2010–2019 (እ.አ.አ)
ቃል ለተገቡልን በረከቶች ብቁነት
ኦክተውበር 2015


11:22

ቃል ለተገቡልን በረከቶች ብቁነት

የአባታችን ቃል የተገቡ ድንቅ በረከቶች ምስል ከአይኖቻችን ፊትለፊት በየቀኑ የትኩረት ማእከል መሆን አለባቸው።

ይህችን እህት አትወዷትምን? የእራሳችሁን ልጅ የመውለድ እድል ያላገኛችሁ አብዛኞቻችሁ ልጆችን በማፍቀር፣ በማስተማር፣ እና በመባረክ ህይወታችሁን እንደምታሳልፉ እናውቃለን። እና፣ ኦ፣ ለዚያም ደሞ የሰማይ አባታችሁ እና እኛ፣ የእናንተ እህቶች፣ ምነኛ እንደምንወዳችሁ!

ወጣት ሴት አዲስ የተወለደችውን ይዛ

በልጆች ክፍል እና በወጣት ሴቶች ክፍል ውስጥ ያላችሁትን እናንተን ውድ ወጣት እህቶችን ጨምሮ፣ ሁላችንም አዲስ የተወለደ ህፃን ልጅን በእጆቻችን የማቀፍ እድሉን አግኝተን አይናችንን እንዲመለከት/ትመለከት አድርገነው/ናት እናውቃለንን? በጣም በቅርቡ በአዲስ ወደ ተፈጠረው ትንሽዬ ንፁህ ሰውነት ውስጥ፣ በሰማይ አባት በተላከው መለኮታዊ መንፈስ ዙሪያ ያለው ቅዱስ ስሜት ተሰምቶናልን? እኔ በጣም ጣፋጭ፣ በጣም ጥልቅ፣ እና በጣም መንፈሳዊ የሆኑ ስሜቶች ተሞክሮ አለኝ።

የእኛ ሰውነቶች የሰማይ አባታችን ቅዱስ ስጦታዎች ናቸው። እነዚህም ግላዊ ቤተመቅደሶች ናቸው። ንፁህ አድርገን ስንጠብቃቸው፣ ለመንፈሳዊ ልጆቹ ሰውነትን በመፍጠር የሰማይ አባታችንን ለማገዝ ብቁ መሆን እንችላለን።

ፕሬዘደንት ፓከር እንደተናገሩት

በፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ ፓከር የመጨረሻ አጠቃላይ ጉባኤ ንግግር ውስጥ፣ በ“ኩኪስ እና መሳም” በሚለው የምናስታውሰው ንግግር፣ እንዲህ ብለው መሰከሩ፣ “ለመባዛት እና ምድርን ለመሙላት የተሰጠው ትእዛዝ…ወሳኝ ነው… እና የሰው ደስታ ምንጭ ነው። ይህን (የመፍጠር) ሀይል በቅድስና በመለማመድ፣ ወደ ሰማይ አባታችን እየቀረብን እንመጣለን እና አምላካዊ የሆነም እንኳን የደስታ ሙሉነትን እናገኛለን። የመባዛት ሀይል የእቅዱ ድንገታዊ ክስተት አይደለም፤ እቅዱ እራሱ ነው።”

እርሳቸውም ቀጠሉ፤

“እውነተኛ ፍቅር የህይወት ምንጭ ውስጥ እነዚያን ቅዱስ ሀይሎች የሚከፍተውን የስሜት መካፈል እስከ ትዳር በኋላ ማቆየትን ያካትታል። ያም ማለት በአካላዊ ፍላጎት ቁጥጥር ስር የመሆን ሁኔታዎች ማስወገድ ማለት ነው። …

“… ምድራዊ ህይወት ውስጥ የሚኖረን ደስታ እና የዘላለም ህይወታችን ለእነዚያ ቋሚ እና አሳማኝ የሚመስሉ አካላዊ ፍላጎቶች በምንሰጠው ምላሽ ላይ የተወሰነ ነው።”1

ውድ እህቶቼ፣ ወጣት እና በጣምም ወጣት ያልሆናችሁ፣ ይህንን ንግግር ሳዘጋጅ ታላቅ ጉጉት ተሰምቶኛል። ወጣቱ አልማ እንደገለፀው፣ “ቅዱስ ስሙን ትጠሩ ዘንድ…እና ያለማቋረጥ እንድትተጉ እንዲሁም እንድትፀልዩ፣ ከሚቻላችሁ በላይም እንዳትፈተኑም፣… በመጨረሻው ቀን ከፍ እንድትሉ፣ ከልቤ እመኛለሁ።”2

ቀጥሎም፣ በአልማ ጊዜ፣ ፀረ ክርስቶስ የሆነው ኮሪሆር፣ “ህዝቡን ሰበከ…፣ ብዙ ሴቶችን በማሳሳት፣” በማለት ሞርሞንም መስክሯል።3

