2010–2019 (እ.አ.አ)
“ስለ ስሜ ምስክርነት ለማካፈል የመረጥኳቸው”
ኦክተውበር 2015


16:54

“ስለ ስሜ ምስክርነት ለማካፈል የመረጥኳቸው”

ዳግም በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በዋና አመራር ቦታዎች ላይ በእድሜ ጠና ያሉ ታላቅ የመንፈሳዊ እና የፍርድ ጥንካሬ ያላቸው ሰዎች መኖራቸው እንዴት ድንቅ ነው።

በ1996 ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ ሂንክሊ 60 ደቂቃ በሚባል የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቀርበው ነበር። ልምድ ያለው እና ንቁ የሆነው ጋዜጠኛ ማይክ ዋለስ በዛ ባሉ ጉዳዮች ፕሬዘዳንት ሂንክሊን ቃለ መጠየቅ አደረገላቸው።

በንግግራቸው ማብቂያ አከባቢ፣ አቶ ዋለስ እንዲህ አለ፣ “ይሄ ያረጁ ሰዎች ቦታ ነው። ይሄ በሽማግሌዎች የሚመራ ቤተክርስቲያን ነው የሚሉ አሉ”

ፕሬዘዳንት ሂንክሊ በደስታ እና ያለ ማንገራገር ምላሽ ሰጡ፣ “ከበላይ ጠና ያለ ሰው፣ በሁሉም የአስተምሮ ንፋስ የማይገፋ የፍርድ ሰው መኖሩ ድንቅ አይደለምን?” (በሚያዝያ 7፣ 1996 (እ.አ.አ) የተሰራጨ)

የእኔ አላማ ዳግም በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በዋና አመራር ቦታዎች ላይ በእድሜ ጠና ያሉ ታላቅ የመንፈሳዊ እና የፍርድ ጥንካሬ ያላቸው ሰዎች መኖራቸው እንዴት ድንቅ እንደሆነ ማብራራት ነው----እና እነዚህን ጌታ “ስለ ስሙ በሁሉም አገሮች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎች፣ እና ህዝቦች ምስክረነት እንዲያካፍሉ የመረጣቸውን…” እኛ ለምን መስማት እና መቀበል (ሞዛያ 2፣9) እንዳለብን ለማብራራት ነው።(ት. እና ቃ. 112፥1)

ይሄን አስፈላጊ ርእስ በአንድነት ስናስብ ሁላችንም በመንፈስ ቅዱስ እንመራ ዘንድ ፀሎቴ ነው።

የህይወት ዘመን ትምህርት

ስለዚህ ርእስ በተወሰነ ጉልህ ምልከታ እናገራለሁ። ላለፉት 11 አመታት፣ በእድሜ ቅደም ተከተል መሰረት የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ እኔ ታናሹ አባል ነበርኩ። በአገልግሎቴ አመታት ወቅት፣ በቀዳሚ አመራር እና አስራ ሁለቱ ጉባኤ ውስጥ የሚያገለግሉት ሰዎች አማካኝ እድሜ 77 አመት ነበር--በዚህ ዘመን ውስጥ በ11 አመታት ክፍተት ላይ የሐዋርያት ትልቁ አማካኝ እድሜ ነው።

አብሬአቸው ካገለገልኩት የጉባኤው አባላት አጠቃላይ የሐዋርያዊ፣ መለኮታዊ፣ ግላዊ፣ እና የስራ ተሞክሮ እና ማስተዋል እኔ ተባርኬያለሁ። ከሽማግሌ ሮበርት ዲ ሄልስ ጋር ከነበረኝ ግንኙነት አንድ ምሳሌ ከእነዚህ መሪዎች ለመማር እና አብሮ ለማገልገል የነበረኝን አስደናቂ እድሎች ያመለክታል።

ከአመታት በፊት ሽማግሌ ሄልስ ከፅኑ ህመማቸው በማገገም ላይ ሳሉ እሁድ ከሰአት በኋላን በቤታቸው ውስጥ አሳልፌ ነበር። ስለ ቤተሰቦቻችን፣ የጉባኤ ሀላፊነቶቻችንን፣ እና ስለ አስፈላጊ ተሞክሮዎች ተወያየን።

የሆነ ነጥብ ላይ ሽማግሌ ሄልስን እንዲህ ብዬ ጠየኩ፣ “ስኬታማ ባል፣ አባት፣ አትሌት፣ የንግድ ስራ አስፈፃሚ፣ እና የቤተክርስቲያን መሪ ሆነህ ነበር። እድሜህ እየገፋ ሲመጣ እና የአካላዊ አቅምህ እያነሰ ሲሄድ ምን አይነት ትምህርቶችን ተምረሀል?”

