2010–2019 (እ.አ.አ)
ስለጸጸቶች እና ውሳኔዎች
ኦክተውበር 2012


ስለጸጸቶች እና ውሳኔዎች

እራሳችንን ቅድስናን እና ደስታን በመፈለግ መለኮታዊ ስንሆን፣ በጸጸት መንገድ ላይ የመሆናችን ሁኔታ ይቀንሳል።

ስለጸጸት

ፕሬዘደንት ሞንሰን፣ እንወድዎታለን። አዲሶችን ቤተመቅደሶች ስለመገነባት እና ስለወንጌል ሰባኪነት አገልግሎት ስላደረጉት በመንፈስ የተመራና ታሪካዊ ማስታወቂያ እናመሰግንዎታለን። በእነዚህም ምክንያት፣ ታላቅ በረከቶችን ወደ እኛና ወደፊት ትውልዶች እንደሚመጡልን እርግጠኛ ነኝ።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ውድ ጓደኞቼ! ሁላችንም ሟች ነን። ይህ እንደማያስደነግጣችሁ ተስፋ አለኝ።

ማንኛችንም በምድር ላይ ለብዙ ጊዜ አንቆይም። በዘለአለማዊ አስተያየት አይንን ከመጨፈን በሚፈጥን አይነት ያጠረ ውድ የአመታት ቁጥሮች አሉን።

ከዚያም ከዚህ እንሄዳለን። መንፈሳችን “ህይወትን ወደ ሰጣቸው ወደ እግዚአብሔር” ይመለሳሉ።” 1 ወደ ሚቀጥለው አለም ስንሄድም ሰውነታችንን እና የዚህ አለም ነገሮችን ትተን እንሄዳለን።

በወጣትነታችን፣ ለዘለአለም የምንኖር ይመስለን ነበር። ከአድማስ አልፎ ያለ መጠን የሌለው የጸሀይ መውጣት አለ ብለን እናስብ ነበር፣ እናም ወደፊት ያለው ለዘለአለም ሳይሰበር የተዘረጋ መንገድ ይመስለን ነበር።

ነገር ግን፣ በእድሜ ስንገፋ፣ ወደኋላ እንመለከታለን እናም ያም መንገድ እንዲት አጭር እንደነበር እንገረማለን። አመታት እንዴት በፍጥነት እንዳለፉም እንደነቃለን። እናም ስለመረጥናቸውና ስላደረግናቸው ነገሮችም ማሰብ እንጀምራለን። በዚህም፣ ለነፍሳችን እርካታ እና ለልባችን ደስታ የሚሰጡ አስደሳች ነገሮችን እናስታውሳለን። ነገር ግን ደግሞም የምንጸጸትባቸውንም፣ እንዲሁም ተመልሰን ለመቀየር የምንመኛቸውን ነገሮች፣ እናስታውሳለን።

ለመዳን የማይችልን በሽተኛ ሰው የምትንከባከብ አንድ ነርስ በሽተኛዎቹ ከዚህ ህይወት ለማለፍ በሚዘጋጁበት ጊዜ የምትጠይቃቸው ቀላል ጥያቂ አለ ብላለች።

“ማንኛውም የምትጸጸቱበት ነገር አለ?” ብላ ትጠይቃለች። 2

ወደ ህይወት መጨረሻ ጊዜ መቅረብ በአብዣኛው ጊዜ ለሀሳብ ግልጽነት ያመጣል እናም ጥልቅ አስተያየት እና የነገሮች ትክክለኛ ገጽታ ይሰጣል። እነዚህ ሰዎች ስለሚጸጸቱት ሲጠየቁ፣ ልባቸውን ይከፍታሉ። ሰአትን ወደኋላ ለመመለስ ቢችሉ ምን እንደሚቀይሩም ያስቡበታል።

ያሉትን ሳስብ፣ በህይወት ከተጠቀምንባቸው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ መርሆች የህይወት መመሪዎቻችንን እንዴት እንደሚነኩ በማወቅ ያስደንቁኛል።

