የሚጮኸውን የመለከት ድምፅ እንዲወጣ ፍቀዱ
በዚህ ባለፈው በጋ ላይ ወላጆቻቸው ከካስማቸው ጋር የመስራቾች ረጅም የእግር ጉዞ እንቅስቃሴ ላይ በነበሩበት ወቅት ሁለቱ ወጣት ወንዶች የልጅ ልጆቻችን፣ እኔ እና ሚስቴ ጋር ለመቆየት መጥተው ነበር፤ ወንዶቹ ልጆች ከቤታቸው ርቀው በቆዩበት ወቅት ፒያኖ መለማመድ እንደነበረባቸው ሴት ልጃችን ማረጋገጥ ፈለገች። የጥቂት ቀናት ከአያቶቻቸው ጋር የሚኖራቸው ቆይታ ልምምዱን ለመርሳት ትንሽ ቀላል እንደሚያደርገው ታውቃለች። አንድ ከሰዓት ላይ 13 አመት ከሆነው የልጅ ልጄ ፣ አንድሪው ጋር፣ ለመቀመጥ እና ሲጫወት ለማየት ወሰንኩ።
ይህ ልጅ ሙሉ ሀይል ያለውና የውጪ እንቅስቃሴዎችን የሚወድ ነው። በማደን እና አሳ በማጥመድ ጊዜውን ሁሉ በቀላሉ ማሳለፍ ይችላል። ፒያኖውን በመለማመድ ላይ ሳለ፣ ፒያኖ ከመለማመድ ይልቅ በቅርብ ካለ ወንዝ ሄዶ አሳ ማጥመድ እንደሚመርጥ መናገር እችላለሁ። እያንዳንዱ አውታሮችን በሃይል እየመታ የተለመዱ መዝሙሮችን ሲጫወት አዳመጥኩት። እየተጫወተ የነበረው እያንዳንዱ የሙዚቃ ኖታ ጣእመ ዜማውን በግልፅ ለይቶ ለማውጣት እንዲያስቸግር በሆነ ሁኔታ ተመሳሳይ አፅእኖት እና ምት ነበራቸው። በአግዳሚ ወንበር ላይ ካጠገቡ ቁጭ በማለት እና በጣእመ ዜማው ቁልፎች ላይ ትንሽ በዛ ያለ ሀይል የመጠቀም እና ጣእመ ዜማውን የሚያጅቡትን ኖታዎች ላይ አናሳ ሀይል የመጠቀም ጥቅምን አብራራሁለት። ስለ ፒያኖው አስገራሚ መካኒካል መሳሪያ ከመሆኑ የበለጠ ነገር እንዳለው አወራን። የራሱን ድምፅ እና ስሜቶች ቀጣይ መሆን እና ለመግባቢያ በጣም ገራሚ መሳሪያ መሆን ይችላል። ልክ አንድ ሰው በለሰለሰ መንገድ ከአንዱ ቃል ወደ ሌላኛው ቃል እንደሚያወራው እና እንደሚንቀሳቀሰው ሁሉ፣ ከአንዱ ወደ ሌላኛው ኖታ ስንሸጋገው የሙዚቃ ቃናውም ፍሰት እንደዛው መሆን አለበት።
ደግሞ ደጋግሞ እየሞከረ ሳለ አብረን ሳቅን፡፡ መጀመሪያ ያልተገሩ ድምፆች ከነበሩት በግልፅ ወደ ሚሰሙ የተለመደ የሙዚቃ ቃና መሆን ሲጀሚር ዲምፕል ያለው ጉንጩ ፈገግታ እየጨመረ መጣ። “እኔ የእግዚያብሄር ልጅ ነኝ፣ እናም እሱ እዚህ ልኮኛል”1 የሚለው መልእክቱ ግልፅ ሆነ።በመልእክቱ ላይ ልዩነት እንዳለ እንደተሰማው አንድሪውን ጠየኩት። “አዎ፣ አያቴ ልዩነቱ ይሰማኛል!” ብሎ መለሰልኝ።
ሀዋሪያው ጳውሎስ ቆሮንጦስ ላይ በፃፈ ጊዜ ግንኙነትን ከሙዚቃ መሳሪያዎች ጋር ስለ ማወዳደር አስተማረን፤
“ ነፍስ የሌለበት ነገር እንኳ ዋሽንትም ክራርም ቢሆንም የድምፁን ልዩነት ባይገልጥ በዋሽንት የሚነፋው ወይስ በክራር የሚመታው መዝሙር እንዴት ይታወቃል?
