በረከቶችን አስቡባቸው
የሰማይ አባታችን ምን እንደምንፈልግ ያውቃል እናም እርሱን ስንጠራ እርዳታ ይሰጠናል።
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በጥቅምት 4፣ 1963 (እ.ኤ.አ) እንደ አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል አንዱ የመሆን ድጋፍ ከተሰጠኝ ይህ ጉባኤ 49ኛው አመት ነው። አርባ ዘጠኝ አመት ረጅም ጊዜ ነው። በብዙ መንገዶች ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በአጠቃላይ ጉባኤ ተነስቼ የመጀመሪያ ንግግርን የሰጠሁበት ግን ብዙ ጊዜ ያለፈበት አይመስልም።
ከጥቅምት 4፣ 1963 (እ.ኤ.አ) በኋላ ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል። በአለም ታሪክ ውስጥ ልዩ በሆነ ጊዜ ነው የምንኖረው። በብዛት ተባርከናል። ግን በአካባቢያችን ያለውን ችግሮችና ኃጢያትን ለመቀበል ፈቃደኝነት ያለውን በመመልከት ተስፋ ላለመቁረጥ ያስቸግራል። በመጥፎው ላይ በማተኮር ሳይሆን በህይወታችን ያለውን በረከቶች ብንመለከት ታላቅ ደስታ እናገኛለን።
ያለፉትን 49 አመታት ሳስብባቸው፣ አንዳንድ ነገሮችን አግኝቻለሁ። ከእነዚያም አንዱ ከቁጥር በላይ የሆኑ አጋጣሚዎች የነበሩኝ ከሁሉም በላይ የሚደንቁ አልነበሩም።በእርግጥም፣ በሚደርሱበት ጊዜ በአብዛኛው ጊዜ የማያስደንቁና ተራ የሆኑ ይመስሉ ነበር። ነገር ግን በኋላ ሳስብባቸው፣ የእኔን ብቻ ሳይሆን፣ ህይወቶችን አበልፅገዋል እናም ባርከዋል። እናንተም ስለህይወታችሁ በጥንቃቄ እንድታስቡባቸው እና ትልቅም ይሁኑ ትንሽ ለተቀበላችኋቸው በረከቶች እንድትመለከቱ አበረታታችኋለሁ።
ባለፉት አመታት የነበሩትን ሳስብባቸው፣ ጸሎታችን እንደሚሰሙና መልስ እንደሚያገኙ ያለኝን እውቀት አጠናክረውልኛል። በመፅሐፈ ሞርሞን በ2ኛ ኔፊ ውስጥ “ሰዎች የሚኖሩትም ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው”1 የሚል እውነት እንዳለ እናውቃለን። አብዛኛው ያ ደስታ የሚመጣው ከሰማይ አባታችን ጋር በጸሎት ለመነጋገር እና እነዚያም ጸሎቶች እንደሚሰሙና መልስ እንደሚያገኙ በማወቅ ነው፣ ምናልባት ይመለሳሉ ብለን በማናስበብት ሁኔታ ቢመጡም፣ በፍጹምነት በሚያፈቅረንና በሚያውቀን እና ደስታችንን በሚፈልግ የሰማይ አባት ይመለሳሉ። እርሱም “ትሁት ሁን፤ እና ጌታ አምላክህ እጅህን ይዞ ይመራሀል፣ እና ለጸሎቶችህም መልስ ይሰጥሀል”2 ብሎ ቃል ገብቶልናል።