ስለወንጌል መሰረታዊ መርሆች ሚስጥራዊ የሆነ ምንም ነገር የለም። በቅዱሳት መጻህፍት አጥንተናቸዋል፣ በሰንበት ትምህርትም ተወያይተናቸዋል፣ እናም ለብዙ ጊዜ ከመስበኪያም ስለእነርሱ ሰምተናል። እነዚህ መለኮታዊ የሆኑ መሰረታዊ መርሆች ያልተጣመሙና ግልጽ ናቸው፤ የሚያምሩ፣ በጣም ጥልቅ፣ እና ሀይለኛ ናቸው፤ እናም ወደፊት የሚኖረንን ጸጸት ለማስወገድ ይረዳናል።

ከማፈቅራቸው ሰዎች ጋር ተጨማሪ ጊዜ ባሳልፍ ኖሮ

ምናልባት ወደሞት የቀረቡ በሽተኛዎች ከሚጸጸቱባቸው ነገሮች መካከል ዋናው ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ብዙ ጊዜ አለማሳለፋቸው ነው።

ወንዶች በአብዛኛው ይህን ለቅሶ ይዘምራሉ፥ “አብዛኛውን ህይወታቸውን በስራ በማሳለፋቸው በጥልቅ ይጸጸታሉ።” 3 ብዙዎች ከቤተሰብና ከጓደኞች ጋር አብሮ የሚያሳልፉት ምርጥ ጊዜዎች አምልጠዋቸዋል። ለእነርሱ ታላቅ ትርጉም ካላቸው ጋር ለማሳደግ የሚችሉትን ጥልቅ ግንኙነት አጥተዋል።

በብዙ ጊዜ በስራ በጣም አንጠመድምን? እናም ለማለት በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በስራ መጠመድን እንደ ክንውን ወይም ታላቅ የህይወት ምልክት እንደሆነ በማሰብ በስራ መጠመዳችንን እንደ ክብር ማዕረግ እንለብሰዋለን።

ይህ ነውን?

ጌታችንን እና ምሳሌአችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እና እርሱ በጋለሊና በኢየሩሳሌም ህዝቦች መካከል የነበረውን አጭር ህይወት አስባለሁ። በስብሰባዎች መካከል ወይም የተዘረዘሩ በፍጥነት መከናወን ያለባቸውን ነገሮች ለማከናወን ብዙ ስራዎችን እየሰራ በአዕምሮዬ አይን ለማይት እሞክራለሁ።

ይህን ለማየት አልችልም።

በዚህ ምትክ ርህራሄ ያለው እና የሚያስብ የእግዚአብሔር ልጅ አላማ ያለው ህይወትን በየቀኑ ሲኖርበት አያለሁ። በአካባቢው ካሉት ጋር ሲሰራም፣ እነርሱም አስፈላጊ እንደሆኑና እንደሚያፈቅራቸው ተሰማቸው። የተገናኛቸውን ሰዎች መጠን የሌለው ዋጋ እንዳላቸው ያውቅ ነበር። ባረካቸው፣ አገለገላቸውም። ከፍ አደረጋቸው፣ ፈወሳቸውም። ውድ የሆነውን ጊዜውንም ሰጣቸው።

በጊዜአችን ከሌሎች ጋር ጊዜ እንደምናሳልፍ ለማስመሰል ቀላል ነው። በኮምፒውተር፣ በፊት አንዱንም ሳንመለከት ብዙ ሺህ ከሆኑ “ጓደኞቻችን” ጋር “ለመገናኘት” እንችላለን። ቲክኖሎጊ አስደናቂ ነገር ለመሆን ይችላል፣ እናም በምናፈቅራቸው አጠገብ ለመሆን በማንችልበት ጊዜ ይህም በጥቅም ላይ ይውላል። ባለቤቴ እና እኔ ከምንወዳቸው የቤተሰብ አባላቶቻችን ርቀን ነው የምንኖረው፤ ይህም እንዴት እንደሆነ ተረድተናል። ነገር ግን፣ ከቤተሰብ ወይም ጓደኞች ጋር የምንገናኘው የሚያስቁ ነገሮችን፣ ተራ የሆኑ ነገሮችን በኮምፒውተር በመላክ፣ ወይም የምንወዳቸውን በኢንተርኔት በሚገኙት በማስተሳሰር ስለሆነ፣ እንደ ግለሰብ እና እንደ ህብረተሰብ በትክክለኛው መንገድ ላይ ያለን አይመስለኝም። ለእንደዚህ አይነት ነገሮች ቦታም አለው፣ ነገር ግን በዚህ ላይ ስንት ጊዜ ለማሳለፍ ፈቃደኞች ነን? ለእኛ በእውነትም በጣም አስፈላጊ ለሆኑት እራሳችንን እና የግል ጊዜአችንን ካልሰጠን፣ አንድ ቀን ጸጸት ይኖረናል።

