ሁሌም ያስታውሱት ዘንድ
ሁሉንም ነገር ለእኔና ለሁላችንም ስለሰጠን ሰው ሕይወት ማጥናትና ማሰላሰል እወዳለሁ።
የመጀመሪያዎቹ ስንኞቹ እንደዚህ የሚሉትን የሕፃናት ክፍል መዝሙር እወደዋለሁ፥
መስማት የምወደውን የኢየሱስን ታሪኮች ንገሩኝ ፣
እዚህ ቢኖር ኖሮ እንዲነግረኝ የምጠይቀውን ነገሮች።
በባህሩ ላይ በነበረበት ጊዜ በመንገዱ ላይ ስለተከሰቱት ነገሮች ታሪክ
ስለ ኢየሱስ ታሪኮች ለእኔ ንገሩኝ።1
ለልጆቻችንና ለቤተሰባችን የክርስቶስን ታሪኮች የመናገር ባህልን ለመፍጠር መጀመር በቤታችን ውስጥ ሰንበትን ቀድሰን ለመጠበቅ ከምናደርጋቸው ለየት ያለ ልምምድ እንደሆነ አምናለሁ።
ይህ በእርግጥ ለየት ያለ መንፈስን ወደ ቤታችን ያመጣል እንዲሁም ከአዳኙ ከራሱ ምሳሌዎችን ለቤተሰባችን ይሰጣል።
ሁሉንም ነገር ለእኔና ለሁላችንም ስለሰጠን ሰው ሕይወት ማጥናትና ማሰላሰል እወዳለሁ።
ስለ ሃጢያት አልባ ሕይወቱ የጥቅስ ምንባቦችን ማንበብ እወዳለሁ፣ በእርሱ ስለታዩ ክስተቶችን የሚናገሩ ጥቅሶችን ካነበብኩኝ በኋላ፣ አይኖቼን ጨፍኜ እነዚህን የሚያስተምሩኝንና በመንፈስ የሚያጠነክሩኝን ቅዱስ ወቅቶች ለመሳል እሞክራለሁ።
እንደዚህ አይነት ወቅቶች፥
-
መሬቱ ላይ ተፋ እና በተፋበት ጭቃ በመስራት የአይነስውሩን ሰው አይኖች ቀባቸውና እንዲህ አለው፣ “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው።” ሰውዬው ታዘዘና ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።2
-
ከነካችው እንደምትፈውስ በማመን የልብሱን ጫፍ የነካችውን ደም የሚፈሳትን ሴት ሲፈውስ።3
-
በውኃው ላይ እየተራመደ ለደቀመዛምርቱ ሲገለፅ ።4
-
ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በኤማሁስ መንገድ ላይ ሲሄዶ እና ለቅዱሳት መጽሐፍ መረዳታቸውን ሲከፍት።5
-
“የእስራኤል አምላክ መሆኔንም ታላቅ እናም የምድር ሁሉ አምላክ መሆኔን እናም ለአለም ኃጢአትም እንደተገደልኩኝ”6 ያውቁ ዘንድ በዚህ በአሜሪካ አሀጉር ላሉ ህዝቦች ሲገለፅና ወደ እርሱ መጥተው ወደ ጎኑና እግሮቹ እጃቸውን ሰደው በእጆቹና እግሮቹ ላይ ያሉትን የሚስማር አሻሮችእንዲነኩ ሲነግራቸው።6
ለልጆቻቸው የክርስቶስን ታሪኮች የሚነግሩ ወላጆች እንዳሉ በማወቄ እደሰታለሁ። ይህንን ያስተዋልኩት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ልጆችን ስመለከት፣ በሕፃናት ክፍል አቀራረቦች እና በሌሎች ክስተቶች ነው።
ስለ ክርስቶስ ላስተማሩኝ ወላጆቼ እንዲሁም ልጆቻችንን ስናስተምር ውድ ባለቤቴንና እኔን ስለረዳን የአዳኛችን ምሳሌ አመስጋኝ ነኝ።
ልጆቼ ለልጅ ልጆቼ የክርስቶስን ታሪክ ሲናገሩ ሳይ ልቤ በደስታ ይሞላል፣ ይህም ከምወዳቸው ጥቅሶች ውስጥ እንደዚህ የሚለውን ያስታውሰኛል። በ 3ኛ ዮሐንስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 4 ውስጥ ነው፣ እንዲህም ይላል፣“ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለም” እናም የልጅልጆቻችን ቢሆኑስ?
