የቤተክርስቲያን ታሪክ
ጄን ኤልዛቤት ማኒንግ ጄምስ


“ጄን ኤልዛቤት ማኒንግ ጄምስ፣” የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶች

“ጄን ኤልዛቤት ማኒንግ ጄምስ”

ጄን ኤልዛቤት ማኒንግ ጄምስ

ጄን ኤልዛቤት ማኒንግ [ከ1822–1908 አካባቢ (እ.አ.አ)] በአሜሪካ ውስጥ አብዛኛዎቹ ጥቁር ሰዎች ባሮች በነበሩበት ዘመን በከነቲከት ውስጥ ነፃ ከሆኑ የአፍሪካ አሜሪካዊ ባልና ሚስት ከተወለዱት አምስት ልጆች ውስጥ የመጨረሻዋ ነች።1 በወጣትነት ዕድሜዋ፣ በ1841 (እ.አ.አ) ክእNew Canaan Congregational [አዲሷ ከነአን ጉባኤ] ቤተክርስቲያን ጋር ተቀላቀለች፣ ነገር ግን ከ18 ወራት በኋላ በ1842–43 (እ.አ.አ) ክረምት አካባቢ፣ እርሷ እና በርካታ የቤተሰብ አባላት በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ለመሆን ተጠመቁ። ጄን እና ከቤተሰቧ መካከል ሌሎቹም ወዲያውኑ በናቩ ካሉት ቅዱሳን ጋር ለመቀላቀል ፈለጉ፣ ስለሆነም በእንፋሎት ጀልባዎች እና በቦይ ጀልባዎች ላይ ለመጓዝ በማቀድ ከከኔቲከት ወደ ኒው ዮርክ ተጓዙ። ሆኖም በዘራቸው ምክንያት የጀልባ ጉዞን ተከልክለው ነበር፣ ስለዚህ ቀሪውን 1,288 ኪ.ሜ. (800 ማይል) በእግር መጓዝ ነበረባቸው። በፒዮሪያ፣ ኢሊኖይ ውስጥ የአከባቢ ባለሥልጣናት የማኒንግ ቤተሰብ ያመለጡ ባሪያዎች ሊሆኑ ስለሚችሉ በማሰብ የነፃነት ሁኔታቸውን ለማረጋገጥ ወረቀት እንዲያሳዩ አስገደዷቸው። ጄን ዘረኝነትን በቀሪ ሕይወቷ ሁሉ የተጋፈጠችው ትግል ነበር።

የጄን ማኒንግ ጄምስ የፎቶግራፍ ምስል

የጄን ማኒንግ ጄምስ ምስል

በቤተክርስቲያን ቤተመጽሐፍት እና ቤተ መዛግብቶች መልካም ፈቃድ የተሰጠ

ወደ ናቩ ከገባች በኋላ፣ ጄን በፍጥነት ከጆሴፍ እና ኤማ ስሚዝ ጋር ወዳጅነት ፈጠረች። ከእነሱ ጋር ትኖር ነበር እናም በቤታቸውም ውስጥ ትሠራ ነበር። በአንድ ወቅት፣ ኤማ ጄንን በክህነት ማኅተም በስሚዝ ቤተሰብ ውስጥ የጉዲፈቻ ልጃቸው እንድትሆን ጋበዘቻት።2 አዲሱን እና እንግዳውን ምግባር ባለመረዳት፣ ጄን አልተቀበለችም፣ ነገር ግን በጆሴፍ የነቢይነት ሚና በጥልቀት ታምን ነበር። በኋላም “ነቢዩ ጆሴፍን አውቅ ነበር” በማለት መሰከረች። “በምድር ላይ ካየኋቸው ሰዎች እጅግ መልካም ሰው ነው። … እሱ ነቢይ እንደነበር እርግጠኛ ነበርኩ ምክንያቱም ይህን አውቅ ነበርና።”3

ከጆሴፍ እና ከእናቱ ሉሲ ማክ ስሚዝ ጋር በተደረጉ ውይይቶች፣ ጄን ስለ መፅሐፈ ሞርሞን እና ስለትርጉሙ የበለጠ ተማረች እና ስለቤተመቅደስ ስነስርአቶች ግንዛቤ እና አክብሮትን አገኘች።