ከእነርሱ ጋር ትርጉም ያለው ጊዜ በማሳለፍ፣ ነገሮች አብረን በማድረግ፣ እና እንደ ሀብት የምናያቸው ትዝታዎችን በመፍጠር፣ የምናፈቅራቸውን ዋጋ እንስጣቸው።

በችሎታዬ በነበረኝ ብኖር ምኞቴ ነበር

ሌላ ሰዎች የሚጸጸቱበት ቢኖር እነርሱ መሆን የሚገባቸውን ወይም የሚችሉትን ለመሆን ባለማቻላቸው ነው። ያለፈውን ህይወታቸውን ሲመለከቱ፣ በችሎታቸው መጠን እንዳልኖሩ፣ ለመዝፈን የሚቻለው እንዳልተዘፈነ፣ ይገባቸዋል።

የምናገረው በሙያ ውጤታማነት መሰላል ላይ ስለመውጣት አይደለም። ያም መሰላ፣ በዚህ ምድር ላይ ምንም ያህል ከፍተኛ የሆነ ቢመስልም፣ በሚጠብቀን በታላቁ የዘለአለም ጉዞ እንደ አንድ እርምጃ ብቻ ነው።

ዝለዚህ ሳይሆን፣ የምናገረው እግዚአብሔር፣ የሰማይ አባታችን፣ ምን አይነት ሰው እንድንሆን ስለፈለገበት ነው።

ገጣሚው እንዳለው፣ “የክብር ዳመናዎች እየተከተሉን”4 ከቅድመ ህይወት ወደ አለም መጣን።

የሰማይ አባታችን እውነተኛ ችሎታችንን ያያል። እራሳችን የማናውቃቸውን ነገሮች እርሱም ስለእኛ ያውቃል። በህይወታችን ውስጥ የተፈጠርንበትን እንድናከናውን፣ መልካም ህይወት እንዲኖረን፣ እና ወደ እርሱ ፊት እንድንመለስ ያነሳሳናል።

አብዛኛውን ጊዜአችንን እና ጉልበታችንን ወዲያው በሚጠፋው፣ ምንም ጥቅም በሌለው፣ እና ጥልቀት በሌለው ላይ ለምን እናሳልፋለን? ተራ የሆነውንና ወዲያው የሚያልፈውን በመከተል ያለውን ጥፋት ለማየት እምቢ እንላለን?

“ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእኛ በሰማይ መዝገብ [መሰብሰባችን]”5 ጥበባዊ የሆነ አይደለምን?

ይህን እንዴት እናደርጋለን? የአዳኝን ምሳሌ በመከተል፣ ያስተማረውን በህይወታችን በመጠቀም፣ እግዚአብሔርን እና ሰዎችን በእውነትም በማፍቀር ነው።

ወደ ደቀ መዝሙርትነት ስንቀርብም እግሮቻችንን በማዘግየት፣ ሰዓታችንን በመመልከት፣ ወይም ስንሰራ ቅሬታን በማሳይት በእርግጠኝነት ይህን ማድረግ አንችልም።

በወንጌሉ ስለመኖር በተመለከተ፣ ጣቱን በውሀ ውስጥ አስገብቶ ለመዋኘት ሄጄ ነበር እንዳለው ልጅ መሆን አይገባንም። እንደ ሰማይ አባታችን ልጆች፣ ከዚህ በላይ የመሆን ችሎታ አለን። ለዚያም መልካም ማሰብ ብቻ ብቂ አይደለም። ማድረግአለብን። ከዚህም በጣም አስፈላጊ በሚሆን ሁኔታ፣ የሰማይ አባት እንድንሆን እንደሚፈልገን መሆን አለብን።