ሽማግሌ ሄልስ ጥቂት ዝም አሉ እና እንዲህ ብለው መለሱ፣ “ሁል ጊዜ የምታደርገውን ለማድረግ ካልቻልክ፣ የበለጠ ዋጋ ያለውን ነገር ብቻ ታደርጋለህ።”

በእርሱ ቀላል እና የአስተውሎ ምላሽ ተገርሜ ነበር። ተወዳጁ ሀዋርያ ጓደኛዬ፣ በስጋዊ ስቃይ እና በመንፈሳዊ ፍተሻ በኩል የተማሩትን የህይወት ትምህርት ከእኔ ጋር ተካፈሉ።

የሰው ውስንነቶች እና ፀባየ ደካማነት

በእድሜ ከመግፋት ተፈጥሮአዊ ምክንያት የሚመጡት አካላዊ ውስንነቶች በእርግጥም አስደናቂ የመንፈሳዊ ትምህርት እና አስተውሎ ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ። የእነዚህን አገልጋዮች ውጤታማነት ይቀንሳል ብለው ብዙዎች የሚያስቧቸው እነዚሁ ምክንያቶች የእነርሱ ጥቂት ጥንካሬዎች መሆን የሚችሉ ናቸው። አካላዊ ውስንነቶች እይታን ሊያሰፉ ይችላሉ። ውስን የሆነ ብርታት ማስቀደም የሚገቡ ነገሮችን ግልፅ ሊያደርግ ይችላል። ብዙ ነገሮችን ማድረግ አለመቻል ታላቅ አስፈላጊነት ወዳላቸው ነገሮች አትኩሮት እንዲኖር የሚመራ ሊሆን ይችላል።

የዘመኑ የአለማችንን ከባድ ችግሮች ለመጋፈጥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ወጣት እና ይበልጥ ንቁ የሆኑ መሪዎች እንደሚያስፈልጉ አንዳንድ ሰዎች ጠቁመዋል። ነገር ግን አላማዎቹን ለማሳካት ጌታ ወቅታዊ ፍልስፍናዎችን እና የአመረር ተግባራትን አይጠቀምም (ኢሳያስ 55፥8–9 ተመልከቱ)። ፕሬዘዳንቱ እና ሌሎች ዋና የቤተክርስቲያኑ መሪዎች በእድሜ ገፋ ያሉ እና በመንፈሳዊ ጠና ያሉ እንደሚሆኑ መገመት እንችላለን።

በቤተክርስቲያን ውስጥ መማክርት ጌታ የገለጠው የአመራር ሂደት የሰው ፀባየ ደካማነት የሚያመጣውን ውጤት ያገናዘበ ነው። ደስ በሚል ሁኔታ፣ የእነዚህ ሰዎች አካላዊ ውስንነት ለእነርሱ እና በእነርሱ ምክንያት የሚመጣውን የመገለጥ መለኮታዊ ምንጭ ፅኑ ያደርገዋል። በእውነተም፣ እነዚህ ሰዎች በትንቢት ከእግዚአብሔር የተጠሩ ናቸው (የእምነት አንቀፅ 1፥5 ተመልከቱ)።

