቱ በኤቫ አልጋ አጠገብ ለመፀለይ በሚንበረከኩ ግዜ፣ የወላጅ አክርስቷ ሮስ ለአየር እንሰሳዎች እና ለሁሌ አረንጓዴ ዛፎች ፣ ለፀሀይ መጥለቅ እና ከዋክብት፣ እናም “በህይወት ለመኖሯ አግራሞት” የሰማይ አባቷን በማመስገን በጣም የሚያምሩትን ፀሎቶቿን ትላለች። ለኤቫ ሮስ እግዚያብሄርን እንደ ጓደኛዋ እንደምታውቀው ነው የመሰላት።

ከጊዜ በኋላ፣ ኤቫ የሚያስደስት ግኝት አገኘች፤ እስካሁን ከምታውቃቸው ሰዎች ሁሉ የወላጅ አክርስቷ ሮስ የበለጠ ደስተኛ ሆና አገኘቻት።

ነገር ግን እንዴት ያ ይሆናል?

ደስተኛ ለመሆን ምን ነበራት?

አግብታ አታውቅም፣ ልጆች የሏትም፣ ከሚያስደነግጠው ድመት ውጪ አጋር የሚሆናት አንድም የለም ነበር እናም ልክ እንደ ጫማዎቿን ማረግ እና ደረጃዎቹን መውጣት የመሰሉትን ቀላል ነገሮች ለማረግ አስቸጋሪ ጊዜያት አሳልፋለች።

ከተማ ስትሄድ፣ የሚያሳፍር ትልቅና የሚያበራ ኮፍያ ታደርጋለች። ነገር ግን ሰዎች አልሳቁባትም። በመሳቅ ፋንታ፣ እሷን ለማናገር በመፈለግ ዙሪያዋን ይከቧታል። ሮስ የትምህርት ቤት አስተማሪ ነበረች፣ እናም ለድሮ ተማሪዎቿ —አሁን ትልቅና የራሳቸው ልጆች ላሏቸው— ቆመው እሷን ማዋራት ያልተለመደ አልነበረም። በህይወታቸው መልካም ተፅእኖ ስለሆነች ያመሰገኗታል። በብዛት ይስቃሉ። አንዳነዴ ያለቅሳሉ።

በጋው እየገፋ ሲሄድ፣ ኤቫ ከሮስ ጋር በዛ ያሉ ሰአታትን አሳለፈች። ረጅም እርምጃዎችን ሄዱ፣ እናም ኤቫ የድንቢጥን እና ወፎችን ልዩነት ተማረች። የጫካ ፍሬዎችን ነቀለች እንዲሁም ከብርትኳኖች ማርማላታ ሰራች። የተወደደውን ቄያቸውን ለቀው፣ ውቅያኖስን በመርከብ በማቋረጥ፣ ከቅዱሳን ጋር ለመሆን ለጥ ያለ ሜዳን ስላቋረጡ ስለ ቅም ቅም የሴት አያቷ ተማረች።

ወዲያው ኤቫ ሌላ ገራሚ ግኝትን አገኘች፤ እስካሁን ከምታውቃቸው ሰዎች ሁሉ የወላጅ አክስቷ ሮስ የበለጠ ደስተኛ መሆንዋን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ኤቫ እራስዋ ከእርሷ ጋር በሆነችበት ግዜ ሁሉ የበለጠ ደስተኛ መሆኗን አገኘች።

አሁን የበጋው ቀናቶች የበለጠ እየገፉ ነበር። ከማወቅዋ በፊት፣ የወላጅ አክስቷ ሮስ በቅርቡ የኤቫ እቤት የመመለሻ ጊዜ እንደሆነ ተናገረች። ምንም እንኳ ኤቫ ለዛ ጊዜ ከደረሰችበት ጊዜ ጀምሮ በጉጉት እየጠበቀች ቢሆንም፣ አሁን ስለ ሁኔታው ምን አይነት ስሜት መሰማት እንደነበረባት እርግጠኛ አልነበረችም። የሚያደባ ድመት እና ውድ የወላጅ አክስቷ ሮስን የያዘውን ይህን እንግዳ ያረጀ ቤት እንደምትናፍቀው ተገነዘበች።

አባቷ መጥቶ እሷን ከመውሰዱ አንድ ቀን በፊት፣ ለሳምንታት ስታሰላስልበት የነበረውን ጥያቄ ኤቫ ጠየቀች። “አክስት ሮስ፣ ለምንድን ነው በጣም ደስተኛ የሆንሽው?”

