2010–2019 (እ.አ.አ)
በዚህ ስራ ብቸኛ አይደላችሁም
ኦክተውበር 2015


15:48

በዚህ ስራ ብቸኛ አይደላችሁም

ከአንድ የክህነት አገልግሎት ወደ ሌላ ስትሄዱ፣ ጌታ በስራው ከእናንተ ጋር እንደሆነ ትመለከታላችሁ።

ወንድሞች፣ እንደ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያት ሽማግሌ ሮናልድ ኤ ራስባንድ ፣ ሽማግሌ ጌሪ ኢ ስቲቨንሰን ፣ እና ሽማግሌ ዴል ጂ ሬንለንድን ጌታ ስለጠራቸው አመስጋኞች ነን። ልቦቻችን፣ ጸሎቶቻችን፣ እና እምነታችን እነርሱን ይደግፋቸዋል።

ስለታላቅ ብቃጣቸው እናውቃለን። ነገር ግን ሁላችንም እንደምንፈልገው፣ ጌታ በስራው ከእነርሱ ጋር እንዳለ በጥሪአቸው ማረጋገጫ ይፈልጋሉ። አዲስ ዲያቆን እናም አዲስ ጥሪ የተቀበለ ብዙ ልምድ ያለው ሊቀ ካህንም ያ ማበረታቻ ያስፈልገዋል።

ያም ብርታት የሚመጣው እርሱ በአገልጋዮቹ እናንተን እንደጠራ በምታዩበት ጊዜ ነው። የማበረታታችሁም የእናንተን ድርሻ ስትወጡ፣ ጌታ ሀይሉን ወደ ጥረታችሁ ላይ እንደሚጨምር እንድታውቁ ለመርዳት ነው።

በጌታ መንግስት ውስጥ የምንቀበለው ማንኛውም ጥሪ ከሰው ፍርዳችን እና ከግል ሀይላችን በላይ የሚያስፈልገው ነው። እነዚህ ጥሪዎች የሚመጣው የጌታ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። አዲሱም ዲያቆን ያ እውነት እንደሆነ ይማራል፣ ነገር ግን ለብዙ አመታት በመማርም ይቀጥላል።

ከልጅ ልጆቼ አንዱ በዚህ ምሽት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በአጠቃላይ የክህነት ስብሰባ ውስጥ ነው ያለው። ከስድስት ቀናት በፊት እንደ ዲያቆን ተሹሞ ነበር። የመጀመሪያው የክህነት አገልግሎት በሚቀጥለው እሁድ ቅዱስ ቁርባንን ማሳለፍ እደሆነ ይጠብቅ ይሆናል። ጸሎቴ ያ ጊዜ በእውነት ምን እንደሆነ ያስተውል ዘንድ ነው።

ለጌታ የሚሰራው ስራ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባው ውስጥ ለሚገኙት ሰዎች ቅዱስ ቁርባንን ማሳለፍ ነው ብሎ ያስብ ይሆናል። ነገር ግን የጌታ እቅድ ሰዎች ዳቦና ውሀን እንዲወስዱ ለማድረግ ብቻ አይደለም። ወደ ዘለአለም ህይወት በሚመራው መንገድ ላይ እንዲጓዙ የሚያደርገውን ቃል ኪድን እንዲጠብቁ ነው። ያም እንዲሆን፣ ጌታ ዲያቆኑ ሰሀኑን ላቀረበለት ሰው መንፈሳዊ ተሞክሮ መስጠት አለበት።

ዲያቆን ጎንበስ ብሎ ነጭ ጸጉር ላላቸው ሴት ሰሀኑን በሚያሳልፍበት ጊዜ፣ ያ ሁኔታ ሲከሰት ተመልክቼ ነበር። እርሳቸውም ዳቦው በጣው ውድ እንደሆነ አድርገው ተመለከቱት። ቁርባኑን ወስደው እጃቸውን ዘርግተው፣ በታላቅ ድምጽ፣ “ኦ፣ አመሰግናለሁ” በማለት፣ የዲያቆኑን ጭንቅላት ለመዳበስ እጃቸውን ሲያነሱ የነበራቸውን ፈገግታ አልረሳም።