የወንጌል ምስክራችንን ማወጃችን መልካም ነው፣ ነገር ግን በዳግም ለተመለሰው ወንጌል ህያው ምሳሌ መሆን ግን የሚሻል ነው። ቃል ኪዳን ለገባናቸው ታማኝ ለመሆን መመኘት ጥሩ ነው፤ ምግባረ ጥሩ የሆነ ህይወት መኖር፣ አስራቶችንና ምጽዋቶችን መስጠት፣ የጥበብ ቃላትን ማክበር፣ እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት የሆኑትን በማድረግ ለገባናቸው ቅዱስ ቃል ኪዳን ታማኝ መሆን ከዚህ በጣም የሚሻል ነው። ለቤተሰብ ጸሎት፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ለማጥናት፣ እና ለመልካም የቤተሰብ መሳተፊያዎች ጊዜ እናስቀምጣለን ማለት ጥሩ ነው፤ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በሙሉ ማድረግ የሰማይ በረከቶችን ወደ ህይወታችን ሁልጊዜም ያመጧቸዋል።

ደቀ መዛሙርትነት ቅድስናን እና ደስታን መከተል ነው። ለራሳችን መሻሻል እና ደስታ የሚመራ መንገድ ነው።

አዳኝን ለመከተል እና እንድንሆን የታቀደክን አይነት ሰው ለመሆን በትጋት እንስራ። የመንፈስን መነሳሻ አድምጠን እንከተል። ይህን ስናደርግም፣ የሰማይ አባት ከዚህ በፊት ስለራሳችን የማናውቃቸውን ነገሮች ይገልጽልናል። ወደፊት ያለውን መንገድ ያበራልናል እናም የማናውቃቸውን እና ምናልባት የማናልማቸውን ችሎታችንን እንድናይ አይኖቻችንን ይከፍትልናል።

እራሳችንን ቅድስናን እና ደስታን በመፈለግ መለኮታዊ ስንሆን፣ በጸጸት መንገድ ላይ የመሆናችን ሁኔታ ይቀንሳል። በአዳኝ ጸጋ ላይ በተጨማሪ ከተደገፍን፣ የሰማይ አባት በእኛ ላይ ባለመው መንገድ ላይ እንደሆንን በተጨማሪም ይሰማናል።

ራሴን ደስተኛ እንድሆን ብፈቅድ ምኞቴ ነበር።

እንደሚሞቱ የሚያውቁት የሚጸጸቱበት ሌላው ነገር የሚያስደንቅ ነው። እነርሱም ራሳቸውን ደስተኛ እንዲሆኑ እንዲፈቅዱ ምኞት አላቸው።

በአብዛኛው ጊዜ መልካም የሆነ የቤተሰብ ሁኔታ፣ መልካም የሆነ የገንዘብ ሁኔታ፣ ወይም ለፈተና መጨረሻ የሚሆኑ አይነት ደስታ የሚያመጣልን ከምናገኘው አልፎ የሚገኝ አንድ ነገር እንዳለ እናልማለን።

ስናረጅም፣ ምንም ጥቅም የሌለውን ወይም ደስታችንን ለመወሰን የማይችለውን የውጪ ጉዳይ ወደኋላ እንመለከታለን።

እኛም ጥቅም አለን።እኛም ደስታችንን እንወስናለን።

እናንተና እኔ በደስታችን ላይ የመጨረሻ ሀላፊነት ያለን ነን።

ባልቤቴ፣ ሄሪየት፣ እና እኔ ቢስክሌትን መንዳት እንወዳለን። የፍጥረትን ወብት በመውጣት መመልከት አስደናቂ ነው። በቢስክሌት የምንጓዝባቸው መንገዶች አሉ፣ ነገር ግን ለምን ያህል እንደምንጓዝና በምን ፍጥነት እንደምንሄድ ከሌሎች ሰዎች ጋር በማመዛዘን አንመለከታቸውም።

