በሙሉ መገረም እቆማለሁ
ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝ ምስክርነት የተገነባው እሱ ለእያንዳችን ያለውን ታላቅ ፍቅሩን ለመረዳት ከቻልኩት ብዙ ልዩ ከሆኑ ተሞክሮዎች ነው።
በአለም ዙሪያ ያላችሁ ውድ ወንድሞቼና እህቾቼ፣ በዚህች ሰንበት ቀን ትሁት የሆነውን ምስክርነቴን እንዳካፍል ለጋበሁኝ የመጀመሪያ አመራር በጣምአመስጋኝ ነኝ። አሁን ያለውን ስሜቶቼን የሚገልፀው ተወዳጁ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መዝሙር ነው፤
ኢየሱስ ባቀረበልኝ ፍቅር ላይ በመገረም እቆማለሁ።
ለእኔ ባቀረበው ሙሉ ፀጋ ግራ በመጋባት።…
ከመለኮታዊ ዙፋኑ ወደ ታች መውረዱ ያስገርመኛል
እንደ እኔ አይነት አመፀኛ እና ኩራተኛ ነብስን ለማዳን፣
እንደ እኔ ላለው ታላቅ ፍቅሩን ሊያካፍል፣
ለማኖር፣ ቤዛ ለመሆን፣ እና ፍትህ ለማስፈን ብቁ ነው።..
ኦ፣ አስደናቂ ነው፣ አስደናቂ ነው ለእኔ!1
ከጥቂት ቀናት በፊት ከቀዳሚ አመራር ጋር ለመገናኘት እና ከውዱ ነብያችን ፕሬሰደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ይህንን ጥሪ ለመቀበል ታላቅ እድል ነበረኝ። “ይህ ጥሪ የመጣው ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” ብለው ሲነግሩኝ ፕሬሰደንት ሞንሰን የነበራቸው ጥንካሬ እና ፍቅር ለሁላችሁም ልመሰክርላችሁ እፈልጋለሁ።
ወዳድ የሆነው ነብያችን ለስለስ ባለ ሁኔታ የተናገሩት ቃላቶች ቁምነገር እና ጥቅም ሳመዛዝን ጥልቅ ውስጤ ድረስ ተጥለቅልቄያለሁ እናም ተወዛውዣለሁ። ፕሬሰደንት ሞንሰን፣ ፕሬሰደንት አይሪንግ፣ ፕሬሰደንት ኡክዶርፍን እወዳቸዋለሁ። እወዳችኋለሁ እናም በሙሉ ልቤ፣ አቅሜ፣ አእምሮኤ፣ እንዲሁም ጥንካሬዬ ጌታን እና እናንተን አገለግላለሁ።
ኦህ፣ ፕሬሰደንት ቦይድ ኬ. ፓከርን እና ሽናግሌዎች ኤል. ቶም ፔሪ እና ሪቻርድ ጂ. ስኮትን እንዴት እንደምወዳቸው። በነኚህ ውድ ወንድሞች እግር ስር ለመሰልጠን እና ለመማር ተባርኬያለሁ። በትንሹም እንኳ በእነሱ ጫማዎች ውስጥ መራመድ አልችልም፣ ሆኖም በትከሻቸው ላይ ረዝሜ በመቆም የጌታን አገልግሎት ለመቀጠል ክብር ይሰማኛል።
እኔ የሆንኩትን እንድሆን የረዱኝን ሰዎች ሳስብ፣ መጀመሪያ ማስበው ጣፋጭና እራስ ወዳድ ያልሆነችውን የዘላለም ጓደኛዬን ሜላንያን ነው። በአመታት ውስጥ ልክ እንደ ሸክላ ጭቃ ጠፍጥፋ ወደ ተሻለ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርትነት እንድሆን ረድታኛለች። የእርሷ ፍቅር አና እርዳታ፣ እንዲሁም አምስቱ ልጀቻችን፣ ባለቤቶቻቸው፣ እናም 24ቱ የልጅ ልጆቻችን፣ ደግፈውኛል። ውድ ቤተሰቤ፣ እወዳችኋለሁ።
ልክ እንደ ጥንቱ ኔፊ፣ በወንጌል ውስጥ ባሉ መልካም ወላጆች ተወለድኩ እናም እነሱም ወደ ኋላ ስድስት ትውልድ ድረስ ከመልካም ወላጆች የተወለዱ ናቸው። ቤተክርስቲያኑን የተቀላቀሉት ቀደምት ቅድመ አያቶቼ ከእንግሊዝ እና ከዴንማርክ ነበሩ። እነኝህ ቀደምት መስራቾች ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሁሉ ነገራቸውን ሰጡ እንዲሁም ለቀጣዮቹ መጪ ትውልደሰቸው ውርስን ትተው አለፉ። በጣም ብዙ ለሆኑት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተሰቦች አመስጋኝ ነኝ፣ እናም ይህ ለሁላችንም ጥረት ለማድረግ አዋጪ ግብ እንደሆነ አውቃለሁ።