የመዘጋጀት ጥምረታዊ ሂደት

በእድሜ እና ለፍርድ ጠና ያሉት በቤተክርስቲያን ዋና አመራር ቦታዎች እንዲያገለግሉ በማድረጉ የጌታን ከፊል ኣላማን እንኳን ቢሆን በወንድሞቼ ውስጥ አስተውያለሁ። እነዚህ ሰዎች በሚወክሉት፣ በሚያገለግሉት እና በሚያፈቅሩት ጌታ ቀጣይ ለሆነ ጊዜ ትምህርት የቀሰሙ ናቸው። የመንፈስ ቅዱስን መለኮታዊ ቋንቋ ለመረዳት እና መገለጥን ለመቀበል የጌታ መንገዶችን የተማሩ ናቸው። እነዚህ ሰዎች እይታቸውን ያጠነከረ፣ አስተውሎተን ያመላከተ፣ በሁሉም ሀገራት እና ሁኔታዎች ላሉ ሰዎች ፍቅርን ያስገኘ፣ እና የዳግም መመለስን እውነታ ያረጋገጠ በጣም ልዩ የእድገት ሂደትን ያሳለፉ ናቸው።

እነዚህ ወንድሞቼ በከባድ አካላዊ ችግሮች እየታገሉ እንኳን ሀላፊነቶቻቸውን ለማሟላት እና ለማጉላት በፅናት ሲጥሩ በተደጋጋሚ ተመልክቻለሁ። እነዚህ ሰዎች ከመከራ የተሰወሩ አይደሉም። በምትኩ፣ በመከራ በመሰቃየት ውስጥ እንኳን ወደ ፊት በጀግንነት እንዲጓዙ የተባረኩ እና የጠነከሩ ናቸው።

ከእነዚህ የጌታ ተወካዮች ጋር አብሮ በማገልገል፣ የእነርሱ ታላቅ ፍላጎት የሰማይ አባታን እና የእርሱ ተወዳጅ ልጅን ፍቃድ ለማወቅ እና ለማድረግ እንደሆነ እኔ ለማወቅ ችያለሁ። ከወንድሞች ጋር በመመካከር፣ የብርሀን እና እውነትን ደረጃ የሚያሳዩ ከሰው እውቀት፣ ምክንያታዊነት፣ እና ተሞክሮ በላይ የሆኑ መነሳሳቶች ተገኝተዋል እና ውሳኔዎችም ተደርገዋል። ግራ በሚያጋቡ ችግሮች ላይ በአንድነት በመስራት፣ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ለጉዳዩ ያለን የጋራ መረዳት በሚያስደንቁ መንገዶች ከፍ ብሏል።

የዚህችን ቤተክርስቲያን መሪዎች የየቀን ግላዊ ማንነት፣ ብቃታቸውን፣ እና ክቡር ባህሪያቸውን በመመልከት ተባርኬያለሁ። የወንድሞች ሰዋዊ ድክመትን አንዳንድ ሰዎች የሚረብሽ እና እምነትን የሚያከሰም አድርገው ይወስዱታል። ለእኔ እነዚያ ፍፁም አለመሆኖች አበረታች እና እምነት አነሳሾች ናቸው።

ተጨማሪ ምልከታ

እስከአሁን ስድስት ወንድሞቼ ምድራዊ አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ እና በአካላዊ ሞት አማካኝነት በመንፈስ አለም ውስጥ ወደ አዲስ ሀላፊነቶች ሲሸጋገሩ ተመልክቻለሁ፤ ፕሬዘዳንት ጀምስ ኢ ፋውስት፣ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ ሂንክሊ፣ ሽማግሌ ጆሴፍ ቢ ዊርዝሊን፣ ሽማግሌ ኤል ቶም ፔሪ፣ ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ ፓከር፣ እና ሪቻርድ ጂ. ስኮት።

እነዚህ ጀግና ወነድሞች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለአለም ሁሉ ለመመስከር ህይታቸውን እንዲሁም “መላ ነብሳቸውን” (ኦምኒ 1፥26) ሰተዋል። የትምህርቶቻቸው ጥቅል ከዋጋ በላይ ነው።

እነዚህ አገልጋዮች የአስርተ አመታት የመሰጠት አገልግሎት ውስጥ የተማሩትን በአገልግሎታቸው ማብቂያ አመታት ሀያል መንፈሳዊ የትምህርቶች ማጠቃለያን ከእኛ ጋር አካፍለዋል። እነዚህ መሪዎች ማካፈል የሚችሉት በጣም ጥቂት ነው ብለው እንዳንድ ሰዎች በሚያምኑበት ጊዜ እነርሱ ታላቅ ዋጋ ያላቸውን እውነቶች አካፈሉ።