ያ ዲያቆን የክህነት ሀላፊነቱን እያሟላ ነበር። ነገር ግን፣ ጌታ የዲያቆኑን ድርጊት አባዛው። ሴትየዋም አዳኝ ያንን ልጅ ወደ እርሳቸው መላኩን እንዳስተዋሉ እርግጥ ነው። ቅድስ ቁርባኑን ወደ እርሳቸው ሲያቀርብ መንፈስ ከእርሳቸው ጋር እንደሚሆን እርግጠኛ ነበሩ። በዚያ ቀን በእንክብካቤ መአከሉ ውስጥ ብቸኛ አልነበሩም። ዲያቆኑም በአገልግሎቱ ብቸኛ አልነበረም።

በአሮናዊ ክህነት ውስጥ ያለ ወጣት አስተማሪ፣ ቤተሰብን ለማስተማር ሲሄድ፣ በጌታ ስራ ተባባሪ እንደሆነ አይሰማው ይሆናል። ወደቤታችን ስለመጣው የቤት ለቤት አስተማሪ ተባባሪ ምስክርነት አሁንም አስታውሳሉ። ቃላቱን መንፈስ አረጋገጣቸው። እርሱ ያን ቀን አያስታውሰው ይሆናል፣ ነገር ግን እኔ አስታውሰዋለሁ።

በቅስና ውስጥ ሲጠራ፣ ጌታ የወጣቱን ጥረት በድጋሜ ያጎላዋል። ለምሳሌ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያጠምቀው ሰው የማያውቀው ወጣት ሰው ሊሆን ይችላል። ትክክለኛውን ቃላት እንደሚል እና ስርዓትን በትክክል እንደሚያከናውን ያስብ ይሆናል።

ነግር ግን ጌታ፣ የእርሱ አገልጋይ የሆነውን፣ የእርሱን ጥረት ያጎላል። የተጠመቀው ሰው በዘለአለም ህይወት መንገር ለመጓዝመርጧል። ጌታ የእርሱን ታላቅ ክፍል ያከናውናል። የጠመቅኩት ልጅ፣ እምባው በፊቱ እየፈሰሰ በጆሮዬ “ንጹህ ነኝ፣ ንጹህ ነኝ” በሚለኝ ጊዜ ይህን ለእኔ ደርሶ ነበር።

ከአንድ የክህነት አገልግሎት ወደ ሌላ ስትሄዱ፣ ጌታ በስራው ከእናንተ ጋር እንደሆነ ትመለከታላችሁ። ይህን የተማርኩት ከብዙ አመት በፊት ከሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዘደንት ጋር በካስማ ጉባኤ በተገናኘሁበት ጊዜ ነበር። በዚህ ጉባኤ ውስጥ የመልከጸዴቅ ክህነትን እንዲቀበሉ የቀረቡ 40 ሰዎች ነበሩ።

የካስማው ፕሬዘደንት ወደ እኔ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፣ “እነዚህ ሰዎች ኤልደር ለመሆን የሚችሉ በብዛት ተሳትፎ ያልነበራቸው ነበሩ።” በመገረም፣ እነዚህን ሰዎች ለማዳን ምን ፕሮግራም እንደነበራቸው ጠየኳቸው።

በቤተክርስቲያኗ መጨረሻ ላይ ወደተቀመጠ ወጣት ሰው ጠቆመኝ። እንዲህም አለ፣ “ያውና። አብዛኛዎቹ ሰዎች ተመልሰው የመጡት በዚያ የካህናት ጉባኤ ፕሬዘደንት ምክንያት ነው።” ያም ወጣት ሰው ካለእቅድ የለበሰ፣ በፊት ለፊቱ ያረጁ ጫማዎች ያሉት እግሮች ተዘርግተው፣ የተቀመጠ ነበር።

ከስብሰባው በኋላ ከእርሱ ጋር እንዲያስተዋውቀኝ የካስማ ፕሬዘደንትን ጠየኩት። ስንገናኝ፣ ባደረገው እንደተደነኩኝ ነገርኩት እና እንዴት እንዳከናወነው ጠየኩት። ትከሻውን አነቃነቀ። ለዚህ ሀላፊነትን ለመውሰድ እንዳልፈለገ ግልጽ ነበር።፡እንዲህም አለ፣ “እኔ አይደለሁም።”

ከዚያም በጸጥታ፣ “በዚህ ከተማ ውስጥ ያሉትን ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች በሙሉ አውቃለሁ። አብዛኛዎቹ የጭነት መኪናዎች አሏቸው። እኔም የጭነን መኪና አለኝ። እነርሱ መኪናቸውን በሚያጥቡበት ቦታ አጥባለሁ። ከጊዜ በኋላ፣ ጓደኛዎቼ ይሆናሉ።