አክስት ሮስ በጥንቃቄ ተመለከተቻት እና ከዚያ ከፊት ወዳለው ምስል ወደተሰቀለበት ክፍል መራቻት። ተሰጥኦ ባለው ውድ ጓደኛ የተሰጠ ስጦታ ነበረው።

“እዛ ምን ይታይሻል?” ብላ ጠየቀቻት።

የምትዘል መስራች ሴት ልጅ

ከዚ በፊት ኤቫ ምስሉን ልብ ብላው ነበር፣ ነገር ግን በእርግጥ ቀረብ ብላ አልተመለከተችውም ነበር። የመስራቾችን አለባበስ የሚመስል ቀሚሰ ያረገች ከሱ ጋር ተያይዞ ብሩህ ሰማያዊ መስመር እየዘለለች ያለች አንድ ሴት ልጅ አለች። ሳሩና ዛፎቹ ብሩህ አረንጓዴ ነበሩ። ኤቫ እንዲህ አለች፣ “የምትዘል የምትመስል የሴት ምስል ነው።”

አዎ፣ በደስታ የምትዘል መስራች ሴት ልጅ ናት፣ አክስት ሮዝ እንዲህ አለች፣ “ለመስራቾች ብዙ ጨለማና አስከፊ ቀናቶች እንደነበሩ ገምታለሁ። ህይወታቸው ከባድ ነበር— መገመት እራሱ አንችልም። ነገር ግን በዚህ ምስል ውስጥ፣ ሁሉ ነገር ብሩህ እና ተስፋ ሰጪ ነው። ይህች ሴት ልጅ እርምጃዎችዋ ላይ ማስፈንጠሪያ አላት፣ ወደ ፊት እና ወደ ላይ እየሄደች ነው።”

ኤቫ ፀጥ ብላ ነበር፣ ስለዚህ የወላጅ አክስቷ ሮስ ቀጠለች፣ በህይወት ውሰጥ በትክክል የማይሄድ በቂ አለ፣ ሰለዚህ ማንኛውም ሰው እራሳቸውን ወደ ክፉ ማሰብ እና ጭንቀት ውስጥ ይከታሉ። ነገር ግን ነገሮች ሲበላሹም የሚያስገርመውን እና የህይወትን ተአምራት ላይ የሚያተኩሩ ሰዎችን አውቃለሁ። እነኝህ ሰዎች ከማቃቸው ሰዎች ሁሉ ደስተኞች ናቸው።

“ነገር ግን” ኤቫ እንዲህ አለች “ማብሪያና ማጥፊያውን ወደ ታች ወይም ወደ ላይ በማረግ ከሀዘን ወደ ደስታ መቀየር አትችይም።”

“አይ፣ በእርግጥ አይሆንም፣“አክስት ሮስ በደስታ ፈገግ አለች፣ “ነገር ግን እግዚያብሄር ሀዘንተኛ እንድንሆን አድርጎ አልቀረጸንም። ደስታ እንዲኖረን ነው የቀረጸን!3 ስለዚህ ካመነው፣ መልካሙን፣ ብሩሁን፣ የህይወት ተስፋ ነገሮችን እንድንገነዘባቸው ይረዳናል። እናም በቂ በሆነ እርግጠኝነት፣ አለማችን ብሩህ ትሆናለች። አይ፣ ወዲያው አይከሰትም፣ ነገር ግን እውነቱን ለመናገር፣ ስንት መልካም ነገሮች ይከሰታሉ? ምርጥ ነገሮች ናቸው ሚመስሉኝ፣ ልክ ቤት እንደሚሰራ ዳቦ ወይም የብርትኳን ማልማላታ፣ ትግስት እና ስራን ይጠይቃል።

ኤቫ ለደቂቃ አሰበች እና እንዲህ አለች፣ “ምናልባት ሁሉ ነገር ፍፁም ሆኖ በህይወታቸው ውስጥ ለሌላቻ ሰዎች ቀላል አይደለም።”

“ውድ ኤቫ፣ በእውነት የእኔ ህይወት ፍፁም ነው ብለሽ ታስቢያለሽን?” ከኤቫ ጋር በሚመቸው ሶፋ ላይ ቁጭ አለች። “ ተስፋ የቆረጥኩበት ጊዜ ነበር፣ መቀጠል አልፈለኩም ነበር።”

“አንቺ?” ብላ ኤቫ ጠየቀች

አክስት ሮዝ በአወንታ ጭንቅላትዋን ነቀነቀችው።“ለህይወቴ የተመኘዋቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ።” በምትናገር ግዜ ኤቫ ሰምታ ማታውቀው የሀዘን ድምጽ ውስጧ ገባ። “አብዛኞቹ አልተከሰቱም። ከአንዱ በኋላ ሌላ የልብ ስብራት ነበር። አንድ ቀን ተስፋ እንዳደረኩት መንገዱ በጭራሽ እንደማይሆንተገነዘብኩኝ። ያ የሚያስጨንቅ ቀን ነበር። ተስፋ ለመቁረጥ እና የተንገላታ ለምሆን ዝግጁ ነበርኩኝ።

“ስለዚህ ምን አደረግሽ?”

