2010–2019 (እ.አ.አ)
ልቤ እነርሱን በማሰላሰል ይቀጥላል
ኦክተውበር 2015


10:10

ልቤ እነርሱን በማሰላሰል ይቀጥላል

የእግዚአብሔርን ቃላት ሰፋ ባሉ እና ጥልቅ በሆኑ ሁኔታዎች ለማሰላሰል እንድትመርጡ በቅንነት እጸልያለሁ።

በስራዬ፣ ኢንቬስተር ነኝ። በእምነቴ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ነኝ።1 በገንዘብ ስራዬ፣ ትክክለኛ የሆነ የገንዘብ ጥበቃ መርሆን እከተላለሁ። በእምነቴ ስኖር፣ እንደ አዳኝ እንድሆን የሚረዱኝን መንፈሳዊ መርሆችን ለመከተል እጥራለሁ።

ግብዣዎች በረከቶችን ያመጣሉ

በህይወቴ የግል ሽልማቶችን ያገኘሁት አስቸጋሪ ነግርን እንዳደርግ አንድ ሰው ስለጋበዘኝ ነው። በዚያ መንፈስ፣ ለእያንዳንዳችሁ ሁለት ግብዣዎችን ልሰጣችሁ እፈልጋለሁ። የመጀመሪያው ግብዣ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው። የሁለተኛው ግብዣ፣ መንፈሳዊ ግንኙነት ያለው ነው። ሁለቱም ግብዣዎች፣ ተቀባይነት ካገኙ፣ ሽልማታቸውን ለማግኘት ለረጅም ጊዜ ተገቢ ጥረት መደረግ አለበት።

የመጀመሪያው ግብዣ

የመጀመሪያ ግብዣ ቀላል ነው፤ በየሳምንቱ ገንዘብ እንድታጠራቅሙ እጋብዛችኋለሁ። የምታጠራቅሙት መጠን ብዙ መሆን አይጠበቅበትም፣ ምርጫውም የእናንተ ነው። የማጠራቀም ልምድን ስታሳድጉ፣ በግል ጥቅም ታገኛላችሁ። በትጋታችሁ ምክንያት ሌሎችን በገንዘብ ለማገዝ እድልም ይኖራችኋል። በየሳምንት ለስድስት ወር፣ ለአመት፣ ለ10 አመት፣ ወይም ለተጨማሪ ጊዜዎች ገንዘብን በማጠራቀም ምን አይነት ጥሩ ውጤት እንደሚኖር አስቡበት። በጊዜ የሚያልፉ ትንሽ ጥረቶች ታላቅ ውጤታ ያመጣሉ።2

ሁለተኛው ግብዣ

ሁለተኛው ግብዣዬ ከመጀመሪያው በጣም የተለየ እና በጣም አስፈላጊ የሆነ ነው። ያም ይህ ነው፥ በየሳምንቱ አንድ አንቀጽን “በማሰላስል-በቃልም ያዙ”።3አሰላስሉ-በቃልም ያዙ የሚለው ቃል በመዝገበ ቃላት ላይ የሚገኝ አይደለም፣ ነገር ግን በልቤ ውስጥ ቦታን አግኝቷል። አሰላስሉ-በቃልም ያዙ ምን ማለት ነው? ይህም በ80 ፐርሰንት አሰላስሉ እና በ20 ፐርሰንት በቃላችሁ ያዙ የሚል ነው ለማለት እፈልጋለሁ።

ሁለት ቀላል ደረጃዎች አሉ፥

መጀመሪያ፣ የቅዱሳት መጻህፍት አንቀጾችን በየሳምንቱ ምረጡ እናም በየቀኑ በምታዩት ቦታ ላይ አስቀምጡት።

ሁለተኛ፣ አንቀጹን በእያንዳንዱ ቀን ለብዙ ጊዜ አንብቡ ወይም አስቡበት እናም የቃላቶቹን እና ዋና ሀረጎችን በሳምንቱ ውስጥ አሰላስሉ።

ህን በየሳምንቱ ለስድስት ወር፣ ለአመት፣ ለ10 አመት ወይም ለተጨማሪ ጊዜ ማድረግ የሚያመጣውን ከፍ የሚያደርጉ ውጤቶችን አስቡ።

ይህን ጥረት ስታደርጉ፣ ተጨማሪ መንፈሳዊነት ይሰማችኋል። የምታፈቅሯቸውንም ትርጉም ባለው መንገዶች ለማስተማር እና ከፍ ለማድረግ ትችላላችሁ።