ነገር ግን፣ አንዳንዴ መፎካከር የሚገባን ይመስለኛል። ራሳችንን ትንሽ ከፍ ባለ ሀይል እንድንሰራ ብናደርግ በጥሩ ሰዓት ለመድረስ ወይም በፍጥነት ለመጓዝ እንደምንችል አስብበታለሁ። እናም አንዳንዴም ለውዷ ባለቤቴ ይህን የመጥቀስ ትልቅ ስህተትንም እሰራለሁ።

እንደዚህ አይነት ለሆነ ሀሳብ ለማቀርበው መልሷም በጣም ደግ፣ ግልጽ፣ እና ቀጥተኛ ነው። ፈገግ ብላ፣ “ዲየትር፣ ይህ ፉክክር አይደለም፤ ይህ ጉዞ ነው። ጊዜውን ተደሰትበት” ትለኛለች።

እንዴት ትክክል ነች!

አንዳንዴ በህይወት ውስጥ በምንጨርስበት መስመር ላይ አተኩረን በጉዞው ደስታን አናገኝም። ከባለቤቴ ጋር በቢስክሌት የምጓዘው መጨረስን ስለምደሰትበት አይደለም። የምሄደው ከእርሷ ጋር ያለኝ አጋጣሚ አስደሳች ስለሆነ ነው።

የሚያልቁበትን ጊዜ በጉጉት በመጠበቅ አስደሳች አጋጣሚዎችን ማበላሸቱ ሞኝነት አይመስልምን?

አስደሳች ሙዚቃን ስንሰማ በዚህ ለመደሰት የመጨረሻው ድምጹ እስከሚጠፋ ድረስ እንጠብቃለን? አንጠብቅም። እናዳምጣለን እናም የተለያዩ ጣእመ ዜማ እና የሙዚቃ ምት ተስማምተው እንዲገናኙ እናደርጋለን።

ጸሎታችንን “አሜን” በማለት ብቻ ወይም ስለመጨረሻው ብቻ በማሰብ እንጸልያለን? አንጸልይም። የምንጸልየው ከሰማይ አባት ጋር ለመቀራረብ፣ መንፈሱን ለመቀበል፣ እና ፍቅሩ እንዲሰማን ለማድረግ ነው።

ደስታ ሁልጊዜ እንደሚገኝ በማወቅ እንዳንደንግጥ፣ የወደፊት ጊዜ እስከሚመጣ ድረስ ደስተኛ ለመሆን መጠበቅ አይገባንም። ህይወት ወደኋላ በመመልከት እንድንደሰትበት የሚሆን አይደለም። ዘማሪው እንደጻፈው፣ “እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።”6

ወንድሞችና እህቶች፣ ጉዳያችን ምንም ቢሆን፣ የምንታገልባቸው ወይም ፈተናዎቻችን ምንም ቢሆኑ፣ በየቀኑ የምናቅፈውና የምንወደው አንድ ነገር አለ። በየቀኑም ከተመለከትንና ካደነቅን ምስጋናን እና ደስታን የሚያመጣልን አንድ ነገር አለ።

ምናልባት በተጨማሪ በልባችን በመመልከት በአይናችን መመልከትን መቀነስ ይገባን ይሆናል። “በልብህ ብቻ በግልጽ ተመልከት። አስፈላጊ የሆነ ማንኛውን ለገር በአይን አይታይም” 7 የሚለውን ይህን ጥቅስ እወደዋለሁ፥

“በሁሉም ነገሮች ምስጋና” እንድንሰጥ ታዝዘናል።8 ስለዚህ ያለንበትን መጥፎ ጉዳይን ከማጉላት ይልቅ ምስጋና ሊኖረን የምንችለውን ትትንሽ ነገሮች በአይንቻችንና በልባን መመልከቱ አይሻልምን?