እህቶች፣ ሰይጣን በእኛ ጊዜ ታላቅ ስኬት ያለው እንደ ኮሪሆር የሆነ ሰንደቅአላማን አንስቷል። አንዳንድ መሳሪያዎቹ ምንድን ናቸው? መሳጭ የፍቅር ልበ-ወለዶች፣ የቲቪ ሳሙና ኦፔራዎች፣ የራቁት ምስል፣ በማህበራዊ ገፆች ያሉ የበፊት የወንድ ጓደኞች። ውድ እህቶች፣ በጣም መጠንቀቅ አለብን! በሴጣን እሳታማ ጦር እየተጫወትን ሳንቃጠል ልንቀር አንችልም። ለመንፈስ ቅዱስ ዘወትር ጓደኝነት ከምግባረ መልካምነት በላይ ብቁ የሚያደርገን ምንም እንዳለ አላውቅም።

ብዙዎች በዛሬው አለም ቅፅበታዊ እርካታን--- ቅፅበታዊ እውቀትንም እንኳን ቢሆን ከኢንተርኔት ለማግኘት ይፈልጋሉ። በተቃራኒው፣ እምነትን እና ትእግስትን ከተለማመድን እና ወደ የእውነት ሁሉ ምንጭ የሆነው የሰማይ አባት ከሄድን በጣም እንባረካለን። ቅዱስ መፅሀፍትን በቅን ልብ እና በኢለምን ጸሎት በማጥናትና በመፈተሽ ብዙ መልሶችና መረጋገጫዎች መምጣት ይችላሉ፣ ነገር ግን በኢንተርኔት እንደዚህ አይነት በረከቶች የሉም። ነብዩ ያቆብ እንዲህ መሰከረ፣ “መንፈስ እውነቱን ይናገራል እንጂ አይዋሽም። ስለሆነም፣ እርሱ ነገሮች በእርግጥ እንዳሉ ይናገራል፣ እናም ነገሮች በእርግጥ እንደሚሆኑ።”4

ውድ እህቶች፣ ከሰማይ አባታችን ደረጃ በታች የሆኑ ማንኛውንም ነገሮች ስንመለከት፣ ስናነብ፣ ወይም ስንለማመድ፣እኛን ያደክሙናል። ወጣትም ሁኑ ያረጃችሁ፣ የምትመለከቱት፣ የምታነቡት፣ የምታዳምጡት ወይም ለማድረግ የምትመርጡት For the Strength of Youthላይ ካሉት የጌታ መርሆዎች የማይጣጣሙ ከሆነ፣ አጥፉት፣ ወደ ውጭ ወርውሩት፣ ቅደዱት፣እና በሩን ዝጉ። ለመንፈስ ቅዱስ ቋሚ አጋርነት ለመብቃት እንደመልካምነት ያለ ሌላ ምንም ነገር አላውቅም!

አዳኝ በገተሰመኔ

ማንኛችንም ፍፁማን አይደለንም፣ ነገር ግን ሀጢአትን ስንፈፅም፣ ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ ፓከር አንድንስታውሰው እንዳደረጉን፥

“ቃል ኪዳኑ፥ ‘የእግዚአብሔር ደግነት እና ምህረት በንስሀ ውስጥ እንደሚንፀባረቀው በሌላ የትም የለም’ የሚል ነው” (ት. እና ቃ. 58፥42)። …

“… የሀጢያት ክፍያው፣ እያንዳንዳችንን እንደገና የሚጠራን፣ ጠባሳን አይተውም። ያ ማለት ያደረግነው ወይም የነበርንበት ምንም ቢሆን ወይም እንዴትም ይሁን የተከሰተው፣ እኛ በእውነት ንስሀ ከገባን፣ ያንን ያስተካክለዋል። የሃጢያት ክፍያውን ሲከፍል አስተካከለው። በጥፋተኛነት ስሜት፣ እንዴት ማምለጥ እንደሚቻል ባለማወቅ የምንደባበቅ ብዙዎቻችን አለን። የክርስቶስን የሀጢአት ክፍያ በመቀበል አምልጡ፣ እና እራስ ምታት የነበረው ሁሉ ወደ ውብነት እና ፍቅር እና ዘለአለማዊነት ሊዞር ይችላል።”5

ሁላችንም ከሚያስፈልገን--ከንስሀ በተጓዳኝ--እኛ ንፁህ እና ፃዲቅ ሆነን እንድንቆይ እንዲረዳን የተሰጡን እርዳታዎች እና መሳሪያዎች ምንድን ናቸው? ህፃናት ክፍል እና ወጣት ሴቶች ሁሉም “የቅዱስ መፅሀፍ ሀይል”6 የሚለውን ያውቃሉ እና ይዘምራሉ! “የፀሎት ሀይል!” “የቤተመቅደስ ሀይል!” “የቃልኪዳን ሀይል!” እና “የቅድስና ሀይል!” የሚሉትን መጨመር እንችላለን?