ለተሰጠኝ ለሚቀጥሉት ትንሽ ደቂቃዎች፣ ጸሎቶች ተሰምተው፣ በኋላም ሲታሰብበት ለህይወቴ እና ለሌሎች በረከቶች ያመጡ መልሶች እንዴት እንደተሰጡ የነበሩኝን አጋጣሚዎች ለመካፈል እፈልጋለሁ። በየቀኑ የምጽፋቸው ማስታወሻዎች በሌላ መንገድ ለማስታወስ የማልችላቸውን ነገሮች እንዳስታውስ ረድቶኛል።
በ1965 (እ.ኤ.አ) የካስማ ጉባኤን እንድሳተፍበትና በደቡብ ፓስፊክ አካባቢ ስብሰባዎችን እንድሳተፍባቸው ተመድቤ ነበር። ይህን አካባቢ የጎበኘሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር፣ እናም ይህም የማይረሳ ጊዜ ነበር። አብዛኛው አጋጣሚዎች ከመሪዎች፣ ከአባላት፣ እና ከወንጌል ሰባኪዎች ጋር ስገናኝ የነበሩኝ መንፈሳዊ ነገሮች ነበር።
በየካቲት 20ና 21 ቅዳሜና እሁድ፣ በብረዝብን ካስማ ጉባኤ ለመሳተፍ በብረዝብን አውስትሬሊያ ነበርን። በቅዳሜው ስብሰባ፣ በሚቀጥለው አካባቢ የነበረ ዲስትሪክት ፕሬዘደንት ጋር ሰዎች አስተዋወቁኝ። ከእርሱ ጋር ስንጨባበጥ፣ ከእርሱ ጋር መነጋገርና እርሱንም መምከር እንደሚያስፈልገኝ ስሜት ተሰማኝ፣ ስለዚህ ይህን ለማከናወን በሚቀጥለው ቀን ለእሁድ ስብሰባ ከእኔ ጋር እንዲመጣ ጠየቅሁት።
ከእሁድ ስብሰባ በኋላ፣ ለመነጋገር እድል ነበረን።፡እንደ ዲስትሪክት ፕሬዘደንት ስላለው ብዙ ሀላፊነቶች ተነጋገርን። ይህን ስናደርግ፣ ስለወንጌል መስበኪያ ስራ እና የሙሉ ጊዜ ወንጌል ሰባኪዎች በአካባቢው ሲያገለግሉ እርሱና አባላቱ እንዴት ለመርዳት እንደሚችሉ ልዩ የሆነ ሀሳቦች እንዳቀርብለት ተሰማኝ። በኋላም ስለዚህ ጉዳይ ያ ሰው እየጸለየ እንደነበረ አወቅሁኝ። ለእርሱም፣ ያ ንግግራችን ጸሎቱ እንደተሰሙና መልስ እንደተሰጣቸው የሚያውቅበት ልዩ ምስክር ነበር። ይህ አስደናቂ ያልሆነ ግንኙነት ነበር ግን ይህም በመንፈስ የተመራና በእዚያ ዲስትሪክት ፕሬዘደንት ህይወትና አመራር፣ በአባላቱ ህይወቶች ውስጥ፣ እና በዚያ ለነበሩት ወንጌል ሰባኪዎች ውጤታማነት ለውጥ ያመጣ ነበር።
ወንድሞቼና እህቶቼ፣ የጌታ አላማ የሚከናወነው እኛ የመንፈስን አመራር ስናዳምጥ ነው። በምንነሳሳበትና በሚሰማን ስንሰራ፣ ጌታ ተጨማሪ ስራዎቹን እንድናከናውን እምነቱን ይሰጠናል።
ባለፈው መልእክቶች እንደጠቀስኳቸው የመንፈስ መነሳሻን ለኋላ አታስቀምጡ። ከብዙ አመቶች በፊት አንድ ቀን እየዋኘሁ እያለሁ፣ በካንሰር እና በቀዶ ጥገና ምክንያት እግሮቹን መጠቀም የማይችለውን ጥሩ ጓደኛዬን በዩንቨርስቲ ሆስፒታል ሄጄ እንድጎበኝ መነሳሻ ተሰማኝ።ወዲያም ከመዋኛው ወጣሁ፣ ለበስኩኝ፣ እናም እርሱን ለመጎብኘት ወዲያው ሄድኩኝ።