የዋና መተንፈሻ መሳሪያ

በየሳምቱ አሰላስሎ-መገምግሙን ካደረጋችሁ፣ በድሮ በባህር ውስጥ በቱባ እየተነፈሰ እንደሚዋኝ ሰው እና አሁን ግን በመተንፈሻ መሳሪያ በባህር ውስጥ በዝልቅ ለመዋኘት እንደወሰኑ ሰዎች ስሜት ይኖራችኋል። በዚያ ውሳኔ፣ የወንጌል መርሆች ዝልቅ መረዳጃ የእናንተ ይሆናል እናም አዲስ መንፈሳዊ አስተያየቶች ህይወታችሁን ይባርኩላችኋል።

ስኩባ ዳይቪንግ

በየሳምንቱ በመረጣችኋቸው አንቀጾች ላይ ስታሰላስሉ፣ ቃላት እና ሀረጎች በልባችሁ ይጻፋሉ።.4 ቃላት እና ሀረጎች በአዕሮዎቻችሁ ውስጥም ይጻፋሉ። በሌላ አባባልም፣ መገምገም በቀላል እና በፍጥረት አይነት ይሆናል። የአሰላስሎ-ገምግሙ ዋና አላማ ሀሳባችሁ የሚሄዱበት ከፍ የሚያስደርግ፣ ከጌታ መንፈስ ጋር በቅርብ የምትቆዩበት፣ ቦታ እንዲሰጣችሁ ነው።

አዳኝ እንዳለው፣ “በአዕምሮአችሁ የህይወት ቃላትን ሁልጊዜም እንደ ሀብት ጠብቁ።”5 ያንን ለማድረግ አሰላስሎ በቃል መያዝ ያንን ቀላል እና የሚያንፅ መንገድ ነው።

ኔፊ አሰላስሎ በቃል የሚይዝ እንደነበር እምነት አለኝ። እንዲህ ብሏል፣ “ነፍሴ በቅዱሳን መፃሕፍት ትደሰታለች፣ እንዲሁም ልቤ [ [ሁልጊዜ], ታሰላስላቸዋለች፣ እንዲሁም እኔ እነርሱን ለልጆቼ ትምህርትና ጥቅም እፅፋለሁ።”6 ቅዱሳት መጻህፍትን ሲጽፍ እና ሲያሰላስል ስለልጆቹ ያስብ ነበር። እናንተ ሁልጊዜ አዕምሮአችሁን በእግዚአብሔር ቃላት ለመሙላት ስትጥሩ ቤተሰባችሁ እንዴት ይጠቀማሉ?

አንቀጾቼ

በቅርቡ አልማ 5፥16 ን አሰላስዬ በቃሌ ያዝኩ። እንዲህም ይነበባል፣ “እኔ እላችኋለሁ፣ በዚያን ቀን የጌታ ድምፅ ለራሳችሁ፣ እናንተ የተባረካችሁ ወደ እኔ ኑ፣ እነሆ ሥራችሁ በምድር ፊት የፅድቅ ሥራ ነው እንደሚላችሁ ትገምታላችሁን?”

በሳምንቱ መጨረሻ ላይ፣ በአዕምሮዬ ውስጥ እንዲህ ነበር የተጻፈው፥ “እናንተ የተባረካችሁ ወደ እኔ ኑ፣ እነሆ ሥራችሁ በምድር ፊት የፅድቅ ሥራ ነውና” (አልማ 5:16).የሚል የጌታን ድምጽ መስማትን አስቡት።

እንደምትመለከቱት፣ ጥቅሱን ቃል በቃል አልያዝኩትም። ነገር ግን፣ የአንቀጹን ዋና ክፍል እና የት እንደማገኘው በተደጋጋሚ አሰላሰልኩኝ። ነገር ግን የዚህ ድርጊት አስደሳቹ ነገር ቢኖር፣ ሀሳቤ የሚሄድበት ከፍተኛ ቦታ ኖረኝ። በሳምንቱ በሙሉ አዳኝ የሚያበረታቱ ቃላት ለእኔ ሲናገር አየሁ። ያም ምስል ልቤን ነካው እናም “የጻድቅ ስራ” ለመስራት ፍላጎት እንዲኖረኝ ለመነሳሳት ረዳኝ። “በሁሉም ሀሳቦች [ወደ ክርስቶስ]”7 ስንመለከት ሊከሰት የሚችለው ይህ ነው።