“በግዜው ምንም አላደረኩም። በቃ ተናድጄ ነብር።በጣም ተከፍቼ ስለነበር ሌሎች ሰዎች ከኔጋር አብረውኝ እንዲሆኑ ምቹ አልነበርኩም።” ከዛ ትንሽ ሳቀች፣ ነገር ግን የተለመደው ቤቱን የሚሞላው ትልቅ ሳቅ አልነበረም። “‘አግባብ አይደለም’ የሚለውን ሙዚቃ ነብር በአእምሮዬ ደጋግሜ ማዜመው። ነገር ግን በስተመጨረሻ ሙሉ ህይወቴን የቀየረው አንድ ነገር አገኘው።”

“ምን ነበር?”

“እምነት፣” አክስት ሮዝ ፈገግ አለች። “እምነትን አገኘሁ። እናም እምነት ወደ ተስፋ መራኝ። እናም እምነት እና ተስፋ አንድ ቀን ሁሉም ነገር ስሜት እንደሚሰጥ መተማመንን ሰጠኝ፣ ያም በአዳኝ ምክንያት ነው፣ ሁሉም መጥፎ ነገሮች መልካም ይደረጋሉ። ከዛ በኋላ፣” ያንን መንገድ ከእኔ በፊት ይሆናል ብዬ እንዳሰብኩት ሀዘን እና አብዋራማ ሳይሆን አየሁት። ብሩ ሰማያዊዎቹን፣ ለምለም አረንጓዴዎችን፣ እናም ፍም የመሰሉ ቀዮችን ማስተዋል ጀመርኩ፣ እናም ምርጫ እንዳለኝ ወሰንኩ— በራሴ ላይ ባዝንም ቀስ በቀስ መሻሻልን አረኩኝ፣ ወይም ትንሽ እምነት ይኖረኝ ነበር፣ እንድታይ እና ደስታ እንዲሰማኝ የሚያደርጉ ነገሮችን አደረኩኝ።” አሁን ይህንን ስትል ድምፅዋ በምስል ውስጥ እንዳለችው ሴት ልጅ ይቦርቅ ነበር።

አክስት ሮስ ከጠረጴዛው ጫፍ ደረሰችና በጣም ያረጀ ቅዱስ መፅሀፍቷን ወደ ጭኗ ሳበችው። ዶክተር ምርመራ እስኪያደርግልኝ ድረስ በጣም ጭንቀት ውስጥ የነበርኩኝ አይመስለኝም ነበር— እራስሽን ከዛ ውስጥ ማውጣት እንደምትችዪ እርግጠኛ አይደለሁም። ነገር ግን እራሴን ወደ ሀዘን ውስጥ እንደከተትኩኝ እርግጠኛ ነበርኩ! አዎ፣ አሳዛኝ ቀናቶች ነበሩኝ፣ ነገር ግን በሀዘን መተከዜ እና መጨነቄ ሊለወጥ አልነበረም—ነገሮችን የበለጠ ያባባሰ ነበር። በአዳኝ ላይ እምነት ማኖር ባለፈው ህይወቴ ምንም ቢከሰትም፣ ታሪኬ አስደሳች አጨራረስ ሊኖረው እንደሚችል አስተማረኝ።

“ያንን እንዴት አወቅሽ?” ብላ ኤቫ ጠየቀች

አክስት ሮስ ከመፅሀፍ ቅዱሷ ውስጥ ገልጽ ከፈተችና እንዲህ አለች፣ “እዚህ እንዲህ ይላል፤

“‘እግዚያብሄር…ከእነርሱ ጋር ያድራል፣ እነሱም ህዝቡ ይሆናሉ፣ እግዚያብሄር ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤

“እምባዎችን ሁሉ ከአይናቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ሀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ስቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀድሞ ስርዓት አልፏልና።”4

የወላጅ አክስት ሮስ ኤቫን ተመለከተቻት። በማንሾካሾክ ላይ ሳለች ፈገግታዋ ትልቅ ነበር፤ ትንሽ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ፣ “ከሰማሻቸው ነገሮች ሁሉ በጣም የሚያምረው ነገር አይደለምን?” አለቻት።

