የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መሰረታዊ መርሆች፣ ጥር 2018 (እ.አ.አ)
ከእርሷ ጋር በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ቦታ፣ በማንኛውም መንገድ ተገናኙ
የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተር ስለአገልግሎት ነው። ኢየሱስ በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ቦታ አገልግሏል። እኛም እንዲህ ለማድረግ እንችላለን።
“ማገልገል” ለሌላ ምቾት እና ደስታ የሚጨምር አገልግሎት መስጠት፣ መንከባከብ፣ ወይም እርዳታ መስጠት ነው። የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተር፣ የምንጎበኛቸውን የምናገለግልበት መንገዶች ስለማግኘት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም አገልግሏል—በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ቦታ። አምስት ሺህ መግቧል፣ ማርያምን እና ማርታን በወንድሟቸው ሞት ጊዜ አፅናንቷል፣ እናም ወንጌሉን በውሀ ጉድጓድ አጠገብ ለሴቷ አስተምሯል። ይህን ያደረገው በልባዊ ፍቅሩ ምክንያት ነው።
የእርሱን ምሳሌ በመከተል፣ እንደ የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪዎች፣ ፍቅር ለምናደርጋቸው ሁሉ መሰረት እንደሆነ በማስታወት፣ የምንጎበኛቸውን እያንዳንዷን ሴቶች ለማወቅና ለማፍቀር እንችላለን። እርሷን ለማገልገል እና እምነቷን ለማጠናከር እንዴት መርዳት እንደምንችል ለማወቅ መነሳሻ ለማግኘት ስንጸልይ፣ “መላእክት የእኛ ተገናኚዎች ከመሆን አይገደቡም።”1
በ1842 (እ.አ.አ) የሴቶች መረዳጃ ማህበር ከተደራጀበት እስከ አሁን ድረስ፣ ሴቶችን ማገልገል ህይወቶችን ባርኳል። ለምሳሌ፣ የ82 አመት መበለት፣ ጆአን ጆንሰን፣ እና የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪ ጓደኛቸው 89 አመት የሆናቸውንና የሳምባ በሽታ ያለቸውን ጎሬቤታቸውን ይጎበኙ ነበር። ጎረቤታቸው በወር አንዴ ብቻ ይፈልጓቸው እንዳልነበር ተመለከቱ፣ ስለዚህ በየቀኑ በግል ወይም በስልክ ይጠይቋቸው ጀመሩ።
ለሌሎች የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪዎች፣ ማበረቻቻ የሚሰጥ የስልክ መልእክት ወይም ኢሜል መላክ ለእህት በዚያ ወር ከሁሉም በላይ የሚሻል ነገር ሊሆን ይችላል። የግል ግንኙነት ማድረግ እና በፍቅር ጸባይ ማድመጥ የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ትምህርት ዋና ክፍል ነው። የዚህ ዘመን ቴክኖሎጂ እና በዘመን የሚከበረው የፊት ለፊት ጉብኝት ይህን በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ቦታ፣ እና በብዙ መንገዶች ለማከናወን ይረዳናል።2 ይም ኢየሱስ እንደሚያገለግለው ማድረግ ነው።
© 2018 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቶች ሁሉ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ. ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/17 (እ.አ.አ)። Visiting Teaching Principles, February 2017. (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic 15045 506