2018 (እ.አ.አ)
ንስሀ ስጦታ ነው
ጥር 2018 (እ.አ.አ)


ልጆች

ንስሀ ስጦታ ነው

የንስሀ ስጦታ ለማየት ወይም ለመንካት የምትችሉት ስጦታ አይደለም። በምትክ፣ ይህም የሚሰማችሁ ስጦታ ነው። ይህም ማለት ትክክለኛ ያልሆነ ምርጫ ስናደርግ፣ ንስሀ ለመግባት እና ሰላምና ደስታ እንደገና ይሰማን ዘንድ እንችላለን።

የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ንስሀ ለመግባት ሁልጊዜም ይረዱናል። ከእያንዳንዱ የንስሀ ደረጃዎች ጋር አብረው የሚሆኑ ስዕሎችን ሳሉ።

ጸጸት ይሰማናል።

ወደ ሰማይ አባት እንጸልያለን፣ ምን እንደነበረ እንነግረዋለን፣ እናም በሚቀጥለው ጊዜ የተሻለ ምርጫ ለማድረግ እንዲረዳን እንጠይቀዋለን።

ይቅርታ እንጠይቃለን እናም ለማሻሻል እንጥራለን።

ሰላም ይሰማናል እናም ምህረት እንደተሰጠን እናውቃለን።