2018 (እ.አ.አ)
ንስሀ ለመግባት ጥብቅ ውሳኔ
ጥር 2018 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

ንስሀ ለመግባት ጥብቅ ውሳኔ

ፕሬዘደንት ሞንሰን እንደገለጹት፣ “ሀላፊነታችን በመለስተኛ አቋም ላይ ያሉትን ወደ ብቁነት፣ ከውድቀት ወደ ውጤተኛነት ከፍ ለማድረግ ነው። ስራችንም እኛ ከምንችለው በላይ የተሻልን ለመሆን ነው።” ብዙ ሰዎች ጥርን እቅዶችን እና የመሻሻል ውሳኔዎችን ለማድረግ፣ በተጨማሪ ፈገግ ለማለት፣ ጤንነት የሚያመጣ ምግብን ለመመገብ፣ ወይም አዲስ ችሎታን ለመማር ይመርጣሉ። እነዚህ እቅዶች ወደተሻለ ወደመሆን እንድንቀየር ሊረዱን ቢችሉም፣ ለመቀየር ከሁሉም በላይ የሚሻለው ንስሀ በመግባት ነው።

ንስሀ መግባት ከባድ ቢሆንም፣ ይህም ስጦታ ነው! ለኃጢያቶቻችን ንስሀ በመግባት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስንመካ፣ ለማደግ እና ለመሻሻል እንችላለን። ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዳሉት፣ “ለ[ደህንነት] እቅድ ወሳኝ ክፍል የሆነው አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ያለ እርሱ የኃጢያት ክፍያ፣ ሁሉም ነገር ጠፊ ነበር።” ንስሀ በመግባት በኩል፣ ከኃጢያታችሁ ንጹህ ለመሆን ለመታጠብ እና በተጨማሪ እንደ እርሱ ለመሆን ለመሻሻል ትችላላችሁ።

እንደ አዳኝ ለመሆን የሚያግዳችሁ ነገሮችን አስቡበት። ቋንቋችሁን ነውን? ጓደኞቻችሁን ወይም ቤተሰባችሁን አያያዝስ? ለመሻሻል የምትችሉትን ካሰባችሁበት በኋላ፣ ለሰማይ አባት ጸልዩ እናም ለመቀየር ያላችሁን ፍላጎት ግለጹ። በኃጢያት ክፍያው ሃይል በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ ድካማችሁን ለማሸነፍ ሊረዳችሁ እንደሚችል አስታውሱ። ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዳስተማሩት፣ “በአዳኛችን የተሰጠው የንስሀ ስጦታ መንገዳችንን እንድናስተካከል ያስችለናል።”