ጌታ ቃል እንደገባም፣ “ሁሉንም ነገሮች በምስጋና የሚቀበል እርሱ የከበረ ይሆናል፤ እናም የምድር ነገሮችም፣ እንዲሁም በመቶ እጥፍ፣ አዎን በብዙ፣ ለእርሱ ይጨመሩለታልና።” 9

ወንድሞችና እህቶች፣ ከሰማይ አባታችን ብዙ በረከቶች፣ ከደጉ የደህንነት አላማው፣ በዳግም ከተመለሰው ወንጌል፣ እና በዚህ ስጋዊ የህይወት ጉዞ ውስጥ ከሚገኙ የሚያምሩ ነገሮች ጋር “ለመደሰት ምክንያት የለንምን?”10

ጉዳዮቻችን ምንም ቢሆኑም፣ ደስተኛ እንድንሆን የልብ ውሳኔ ይኑረን።

ስለውሳኔዎች

አንድ ቀን ከዚህ ስጋዊ ህይወት ወደሚቀጥለው ህይወት ልናመልጠው የማንችለውን እርምጃ እንወስዳለን። አንድ ቀን ስለህይወታችን ወደኋላ ተመልክተን የተሻለ ለመሆን እንደምንችል፣ የተሻለ ውሳኔ ለማድረግ እንደቻልን፣ ወይም ጊዜአችንን በጥበብ እንደተጠቀምን እናስብበት ይሆናል።

የህይወትን ጥልቅ ጸጸት ለማስወገድ ዛሬ አንዳንድ ውሳኔዎችን ማድረግ ጥበባዊ ነው። ስለዚህ፣ እነዚህ እናድርግ፥

  • ከምናፈቅራቸው ጋር ብዙ ጊዜ ለማሳለፍ እንወስን።

  • እግዚአብሔር እንድንሆን የፈለገን አይነት ሰው ለመሆን በጣም እንወስን።

  • ሁኔታዎች ምንም ቢሆኑም ደስታን ለማግኘት እንወስን።

የነገዎቹ ጥልቅ ጸጸቶች ዛሬ አዳኝን በመከተል ለማስወገድ እንደሚቻሉ እመሰክራለሁ።፡ኃጢያት ከሰራን ወይም ስህተት ካደረገን፣ አሁን የምንጸጸትበት ምርጫዎችን ካደረግን፣ ምህረት ለማግኘት የምንችልበት ውድ የሆነው የክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አለ። ወደኋላ ለመመለስና የተደረገውን ለመቀየር አንችልም፣ ነገር ግን ንስሀ ለመግባት እንችላለን። አዳኝ የጸጸት እምባችንን ለመጥረግ 11እና የኃጢያትን ሸክም ለማውረድ ይችላል።12 የኃጢያት ክፍያው ያለፈው እንድንተው እና በንጹህ እጆች፣ በንጹህ ልብ፣ 13 እና የተሻለ ለማድረግና የተሻለ ለመሆን በመወሰን ወደፊት እንድንሄድ ይፈቅድልናል።

አዎን፣ ይህ ህይወት በፍጥነት ያልፋል፤ ቀኖቻችን በፍጥነት የሚጠፉ ይመስላሉ፤ እና አንዳንዴም ሞት የሚያስፈራ ይመስላል። ይህም ቢሆን፣ መንፈሳችን ለመኖር ይቀጥላል እናም አንድ ቀን የዘለአለም ክብርን ለመቀበል ከሞት ከተነሳው ሰውነታችን ጋር ይገናኛል። በመሀሪው ክርስቶስ ምክንያት ሁላችንም እንደገና እና ለዘለአለም ለመኖር እንደምንችል እመሰክራለሁ። በአዳኛችን እና በቤዛችን ምክንያት፣ አንድ ቀን “የሞት መውጊያ በክርስቶስ ተውጧል” 14 የሚለው ትርጉሙ ምን እንደሆነ በእውነት ገብቶን እንደሰትበታለን።

እንደ እግዚአብሔር ልጆች መለኮታዊ እጣ ፈንታችንን የምናሟላበት መንገድ አንድና ዘለአለማዊ ነው። ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ ይህን ዘለአለማዊ መንገድ ዛሬመጓዝ አለባችሁ፤ አንድንም ቀን በቸልተኝነት ለመመልከት አንችልም። በእውነት ለመኖር ለመሞት እስከምንደርስ ድረስ እንዳንጠብቅ ጸሎቴ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።