ቀጣዩ እርምጃችሁ
አፍቃሪያችሁ የሰማይ አባት እና እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እነርሱ ለመምጣት ቀጣዩን እርምጃ እንድትወስዱ የጋብዧችኋል።
ከድንቅ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጋር በቅርቡ በነበረ ስብሰባ ወቅት ልቤ ተነካ። “ከሰማይ አባት ጋር ዳግም መኖር የሚፈልግ ማነው?” የሚለው ጥያቄ ተጠይቋል። ሁሉም እጆች ወደ ላይ ተነሱ። “አሳካዋለሁ ብሎስ የሚተማመን ማነው?” የሚል ነበር ቀጠዩ ጥያቄ። በሚያሳዝን እና በሚያስገርም መልኩ፣ አብዛኛው እጆች ወደ ታች ሆኑ።
አሁን በሆንነው እና መሆን በምንፈልገው መሀል ያለውን ልዩነት ስናስተውል፣ አብዛኞቻችን እምነትን እና ተስፋን ለመቁረጥ እንድንመርጥ ይፈታተነናል።1
“ንፁህ ያልሆነ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ሊሆን አይቻለውም”2 በዛም ምክንያት፣ እንደገና ከእርሱ ጋር ለመኖር ከሀጢአት የነፃን3 እና የተቀደስን መሆን ይገባናል።4 ይህንን ማድረግ ያለብን ብቻችንን ቢሆን ኖሮ፣ ማንኛችንም አናሳካውም ነበር። ነገር ግን ብቻችንን አይደለንም። በእርግጥም፣ በፍፁም ብቸኛ አይደለንም።
በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሀጢአት ክፍያው አማካኝነት እኛ የሰማይ እርዳታ አለን።5 አዳኝ እንዲህ አለ፣ “በእኔ እምነት ካላችሁ እኔ ያስፈልጋል የምለውን መንኛውንም ነገር ለመስራት ስልጣን ይኖራችኋል።”6 እምነት ሲለማመዱት ይጠነክራል።
በሰማይ ወዳለው አባታችን ለመመለስ በምናደርገው ጉዞ ውስጥ የሚረዱንን ሶስት መርሆዎች በጋራ እናስብባቸው።
እንደ ልጅ መሆን
የመርህ ትንሹ የልጅ ልጃችን አመላክቷል። ዳዴ ማለት እና ከዛም መቆም ከተማረ በኋላ፣መራመድ ለመሞከር ተዘጋጀ። በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሙከራዎቹ፣ ወደቀ፣ አለቀሰ፣ እና እንደዚህ የሚል አይነት እይታን አሳየ፣ “ይሄን መቼም መቼም ቢሆን ደግሜ አልሞክረውም! በቀላሉ ዳዴ እያልኩ ነው የምቀጥለው።”
ሲንገዳገድ እና ሲወድቅ፣ አፍቃሪ ወላጆቹ ተስፋ የለውም ወይም መቼም አይራመድም ብለው አላሰቡም። በምትኩ እርሱን በመጥራት በእጃቸው ደገፉት፣ እና አይኑን በእነርሱ ላይ አድርጎ፣ ወደ አፍቃሪ ጥሪያቸው ለመጠጋት እንደገና ሞከረ።
አፍቃሪ ወላጆች በትክክለኛው መንገድ በምናደርገው ትንሽ እርምጃ እንኳን በተዘረጉ እጆች ሊቀበሉን ሁሌም ዝግጁ ናቸው። ደጋግሞ የመሞከር ፍላጎታችን ወደ መሻሻል እና ወደ ስኬት እንደሚያመራን ያውቃሉ።
የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ፣ እንደ ህፃን ልጅ መሆን እንዳለብን አዳኝ አስተምሯል።7 ስለዚህ፣ በመንፈሳዊ መልኩ ለመናገር፣ የመጀመሪያው መርህ እንደ ልጅ ያደረግናቸውን ማድረግ ያስፈልገናል።8
በሰማይ ባለው አባታችን እና በአዳኛችን ላይ ትኩረት ለማድረግ ባለን የልጅነት ትህትና እና ፍላጎት፣ ብንወድቅም እንኳን በፍፁም ተስፋ ሳንቆርጥ ወደ እነርሱ እንራመዳለን። በእያንዳንዱ የእምነት እርምጃ አፍቃሪው የሰማይ አባታችን ይደሰታል፣ እና ብንወድቅ፣ ዳግም ለመመለስ እና ለመሞከር ባለን እያንዳንዱ ጥረት ይደሰታል።
በእምነት መተግበር
