“ከወደዳችሁኝ፣ ትእዛዛቴን ጠብቁ”
የእግዚያብሔር ትእዛዛት እሱ ለእኛ ያለውን ፍቅር መግለጫዎች ናቸው፣ እንዲሁም ለትእዛዛቱ መታዘዝ እኛ ለእርሱ ያለንን ፍቅር መግለጫ ነው፡፡
የመጀመሪያዋ ሴት ልጃችን፣ ጄብ፣ ሶስተኛ የሴት ልጇን ከሆስፒታል ወደቤት ስታመጣ፣ ለመርዳት ወደቤቷ ሄድኩኝ። የመጀመሪያ ሴት ልጇን ወደ ትምህርት ቤት ካደረስን በኋላ፣ ጄን ከሁሉም በላይ የሚያስፈልጋት እረፍት እንደሆነ ወሰንን። ስለዚህ ከሁሉም በላይ እርዳታ የምሰጣት ሴት ልጇ ክሎዊን ወደቤቴ ብወስድ እና እናቷና አዲሷ ህጻን እህቷ ትንሽ የፀጥታ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ ነበር።
ክሎዊን በመኪና መቀመጫዋ ውስጥ በቀበቶ አሰርኳት፣ የራሴን መቀመጫ ቀበቶ አሰርኩኝ፣ እና ከእነርሱ ቤት መኪናውን አየነዳሁ ወጣሁ። ነገር ግን፣ ከሚኖሩበት መንገድ መጨረሻ ላይ ከመድረሳችን በፊት፣ ክሎዊ የመቀመጫ ቀበቶዋን አውልቃ ቆማ፣ ከትከሻዬ በላይ ሆና ታነጋግረኝ ነበር! መኪናውን በመንገዱ ጎን ላይ አቆምኩኝ፣ ወጣሁ፣ እና በመቀመጫዋ በቀበቶ አሰርኳት።
እንደገና ጀመርን ነገር ግን ከአጭር ጊዜ በኋላ ከመቀመጫዋ እንደገና ተነስታ ነበር። እንደገናም እንደዚህ አደረግሁኝ፣ ነገር ግን በዚህ ግዜ ወደመኪናው ገብቼ ከመቀመጤ በፊት ክሎዊ ተነስታ ቆማ ነበር።
ስለዚህ በመኪና ውስጥ በመቀመጥ፣ በመንገዱ ጎን ላይ መኪናውን በማቆም ከሶስት አመት ልጅ ጋር በሀይል መታገል ላይ ነበርኩኝ። እርሷም እያሸነፈችኝ ነበር።
በመኪና መቀመጫዋ ላይ በቀበቶ በመታሰር መቆየቷ በጣም ጥሩ ሀሳብ እንደሆነ ለማሳመን የምችለውን ሁሉ ጣርኩኝ። አላመነችበትም ነበር! በመጨረሻም ይህ ከሆነ/ከዚያም የሚል አቀራረብን ለመሞከር ወሰንኩኝ።
እንዲህ አልኳት፣ “ክሎዊ፣ በመኪና መቀመጫሽ ላይ በመታሰር ከቆየሽ፣ በአያትሽ ቤት ወዲያው ስትደርሺ በፕሌይ ዶው እንጫወታለን።”
ምንም አልመለሰችም።
“ክሎዊ፣በመኪና መቀመጫሽ ላይ በመታሰር ከቆየሽ፣ በአያትሽ ቤት ስንደርስ ዳቦ እንጋግራለን።
ምንም አልመለሰችም።
እንደገና ሞከርኩኝ። “ክሎዊ፣በመኪና መቀመጫሽ ላይ በመታሰር ከቆየሽ፣ ከሱቅ ጣፋጭ ነገሮችን እገዛልሻለሁ!”