ጄን ከኒው ጀርዚ ወደ ወንጌል ተለውጦ የመጣ ነፃ የሆነውን ጥቁር ሰው አይዛክ ጄምስ አገባች። እነርሱ፣ ከጄን ልጅ ሲልቪስተር ጋር፣ በ1846 (እ.አ.አ) ከናቩ ወጥተው ከቅዱሳኑ ጋር ወደ ምዕራብ ተጓዙ። በዚያው ዓመት ሰኔ ውስጥ፣ የጄን እና የአይዛክ ልጅ ሲላስ ተወለደ። በቀጣዩ ዓመት ቤተሰቡ በ1847 (እ.አ.አ) መኸር ላይ ታላቅ ሜዳውን አቁርጦ በመሄድ ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ደረሱ። አይዛክ እና ጄን ስድስት ተጨማሪ ልጆች ነበሯቸው፣ ሁለቱ ብቻ ከጄን ሞት በኋላ አልፈው ኖሩ። እንደሌሎቹ ቀደምት የሶልት ሌክ ሸለቆ ሰፋሪዎች ሁሉ፣ ጄን እና አይዛክ ለቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልገውን ለማቅረብ ጠንክረው ሰርተዋል። አይዛክ እንደ የጉልበት ሰራተኛ እና አልፎ አልፎም እንደ ብሪገም ያንግ ጋሪ ነጂ ይሰራ ነበር፣ እና ጄንም ጨርቅ በመፈተል እና ልብስ በመስራት፣ እናም በናቩ ውስጥ እንዳደረገችው ልብሶችን በማጠብ ሰራች።

አይዛክ እና ጄን በ1870 (እ.አ.አ) በጋብቻ ውስጥ በተፈጠረው ውጥረት የተነሳ ተፋቱ። ጄን በኋላም ከቀድሞው ባሪያ ከነበረ ፍራንክ ፐርኪንስ ጋር ለአጭር ሁለት ዓመታት ተጋብታ ነበር፣ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ እንደ ብቸኛ ወላጅ እና አያት ህይወትን እንደገና ቀጠለች። የገንዘብ እጥረት እና የሦስት ልጆች ሞት ጄን ወደ ሥራ እንድትመለስ አደረጋት። እሷም ሳሙና ሰርታ ትሸጥ የነበረ ሲሆን፣ ሁለት ወንዶች ልጆቿም በቀን ሠራተኝነት ተቀጥረው ነበር። አይዛክ ለ20 ዓመታት ያህል ከሶልት ሌክ ስቲ ውጢ ቆይቶ ከቆየ በኋላ፣ በ1890 (እ.አ.አ) ወደ ሶልት ሌክ ሲቲ ተመለሰ፣ የቤተክርስቲያኗን አባልነቱን አሳደሰ እና ከጄን ጋር ጥሩ ግንኙነት ፈጠረ። ከአንድ አመት በኋላ በሞተ ጊዜም፣ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በቤቷ ውስጥ ተደርጎ ነበር።

በሕይወቷ ችግሮች ሁሉ፣ ጄን በወንጌል ትምህርቶች ላይ ባላት እምነት በታማኝነት ቆይታለች እና የቤተክርስቲያኗ አባልነቷንም ከፍ አድርጋ ተመልክታለች። ለቤተመቅደስ ግንባታ ብልግስና ሰጥታለች እናም በሴቶች መረዳጃ ማህበር እና በወጣት ሴቶች ማጠናቀቂያ ማህበር ውስጥ ተሳትፋለች።4 ጄን ራእዮችን፣ ህልሞችን፣ በእምነት መፈወስን እና በልሳኖች መናገርን ጨምሮ የመንፈስ ስጦታዎችን በብቃት አጋጥሟታል። በሕይወቷ ስትገፋም እንዲህ በማለት ጽፋለች፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ ያለኝ እምነት ዛሬም እንደዚያ ጠንካራ ነው፣ አዎን፣ ቢቻል መጀመሪያ ከተጠመቅኩበት ቀን የበለጠ ጠንካራ ነው።”5

በ1884 እና 1904 (እ.አ.አ) መካከል፣ ጄን የቤተክርስቲያኗ መሪዎችን፣ ጆን ቴይለር፣ ዊልፎርድ ውድሩፍ፣ ዚና ዲ. ኤች. ያንግ፣ እና ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝን የግል የቤተመቅደስ ቡራኬዋን ለመቀበል እና ለመታተም ፈቃድ ጠየቀች።6 በዚያን ጊዜ፣ ጥቁር የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ወንዶች እና ሴቶች በአብዛኛዎቹ የቤተመቅደስ ስርዓቶች ውስጥ እንዲሳተፉ አልተፈቀደላቸውም ነበር። በ1888 (እ.አ.አ) የካስማ ፕሬዘዳንት አንገስ ኤም. ካነን ለሟች ዘመዶቿ ጥምቀት እንድታደርግ ፈቀደላት።7 የቤተክርስቲያኗ መሪዎችም በመጨረሻ በ1894 (እ.አ.አ) በጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ ውስጥ እንደ አገልጋይ ሆና በወኪል እንድትታተም ፈቀዱላት፣ ይህም ልዩ የሆነ ክስተት ነበር። ምንም እንኳን በሕይወት ዘመኗ የቤተመቅደስ ቡራኬን ወይም የቤተሰብን ማህተሞችን ባታገኝም፣ እነዚህ ሥርዓቶች በ1979 (እ.አ.አ) እሷን በመወከል ተከናውነዋል።8