መታገል አለብን

“ይህን ለምን አደርጋለሁ?” ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። ምላሼም፣ ክፉነት በሚስፋፋበት ጊዜ ውስጥ ነው የምንኖረው። ነባራዊ ሁኔታን ለመቀበል እና በምንመለከትበት በሙሉ የሚያስጠሉ ቃላትን እና ኃጢያተኛ የሆኑትን ለማየት በመቀበል መልስ አለመስጠት አንችልም። መታገል አለብን። አዕምሮዎቻችን ከፍ በሚያደርጉ ሀሳቦች እና ቅርጾች ሲሞሉ፣ እኛም “ሁልጊዜ ስናስታውሰው፣”8 ለጉድፍ እና ቆሻሻ ምንም የቀረ ቦታ አይኖርም።

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም “ያላቸውን ነገሮች እንዲያሰላሉ” ጋብዟል።9 የአሰላስሎ በቃል መያዝን ለግላችሁ እና ለቤተሰብ ቅዱስ መጻህፍት ጥናት እንደተጨማሪ ሀሳብ ተመልከቱት፣ ነገር ግን ይህን እንደመተኪያ እንዲሆን በፍፁም አታድርጉት። የአሰላስሎ በቃል መያዝ በመንፈሳዊ ምግባችሁ ቀስ በቀስ በሰውነት ውስጥ እንደሚለቀቅ ቫይታሚን አይነት ነው።

ይህ በጣም ከባድ ነው

እናንተም “አሰላስሎ በቃል መያዝ ለእኔ በጣም ከባድ ነው” ትሉ ይሆናል። በዚህ ተስፋ አትቁረጡ። ከባድ ነገር መልካም ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ብዙ ከባድ ነገሮችን እንድናደርግ ይጋብዘናል፣ ምክንያቱም በጥረታችን ውጤት እንደምንባረክ ያውቃልና።10

ቅዱሳን መጸሀፍት በስልከ ላይ

አንዱ ወጣት ጎረቤታችን አሰላስሎ በቃል የሚይዝበት ቀላል መንገድ አገኘ። በየሳምንቱ የሚያጠናውን የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች በእጅ ስልኩ የመጀመሪያ የእይታ ቦታ ላይ አስገባው። ሌላ ልትሞክሩት የምትችሉት ሀሳብም ጥቅሳችሁን ከወንድምና እህታችሁ፣ ከልጃችሁ፣ ወይም ከጓደኛችሁ ጋር መካፈል ነው። ባለቤቴ ጁሊ እና እኔ እርስ በራስ እንረዳዳለን። በየእሁዱ ጥቅሶቻችንን እንመርጣለን። የእርሷን በፍሪጅ ላይ ታስቀምጣለች። የእኔን በመኪናዬ ላይ አስቀምጠዋለሁ። ከዚያም ስለጥቅሳችን ያለንን ሀሳብ እንካፈላለን። ጥቅሳችንን ከልጆቻችን ጋር ለመወያየትም እንወዳለን። ይህን ስናደርግ፣ ስለ እግዚአብሔር ቃል ያላቸው ሀሳብ ከእኛ ጋር ለመካፈል የሚመች ያደርግላቸዋል።

እህት ዱራንት ጥቅስን በፍሪጅ ላይ ማስቀመጧ
ወንድም ዱራንት ጥቅስን በመኪና ውስጥ ማስቀመጡ

ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ እና ሚስዮኖች በየሳምንቱ ቅዱስ መጻህፍትን በሚካፈሉበት እና አንዳንዴ ከዚህ ጋር የተያያዘ ሀሳብ ወይም ምስክርነት የሚካፈሉበት የኢንተርኔት ቡድን ጁሊ እና እኔ አባል ነን። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዋ ሴት ልጄ እና ጓደኞቿ በማህበራዊ መገናኛዎች እና በፅሁፍ መልእክት የቅዱስ መጻህፍት ጥቅሰቶችን እርስ በራስ ይካፈላሉ።

ወጣት ሴት በማህበራዊ መገናኛ ላይ ጥቅስን ሲካፈሉ

በቡድኖቻችሁ ሌላ ሀይማኖት ያላቸውን ለመጨመር አታመንቱ። እነርሱም ሀሳባቸውን ከፍ የሚያደርጉበት እና ወደ እግዚአብሔር ለመቅረድ ስሜት የሚያገኙበትን እየፈለጉ ናቸው።

ጥቅሞቹ ምንድን ናቸው?