ለሶስት ጊዜ ከሞከርኩኝ በኋል፣ የማይሰራ ሙከራ እንደሆነ ተረዳሁ። ወስና ነበር፣ እና ምንም ይህ ከሆነ/ከዚያም የሚል ነገር በመኪና መቀመጫዋ ላይ በመታሰር ለምቆየት የሚያሳምናት አልነበረም።
ቀኑን በሙሉ በመንገድ ጎን ላይ ቆመን ማሳለፍ አንችልም፣ ነገር ግን በህግ ታዛዥ ለመሆን ፈልግሁኝ እናም ክሎዊ ቆማ መኪና መንዳቱ አደገኛ ነበር። በፀጥታ ፀለይኩ እናም “አስተምሪያት” የሚል የመንፈስ ሹክሹክታን ሰማሁ።
እርሷን ለማየት ዞር አልኩኝ እና የመታሰሪያ ቀበቶዬን ከሰውነቴ እንዲርቅ በማድረግ አሳየኋት። እንዲህም አልኩኝ፣ “ክሎዊ፣ ይህን የመቀመጫ ቀበቶ የማስረው እራሴን ለመጠበቅ ነው።ነገር ግን አንቺ ቀበቶውን አላሰርሺም፣ እና ደህና አትሆኚም። አንቺ ብትጎጂ እኔ በጣም አዝናለሁ።”
ተመለከተችኝ፤ አእምሮዋ በመዞር ስታስብበት እመለከት ነበር እና መልሷን ለመስማት በጉጉት ጠበቅኩኝ። በመጨረሻ አይኗ በራ፣ እና እንዲህ አለች፣ “አያቴ፣ መቀመጫ ቀበቶዬን እንዳስር የምትፈልጊው ስለምትወጂኝ ነው!”
ስለፍቅሬ ስገልጽላት መንፈስ መኪናውን ሞላው። ያን ስሜት ለማጣት አልፈልግም፣ ነገር ግን እድል እንዳገኘሁ አወቅኩኝ እና በመኪና መቀመጫዋ እርሷን ለማሰር ወጣሁ። ከዚያም እንዲህ ጠየቅኳት፣ “ክሎዊ፣ እባክሽ በመቀመጫሽ ትቆያለሽ?” ጣፋጭ ለመግዛት ሱቅ እስክንደርስ ድረስ እንዳልኳት አደረገች። ከሶቁ ጀምሮ ቤት እስከምንደርስም ድረስ በመቀመጫዋ ቆየች፣ ክሎዊ ስላልረሳችም በዚያ ዳቦን ጋገርን እናም በፕሌይ ዶው ተጫወተች!
በዚያ ቀን በመንገድ በምነዳበት ጊዜ፣ “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ”1 የሚለቅ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስ አእምሮይን ሞላው። ልጆቻችንን የምናስተምርበት፣ የምንመራበት እና የምንጠብቅበት ህግጋቶች አሉን። ለምን? ምክንያቱም ለእነርሱ ባለን ታላቅ ፍቅር ነው። ነገር ግን በመኪና መቀመጫዋ ላይ ታስራ እንድትቆይ የፈለኩት ስለምወዳት እንደሆነ ክሎዊ እስከምታውቅ ድረስ፣ እንደ ገደብ ነው ብላ ያሰበችውን ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረችም። የመኪና መቀመጫ ቀበቶዋ ነጻነቷን እንደሚገድብ ተሰምቷት ነበራ።
እንደ ክሎዊ፣ ትእዛዛትን እንደ ገደብ ለመመልከት እንችላለን። የእግዚአብሔር ህግ የግል ነጻነታችንን እንደሚገድብ፣ ነጻ ምርጫችንን እንደሚወስድብን፣ እና እድገታችንን እንደሚገድብብን ይሰማን ይሆናል። ነገር ግን ታላቅ መረዳትን ስንሻ፣ አባታችን እንዲያስተምረን ስንፈቅድ፣የእግዚያብሔር ትእዛዛት እሱ ለእኛ ያለውን ፍቅር መግለጫዎች መሆናቸውን፣ እንዲሁም ለእሱ ትእዛዛት መታዘዝ እኛ ለእሱ ያለንን ፍቅር መግለጫ መሆኑን ማየት እንጀምራለን፡፡
እንደ ምሳሌ፣ ራሳችሁን በመንገድ ዳር ላይ ቆማችሁ ካገኛችሁት፣ ምትከተሉዋቸው ከሆነ፣ በመንገዱ ላይ በደህንነት ለመመለስ የሚረዷችሁን ጥቂት መርሆች ሀሳብ ልሰጣችሁ?2