የቤተመቅደስ ልብስን በአግባቡ ከመልበስ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ታላቅ በረከቶች እና የሚጠበቁ ቃልኪዳኖችም አሉ። ከሰማይ አባቴ የተሰጡኝ የልኡልና ልብሶችን እንደመልበስ አይነት ምልክታዊ እንደሆነ ያህል ይሰማኛል። ልብሱን በትክክል ለመልበስ ስንጥር፣ ለእርሱ ያለንን የፍቅር እና መሰጠት ታላቅ ምልክት አባታችን እንደሚያስተውል እመሰክራለሁ። ያ ከእርሱ ጋር የገባነው ቃልኪዳን ማስታወሻ ነው እና እርሱ እንዲህ ሲል ቃል ገባ፣ “እኔ፣ ጌታ የምለውን የምታደርጉ ከሆነ እኔ ባልኩት እገኛለሁ፤ የምለውን የማታደርጉ ከሆነ ግን፣ ቃልኪዳን አይኖራችሁም።”7

በቅርቡ በባለቤቶቿ ሱስ እና አለመታመን ሁለት ፍቺዎችን የፈፀመች የድሮ ጓደኛዬን ሳናግራት ነበር። እርሷ እና ሶስት ልጆቿ በጣም ተሰቃይተዋል። እንዲህ ስትል ተማፀነች፣ “በፅድቅ ለመኖር በጣም ሞክሬያለሁ። ለምንድን ነው በጣም ብዙ መከራ የነበረብኝ? ስህተት የሰራሁት ምንድነው? የሰማይ አባት እኔ ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልገው? እፀልያለሁ እና ቅዱስ መጽሐፍቶቼን አነባለሁ፣ ልጆቼን እረዳለሁ፣ በብዛት ቤተመቅደስ እሄዳለሁ።”

ይህችን እህት ሳዳምጥ፣ እንዲህ ብዬ ለመጮህ ተሰምቶኝ ነበር፣ “እያደረግሽው ነው! የሰማይ አባት የሚፈልገውን እና እንድታደርጊ የሚጠብቀውን ሁሉ እያደረግሽ ነው!”

መረዳት በሚቻል ሁኔታ፣ ህይወታችን በአስደንጋጭ ችግሮች ውስጥ ሲሆን፣ የሰማይ አባት ቃል የተገቡ በረከቶች “በጣም የራቁ” መሆናቸውን ብዙዎች ይገልፃሉ። ነገር ግን አልማ ለልጁ እንዲህ ሲል አስተማረ፣ “ይሄ ህይወት እግዚአብሔርን ለማግኘት… የመዘጋጃ ጊዜ ነው።”8 ሁሉንም በረከቶች መውሰጃ አይደለም። ፕሬዘዳንት ፓከር እንዳብራሩት፣ “‘እናም ከዛ ሁሌ በደስታ ኖሩ’ የሚለው በሁለተኛ ድርጊት ላይ በፍፁም አልተፃፈም። ሚስጥሮች ሲፈቱ እና ሁሉም ነገሮች ሲስተካከሉ፣ ያም መስመር በሶስተኛው ድርጊት ውስጥ ይካተታል።”9 ስለሆነም፣ የሰማይ አባታችን ድንቅ ቃል የተገቡ በረከቶች ምልከታ በአይኖቻችን ፊት የትኩረት ማእከል መሆን አለባቸው---የእርሱ ጥልቅ ምህረት የየቀን ልምምዳችንን ጨምሮ ነው።10

ያሉን ብዙ መከራዎች ለምን እንዳሉን አላውቅም፣ ነገር ግን፣ እህቶች፣ ሽልማቱ ታላቅ፣ ዘለአለማዊ እና የማያልቅ ስለመሆኑ፣ አስደሳች እና ከመረዳታችን በላይ ስለሚሆን በሽልማቱ ወቅት ለመሀሪው፣ ደጉ፣ አፍቃሪው አባታችን “የሚጠበቅብን ሁሉ ብቻ ነበርን?!” ለማለት እንኳን እንደምንፈልግ የእኔ ግላዊ ስሜቴ ነው። የሰማይ አባታችን እና አዳኛችን ለእኛ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር በየቀኑ ማስታወስ እና ማስተዋል ብንችል፣ ከእነርሱ ጋር ተመልሶ ለመኖር የጠየቁንን ሁሉ ለማድረግ ፍቃደኞች እንሆናለን። ውድ እህቶች፣ በስተመጨረሻው፣ እነዚያ መከራዎች ለዘለአለማዊ ህይወት እና በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለመኖር የሚያበቁን ከሆነ፣ እዚህ መሰቃየታችን ምን ያሳጣናል?

ሰውነቶቻችን የሰማይ አባታችን ቅዱስ ስጦጣዎች መሆናቸውን እና ህይወታችንን በአዳኛችን የኃጢያት ክፍያ በኩል ንፁህ በማድረግ በየቀኑ ከፊታችን ያሉት በአባታችን ቃል የተገቡ በረከቶችን ምስል ስንጠብቅ፣ “አባታችን ያለው ሁሉ” የእኛ ይሆናል11 ። በተቀደሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።