“ከዚያም በህይወታቸው አንድ ነገር ትክክል እስከማይሆን ድረስ እጠብቃለሁ። ሁልጊዜም ይሆናል። ስለዚህ ይነግሩኛል። አዳምጣለሁ እናም ስህተት በእነርሱ ላይ አልጥልም። ከዚያም፣ ‘በህይወቴ አንድ ነገር ጥሩ አይደለም። ከዚህ የሚሻል ነገር መኖር አለበት፣’ ሲሉ፣ ምን እንደጠፋ እና የት እንደሚያገኙት እነግራቸዋለሁ። አንዳንዴ ያምኑኛል፣ እና ሲያምኑኝ፣ ይዤአቸው እሄዳለሁ።”

እርሱ ለምን ረጋ ያለ እንደሆነ ለመመልከት ትችላላችሁ።ያደረገው ትንሽ ክፍል እንደሆነ እና ጌታ የቀረውን እንደሚያደርግ ስለሚያውቅ ነው። እነዚያን ሰዎች በችግራቸው ልባቸውን የነካው ጌታ ነበር። ለእነርሱ የተሻለ ነገር እንዳለ ስሜት የሰጣቸው እና እንደሚያገኙት ተስፋ የሰጣቸው ጌታ ነበር።

እንደ እናንተ የጌታ አገልጋይ የነበረው ወጣት ሰው ትንሽ ክፍሉን ካከናወነ፣ እርሱ ወደሚሰጣቸው ቤት እና ደስታ መንገድ ጌታ እንደሚረዳቸው ያምን ነበር። እርሱም ሰጥቷቸዋል። ጌታ እንደ ሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዘደንት የጠራው የድርሻውን እንዲያከናውን እንደሆነም ያ ሰው አውቋል።

በአገልግሎታችሁ እንደዚያ ወጣት የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዘደንት የነበረው የሚያስደንቅ እና የሚታይ ውጤታማነት የማይኖራችሁ ጊዜዎች ይኖራሉ። ይህም ጌታ፣ በስራው ውስጥ የድርሻችሁን እንደምታከናወኑ በማወቅ፣ ስልጣን ባላቸው አገልጋዮቹ እንደጠራችሁ የምትተማመኑበት ጊዜ ነው። በጌታ አገልግሎት ማመን ብቅድመ አያቴ በሔንሪ አይሪንግ የሚስዮን አገልግሎት ጊዜ በጣም አስፈላጊ ነበር።

የተጠመቀው በመጋቢት 11፣ 1855 (እ.አ.አ)፣ በሴንት ሉውስ፣ ምዙሪ ውስጥ ነበር። ከዚያ አጭር ጊዜ በኋላ በእራስታስ ስኖው ወደ ካህንነት ተሾመ።ኦርሰን ስፔንሰር ወደ ቸረኪ ኔሽን እንደ ሚስዮን እንዲያገለግል በጥቅምት 6 ተጠራ።1 በጥቅምት 11 እንደ ቤተክርስቲያኗ ሽማግሌ ተሾመ። በፈረስ ወደ ቸረኪ ሚስዮን በጥቅምት 24 ሄደ። 20 አመቱ ነበር እና በወንጌል ከተለወጠ ሰባት ወራት ብቻ ነበር የሆነው።

ማንኛውም ካህን ብቁ ያለመሆን ወይም ዝግጁ አለመሆን እንዲሰማው ምክንያት ቢኖረው፣ ከሰባት ወር በፊት የተጠመቀው ሔንሪ ነበር። ለመሄድ ብርታት የነበረው እግዚአብሔር ስልጣን ባላቸው አገልጋዮቹ እንደጠሩት በማመኑ ነበር። ይህም የብርታቱ ምንጭ ነበር። በክህነት ውስጥ ጥሪያችሁ ምንም ቢሆን፣ ያም የመቋቋም ችሎታችሁ ምንጭ መሆን አለበት።