እህት ዱራንት ቅዱስ መፅሐፍትን ስታጠና

ስለዚህ፣ ጥቅሞቹ ምንድን ናቸው? ጁሊ እና እኔ በየሳምንቱ አንድ ጥቅስን በማሰላሰል በቃል ስንይዝ ከሶስት አመት በላይ ሆነን። በመጀመሪያ፣ የ20 አመት አላማ አቀድን። በቅርብ ቀን እንዲህ አለችኝ፣ “ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዱሳት መጻህፍትን በየሳምንቱ ለ2 አመታት በማሰላሰል በቃል እንድንይዝ ስትጋብዘኝ፣ ለአንድ ወርም እንኳን ማድረግ መቻሌ አሳስቦኝ ነበር። እነዚህ ጥርጣሬዎች አሁን የሉኝም። በየሳምንቱ የቅዱስ መጻህፍት ጥቅሶችን በፍሪጅ ላይ ለማስቀመጥ እና በየጊዜው ስመለከተው አሰላስሌ በቃል መያዝ እንዴት አስደሳች መሆናቸው ደንቆኛል።”

ለስድስት ሳምንቶች አሰላስለው በቃል ከያዙ በኋላ፣ በቴክሳስ የሚኖሩ እህት እንዲህ አሉ፥ “ምስክርነቴ ተጠናክሯል… እናም ወደ ሰማይ አባቴ መቅረቤ ተሰምቶኛል። …የእግዚአብሔር ቃል የተሻለ ለመሆን እንዴት እየቀየረኝ መሆኑን ወድጄዋለሁ።

አንድ ወጣት ጓደኛ እንደጻፈችው፥ “[አሰላስሎ በቃል ለመያዝ] መቻል ያስደስተኛል ምክንያቱም አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ላይ ለማተኮር እንድችል አድርጎኛል።”

ከሚስዮኖቻችን አንዱ ይህን አካፈለ፥ “ከሰኔ 2014 ጀምሮ በየሳምንቱ አንድ አንቀጽን የአሰላስሎ-ገምግሙ አድርጌአለሁ፣ እናም እወደዋለሁ።… እነዚህ ቅዱሳት መጻህፍት አስፈላጊ በሆኑ ጊዜያት ልመካባቸው የምችልባቸው አይነት ጓደኞቼ ሆነዋል።

በእኔ ጉዳይ፣ በየሳምንቱ አሰላስዬ በቃል ስይዝ መንፈስ በይበልጥ ሙሉነት ይሰማኛል። “ምግባር [ሀሳቤን] ያለማቋረጥ እንዲያሳም”11 በማድረግ ለቅዱሳት መጻህፍት ያለኝ ፍቅር ጨምሯል።

ኔፊ ያካፈለውን ግብዣ እና ታላቅ በረከት አስቡ፥ “ስለሆነም አብም የምትቀጥሉ ከሆነ፣ የክርስቶስን ቃል ብትመገቡ፣ እናም እስከመጨረሻው ብትፀኑ፣ እነሆ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል ይላል።”12 “በክርስቶስ ቃል መመገብ” በሚለው መንፈስ ውስጥ አሰላስሎ በቃል መያዝ የሚጣፍጥ ምግብን እንደመብላት እና ከዚያም ይህን በሙሉ ለመደሰት ቀስ በቀስ እንደማኘክ ነው።

ሴት ሰላጣን ስታጣጥም

የእናንተ ጥቅስ ምንድን ነው?