ሁለተኛው መርህ በሁለት አማኝ ቅዱሳን ተመላክቷል፣ ሁለቱም ዘለአለማዊ አጋር ለማግኘት ጥልቅ ፍላጎት ነበራቸው። ሁለቱም በፀሎት መንፈስ በእምነት የተሞሉ እርምጃዎችን ወሰዱ።
ዩሪ፣ የራሽያ የኋለኛው ቀን ቅዱስ፣ ወደ ቤተመቅደስ እረጅም ጉዞ ለማድረግ መስዋእት አደረገ እናም አጠራቀመ። ባቡር ውስጥ ብሩህ የሆነ ገፅታ ያላትን ቆንጆ ሴት አስተዋለ፣ እናም ወንጌልን ለእርሷ ማካፈል እንዳለበት ተሰማው። ሌላ ምን ማድረግ እንዳለበት ባለማወቁ፣ከመፀሐፈ ሞርሞን ማንበብ ጀመረ፣ ታየኛለች ብሎ ተስፋ በማድረግ።
ሴቷ፣ ማሪያ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱስ እንደነበረች ዩሪ አልተገነዘበም ነበር። ዩሪም እራሱ አባል መሆኑን ባለማወቅ፣ እና ወንጌልን ለእርሱ ለማካፈል የተሰማትን መነሳሳት በመከተል፣ እርሱ ይመለከታል ብላ ተስፋ በማድረግ፣ ማሪያ ከመፀሐፈ ሞርሞን ማንበብ ጀመረች።
እናም፣ በማከታተል ቀና ብለው ተመለከቱ፣ በእያንዳንዳቸው እጅ ላይ መፅሐፈ ሞርሞን በማየታቸው ዩሪ እና ማርያ ተደነቁ፣ እናም አዎ፣ በፍቅር ከወደቁ በኋላ፣ በቤተመቅደስ ተጋቡ። ዛሬ፣ የቮሮንዝ፣ ራሽያዎቹ ዩሪ እና ማርያ ኩችፖቭ፣ እንደ ዘለአለማዊ ጥንዶች፣ በራሽያ ለቤተክርስቲያኑ እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።
እዚህ ላይ ትኩረቱ እነዚህ ጥንዶች በእምነት ለመተግበር ባላቸው ፍላጎት ላይ ብቻ አይደለም። ስለ ሁለተኛው መርህም ጭምር ነው---ጌታ በእምነት ለመተግበር ያለንን ፍላጎት ከማጣመርም በላይ ያደርጋል። እርምጃን ለመውሰድ ያለን ፍላጎት ገና አላበቃም፤ ቃል የተገቡት የጌታ በረከቶችን ያስከትላል።
የሰማይ አባታችን እና አዳኛችን እኛን ለመባረክ ይጓጓሉ። ከሁሉም በላይ፣ የሚጠይቁን ከባረኩን በረከት ውስጥ አስር እጁን ብቻ ነው እናም የሰማይ መስኮቶች እንደሚከፈቱ ቃል ገብተዋል!9
በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ለመተግበር ስንፈልግ እና ተጨማሪ እርጃን ስንወስድ፣ በተለይም ለውጥ እና ንስሀን የሚጠይቅ ምቹ ያልሆነ እርምጃ፣ በጥንካሬ እንባረካለን።10
በቀጣዩ እርምጃችንም ጌታ እንደሚመራንም እመሰክራለሁ። በመሞከር፣ ንሰሀ በመግባት፣ እና በሰማይ አባታችን እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ወደ ፊት በመግፋት ለመቀጠል ፍላጎት ካለን ጥረቶቻችንን ከእርሱ ሀይል ጋር ከማጣመርም በላይ ያደርጋል።
መንፈሳዊ ስጦታዎች ቃል የተገቡት እግዚአብሔርን ለሚወዱ እና ሁሉንም ትእዛዛቱን ለሚጠብቁት ብቻ አይደለም፣ በሚያስመሰግን መልኩ፣ “እንደዚያ ለማድረግ ልምንሻም”11 ሰዎች ጭምር ነው። ጥንካሬ የተሰጠው በመሻት እና በመሞከር ለሚቀጥሉ ነው።
ወደ ሰማይ አባታችን የምንመለስበት መንገድን የሚጠቁሙን አመላካቾች የቅዱስ ቁርባን ስርአት ቋሚ ቃልኪዳን እና የእኛ የሰንበት ቀን አከባበር ናቸው። ሰንበት ለእኛ ከጌታ የተሰጠ ስጦታ መሆኑን ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ፕሬዘዳንት ሩሴል ኤም ኔልሰን አስተምረውናል። የእኛ ሳምንታዊ የሰንበት ልባዊ አክብሮት እኛ ጌታን እንደምንወደው የሚያሳይ ጠቋሚ ነው።12