ህይወቴን ለዚህ ጥሪ ላማዘጋጀት ሌሎች ብዙ ሰዎች አስተዋፅኦ አድርገዋል። የልጅነት ጓደኞች እና ቤተሰቤ፣ የቀደሙ መሪዎቸ፣ አስተማሪዎቸ፣ እናም የእድሜ ልክ መካሪዎቼን ያጠቃልላል። ቀደምት ከምስራቃዊ ስቴትስ ምሽኔ የነበሩትና ከኒው ዮርክ፣ ኒው ዮርክ ደቡብ ምሽን የነበሩት የተወደዱ ምስዮናውያንንም ማጠቃለል ይገባኛል።
ከሰባዎች ወንድሞች ጋር ማገልገልን ከፍተኛ ዋጋን ሰጥቼዋለሁ። ለ15 አመታት ያክል ከታላቆቸቹ ጉባኤችዎ መካከል አንዱ የሆነው እና በፍቅር ከተሞላ ወንድማማእችነት ውስጥ ነበርኩ። ውድ አጋር አገልጋዮች፣ አመሰግናችኋለሁ። አሁን ደግሞ በአዲስ ጉባኤ ውስጥ አባል መሆንን ወደ ፊት እመለከታለሁ። ፕሬሰደንት ሩሰል ኤም. ኔልሰን ፍቅሬ ለአንተና ለእያንዳንዱ የአስራ ሁለቱ ጉባኤ አባላት ጥልቅ ነው።
እህት ራስባንድ እና እኔ በአለም ዙሪያ ያሉ ጉባኤዎች እና ምሽኖች በተሰጠን ብዙ የቤተክርስቲያን ጥሪ ወቅት ላይ አባላትን ለ፣ጎብኘት ተባርከናል። በሁሉም ቦታ ያሉትን የኋለኛው ቅን ቅዱሳንን እንወዳቸዋለን! እምነታችሁ የኛን እምነት አሳድጓል፤ ምስክርነታችሁ የኛ ምስክርነት ላይ ጨምሯል።
አሁን፣ ለእናንተ አንድ ትንሽ መልእክት መተው ከቻልኩ፣ ይህ ይሆናል፤ ጌታ እንዲህ አለ፣ “እኔ እንደወደድኋችሁ፤ እርስ በእርስ ተዋደዱ።”2 ምንም ምርጫ እንደለተሌለ እርግጠኛ ነኝ፣ እናንተ ወይም ሌላ ሰው የሚሰራውን ሀጢያት ወይም ስህተት ለእናንተ ወይም ለእነርሱ ያለውን ፍቅር መቀየር አይችልም። ያ ማለት ደግሞ ሀጢያት የሆነ ተግባርን ሸፍኖ ያልፋል ወይም ችላ ይላል ማለት አይደለም- እርግጠኛ ኘኝ አያድገውም- ነገር ግን ለባልንገሮቻችን በፍቅር ለመጋበዝ፣ ያለማቋረጥ መስራት፣ለማገልገል፣ እናም ለማዳን እጃችንን መዘርጋት አለብን ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጥልቅ እውነት ያስተምር ዘንድ የቀደምት ሰዎች ጎሳን፣ ማእረግን እና ሁኔታዎችን ተመለከተ።
ምስክርነቴን ስቀበል ብዙ ግዜያት ተጠይቄያለሁ።
በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ አለማመኔን ማስታወስ አልችልም። ከመለአክት እናቴ ጉልበቶች ስር ጀምሮ፣ ቅዱሳን መፅሀፍትን እና የወንጌል ታሪኮችን በማንበብ ሳለሁ ድረስ ወድጃቸዋለሁ።ያ ቀደምት የነበረው እምነቴ አሁን ወደ እውቀት እና ፀሎታችንን ወደ ሚሰማው እና ሚመልሰው የሰማይ አባት ምስክርነት አድጓል። ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝ ምስክርነት የተገነባው እሱ ለእያንዳችን ያለውን ታላቅ ፍቅሩን ለመረዳት ከቻልኩት ብዙ ልዩ ከሆኑ ተሞክሮዎች ነው።
ለአዳኛችን የሀጢያት ክፍያ አመስጋኝ ነኝ እናም ልክ እንደ አልማ በእግዚያብሄር መለከት እናገር ዘንድ እመኛለሁ።3 ዮሴፍ ስሚዝ የተመለሰው ወንጌል የእግዚያብሄር ነብይ እንደሆነ እና መፅሀፈ ሞረሞን የእግዚያብሄር ቃል እንደሆነ አውቃለሁ። እንዲሁም ፕሬሰደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ዛሬ በምድር ላይ ያለ የእግዚያብሄር እውነተኛ አገልጋይ እና ነብይ እንደሆነ አውቃለሁ።
ነብያችንን ስንከተል፣ በልቦቻችን ለሌሎች ልግስና ይኖረን ዘንድ እና ህያው ምስክሮች እንሆን ዘንድ ፀሎቴ ነው እናም በእርግጥም “ኢየሱስ ባቀረበልኝ ፍቅር በሙሉ መገረም እቆማለሁ[እኛ]።” ኦህ፣ [ለእናነተ እና ለ] እኔ “እፁብ ድነቅ፣ እፁብ ድነቅ፣” ይሁንልን እላለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።