በየሳምንቱ አንድ የቅዱስ መጻህፍት አንቀጽ በዚህ ወር ጀምሮ አሰላስላችሁ በቃል ትይዛላችሁን? ለዚህ አመት በሙሉስ? ጁሊ እና እኔ በቴክሳስ ዳላስ ያሉ ሚስዮኖቻችንን በሙሉ ለ 20 አመት ከእኛ ጋር አሰላስለው በቃል እንዲይዙ ጋብዘናል። የመጨረሻውን መስመር በአጭር 17 አመት እንደርሳለን። ከዚያም ሌላ ሀሳባችንን ከፍ ለማድረግ እና ወደ ክርስቶስ ለመቅረብ አዲስ አላማ እናቅዳለን።

እኛን “ጥቅሳቹ ምንድን ነው?” ብሎ በመጠየቅ ማድረጋችንን ለማረጋገጥ ትችላላችሁ።፡ነገር ግን ይህን ካደረጋችሁ፣ ቅዱሳት መጻህፍታችሁን ለመካፈል የተዘጋጃችሁ ሁኑ። እያንዳንዳችን በዚህ ልውውጥ ምክንያት ከፍ እንደረጋለን።

በየሳምንቱ ለሚቀጥሉት ትንሽ ወሮች ወይም አመቶች ወይም ለረጅም ጊዜ በልባችሁ እና በአዕምሮአችሁ ላይ አዲስ አንቀጽ መጻፋችሁ ህይወታችሁን እና የቤተሰብ ህይወት እንዴት እንደሚቀይር ልታስቡት ትችላላችሁን?

ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌአችን ነው

ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳት መጻህፍት ፍቅር ያሳደገው በእድሜው መጀመሪያ ላይ ነበር። በ12 አመቱ ከጥበባዊ ዶክተሮች ጋር ትርጉም ያለው መወያየት ለማድረግ የቻለው13 እንደ ትንሽ ልጅነቱ ቅዱሳት መጻህፍትን ያነብ እና ያሰላስል ስለነበር መሆን አለበት። ሚስዮኑን የጀመረው በ30 አመቱ ነበር፣14 እናም ቅዱሳት መጻህፍትን በመጀመሪያ ጀምሮ እና በአገልግሎቱ በሙሉ ይጠቅስ ነበር።15 ኢየሱስ ለ 20 አመታት ለሚስዮኑ ለመዘጋጀት ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያጠና እና ሲያሰላስል ነበረ ለማለት አይቻልምን? በወደፊት የማስተማር እና ቤተሰባችሁንና ሌሎችን ለመባረክ እድሎች እንዲኖራችሁ ራሳችሁን ለማዘጋጀት ዛሬ ማድረግ የሚገባችሁ አንዳንድ ነገሮች የሉምን?

እምነታችሁን ተለማመዱበት እና አድርጉት

ለማጠቃለል፣በየሳምንቱ ገንዘብ እንድታጠራቅሙ እንደምትወስኑ ተስፋ አለኝ። እምነታችሁን ተለማመዱበት፣ ራሳችሁን ተቆጣጠሩ፣ እናም ይህን አድርጉ። የእግዚአብሔርን ቃላት በተራዘመ እና በዘለቀ ሁኔታ በየሳምንቱ ለማሰላሰል እንድትመርጡም ጸሎቴ ነው። እምነታችሁን ተለማመዱበት፣ ራሳችሁን ተቆጣጠሩ፣ እናም ይህን አድርጉ።

እንደመጀመሪያው ገንዘብ ማጠራቀም ግብዣ ሳይሆን፣ የሁለተኛው ነፍስ የሚያድን ግብዣ ለራሳችሁ ለዘለአለም የምትጠብቁት--ከዚህ አለም ብል እና ዝገት ነጻ የሆነ፣ ነው።16

ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን ይህን ግልጽ ምክር እና ቃል ኪዳን አቅርበዋል፥ “ቅዱሳት መጻህፍትን በጥንቃቄ አጥኑ። በእነዚህም ላይ አሰላስሉ እናም ጸልዩ። ቅዱሳት መጻህፍት መገለጥ ናቸው፣ እናም ተጨማሪ መገለጦችን ያመጣሉ።17

ማጠቃለያ

በየሳምንቱ በአዕምሮአችሁ እና በልባችሁ ላይ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስን መጻፋችሁ እንደማይፀፅታችሁ ቃል እገባላችኋለሁ። ቀጣይ የሆነ መንፈሳዊ አላማ፣ መጠበቂያ፣ እና ሀይል ስሜት ይኖራችኋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ ስሰራ ያያችሁትን ስሩ”18 ያላቸውን ቃላት አስታውሱ። ቃላቱን በህይወታችን በሙሉ እንተግብር፣ ስለዚህ የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።