በተደጋጋሚ ስለክርስቶስ፣ሰንበትን ስለማክበር፣እና በእያንዳንዱ እሁድ ለአዳኙ ክብር ስንል ቅዱስ ቁርባንን ስለመካፈል ስለሚያስተምሩን መሪዎቻችን አመስጋኝ ነኝ።
የክርስቶስን ታሪኮች ስናጠና ሰንበትንና ቅዱስ ቁርባንን የበለጠ ተወዳጅ ይሆናሉ። ይህን በማድረግ፣ እምነታችንን እና ምስክርነታችንን የሚገነባውን እንዲሁም ቤተሰባችንን የሚጠብቁትን ባህሎች እንፈጥራለን።
ከተወሰነ ሳምንታት በፊት፣ ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ የተሰጠውን የሽማግሌ ረስል ኤም ኔልሰንን መልዕክት በድጋሜ ሳጠና በነበርኩበት ሰአት እና ስለ ሰንበት ቀን እያሰላሰልኩኝ በነበርኩበት ሰአት፣ ቅዱስ ቁርባንን መውሰድ ለቻልኩበት በረከትና እድል ጥልቅ የሆነ ምስጋና ተሰማኝ። ለእኔ ያ በጣም ሐይማኖታዊ፣ ቅዱስና መንፈሳዊ ወቅት ነው። የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እጅግ በጣም ያስደሰተኛል።
በጥልቅ ሃሳቤ ውስጥ፣ በዳቦውና በውኃው ላይ የሚደረጉትን በረከቶች በጥንቃቄ አጠናሁ። ከቅዱስ ቁርባኑ ጋር የሚዛመደውን ክስተት በአእምሮዬና በልቤ ውስጥ ማሰላሰል ጀመሩኩኝ።
በማሰላሰል መንፈስ ውስጥ እያለሁ የመጀመሪያውን እርሾ የማይገባበትን የቂጣ ድግስ ፋሲካ የት መዘጋጀት እንዳለበት ለቀረበለት ለደቀመዛሙርቱ ጥያቄ እንዲህ ብሎ ስለመለሰት ቀን አሰብኩኝ፣ “እርሱም ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ መምህር ጊዜዬ ቀርቦአልና ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል በሉት አለ።”7
በአእምሮዬ ውስጥ በዛ ቀን ከእርሱ ጋር አብሮ ለመብላት ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሲገዙና ጠረጴዛውን በጥንቃቄ ሲያዘጋጁ ለመሳል ሞከርኩኝ። ለእርሱና ለ12 የሚወዳቸው ደቀ ማዛሙርቱ፣ ባጠቃላይ ለ13 ሰዎች የሚበቃ ጠረጴዛ።
ክርስቶስ አብሯቸው ሲመገብ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጠኛል” ብሎ ያወጀውን ነገር ስስል አለቀስኩኝ። .”8
ያዘኑ ደቀ መዛሙርቶቹ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እሆንን?” ብለው ሲጠይቁት አሰብኩኝ። ?”9
ከዛ ይሁዳም መልሶ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቀ፣ እርሱም በዝግታ “አንተ አልህ።” ብሎ መለሰ።.10
እነዛን የፈወሱ፣ ያፅናኑ፣ ያበሩና የባረኩ እጆች ኢየሱስ ዳቦውን ቆርሶ “እንካችሁ፣ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው” ሲል መሳል እችላለሁ።11
ከዛም በወይን የተሞላው ጽዋን አንስቶ አመሰገነ እና ጽዋውን “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።”12
አዕምሮዬ ውስጥ፣ ደቀ መዛሙርቶቹን አንድ በአንድ አይናቸው ውስጥ በጣም ለሚወዱት ለመምህሩ ያላቸውን ጭንቀት ተመለከትኩኝ። እዛ ከእነርሱ ጋር አብሬ ተቀምጬ ሁሉን ነገር ያየሁ ያክል ነበር። ለእኔ ሲል ለማድረግ ለተዘጋጀው ነገር በልቤ ውስጥ ከባድ ህመምና ሀዘን ተሰማኝ።
ነፍሴ የተሸለ ሰው ለመሆን በሚያስገርም ፍላጎት ተሞልታ ነበር። በንስሃና በሃዘን በጌተሰማኔ የፈሰሰውን ደሙን ለማቆምና ለማስቀረት በጥልቅ ተመኘሁ።
ከዛ እርሱን በማሰብ በእያንዳንዱ ሳምንት በምንካፈለው በቅዱስ ቁርባኑ ላይ አሰላሰልኩኝ፣ እናም ይህን በማደርግበት ጊዜ በዳቦውና በውኃው በረከት ላይ ስላለው እያንዳንዱ ቃል በጥልቅ አሰብኩኝ። ዳቦው ሲባረክ “እናም ሁልጊዜ ያስታውሱት ዘንድ” የሚሉትን ቃላት እንዲሁም ውኃው ሲባረክ “እነሱም ሁልጊዜ ያስታውሱት ዘንድ” የሚሉትን ቃላት በጥብቅ አሰብኩኝ።13