ሔንሪ አይሪንግ ለሚያስቸግሩ ሶስት አመታት ካገለገለ እና በሚስዮን ፕሬዘደንት ሞት ላይ ፣ ሔንሪ አይሪንግ በሚያዝያ 6፣ 1858 (እ.አ.አ) በተደረገ ስብሰባ ውስጥ ፕሬዘደንት እንዲሆን ተሹሞ ተመርጦ ነበር። አዲስ ዲያቆን ይደነቅ እና ይደነግጥ እንደሚሆን እርሱን እንደዚህ ነበር። እንዲህም ጻፈ፣ “በዚያ ሀላፊነት ባለው ጥሪ መጠራቴ የጠበኩት አልነበረም፣ ነገር ግን የወንድሞች ፈቃድ ስለሆነ፣ በዚያም ጊዜ ታላቅ ደካማነት እና ልምምድ እንደሚያጥረኝ እየተሰማኝ፣ ይህን በደስታ እቀበለዋለሁ።”2

አሁን ፕሬዘደንት አይሪንግ የነበረው ወደ ቸረኪ፣ ክሪክ፣ እና ቾታዋ ህዝቦች በ1859 (እ.አ.አ) ተጓዘ። የእሱ ጥረት፣ ጌታ፣ ሔንሪ እንደዘገበው፣ “በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ቁጥር” ጨመረ። ሁለት ቅርንጫፎችን አደራጀ ነገር ግን “በስራው ውስጥ በጣም ጥቂቶች ብቻ አሉ” በማለት ጠቆመ።3

ከአመት በኋላ፣ ሔንሪ ከሚያገለግላቸው ሰዎች መካከል ያሉት የፖለቲካ መሪዎች የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሚስዮኖች ስራቸውን ለማከናወን እንደማይፈቅዱ አስቸጋሪው እውነት አጋጠመው። ምን ማድረግ እንደሚገባው ሲያሰላስል፣ ከቀደመው የሚስዮን ፕሬዘደንት ሚስይኑን እስከ 1859 (እ.አ.አ) ድረስ እንዲያራዝም የተሰጠውን መመሪያ አስታወሰ።4

በዛ ዓመት ጥቅምት ውስጥ፣ ሔንሪ መመሪያ እንዲሰጡት ለፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ ጻፈ፣ ነገር ግን ለጥያቄው መልስ አላገኘም። ሔንሪ እንደዘገበው፣ “ከቤተክርስቲያኗ አመራም ምንም ባለመስማቴ፣ በዚህ እንድቆይ ወይም ወደ ፅዮን እንድሄድ ሀሳቡን እና ፍላጎቱን እንዲገልጽልኝ በጸሎት ወደ ጌታ ተጣራሁ።

እንዲህም ቀጠለ፥ “እንደ ጸሎቴ መልስ የሚቀጥለው ህልም ተሰጠኝ። በ[ሶልት ሊክ] ስቲ እንደደረስኩኝ እና ወደ [ፕሬዘደንት ያንግ] ቤሮ በመሄድ፣ በዚያም እንዳገኘኋቸው አለምኩ። እንዲህም አልኳቸው፥ ‘[ፕሬዘደንት] ያንግ፣ ሚስዮኔን ትቼ መጣሁ፣ በራሴ ምርጫም መጣሁ፣ ነገር ግን በዚህ ስህተት ካለው፣ ለመመለስ እና ሚስዮኔን ለመጨረሽ ፈቃደኛ ነኝ።’ [በህልሙ ነቢዩ እንዲህ መለሱ፥ ‘ለበቂ ጊዜ ቆይተሀል፣ ይህም መልካም ነው።”

ሔንሪ በጆርናሉ ላይ እንደዚህ ፃፈ፣ “በሙሉ የተሟሉ ህልሞች ከዚህ በፊት ስለነበሩኝ፣ ይህም እንደሚሆን እምነት ነበረኝ እና በውጤቱም ወዲያው መዘጋጀት ጀመርኩኝ።”

አብዛኛውን መንገድ በእግር በመጓዝ፣ ወደሶልት ሌክ ስቲ በነሀሴ 29፣ 1860 (እ.አ.አ) ደረሰ። በሚቀጥለው ቀን፣ ወደ ብሪገም ያንግ ቢሮ ውስጥ ተራምዶ ገባ።5

ሄንሪ ያጋጠመውን በእነዚህ ቃላት ገልጿቸው ነበር፥ “[ፕሬዘደንት] ያንግን ጎበኘሁ እርሳቸውም በደግነት ተቀበሉኝ። እንዲህም አልኳቸው፣ ‘[ፕሬዘደንት] ያንግ ሳልጠራ መጥቻለሁ፣ ያደረኩት ስህተት ከሆነ፣ ለመመለስ እና ሚስዮኔን ለመፈጸም ፈቃደኛ ነኝ።’ [ብሪገም ያንግም] እንዲህ መለሱ፥ ‘መልካም ነው፣ አንተን እየጠበቅን ነበር።’”