በእርግጥ የሚያምር ይመስላል፣ ኤቫ እንዲህ አሰበች

የአያት እህት ሮዝ ጥቂት ገፆችን አገላበጠች እና ኢቫ እንድታነብ ወደ አንድ ጥቅስ ጠቆመች፤ “ነገር ግን አይን ያላያቸው ጆሮም ያልሰማቸው በሰው ልብ ያልታሰቡ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው።”5

“ክብር ባለው የወደፊት ህይወት፣” አክስት ሮስ እንዲህ አለች፣ “ እንዳቀድነው በማይሄዱ ባለፉ ወይም አሁን ባሉ ነገሮች ላይ ለምን እንዋጣለን?”

ኢቫ የአይኖቿ ሽፋሽፍት አካባቢ ያለ ቆዳዋ ተጨማደደ( ግራ ገባት )። “ነገር ግን ቆይ አንዴ ጠብቂኝ፣” አለች። ደስተኛ መሆን ማለት ወደ ፊት የሚመጣውን ደስታ መጠበቅ ማለት ነው እያልሽ ነው? ደስታችን ለዘላለም ነውን? ጥቂቶቹ አሁን ሊከሰቱ አይችሉምን?”

“ኦህ፣ በእርግጥ መሆን ይችላል!” አክስት ሮስ በደስታ አለች። “ውድ ልጅ፣ አሁን የዘላለም አንዱ አካል ነው። ከሞትን በኋላ ብቻ አይደለም ሚጀምረው! አሁን ከፊትሽ ወደ ተቀመጠው ደስታ እምነት እና ተስፋ አይኖችሽን ይከፍቱታል።

“እንዲህ የሚል ግጥም አውቃለሁ፣ ‘ዘላለም በአሁኖች ነው የሚሰራው።’6 የእኔ ዘላለም ‘በአሁን’ ጭለማ እና አስፈሪ እንዲሰራ አልፈለኩም።’ ጥርሴን በመንከስ፣ አይኖቼን በመጨፈን፣ እና በቅርብ ወደ መራራው በመጽናት ህይወቴን ከሌሎች አርቄ መኖር አልፈለኩም። እምነት አሁን በደስታ የምኖርበት ተስፋ ሰጠኝ።

“እና ከዚያ ምን አደረግሽ?” በማለት ኤቫ ጠየቀች።

“ህይወቴን ትርጉም ባላቸው ነገሮች በመሙላት በእግዚያብሄር ቃልኪዳኖች ላይ እምነትን ተለማመድኩ። ትምህትር ቤት ገባሁ። ትምህርትን አገኘሁ። ያ ወደ ምወደው ስራ መራኝ።”

ኤቫ ስለዚህ ጥቂት አሰበችና እንዲህ አለች፣ “ነገር ግን በእርግጥ በስራ መጠመድ አይደለም ደስተኛ ያረገሽ። በስራ የተጠመዱ ብዙ ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች አሉ።”

“እንዲህ በጣም ለጋ እድሜ ላይ ላለ ሰው እንዴት ነው ብልህ መሆን ይቻላል?” አክስት ሮስ ብላ ጠየቀች። “ በጣም ትክክል ብለሻል። እና አብዛኞቹ በስራ የተጠመዱት፣ ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች በአለም ላይ ካለው ሁሉ በጣም ትርጉም ያለውን አንድ ነገር— ክርስቶስ የወንጌሉ ዋና ነገር ነው ያለውን ረስተዋል።”

“እና ምንድን ነው እሱ?” በማለት ኤቫ ጠየቀች።

ሮስ እንዲህ አለች “ፍቅር ነው—ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር፣” “አየሽ፣ በወንጌል ውስጥ ያለ ሁሉ ነገር መሆን ያለባቸው እናም ግዴታዎች እና አድርጉዎች — ወደ ፍቅር ይመራሉ። እግዚያብሄርን ስንወድ፣ ልናገለግለው እንፈልጋለን። እንደሱ መሆንን እንፈልጋለን። ባልንጀሮቻችንን ስንወድ፣ ስለ ራሳችን ችግሮች ብዙ ማሰብ እናቆምና ሌሎችን የነሱን ችግሮች ለመፍታት እንረዳለን።”7

“እናም ያ ነው ደስተኞች ሚያደርገን?” ብላ ኤቫ ጠየቀች።

የወላጅ አክስቷ ሮስ ጭንቅላትዋን በአወነታ ነቀነቀችና ፈገግ አለች፣ አይኖችዋ በእምባ ተሞልተዋል። “አዎ፣ ውዴ። ነው ደስተኛ የሚያረገን።