እርሷም በሚያዝያ 16 ቀን 1908 (እ.አ.አ) በ95 ዓመቷ፣ ሁሌም ታማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በመሆን አረፈች። የDeseret News [ዴዘሬት ጋዜጣ] እንደዘገበው፣ “በእምነት እና በታማኝነት ከጄን ማኒንግ ጄምስ የበለጠ የሚታወቁት ጥቂቶች ነበሩ፣ እናም በምድራዊም ነገር ትሁት ብትሆንም ጓደኞቿ እና የምታውቃቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ነበሩ።”9

ማስታወሻዎች

  1. የጄን እናት በባርነት የነበረች ቢሆንም፣ ግን በከነቲኬት የቀስ በቀስ ነፃ የማድረግ ህግ አማካኝነት ነፃ ሆነች። ጄን ነጻ ሆና ነበር የተወለደችው፣ ሆኖም ጄን ከክልሉ እስክትወጣ ድረስ በግዛቱ ውስጥ ባርነት ህጋዊ ነበር። በአጠቃላይ ስለጄን ሕይወት፣ የሄንሪ ጄ ቮልፊንገርን “A Test of Faith: Jane Elizabeth Manning James and the Origins of the Utah Black Community [የእምነት ፈተና፥ ጄን ኤሊዛቤት ማኒንግ ጄምስ እና የዩታ ጥቁር ማህበረሰብ አመጣጥ]” የሚለውን በክላርክ ኖልተን ህትመት፣ Social Accommodation in Utah [በዩታ ውስጥ ማህበራዊ ስምምነት] [ሶልት ሌክ ስቲ፣ የዩታ ዩኒቨርሲቲ፣ 1975 (እ.አ.አ)]፣ 126-75 እና ክውንሲ ዲ. ኒውል፣ “The Autobiography and Interview of Jane Elizabeth Manning James [የጄን ኤልዛቤት ማኒንግ ጄምስ የግል ታሪክና እና ቃለ መጠይቅ]፣” Journal of Africana Religions [የአፍሪካና ኃይማኖቶች ማስታወሻዎች]፣ ይዘት 1፣ ቁጥር 2 [2013 (እ.አ.አ)]፣ 251–91 ተመልከቱ።

  2. ዚና ዲ. ኤች ያንግ ለጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ የላከችው ደብዳቤ፣ ጥር 15፣ 1894 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተ-መጽሃፍ፣ ሶልት ሌክ ስቲ።

  3. “‘Aunt’ Jane James [’አክስት’ ጄን ጄምስ]፣” በ“ጆሴፍ ስሚዝ፣ ነቢዩ” ውስጥ፣ Young Woman’s Journal [የወጣት ሴቶች ማስታውሻ]፣ ይዘት 16፣ ቁጥር 12 [ታህሳስ 1905 (እ.አ.አ.)]፣ 551፣ 553።

  4. ስምንተኛ የአጥቢያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማስታወሻዎች እና መዛግብቶች፣ 1867 -1969 (እ.አ.አ)፣ ስምንተኛ አጥቢያ፣ ሊበርቲ ካስማ፣ ነሐሴ 20 ቀን 1874 (እ.አ አ)፤ ጥቅምት 20 ቀን 1874 (እ.አ.አ)፤ ታህሳስ 21 ቀን 1874 (እ.አ.አ)፤ ጥር 20 ቀን 1875 (እ.አ.አ)፤ መጋቢት 22 ቀን 1875 (እ.አ.አ)፤ ግንቦት 20 ቀን 1875 (እ.አ.አ)፤ ህዳር 20፣ 1875 (እ.አ.አ)፣ ይዘት 1፣ የቤተክርስትያን ታሪክ ቤተ-መጽሐፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ [ጄን ለአጭር ጊዜ ፐርኪንስ በሚባለው የመጨረሻ ስም ትታወቅ ነበር]፤ “Ladies Semi-monthly Meeting [የሴቶች የግማሽ-ወርሃዊ ስብሰባ]፣” Woman’s Exponent [የሴቶች ገላጭ]፣ ይዘት 22፣ ቁጥር 9 [ታህሳስ 1፣ 1893 (እ.አ.አ)]፣ 66። ጄን ለሴንት ጆርጅ፣ ለሎገን እና ለማንታይ ቤተመቅደሶች ግንባታ ገንዘብ ለገሰች እና ለላማናውያን (ህንድ) ተልእኮ አስተዋፅኦ አበርክታለች። ሊንዳ ኪንግ ኒውል እና ቫሊን ቲፒትስ ኤቨሪ፣ “Jane Manning James [ጄን ማኒንግ ጄምስ]፣” ኤንዛይን፣ ነሃሴ 1979 (እ.አ.አ)፣ 29 ይመልከቱ።