መጀመሪያ፣ እግዚአብሔርን እመኑ። ለእናንተ ባለው ዘለአለማዊ እቅድ እመኑ። እያንዳንዳችን “የሰማይ ወላጆች ተወዳጅ ወንድ እና ሴት ልጆች ነን።” ለእኛ ያላቸው ፍቅር በትእዛዛቶች የሚታዩ ናቸው። “የምድራዊ ልምምዶችን ስናገኝ” ትእዛዛት የሚያስተምሩን፣ የሚመሩን፣ እና የሚጠብቁን አስፈላጊ መመሪያዎች ናቸው።.”3
በቅድመ ህይወት አለም ውስጥ የእግዚአብሔርን እቅድ ለመቀበል ነጻ ምርጫችንን ተጠቀምን፣4 እናም በእርሱ እቅድ ውስጥ ለእኛ ስኬት በእግዚአብሔር ዘለአለማዊ ህግ መታዘዝ አስፈላጊ እንደሆነ ተማርን። “ይህ አለም ከመመስረቱ አስቀድሞ ሁሉም በረከቶች የሚመረኮዙበት በሰማያት ውስጥ ሊሻር የማይችል የታወጀ ህግ አለ።”5 ይህን ህግ ካከበርን፣ በረከቶችን እንቀበላለን።
ከስጋዊ አጋጣሚዎች ጋር ካሉት ከስህተቶች፣ ከተቃርኖዎች፣ ከእድሎች፣ እና ከትምህርቶች ሁሉ ጋር፣ እኛ ብንረሳቸውም፣ እግዚአብሔር ያለንን ዘለአለማዊ እጣ ፈንታ አይረሳም። “ምክንያቱም እግዚአብሔር ልጆቹ እንዲመለሱ ስለሚፈልግ”6 እርሱን ማመን እንችላለን። በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ የኃጢያት ክፍያም መንገድ ሰጥቶናል። የኃጢያት ክፍያ “የደህንነት እቅድ ዋና ክፍል ነው።”7
ቀጥሎም፣ በኢየሱስ ታመኑ። የመታዘዝ እና የፍቅር ዋና መግለጫ የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ ነው። ለአባቱ ፍቃድ እራሱን በመስጠት፣ ለእኛ ሲል ህይወቱን ሰጠ። እንዲህ አለ፣“እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፤ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።”8
ኢየሱስ እንዳስተማረው፥
ጌታ አምላክሀን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።
ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፤ ባልንጀራህን እንደነፍስህ ወደድ።9
በእያንዳንዱ እሁድ ገደብ የሌለውን የኃጢያት ክፍያውን ምልክት በመውሰድ የአዳኛችንን ንጹህ ፍቅር ለማሰላሰል እና ለማስታወስ እድል አለን። በቅዱስ ቁርባን ጊዜ፣ እጆች እና ክንዶች ዳቦን እና ውሀን ለማስተላለፍ ሲዘረጉ እመለከታለሁ። እናም ክንዴን ስዘረጋ እና ስካፈል፣ ሁልጊዜ እርሱን ለማስታወስ ስሙን በራሴ ላይ ለመውሰድ እና ትእዛዛቱን ለማክበር ፈቃደኛ እንደሆንኩም ቃል ኪዳን እገባለሁ። እርሱም “መንፈሱ ሁሌም ከእኛጋ እንዲሆን” ቃል ይገባል።].”10
ሶስተኛዪቱ፣ የመንፈስን ሹክሹክታ ማመን። ከክሎኤ ጋር በነበረኝ ቆይታ ጊዜ መንፈስ የቅዱሳት መፃሀፍት ጥቅስ ሹክ እነዳለኝ ታስታውሳላችሁ? የዮሀንስ ወንጌል 14፡15 ነበር፤ ከወደዳችሁኝ ትዛዛቴን ጠብቁ፡፡ የሚለው ነበር፡፡ እናም እነኝህ ጠቃሚ ጥቅሶች ይከተላሉ፤
“እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
“እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።”11
በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተረጋገጡ እናንዳንዱ አባላት ለመንፈስ ቅዱስ አጋርነት መብት አላቸው። ጾም፣ ጸሎት፣ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት፣ እና ታዛዥነት የመንፈስ መነሳሳትን የመስማት ችሎታችንን በጣም ያሳድጋሉ።