“ደግሞም መለከት የማይገለጥን ድምፅን ቢሰጥ ለጦርነት ማን ይዞራል?”2
የወንጌልን መልእክት በግልጽ እና ከልብ የሚያስተምሩ ደቀመዛሙርት አለም ቢያስፈልጋት ከየትኛው ጊዜ በላይ የሚያስፈልጋት አሁን ነው። የመለከቱ ጥርት ያለ ድምፅ ያስፈልገናል።
በእርግጥ ክርስቶስ ምርጡ ምሳሌያችን ነበር። ትክክለኛ ለነበረው ነገር እንድንቆም ሁሌም ብርታትን አሳይቶናል። እግዚብሄርን እና ባልንጀሮቻችንን እንድንወድ፣ የእግዚያብሄርን ትእዛዛት ሁሉ እንድንጠብቅ እና ለአለም ምሳሌ እንድንሆን ሲጋብዘን የሱ መልእክቶች ከጥንት እስካሁን ድረስ ተመሳሳይ ናቸው። በሱ ጊዜ ለነበሩት ምድራዊ ስልጣኖችን ያላቸውን ወይም ገዢዎችን ተቃርኖ ሲናገር፣ በሰማይ አባቱ ለሱ የተሰጠውን ሚሲዮን እነዚህ ሰዎች ቢቃረኑትም እንኳ ፈሪ አልነበረም። ቃላቶቹ የተቀረፁት ግራ ለማጋባት ሳይሆን የሰው ልቦች ላይ መልካም ተፅእኖ ለማድረግ ነበር። በተናገረውና ባደረገው ነገር ሁሉ የአባቱን ፈቃድ በግልፅ አወቀ።
በበዓለ ሀምሳ ቀን ጊዜ በብርታት እና በግልፅ የአለምን ሰዎችን የተጋፈጠውን፣ የጴጥሮስን ምሳሌም ወደዋለሁ። በዛች ቀን ቀደምት ቁዱሳኖችን በልሳን ቋንቋ ሲያወሩ ስለሰሟቸው ሰክረው መስሏቸው ለመውቀስ ከብዙ ሃገራት መተው ተሰብስበው ነበር። ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ከሱ ጋር ስለነበር፣ ቤተክርስቲያኑን እና አባሎቹን ለመከላከል ቆመ። በነኚህ ቃላቶች መሰከረ፤ “አይሁድ በእየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፣ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፣ ቃሎቼንም አድምጡ።3
ከዚያ በኋላ ስለ ክርስቶስ የያዘ ጥቅስን ከቅዱሳን መፅሃፍ ጠቀሰና ጠንካራ ምስክርነቱን አካፈለ፤ “አለ። እንዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚያብሄር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።”4
ብዙዎች ይህን ቃላቶች ሰሙ፣ መንፈስ ተሰማቸው፣ እናም 3,000 ነፍሶች የቀደምቷን ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ። ይህ አለማችን በቤተክርስቲያንዋ ላይ ተቃርኖ አመከካከት የሆነ በሚመስል ጊዜ፣ የሆነ አንድ ወንድ ወይም ሴት ለመመስከር ፈቃደኛ ሲሆን ለውጥን ማምጣት መቻሉ ሀይለኛ ማረጋገጫ ነው።
እኛ እንደ ቤተክርስቲያን አባሎች ለእግዚአብሔር ትምህርት እና ለእርሱ ቤተክርስቲያን ስንቆም እና በሀይል ለመመስከር ውሳኔን ስናስተላልፍ፣ በውስጣችን የሆነ ነገር ይለወጣል። ምስሉን በላያችን ላይ እንቀበላለን። በመንፈስ ከእርሱ ጋር ቅርብ እንሆናለን። ከዚያ እሱ ከፊታችን በመሄድ እና ከቀኝ እጃችን እና ከግራ እጃችን በኩል ይሆናል እናም መንፈሱ በልቦቻችን ይሆናል፣ እናም የእርሱ መላእክቶች እኛን ከፍ ለማድረግ በዙሪያችን ይሆናሉ።5
ትምህርቱ ከአለምን የአሁን ሃሳቦች ጋር ሳይስማማ ሲቀር፣ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ለትምህርቱ ሰበብ ለማበጀት አይሞከሩም። ጳውሎስ “በክርስቶስ ወንጌል አላፍርም፤ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚያብሄር ኋይል ለማዳን ነውና።”6 በማለት በድፍረት ያወጀ ሌላው ጀግና ደቀመዛሙርት ነበር። እውነተኛ ደቀመዛሙርት ለማድረግ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ጌታን ይወክላሉ። እውነተኛ ደቀመዛሙርት የሰዎችን ልቦች ለማነሳሳት እንጂ ለማጥቃት ፍላጎት አይኖራቸውም።
ብዙ ጊዜ ለክርስቶስ ለመቆም የሚያመች ወይም አመቺ አይደለም። ጳውሎስ ንጉስ አግሪጳ ፊት ተጠርቶ እራሱን እንዲከላከል እና ታሪኩን እንዲናገር ሲጠየቅ የሆነው ነግር ተመሳሳይ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። ጳውሎስ፣ ያለ ምንም ማቅማማት፣ ይህ አስቸጋሪ ንጉሱ ለትንሽ ክርስቲያን ለመሆን ደርሶ እንደነበር እንዳመነ ያክል እምነቱን በታላቅ ኃይል አወጀ።
የጳውሎስ ምላሽ መናገር የፈለገውን ሙሉ ለሙሉ ህዝቡ እንዲረዱ ያለውን መሻት ያሳያል። ጳውሎስ የሰሙት ሁሉ “ለትንሽ” ክርስቲያን እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን “ሁሉም በአንድ ላይ” የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ መሻት እንደነበረው ለንጉስ አግሪጳ ነገረው።7 በግልፅ የሚናገሩ ይህንን ማሳካት ይችላሉ።
በመፅሀፈ ሞረሞን ውስጥ የሌሂን ህልም ታሪክ ባጠናውባቸው አመታቶች ሁሉ፣8 በጣም አመፀኞች ብቻ የሚኖሩበት ስለ ትልቅና ሰፊ ህንፃ ሁሌም አስባለሁ። ህንፃው በሰዎች ተሞልቶ ነበር፣ የእግዚያብሄርን ቃል የሚወክለውን፣ የብረት ዘንጉን በያዙ፣ እና የእግዚያብሄርን ፍቅር ወደ ሚወክለው የህይወት ዛፍ ወደ ሚጓዙት ታማኞች ላይ ይሳለቁ እና እጃቸውን ይጠቁሙ ነበር። አንዳንዶቹ የሚሳለቁባቸውን ሰዎች ጫና መቋቋም አቃታቸው እና ወደ ተከለከለው መንገድ ገቡ። ሌሎች ደሞ እነሱን ለመቀላቀል ወደ ህንፃው ለመሄድ ወሰኑ። ወቀሳዎችን እና የአለምን መልእክቶችን በመቃወም በድፍረት የመናገር ብርታት አልነበራቸውምን?
