“ጆሴፍ ስሚዝ እና ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት፣” የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶች
“ጆሴፍ ስሚዝ እና ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት”
ጆሴፍ ስሚዝ እና ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት
የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ጋብቻ፣ የጌታ ቋሚ የሆነ የጋብቻ ሕግ እንደሆነ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ያምናሉ።1 በቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ በነበሩት ዘመናት፣ ጌታ አንዳንድ ህዝቡን ከአንድ በላይ ሚስትን በማግባት እንዲተገብሩ አዝዞ ነበር—ይህም አንድ ወንድ ከአንድ ሴት በላይ ማግባት መቻሉ ነው።2 አንዳንድ የቀድሞ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትም በእግዚአብሔር ነቢያት በኩል የተሰጠውን ይህን ትእዛዝ ተቀበሉ እናም ታዛዥ ሆኑ።
ጆሴፍ ስሚዝ ከአንድ ሚስት በላይ እንዲያገባ ያዘዘው ራዕይ ከተቀበለ በኋላ፣ ብዙ ሚስቶችን አገባ እናም ይህንን ተግባርም ለቅርብ ጓደኞቹ አስተዋወቀ። ይህ መርህ በግል ለጆሴፍ እና ለሌሎች የቤተክርስቲያኗ አባላት በጣም ተፈታታኝ ከሆኑት የዳግም መመለስ ገጽታዎች ውስጥ አንዱ ነው። ከአንድ በላይ ሚስት የማግባት ተግባር እምነትን የሚፈትን እና ውዝግብንና ተቃውሞን ያስነሳ ነበር። ይህ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ተግባር የሆነውን ዳግም መመለስ ለእነሱ መረዳት ሙሉ በሙሉ እንግዳ ቢሆንም ጥቂት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በመጀመሪያ ተቀበሉት። ግን ብዙዎች በኋላ ላይ ማመንታታቸውን እንዲያሸንፉ እና ይህን ተግባር ለመቀበል ድፍረትን ስለሰጣቸው ኃይለኛ መንፈሳዊ ተሞክሮ መስክረዋል።
ተሳታፊዎች ድርጊቶቻቸውን በሚስጥር እንዲጠብቁ ተጠይቀው ስለነበር፣ ስለ የቀድሞ የብዙ ሚስት ጋብቻ ተግባር ብዙ ዝርዝሮች አይታወቁም። የቀድሞ የብዙ ሚስቶች ጋብቻ ታሪካዊ መዝገብ ስለዚህ የሳሳ ነው፥ የዘመኑ ጥቂት መዝገቦች ዝርዝሮችን ይሰጣሉ፣ እናም በኋላ ላይ የመጡ ትውስታዎች ሁልጊዜ አስተማማኝ አይደሉም። ቅዱሳን በጆሴፍ ስሚዝ እና በሌሎች የቀድሞ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የብዙ ሚስት ጋብቻን አስመልክቶ ብዙ ጠቃሚ ታሪኮችን ይናገራሉ። የቀድሞውን የብዙ ሚስት ጋብቻን በተመለከተ ለበለጠ መረጃ፣ “Plural Marriage in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints [በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የብዙ ሚስቶች ጋብቻ]፣” Gospel Topics Essays [የቤተክርስቲያን ርዕሰ መጣጥፎች]፣ topics.churchofjesuschrist.org፣ ይመልከቱ።
ተዛማች ርእሶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ ኤማ ሄል ስሚዝ፣ ፋኒ አልገር፣ Nauvoo Expositor [የናቩ ገላጭ]