በክፍሉ ስገባ፣ ማንም በክፍሉ እንደሌለ አየሁ። ስጠይቅም ለመንቀሳቀስ በሚሄድበው በሆስፒታሉ መዋኛ ቦታ ይገኝ እንደሚሆን ሰማሁ። ይህም ነበር። እራሱን በሜቀመጥበት ጋሪ ገፍቶ በክፍሉ የነበረ ብጨኛ ተጠቃሚ ነበር። በመዋኛው ቦታም በሚርቀ ክፍል ነበር። ሰላም አልኩት እና እርሱም ወደ እኔ መጣ። በደንብ ተነጋገርን፣ እናም ወደ ሆስፒታል ክፍሉ ሄደን በረከት ሰጠሁት።
በኋላም ጓደኛዬ በዚያ ቀን ተስፋ ቆርጦ ህይወቱን ለመውሰድ ያስብበት እንደነበረ አወቅሁኝ። ማረፊያ እንዲሰጠው ጸልዮ ነበር ግን ጸሎቶቹ መልስ የማያገኙ መስሎት ነበር። የሜቀመጥበትን ጋሪ ወደ ውሀው ጥልቅ ቦታ በመውሰድ ችግሩን የሚያፈጽምበት መንገድ እንደሆነ አስቦበት ነበር ወደ መዋኛ ቦታው የገባው። እዚያም የደረስኩት ከሰማይ የመጣ መነሳሻ ለሆነው በማውቀው መልስ በመስጠት አስፈላጊ በሆነው ጊዜ ነበር የደረስኩት።
ጓደኛዬ ለብዙ አመቶች ለመኖር ቻለ፣ እነዚህም በደስታና በምስጋና የተሞሉ አመቶች ነበሩ። በዚያ አስፈላጊ ቀን በመዋኛ ቦታ ላይ በጌታ እጅ መሳሪያ ለመሆን በመቻሌ ደስተኛ ነኝ።
አንድ ጊዜ፣ ጓደኞችን ከጎበኘን በኋላ እህት ሞንሰን እና እኔ ወደቤት እየነዳን እያለን፣ አንድ ጊዜ በዎርዳችን ይኖሩ የነበሩትን ባለቤታቸው የሞቱባቸውን ሴት ለመጎብኘት ስሜት መጣብኝ።ስማቸው ዜላ ቶማስ ነበር። እንክብካቤ በሚያገኙበት ቦታ ነበር የሚኖሩት። በዚያ ቀን በጣም ቢደክሙም በመኝታቸው ላይ በሰላም አርፈው ነበር።
ዜላ አይነ ስውር ነበሩ፣ ነገር ግን ድምጻችንን መዲያው አወቁት። ጌታ ወደ ቤት ለመመለስ የሚፈልጋቸው ከሆነ ለመሞት እንደተዘጋጁ በመናገር፣ በረከት እንድሰጣቸው ጠየቁኝ። በክፍሉም አስደሳችና ሰላም የሆነ መንፈስ ነበር፣ እናም ሁላችንም በስጋ የነበራቸው ጊዜ አጭር እንደነበረ አወቅን። ዜላ እጄን ያዙ እና እኔ እንድመጣና በረከት እንድሰጣቸው በሀይል ይጸልዩ እንደነበሩ ነገሩኝ። ከሰማይ አባት በተሰጠን ቀጥተኛ ምሪት ምክንያት እንደመጣን ነገርኳቸው። ምናልባት ወደፊት በህይወት እንደገና ላላያቸው እንደማይሆን በማወቅ፣ ራሳቸውን ሳምኩኝ። ይህም እውነት ሆነ፣ ምክንያቱም በሚቀጠለው ቀን ሞቱ። ወደ ተወዳጇ ዜላ መፅናኛና ሰላም ለመስጠት መቻሌ ለእርሳቸው እና ለእኔ በረከት ነበር።