ሔንሪ ደስታውን እንዲህ በማለት ገለጸ፣ “በዚህም ህልሜ ተሟላ።”6

ደስታው የመጣው ጌታ ከእርሱ ጋር ሲሰራ እና እርሱን ሲጠብቀው እንደነበረ በማረጋገጡ ነው። ለሁላችንም እውነት የሆነውን ተማረ፣ የጌታ አገልጋዮች የጌታን ፈቃድ ለማወቅ ይነሳሳሉ። እናም እኔም እንዳደረኩት፣ ሔንሪ አይሪንግ ነቢዩ፣ እንደ ካህናት ፕሬዘደንት፣ የጌታ አገልጋዮችን እንዲጠብቁና እንዲንከባከቡ እንደሚነሳሱ አረጋገጠ።

የክህነት ጥሪአችሁ ምንም ቢሆን፣ የሰማይ አባት ስለእናንተ እንደማያውቅ የተሰማችሁ ጊዜም ይኖራል። ፈቃዱን ለማወቅ፣ እና እርሱ የሚጠይቃችሁን ማንኛውንም ለማድረግ እና በትክክል ለማከናወን ባለ ቅን በሆነ ፍላጎት ለእርሱ ከጸለያችሁ መልስን ትቀበላላችሁ።

የሰማይ አባት እንደሚያውቃችሁ፣ በአገልግሎታችሁ እንደሚያመሰግናችሁ፣ እና “አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ”7 የሚለውን ሰላምታ ለመስማት ብቁ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ ይፈቅድላችኋል።

እያንዳንዱ ካህን ሀላፊነት ያለበትን ነፍስ ለማዳን በእምነት እንዲጥር ጸሎቴ ነው። እግዚአብሔር በጥረታችሁ ላይ ሀይሉን ይጨምራል። በወንጌል መንገድ ወደ ደስታ የሚያመጣቸውን እና ከሀዘን ዞር የሚያደርጋቸው ምርጫዎችን እንዲያደርጉ ልቦች ይነካሉ።

እያንዳንዱ ካህን የሰማይ አባትን፣ የአዳኝን፣ እና የእግዚአብሔር ነቢይን ፍቅር እና ጥበቃ በጥሪያቸው እንዲሰማቸው ጸሎቴም ነው።

በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስገልግሎት ውስጥ እንዳለን እመሰክርላችኋለሁ። ችሎታችንን እና ፍላጎታችንን በማወቅ ወደ አገልግሎቱ እንደተጠራን እመሰክራለሁ። ያለንን በሙሉ በእርሱ አገልግሎት ስንሰጥ፣ ከምንጠብቀው በላይ ጥረታችንን እንደሚባርክ እመሰክራለሁ። የእግዚአብሔር ነቢይ፣ በምድር ላይ ሁሉ የክህነት ፕሬዘዳንት የሆነው፣ በእግዚአብሔር እንደሚነሳሳ እመሰክራለሁ።

በሁሉም ቦታዎች ለሚገኙ ታማኝ የክህነት ተሸካሚ ምሳሌዎች አመስጋኝ ነኝ። የሰማይ አባት እና አዳኝ የድርሻችሁን ስለምትወጡ አመስጋኝ ናቸው። እናንተን ያውቃሉ እናም ያፈቅሯችኋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “Minutes of the Conference,” St. Louis Luminary, Oct. 13, 1855, 187 ተመልከቱ።

  2. Henry Eyring letter to Brigham Young, Oct. 7, 1858, Brigham Young Office Files, Church History Library, Salt Lake City።

  3. Henry Eyring report to Church Historian’s Office, Aug. 1860, Missionary Reports, Church History Library, Salt Lake City።

  4. Henry Eyring letter to Brigham Young, Oct. 9, 1859, Brigham Young Office Files, Church History Library, Salt Lake City ተመልከቱ።

  5. President’s Office Journals, Aug. 31, 1860, vol. D, 137, Brigham Young Office Files, Church History Library, Salt Lake City ተመልከቱ።

  6. Henry Eyring reminiscences, 1896, typescript, 27–28, Church History Library, Salt Lake City።

  7. ማቴዎስ 25፥23