“ስሙን በላያችን ላይ ለመውሰድ፣ እና ሁሌም እርሱን ልናስታውስ፣ እናም ትእዛዛቱን ልንጠብቅ ፍቃደኞች መሆናችንን”13 በእያንዳንዱ የሰንበት ቀን እናሳያለን። በንሰሀ ለተሞላው ልባችን እና ለመሰጠታችን ምላሽ፣ ጌታ ቃል የተገባውን የሀጢያት ስርየት ያድሳል እናም “ሁልጊዜም መንፈሱ ከእኛ ጋር እንዲሆን”14 ያስችለናል። የመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ ያሻሽለናል፣ ያጠነክረናል፣ ያስተምረናል፣ እናም ይመራናል።
በእያንዳንዱ ሰንበት እርሱን በማስታወስ፣ በእነዚህ ሁለት አስፈላጊ አመልካቾች ልባችንን ወደ አዳኝ የምናዞር ከሆነ፣ በጌታ ቃል በተገቡ በረከቶች ጥረቶቻችን በድጋሜ ብቁ ይደረጋሉ። ያ ቃል ተገብቶልናል፣ ከልብ በሆነ የሰንበት ቀን አክብሮት፣ የምድር ሙላት የእኛ ይሆናል።15
ወደ ሰማይ አባት መመለሻ መንገዱ ወደ ጌታችን ቤት ያመራል፣ ለእኛ እና ለተለዩን የምናፈቅራቸው ሰዎች የሚሆኑ የመዳን ስርአቶችን የምንቀበልበት ቦታ ነው። ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ ፓከር እንዲህ አስተማሩ፣ “ስርአቶች እና ቃልኪዳኖች ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረን ሰነዶች ናቸው።”16 እያንዳንዳችን ሁሌም ብቁ እንድንሆን እና በቋሚነት ለማገልገል የቤተመቅደስ መግቢያን እንድንጠቀም እፀልያለሁ።
ተፈጥሮአዊውን ሰው ማሸነፍ
ሶስተኛው መርህ ይህ ነው፤ የማራዘም፣ የመተው፣ እና ተስፋ የመቁረጥ መነሳሻ የሆነውን ተፈጥሮአዊውን ሰው መጋፈጥ አለብን።17
በቃልኪዳን መንገድ እያደግን ስንመጣ፣ አንዳንዴ ብዙ የሆኑ ስህተቶችን እንሰራለን። ለማሸነፍ ሀይል የሌለን በሚመስል ስሜት አንዳንዶቻችን ከባህሪ እና ሱሶች ጋር እንታገላለን። ነገር ግን በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን የተግባር እና የሀይል መርህ ነው።18 ለመተግበር ፍላጎት ካለን፣ ንስሀ ለመግባት እና ለመለወጥ በጥንካሬ እንባረካለን።
የምንወድቀው አንድ የእምነት እርምጃን ለመውሰድ ካቃተን ብቻ ነው። መቼም ጥሎን በማያውቀው እና በማይጥለን አዳኝ ላይ ቀንበራችን በእምነት ካስደገፍን ለንወድቅ አይቻለንም!
ቃል የተገቡ በረከቶች
እያንዳንዱ በእምነት የተሞላ እርምጃ ከሰማይ በሚሰጥ እርዳታ እንደሚሳካ ቃል እገባለሁ። ለሰማይ አባት ስንፀልይ፣ በአዳኛችን ስንደገፍ እና ስንከተለው፣ እና መንፈስ ቅዱስን ስናዳምጥ ምሬት ወደ እኛ ይመጣላ። በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ መስዋእትነት አማካኝነት ጥንካሬ ይመጣል።19 በእግዚአብሔር ፀጋ አማካኝነት መዳን እና ይቅር መባል ይመጣል።20 ጌታ ለእኛ ባለው ጊዜ ላይ በመታመን ጥበብ እና ትእግስት ይመጣል። በህይወት ያሉትን ነብያ፣ ቶማስ ኤስ ሞንሰንን በመከተል ጥበቃ ይመጣል።
በብቁነት ወደ ሰማይ አባታችሁ እና ወደ አዳኛችን ለመመለስ እና ወደ ሚሞቀው ጉያቸው ስትገቡ “ደስታ ይኖራችሁ ዘንድ”21 ነበር የተፈጠራችሁት።
ስለነዚህ እሙን እውነታዎች እመሰክራለሁ። የእናንተ አፍቃሪ የሆኑት የሰማይ አባታችሁ እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ህያው ናቸው። እናንተን ያውቋችኋል። ያፈቅሯችኋል። ወደ እነርሱ ቀጣይ እርምጃ እንድትወስዱ በፍቅር ይጋብዟችኋል። አትጠብቁ። አሁኑኑ እርምጃውን ውሰዱ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።