የሌላን ሰው ህይወት ለመባረክ ያለው እድል በማይጠበቅበት ጊዜ ነው የሚመጣው። በ1943–84 (እ.ኤ.አ) አንድ በጣም ብርድ በሆነ የቅዳሜ ምሽት፣ ሚድዌይ በሚባለው በዩታ ከተማ ወዳለን ቤት እህት ሞንሰን እና እኔ እየነዳን ነበር። በዚያ ጊዜ መጠነሙቀቱ ከዜሮ በታች 31 ድግሪ ሴልሲየስ ነበር፣ እናም በቤታችን ሁሉም መልካም እንደሆነ ለማወቅ ፈልገን ነበር። ሁሉንም ተመለከትን እና መልካም እንደሆነ ካየን በኋላ ወደ ሶልት ሌክ ለመመለስ መሄድ ጀመርን። በመንገዱ ለትንሽ ጊዜ ከተጓዝን በኋላ መኪናው መስራት አቆመ። በዚያ ምሽት እንደበረደኝ ከዚህ በፊት በርዶኝ አያውቅም ነበር።
ወደሚቀጥለው ከተማ መኪናዎች በፍጥነት ያለፉን በእግር መሄድ ጀመርን። በመጨረሻም አንድ መኪና ቆመልንና አንድ ወጣት እርዳታን አቀረበልን። በብርዱ ምክንያት በመኪናችን ውስጥ የነበረው ጋዝ ወፍሮ ነበር። በምድዌይ ወዳለው ቤታችን ሰውየው ነድቶ ወሰደን። ለሰጠን እርዳታ ልከፍለው ብሞክርም እምቢ አለኝ። እርሱ የቦይ ስካውት እንደሆነና ጥሩ ነገር ለማድረግ እንደፈለገ ነገረን። ማን እንደሆንኩኝ ነገርኩት እናም እርሱም እርዳታ ለመስጠት እድል ስላገኘ ምስጋናውን አቀረበ። ወደ ወንጌል ለማገልገል የሚሄድበት እድሜ ላይ የደረሰ ስለመሰለኝ፣ በወንጌል ሰባኪነት ለማገልገል አላማ እንዳለው ጠየቅሁት። ምን ማድረግ እንደሚፈልግ ለማወቅ እርግጠኛ እንዳልሆነ ነገረን።
በሚቀጥለው ሰኞ ጠዋት ለዚህ ወጣት ሰው ደብዳቤ ጻፍኩለትና ለደግነቱ አመሰገንኩት። በሙሉ ጊዜ በወንጌል ሰባኪነት እንዲያገለግል አበረታታሁት። ከጻፍኳቸው አንዱን መጽሀፍ አስገባሁና ስለወንጌል ሰባኪነት የሚናገረውን ምዕራፎች አሰመርኩባቸው።
ከሳምንት በኋላ እናቱ ደወለችልኝና ልጇ ጥሩ ልጅ እንደሆነ ግን በጓደኞቹ ምክንያት በወንጌል ሰባኪነት የማገልገል ፍላጎቱ እየቀነሰ እንደመጣ ነገረችኝ። እርሷና አባቱ ልቡ እንዲቀየር ሲጸልዩ እንደነበረ አመለከተች። ስሙንም በፕሮቮ ቤተመቅደስ የጸሎት ዝርዝር ውስጥ አስገብተውም ነበር። በአንድ መንገድ ልቡ በመልካም እንዲነካና የሙሉ ጊዜ ወንጌል ሰባኪ ለመሆንና ጌታን በታማኝነት ለማገልገል ያለው ፍላጎት እንዲመለስለት ተስፋ ነበራቸው። በዚያ ብርድ ጠዋት የደረሰውን ነገር ለእርሱ የጸለዩበትን መልስ እንደተሰጠ እንደምትመለከተውም ነገረችኝ።
ከብዙ ወሮች እና ከወጣቱ ጋር ለብዙ ጊዜ ከተነጋገርን በኋላ፣ እህት ሞንሰንና እኔ ወደ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ቫንኩበር የወንጌል መስበኪያ ቦታ ከመሄዱ በፊት ለነበረው የወንጌል ሰባኪ ንግግር ላይ ለመገኘት በመቻላችን በጣም ተደስተን ነበር።
በዚያ በታህሳስ ምሽት መንገዳችን የተተላለፈበት ምክንያት በእድል ነውን? እንዲህ እንደሆነ አላምንም። የተገናኘነው አባትና እናት ከልብ ለሚወዱት ልጅ ለጸለዩት መልስ እንደሆነ አምናለሁ።