  5. Jane Elizabeth Manning James autobiography [የጄን ኤልሳቤጥ ማኒንግ ጄምስ የህይወት መፅሃፍ]፣ በ1902 (እ.አ.አ) አካባቢ፣ ለኤሊዛቤት ጄ. ዲ. ራውንዲ በአፍ ታሪክ የተሰጠ፣ የቤተክርስቲያን የታሪክ ቤተ-መጻሕፍት፣ ሶልት ሌክ ስቲ፣ 22።

  6. ጄን ኢ. ጄምስ ለጆን ቴይለር ደብዳቤ፣ ታህሳስ 27 ቀን 1884 (እ.አ.አ)፤ ጄን ኢ ጄምስ ለጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ የላከችው ደብዳቤ፣ የካቲት 7 ቀን 1890 (እ.አ.አ)፤ ጄን ኢ ጄምስ ለጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ የላከችው ደብዳቤ ነሐሴ 31 ቀን 1903 (እ.አ.አ)።

  7. አንገስ ኤም. ካነን ለጄን ኢ. ጄምስ የተላከ ደብዳቤ፣ ሰኔ 16 ቀን 1888 (እ.አ.አ)፤ በተጨማሪም የቶኒያ ሬተርን “Black Saviors on Mount Zion: Proxy Baptisms and Latter-day Saints of African Descent [በጽዮን ተራራ ላይ ያሉ ጥቁር አዳኞች፥ የውክልና ጥምቀቶች እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የአፍሪካውያን ትውልድ]፣” Journal of Mormon History [የሞርሞን ታሪክ ማስታወሻዎች]፣ ይዘት 43፣ ቁጥር 4 [ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)፣ 100–123 ይመልከቱ።

  8. Jane Elizabeth Manning James autobiography [የጄን ኤልዛቤት ማኒንግ ጄምስ የህይወት ታሪክ]፣ በ1902 (እ.አ.አ) ገደማ። ጄን በ1902 እና በ1908 (እ.አ.አ) መካከል በሶልት ሌክ ስቲ ውስጥ የራስዋን የህይወት መጽሃፍ በአፍ ታሪክ ነግራለች፤ ሮናልድ ጂ. ኮልማን እና ዳርዮስ ኤ. ግሬይ “Two Perspectives: The Religious Hopes of ‘Worthy’ African American Latter-day Saints before the 1978 Revelation [ሁለት አመለካከቶች፥ ከ1978 (እ.አ.አ) ራዕይ በፊት ያሉት “የብቁ”” አፍሪካዊ አሜሪካዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሃይማኖታዊ ተስፋዎች]፣ በኒወል ጂ. ብሪንግሀርስት እና ዳረን ቲ. ስሚዝ፣ ቅጂዎች ውስጥ Black and Mormon [ጥቁር እና ሞርሞን] [Urbana: University of Illinois Press [ኡራባና፥ የኢለኖይ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጣ] ፣ 2004 (እ.አ.አ)]፣ 54። በክውንሲ ዲ. ኒውል፣ “The Autobiography and Interview of Jane Manning James [የጄን ኤልዛቤት ማኒንግ ጄምስ የግል ታሪክ እና ቃለ መጠይቅ]፣” Journal of Africana Religions [የአፍሪካና ኃይማኖቶች ማስታወሻዎች]፣ ይዘት 1፣ ቁጥር 2 [2013 (እ.አ.አ)]፣ 256፣ 275 (ማስታወሻ 34)።

  9. “Death of Jane Manning James [የጄን ማኒንግ ጄምስ መሞት]፣” Deseret News [ዴዘረት ዜና]፣ ሚያዝያ 16፣ 1908 (እ.አ.አ)።