“ሁልጊዜ እርሱን ማስታወስ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ አሰብኩኝ።
ለእኔ ይህ ማለት፥
-
ይህ የሚያምር ምድር በእርሱ ሲሰራ ቅድመ ምድራዊ ሕይወቱን ማስታወስ፤14
-
በቤተልሔም ይሁዳ በከብቶች ግርግም ውስጥ ውልደቱን ማስታወስ፤15
-
እናም የ12 አመት ሕፃን ልጅ እያለ ዶክተሮችን በቤተ-መቅደስ ውስጥ አስተማረ፤16
-
ለምድራዊ ስራ ለመዘጋጀት ለብቻው ወደ ምድረ በዳ መሄዱን ማስታወስ፤17
-
በደቀ መዛሙርቱ ፊት ሲለወጥ ያስተማራቸውን ነገር ማስታወስ፤18
-
ከደቀ መዛሙርቶቹ ጋር በመጨረሻው እራት ላይ ቅዱስ ቁርባንን ያስተዋወቀውን ማስታወስ፤19
-
በጌተሰማኒ የአትክልት ቦታ ሄዶ ለሃጢያታችን፣ ለህመማችን፣ መከፋታችን እጅግ ከመሰቃየቱ የተነሳ በሰውነቱ የቆዳ ቀዳዳዎች ደም አፈሰሰ፤20
-
ከብዙ ስቃይና ከባድ ህመም በኋላ እዛው በጌተሰማኒ ጓደኛ ብሎ በጠራው ከደቀ መዛሙርቱ በአንዱ በመሳም መከዳቱን ማስታወስ፤21
-
ወደ ጲላጦስና ወደ ሔሮድ ለፍርድ ሲወሰድ ማስታወስ፤22
-
ሲዋረድ፣ በቡጢ ሲመታ፣ ሲተፋበት፣ ሲደበደብና በጅራፍ ሲገረፍ ሰውነቱ መተልተሉን ማስታወስ፤23
-
የእሾህ አክሊል በሚያሰቅቅ ሁኔታ በእራሱ ላይ ሲደረግ ማስታወስ፤24
-
እራሱ የሚሰቀልበትን መስቀል ተሸክሞ ወደ ጎለጎታ የሄደበትንና እዛ በመስቀሉ ላይ በሚስማር የተመታበትን፣ ሁሉንም አይነት አካላዊና መንፈሳዊ ህመሞችን የተሰቃየበትን ማሰታወስ፤25
-
በመስቀሉ ላይ እያለ በቸርነት በመሞላት ወደ ሰቀሉት ሰዎች በመመልከትና አይኖቹን ወደ ሰማይ በማንሳት “አበት ሆይ፣ ሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብሎ የተማጸነውን ማስታወስ፤26
-
መላ የሰው ዘርን የማዳን ተልኮዉን ማሟላቱን በማወቅ ነፍሱን ወደ አባቱ፣ የእኛም አባት እጆች አሳልፎ የሰጠውን ማስታወስ፤27
-
የእኛን ትንሳኤ ያረጋገጠውንና በምርጫችን ላይ በመወሰን ለዘላለም ከጎኑ ለመኖር ያስቻለንን አስገራሚ ትንሳኤውን ማሰታወስ፤28
በተጨማሪም ቅዱስ ቁርባኑ ሲባረክ እኛ ሁልጊዜ እርሱን እንደምናስታውስ፣ የእርሱም መንፈስ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደሚሆንቃል-ኪዳኑንን ለመቀበል በቅዱስ ቁርባን ፀሎት ላይና በፀሎቱ ልዩና ትርጉም ባላቸው ቃሎች ላይ ማሰላሰል።29
ጌታ መቼ ራዕይ እንደሚሰጠን የራሱ የጊዜ ሰሌዳ እንዳለው አምናለሁ። ይህንን በጣም ግልፅ በሆነ ሁኔታ የተረዳሁት እንደዚህ የሚሉትን መክብብ 3፥1፣ 6 ሳጠና ነው።
“ለሁሉ ዘመን አለው. ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው፥
“ ለመፈለግ ጊዜ አለው፣ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፣ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፣ ለመጣልም ጊዜ አለው።”
ቅዱስ ቁርባን፣ ስለ ውድ ልጁ፣ ስለ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ እኛን የሚያስተምርበት እኛም ራዕይን የምንቀበልበት የሰማይ አባት ጊዜ ነው። ይህንን እውቀት ለመጠየቅና ለመቀበል “አንኳኩ ይከፈትላችሁማል”30 የሚለው ሰአቱ ነው። ለዚህ እውቀት በክብር እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት ጊዜ ነው፣ እናም ከጠየቅን፣ ከስፍር በላይ ሕይወቶቻችንን የሚባርከውን ይህንን እውቀት እንደምንቀበል ምንም ጥርጣሬ የለኝም።
ሰንበትን፣ ቅዱስ ቁርባንን እና ምን ማለት እንደሆነ እወዳለሁ። ጌታን በሙሉ ነፍሴ እወደዋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም። አሜን።