አዕምሮዋችሁ በጥርጣሬ እና ግራ በመጋባት ሲሞላ፣ አብ እና ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስጋዊ ህይወት ጉዞ አደጋዎች ውስጥ በደህና እንድትጓዙ እንዲመራችሁ መንፈስ ቅዱስ ይልኩላችኋል። እንድታስታውሱ ይረዳችኋል፣ ያጽናናችኋል፣ እና “በተስፋ እና ፍፁም ፍቅር” ይሞላችኋል።.”12
አራተኛ፣ በህይወት ያሉ ነቢያትን ምክር እመኑ። የሰማይ አባታችን ቃሉን የምንሰማበት እና ህጉን የምናውቅበት መንገድ በነቢያቱ በኩል አዘጋጅቶልናል። ጌታ እንዳወጀው፣ “ቃሌ…ይፈጸማል፣ በእኔ ድምጽ ሆነ በአገልጋዮቼ ድምጽ፣ አንድ ነው…።”.”13
በቅርቡ፣ በህይወት ያሉ ነቢያት “የሰንበትን ቀን [እንድን]ቀድስ፣”14 እና የጾምን ህግ እንድንጠብቅ መክረውናል። ለዚህ ሐዋርያዊ ምክረ መታዘዝ እምነታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስናሳድግ እና ሌሎችን ለመውደድ እና ለመንከባከብ እጃችንን ስንዘረጋ እርሱን እና ባላገራችንን እንደ እራሳችን ለመውደድ የተሰጠንን የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንድንታዘዝ መንገዱን ያዘጋጃል።15
ጌታ ነብያቱ በኩል ያስተማረውን ቃል በመከተል ውስጥ ደህንነት አለ፡፡ እግዚያብሄር ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ነቢይ እንዲሆኑ እና የቀዳሚ አመራር አማካሪዎችን እና የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ጉባኤ አባላትን እንደ ነቢያትን ባለራዕይ፣ እና ገላጮች እንዲሆኑ ጠርቷቸዋል። ፍራቻ፣ ጥፋት፣ ጠላት፣ እናም ቁጣ እያደገ በመጣበት አለም ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንዴት እንደሆኑ ወደ እነሱ መመልከት እንችላለን ፣ በልግስና፣ በእይታ፣ በድምጽ፣ እና ሊረብሹ ለሚችሉ ነገሮች ምላሽ በመስጠት በመሞላት፡፡ ስለ ክርስቶስ ይመሰክራሉ እናም ምስክር በሆኑት፣ ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር በሆነው፣ በፍቅር ይመልሳሉ፡፡
ከክሎዊ ጋር ከነበረኝ ልምድ በኋላ፣ ትእዛዛት እና ፍቅር የሚለውን ጥቅስ ለማግኝት ቅዱሳት መፅሀፍትን መረመርኩ፡፡ ብዙም አገኘህ፡፡ የእሱ ትእዛዛት እሱ ለእኛ ያለውን ፍቅር መግለጫዎች ናቸው፣ እንዲሁም ለእሱ ትእዛዛት መታዘዝ እኛ ለእሱ ያለንን ፍቅር መግለጫ ነው፡፡
እግዚአብሔር፣ የሰማይ አባታችንን፣ ስናምን፤ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን እና የኃቲያት ክፍያውን ስናምን፤ የመንፈስ ጸጥተኛ ንግግርን ስናምን፤ እና የህያው ነቢያትን ምክር ስናምን፣ ከመንገድ ጫፍ የምንወጣበትን እና፣ በመፅናት ብቻ ሳይሆን፣ በደህንነት፣ ውደቤት በምንሄድበት ደስታን በማግኘት፣ የምንጓዝበትን መንገድ እናገኛለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።