በጭራሽ ተመሳሳይ አልነበረችም

በሚቀጥለው ቀን ኤቫ የወላጅ አክስቷ ሮስን አቀፈቻትና ላረገችው ነገር ሁሉ አመሰገነቻት። ወደ ቤተሰቦቿ እና ጓደኟቿ እናም ወደ ቤቷ እናም ጎረቤቶቿ መኖሪያ ተመለሰች።

ነገር ግን ተመሳሳይ ሰው አልነበረችም።

ኤቫ እያደገች ስትመጣ፣ በአብዛኛውን ጊዜ የወላጅ አክስቷ ሮስን ቃላቶች ታስባቸው ነበር። ኤቫ በመጨረሻ አገባች፣ ልጆችን አሳደገች፣ እናም ረጅም እና የሚያምር ህይወትን ኖረች።

እናም አንድ ቀን፣ በራስዋ ቤት ውስጥ በቆመችበት ሰአት፣ የመስራቾችን አለባበስ የሚመስል ቀሚሰ ያረገች ከሱ ጋር ተያይዞ ብሩህ ሰማያዊ መስመር እየዘለለች ያለውን የአንድ ሴት ልጅ ምስል እያደነቀች፣ የወላጅ አክስቷ ሮስ በዛ በአስገራሚው በጋ ላይ የነበሩበትን እድሜ እሷም ተመሳሳይ እድሜ ላይ እንደደረሰች ተገነዘበች።

የምትዘል መስራች ሴት ልጅ

ይህንን በተገነዘበች ጊዜ፣ ልዩ የሆነ ፀሎት በልቧ ውስጥ እንደሞላ ተሰማት። እናም ኤቫ ለህይወትዋ፣ ለቤተሰቧ፣ ለተመለሰው የክርስቶስ ወንጌል፣ የወላጅ አክስቷ ሮስ በጣም ከረጅም ግዜ በፊት ስላስተማረቻት8 ስለ እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር ምስጋና ተሰማት።9

በረከት

የተወደዳችሁ የክርስቶስ እህቶቼ፣ በዚህ ታሪክ ውስጥ አንድ ነገር ልባችሁን እንደነካው እና ነፍሳችሁን እንዳነሳሳው ተስፋ እና ፀሎቴ ነው። እግዚያብሄር እንደሚኖር እና እንደሚወዳችሁ አውቃለሁ።

በራሳችሁ የብሩህ ደቀመዛሙርትነት መንገድ ላይ በምትጓዙ ግዜ፣ በመንገዳቹ ላይ እያንዳንዱ እርምጃችሁን እምነት እንዲያጠነክረው፣ ያ ተስፋ የሰማይ አባት ለእናንተ እንዳስቀመጠው ክብሮች አይናችሁን እንዲከፍት፤ እና ያ ለእግዚያብሄር ያለ ፍቅር እና ለልጆቹ ሁሉ ያለው ፍቅር ልቦቻችሁን እንዲሞሉ እፀልያለሁ። የጌታ ሐዋሪያ እንደመሆኔ፣ ይህንን የምተወው እንደ ምስክርነቴ እና በረከቴ ነው፣ በእየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ለምሳሌ ማቴዎስ 13፥24–3018፥23–3520፥1–1622፥1–1425Luke 10፥25–3715፥11–32 ተመልከቱ።

  2. ለምሳሌ፣ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Guided Safely Home፣” Ensign or Liahona፣ ህዳር 2014፣ 67–69፤ “Love—the Essence of the Gospel፣” Ensign or Liahona፣ ግንቦት 2014፣ 91–94፤ “We Never Walk Alone፣” Ensign or Liahona፣ ህዳር 2013፣ 121–24፤ “Obedience Brings Blessings፣” Ensign or Liahona፣ ግንቦት 2013፣ 89–92 ተመልከቱ።

  3. 2 ኔፊ 2፥25 ተመልከቱ።

  4. ራዕይ 21፥3–4

  5. 1 ቆሮንቶስ 2፥9

  6. “Forever—is composed of Nows፣” in Final Harvest: Emily Dickinson’s Poems፣ sel. Thomas H. Johnson (1961)፣ 158፤ see also poetryfoundation.org/poem/182912።

  7. ሉቃስ 9፥24 ተመልከቱ።

  8. “Often the prickly thorn produces tender roses” (Ovid፣ Epistulae ex ponto፣ book 2፣ epistle 2፣ line 34፤ “Saepe creat molles aspera spina rosas”)።

  9. ሞሮኒ 7፥42 ተመልከቱ።