እንደገናው፣ ወንድሞቼናእህቶቼ፣ የሰማይ አባታችን ምን እንደምንፈልግ ያውቃል እናም እርሱን ስንጠራ እርዳታ ይሰጠናል። የሚያሳስቡን ነገሮች በጣምም ትንሽ ናቸው ብዬ አላምንም። ጌታ በህይወታችን ድርጊቶች በሙሉ የሚያስብ ነው።
በብዙ መቶዎች የሆኑትን ስለነካው በቅርብ ስለነበረኝ አጋጣሚ በመናገር ንግግሬን ለመፈጸም እሞክራለሁ። የነበረውም ከአምስት ወር በፊት በካንሳስ ከተማ ቤተመቅደስ ባህል ማክበሪያ ቀን ነበር። በህይወታችን እንደሚደርሱት ሌሎች ነገሮች አይነት፣ ይህም ሁሉም ነገር መልካም የሆነበት ሌላ አጋጣሚ መስሎ ነበር። ነገር ግን፣ ቤተመቅደሱ ከመባረኩ በፊት ከነበረው የባህል ማክበሪያ ድርጊቶች ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደነበረው ሳውቅ፣ የዚያ ምሽት ድርጊት ልዩ እንደሆነ ገባኝ። በጣም የሚያስደንቅም ነበር።
ቤተመቅደስን ከመቀደስ ጋር በባህል ማክበሪያ ሁሉ እንደሚደረገው፣ የካንሳስ ከተማ ምዙሪ የቤተመቅደስ አውራጃ ወጣቶች በተለያዩ ቦታ የእራሳቸውን ክፍል ተለማምደው ነበር። ሀሳባቸውም የባህል ማክበር በነበረበት በዚያ ቅዳሜ ጠዋት ተገናኝተው ምን ማድረግ፣ የት መቆም፣ በመካከላቸው ስንት ቦታ መኖር እንዳለበት፣ ከአዳራሹ እንዴት መውጣት እንደሚገባቸውና ሌሎችን በመለማመድ በዚህ ሀላፊነት ያላቸው የተለያዩ ድርጊቶችን አቀናጅተው የመጨረሻው ድርጊት በደንብ የተዘጋጀ እንዲሆን ከማድረግ እንዲቻላቸው ነበር።
በዚያ ቀን አንድ ብቻ ችግር ነበር። የሚደረገው በሙሉ በትልቅ ቲቭ እንዲታይ የተቀረጸ ነገር ላይ የሚመካ ነበር። እነዚህ የተቀረሱ ነገሮች ለማክበሪያው ድርጊት በጣም አስፈላጊ ነበሩ። ይህም ሁሉንም ነገሮች አንድ ላይ የሚያገናኝ ብቻ ሳይሆን፣ በቴሌቪዥን የሚታዩት ነገሮች ቀጥለው የሚመጡትን ድርጊቶች ያስተዋውቅ ነበር። በቪድዮ የሚታዩት የማክበር ድርጊቶች በሙሉ የሚመኩበት ነበር። ነገር ግን ትልቁ ቴሌቪዥን አይሰራም ነበር።
ወጣቶቹ የሚለማመዱባቸውን ጊዜ እያጡ፣ ሙያተኛ ሰዎች ለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት በጣም ሞከሩ። ሁኔታው የሚቻል ያልሆነ መምሰል ጀመረ።
ጸሀፊና መሪ የነበረቸው ሱዛን ኩፐር ስንዲህ ገለጸች፣ “አላማችንን ስንቀያይር፣ የማይሰራ እንደሆነ አውቀን ነበር።… መርሀ ግብሩን ስንመለከት፣ ከምንችለው በላይ እንደሆነ አወቅን፣ ነገር ግን ከበታች ከሁሉም በላይ ጥንካሬአችን የሆነ ነገር እንዳለ አወቅን፣ ይህም 3 ሺህ ወጣቶች ነበሩ። ወደታች ወርደን ምን እንደደረሰ እነርሱን መንገርና እምነታቸውን መሳብ አስፈለገን።” 3