የአሁኑን አለም ከእግዚያብሄር መንገድ እየራቀ ሲሄድ በምመለከትበት ግዜ፣ ይህ ህንፃ በይዘቱ እያደገ ይመስለኛል። ብዙዎች ወደ ትልቁና ሰፊ ህንፃው መተላለፊያዎችን እየተራመዱ እራሳቸውን በሚያገኙበት ጊዜ የሱ የባህል አካል እየሆኑ መሄዳቸውን አይገነዘቡም። አብዛኛውን ጊዜ ለፈተናዎች እና ለአለም መልእክቶች እጅ ይሰጣሉ። ቀስ በቀስ ከሚወቅሱት ሰዎች እና ከሚሳለቁ ሰዎች ጋር ተደባልቀው ሲወቅሱና ሲሳለቁ እናገኛቸዋለን።
ለአመታት ያህል የተሳላቂዎች የህዝብ ብዛት ታማኞች ህይወታቸውን የሚኖሩበት መንገድ ላይ እያሾፉ ይመስለኝ ነበር፣ ነገር ግን ከዛሬው ህንፃ የሚወጡት ድምፆች በድምፅ ቃና እና በአቀራረብ ተለውጠዋል። አንዳንድ የቤተክርስቲን ታሪክ ክፍሎችን ወይም ነብይ እና ሌሎች መሪዎች ላይ የሚጎዳ ወቀሳ በማቅረብ በማጥቃት የሚሳለቁ ሰዎች ቀላሉን የወንጌል መልእክት ብዙ ጊዜ ወደ ታች ለማድረግ ይጥራሉ። እንዲሁም ምድር ከተፈጠረች ጀምሮ የተሰጠውን፣ የትምህርታችን ዋና ክፍልን እና የእግዚያብሄር ህግንም እያጠቁ ነው። እኛ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ መዛሙርት እና የእሱ ቤተክርስቲያን አባል እንደመሆናችን፣ ያንን የብረት ዘንግ በጭራሽ መልቀቅ የለብንም። የሚጮኸውን መለከት ድምፅ ከነፍሶቻችን ማረግ አለብን።
ቀላሉ መልእክት እግዚያብሄር አፍቃሪ የሰማይ አባት እንደሆነ እና ኢየሱስ ክርስቶስ ልጁ እንደሆነ ነው። ወንጌሉ በህይወት ባሉ ነብያቶች አማካኝነት በዚህ በኋለኛው ቀናት እንደተመለሰ እና መፅሀፈ ሞረሞን የእሱ ማስረጃ መሆኑ ነው። የደስታ መንገድ መጀመሪያ እንደተደራጀው እና በሰማይ አባታችን እንደተገለፀው መሰረታዊ በሆነው በቤተሰብ መዋቅር ነው። ይሄ ብዙዎች መገንዘብ የሚችሉት የተለመደ የእውነት መልእክት ነው፣ ምክንያቱም ከዚ ህይወት በፊት ከነበረው ህይወት ሰምተውታል።
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እንደመሆናችን፣ ለመቆም እና ለመመስከር ጊዜያችን ነው። የወንጌል ጣእመ ዜማ ኖታዎች ከአለም ጫጫታ በላይ ለመነሳት ጊዜው ነው። የአዳኝ እና ነፃ አውጪዉ መልእክት ላይ ምስክርነቴን እጨምራለሁ። ህያው ነው! ወንጌሉ ተመልሷል እናም የደስታ እና የሰላም በረከቶች ትእዛዛቱን በመኖር እና በእርሱ መንገድ በመጓዝ መጠበቅ ይችላሉ። ይህ ምስክርነቴ ነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።