በቅዱሰን መጽሐፍት ውስጥ ያሉ ታላቅ ነብያትን የማጠቃለያ ትምህርቶች አስቡ። ለምሳሌ፣ ኔፊ መዛግብቱን በእነዚህ ቃላት ፈፀመ፤ “ለዚህም ነበር ጌታ ያዘዘኝ፣ እና እታዘዛለሁ” (2ኛ ኔፊ 33፣15)

በህይወቱ ማብቂያ አከባቢ፣ ያዕቆብ እነዲህ ገሰፀ፤

“እንግዲህ አቤቱ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ንስሀ ግቡ፣ በጠባቡም ደጅ ግቡ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትን እስከምታገኙ ድረስ በጠባቡ ጎዳና ቀጥሉ።

“አቤቱ ብልህ ሁኑ፤ ከዚህ የበለጠ ምን ማለት እችላለሁ?” (ያዕቆብ 6፥11 – 12)።

እና ሞሮኒ ሰሌዳዎቹን የማዘጋጀት ስራውን በትንሳኤ ላይ ተስፋ በማድረግ አጠናቀቀ፥ “እናም አሁን ሁላችሁንም እሰናበታችኋለሁ። መንፈስና ስጋዬም በአንድ ላይ እስከሚሆን እናም በታላቁ ያህዌህ፣ ዘለዓለማዊ ዳኛ በሆነው ፊት፣ በአስደሳቹ የፍርድ ወንበር ህያዋንን እና ሙታንን ለመገናኘት ድል አድርጌ ወደ ሰማይ እስከምመጣ ድረስ በፍጥነት በእግዚአብሔር ገነት ለማረፍ እሄዳለሁ” (ሞሮኒ 10፥34)።

በኋለኛው ቀን ነብያት እና ሐዋርያት መቋጫ ትምህርቶች እና ምስክርነቶች ለመማር እኔ እና እናንተ ተባርከናል። የዛሬ ስሞች ኔፊ፣ ያቆብ፣ እና ሞሮኒ አይደሉም--ነገር ግን ፕሬዘዳንት ጀምስ ኢ ፎስት፣ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ ሂንክሊ፣ ሽማግሌ ጆሴፍ ቢ ዊርዝሊን፣ ሽማግሌ ኤል ቶም ፔሪ፣ እና ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ ፓከር ናቸው፣ እና ሽማግሌ ስኮት።

የእነዚህ የተወደዱ ሰዎች ማጠቃለያ መልእክቶች የበለጠ ዋጋ አላቸው ወይም ከአገልግሎታቸው የበለጠ ዋጋ አላቸው እያልኩኝ አይደለም። ሆኖም፣ የመንፈሳዊ ትምህርታቸው እና የህይወት ልምዶቻቸው እነዚህ መሪዎች በሙሉ ትክክለኛነት እና ታላቅ ሀይል ዘለአለማዊ እውነታዎች ላይ እንዲያተኩሩ አስችሏቸዋል።

ፕሬዘዳንት ጄምስ ኢ. ፎስት

በሚያዝያ 2007 (እ.አ.አ) የመጨረሻ አጠቃላይ ጉባኤው ወቅት፣ ፕሬዘዳንት ፎስት እንዲህ አወጁ፥

“አዳኝ በሀጢያት ክፍያው አማካኝነት ለሁላችንም ውድ ሰላምን ሰጠን፣ ነገር ግን ይሄ ሊመጣ የሚችለው የንዴት፣ ክፋት፣ ወይም በቀል አሉታዊ ስሜቶችን ለማስወገድ ፍቃደኞች ከሆንን ብቻ ነው። …

“ይቅር ለመባል ይቅር ማለት እንደሚገባን እናስታውስ።… በሙሉ ልቤ እና ነብሴ፣ ‘ሁሉንም ሰዎች ይቅር ለማለት’ የአዳኝ ምክርን ስንከተል ሊመጣ ስለሚችለው የፈውስ ሀይል አምናለሁ [ ት. እና ቃ. 64፥10 ]” (“The Healing Power of Forgiveness,” Liahona, May 2007, 69)።

ከምወደው ሰው እና ከማውቃቸው ሰዎች ሁሉ በጣም ይቅር ባይ የሆነው የፕሬዘዳንት ፎስት መልእክት የህይወት ዘመን ሀያል ትምህርት ነው።

ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ

ፕሬዘደንት ሒንክሊ በመጨረሻቸው አጠቃላይ ጉባኤ በ ሚያዝያ 2007 (እ.አ አ) እንደመሰከሩት፥ “የነቢዩ ዮሴፍ ጥሪን፣ ስራዎቹን፣ ለዘለአለማዊ እውነት ሰማእት በመሆን በደሙ ምስክርነቱን ስለማተሙ ያለኝን ምስክርነት ማረጋገጫ ሰጣለሁ። የመጀመሪያው እና ተከትሎ ስለመጣው ራእይ እውነታን ስለመቀበል የሚሰነዘሩ ጥያቄዎችን እኔ እና እናንተ እንጋፈጣለን። በዛ እውነታ ጥያቄ ላይ የዚህች ቤተክርስቲያን ትክክለኛነት ይወሰናል። እኔ እንደምመሰክረው፣ ያ እውነት ከሆነ፣ እኛ የምንሳተፍበት ስራ በምድር ላይ በጣም አስፈላጊው ስራ ነው” (“The Stone Cut Out of the Mountain፣” Liahona, Nov. 2007, 86)።

የፕሬዝዳንት ሂንክሊ ምስክርነት ከምወዳው እና የእግዚአብሔር ነብይ እንደሆነ ከማውቀው ሰው የመጣ የህይወት ዘመን ሀያል ትምህርት ነው።

ሽማግሌ ጆሴፍ ቢ. ዊርትሊን

የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ዊርዝሊን የመጨረሻ የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቱን ያካፈለው በጥቅምት 2008 (እ.አ.አ) ነበር።

“ከረጅም ጊዜ በፊት የኔ ቡድን የእግር ኳስ ጨዋታን ሲሸነፍ በዛ ቀን እናቴ ለእኔ የሰጠችኝን ምክር አሁንም አስታውሳለሁ፤ ‘የሆነው ይሁን፣ እና ያንን ውደደው።’

“… መከራ፣ በአግባቡ ከተጋፈጥነው፣ በህይወታችን ውስጥ በረከት ሊሆን ይችላል። …

“ደስታን ስንፈልግ፣ዘለአለማዊ እይታዎችን ስንሻ፣ የማካካስን መርህ ስረዳ፣ እና ወደ ሰማይ አባታችን ስንቀርብ፣ በችግሮች እና ፈተናዎች መፅናት እንችላለን። እናቴ እንዳለችው፣ እኛም ‘የሆነው ይሁን፣ እና ያንን መውደድ ነው’ ማለት እንችላለን። (“Come What May, and Love It፣” Liahona, Nov. 2008, 28)።

የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ዊርዝሊን መልእክት በአዳኝ በመታመን ችግሮችን የማሸነፍ ህያው ማስተማሪያ ከሆነ እና ከምወደው ሰው የተሰጠ የህይወት ዘመን ሀያል ትምህርት ነው።

ሽማግሌ ኤል. ቶም ፔሪ

የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ፔሪ ከስድስት ወራት በፊት በዚህ መድረክ ቆሞ ነበር። በዚያ ጊዜ፣ በአጠቃላይ ጉባኤ ምስክርነቱ የመጨረሻ ይሆናል ብለን መገመት አንችልም ነበር።

“ምስክርነቴን በማካፈል ልጨርስ (እና በዚህ ምድር የዘጠኝ አስርተ አመታት ቆይታዬ ይህን ለማለት ሙሉ በሙሉ ብቁ ያደርገኛል)፣ እድሜዬ በጨመረ ቁጥር፣ ቤተሰብ የህይወት ማእከል መሆኑን እና ለዘለአለማዊ ደስታ ቁልፍ መሆኑን የበለጠ አስተውላለሁ።

“የእኔን ህይወት ሙሉ ያደረጉትን፣ እና አዎ፣ ዘለአለማዊ ያደረጉትን ባለቤቴን፣ ልጆቼን፣ የልጅ ልጆቼ እና የልጅ ልጅ ልጆቼን እና ሌሎች ቤተሰቦችን አመሰግናለሁ። ስለዚህ ዘለአለማዊ እውነት በጣም ጠንካራ እና ቅዱስ ምስክርነቴን አካፍላለሁ” (“Why Family and Marriage Matter—Everywhere in the World፣” Liahona, May 2015, 42)።

የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ፔሪ መልእክት በቤተሰብ እና ዘለአለማዊ ደስታ መካከል ስላለው ግንኙነት ሰፊ ከሆነው ተሞክሮ ከተረዳ እና ከምወደው ሰው የመጣ የህይወት ዘመን ሀያል ምስክርነት ነው።

ፕሬዝዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር

ከስድስት ወራት በፊት በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ፕሬዘዳንት ፓከር በአብ የደስታ እቅድ፣ የአዳኝ የሀጢያት ክፍያ፣ እና ዘለአለማዊ ቤተሰቦች ላይ ያተኮረ ነበር።

“ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እና የህያው እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እመሰክራለሁ። የቤተክርስቲያን እራስ ሆኖ ቆሟል። በእርሱ የሀጢአት ክፍያ እና በክህነት ሀይል፣ በምድር የጀመሩ ቤተሰቦች ለዘለአለም አንድ መሆን ይችላሉ። …

“ስለ ምንም ያህል ከባድ ወይም እረጅም ጊዜ ወይም ምንም ያህል ተደጋጋሚ ቢሆንም እያንዳንዱን ጉድፍ አጥቦ ሊያፀዳ ስለሚችለው ስለ የሀጢያት ክፍያ በረከቶች በጣም አመስጋኝ ነኝ” (“The Plan of Happiness፣” Liahona, May 2015, 28)።

የፕሬዘዳንት ፓከር የመጨረሻ መልእክት “የቤተክርስቲያን እንቅስቃሴዎች ሁሉ አንድ ወንድ እና ሴት ከልጆቻቸው ጋር በቤታቸው ውስጥ ደስተኛ እንዲሆኑ፣ ለወቅቱ እና ለዘለአለም አብረው እንዲታተሙ ለማድረግ” መሆኑን በጉልህ እና በተደጋጋሚ ካወጀ ሰው የህይወት ዘመን ሀያል ትምህርት ነው” ( Liahona, May 2015, 26)።

ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት

ሽማግሌ ስኮት በመጨረሻቸው አጠቃላይ ጉባኤ ንግግር በጥቅምት 2015 ውስጥ እንዳወጁት፥ “ወደ ስጋዊ ህይወት የመጣነው በፈተናዎች ለማደግ ነው። ፈተናቆች እንደ ሰማይ አባታችን እንድንሆን ይረዱናል፣ እናም የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እነዚህን ፈተናዎች እንድንፅናና ያደርጋል። ወደ እርሱ ስንመጣ፣ ፈተናዎችን፣ እያንዳንዱን የልብ ስቃይ፣ ለመጋፈጥ እንደምንችል እመሰክራለሁ” (“Make the Exercise of Faith Your First Priority,” Liahona, Nov. 2014, 94)።

የሽማግሌ ስኮት መልእክት በአለም ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ስን ልዩ ምስክር የሆነ እወዳጅ እና የማፈቅረው ሰው የህይወት ሁሉ ትምህርት ነበር (ት. እና ቃ. 107፥23 ተመልከቱ)።

የተስፋ ቃል እና ምስክርነት

“በእኔም ድምፅ ሆነ ወይም በአገልጋዮቼ ድምፅ፣ አንድ ነው” (ት እና ቃ 1፥38)። በጌታ የተመረጡ ተወካዮቹ ያስተማሩትን ዘለአለማዊ እውነታ እንስማ እና እንከተል። ያንን ስናደርግ፣ በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት እንደሚጠነክር፣ እና ለልዩ ጉዳዮቻችን እና ፍላጎታችን መንፈሳዊ ምሬት እና ጥበቃ እንደምናገኝ ቃል እገባለሁ።

ስለ ስሙ ምስክርነት እንዲሰጡ በተመረጡት በአገልጋዮቹ አማካኝነት የተመለሰውን እና አሁን ያለውን ቤተክርስቲያኑን ጉዳይ ህያዉ ክርስቶስ እንደሚመራ እመሰክራለሁ። ይህንም በቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።