ወደ መሰብሰቢያው ሰዎች ለመምጣት ከመጀመራቸው ከአንድ ሰዓት በፊት፣ 3 ሺህ ወጣቶች ተንበርክከው አብረው ጸለዩ። በትልቁ ቲቪ ላይ የሚሰሩት ይህን ለመጠገን ምን ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲያውቁ መነሳሻ እንዲኖራቸው ጸለዩ፤ አጭር መለማመጃ ጊዜ ስለነበራቸው፣ የሰማይ አባታቸውንም እነርሱ እራሳቸው ለማድረግ የማይችሉትን እንዲያድርግላቸው ጠየቁ።
ስለዚህ ድርጊት የጻፈ አንድ ሰውም እንዲህ አል፣ “ወጣቶቹ ሊረሱት የማይችሉት ጸሎት ነበር፣ ይህም መሬቱ ጠንካራ ስለሆነ ሳይሆን መንፈስ በጣም ተሰምቷቸው ስለነበር ነውና።”4
ችግሩ ምን እንደሆነ እንደታወቀ እንደተጠገነ አንዱ ሞያተኛ መጥቶ የነገራቸው ከብዙ ጊዜ በኋላም አልነበረም። መፍትሄው የተገኘው “በእድል” ነበር አለ፣ ነገር ግን እነዚያ ወጣቶች በሙሉ ምን እንደነበር ያውቁ ነበር።
በአዳራሹ ውስጥ ስንገባ፣ የቀኑ ችግር ምን እንደነበር አላወቅንም ነበር። ያወቅነውም በኋላ ነበር። የተመሰከርነው ግን ካየኋቸው ሁሉ በላይ መልካም የነበረ በደንብ የተዘጋጀ ድርጊት ነበር። ወጣቶችም በዚያ የነበሩት ሁሉ የተሰማቸው አስገራሚና ሀይለኛ መንፈስ ነበራቸው። የት መግባት እንደነበረባቸው፣ የት መቆም፣ እና ከሌሎች ጋር እንዴት መስራት እንደሚገባቸው አውቀው ነበር። የተለማመዱበት ጊዜ አጭር እንደነበረ እና አብዛኛዎቹ የቀረቡት ድርጊቱን የተለማመዱ እንዳልነበሩ ሳውቅ፣ በጣም ተደንቄ ነበር። ይህን ማንም ሊያውቀው የማይችል ነበር። ጌታም እነርሱ ለማድረግ ያልቻሉትን አድርጓልና።
ጌታ መንግስቱን በሙሉ ለማነሳሳትና ለመምራት እየቻለ፣ ስለአንድ ሰው፣ ወይም አንድ የባህል መከበሪያን ወይም አንድ ትልቅ ቲቪን፣ በተመለከተ ምሪት ስለሚሰጥበት መገረሜን አላቆምም። ይህን ማድረግ መቻሉ ለእኔ ምስክርነት ነው።
ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ጌታ በህይወታችን በሙሉ ውስጥ አለ። ያፈቅረናል። ሊባርከን ይፈልጋል። የእርሱን እርዳታ እንድንፈልግ ይፈልጋል። እርሱም ይመራናል፣ እናም ጸሎታችንን ሲሰማና መልስ ሲሰጥ፣ እርሱ በዚህና አሁን የሚፈልግልንን ደስታ እናገኛለን። በህይወታችን ውስጥ የሚገኙትን በረከቶች እንድናውቅ የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።