2010 (እ.አ.አ)
ማንም ፍጹም አይደለም
ማርች 2010


ወጣቶች

ማንም ፍጹም አይደለም

እንደኔፊ በጥብቅ ታዛዥ፣ በጣም ታማኝ፣ እና በዝልቅ መንፈሳዊ ለመሆን ሁልጊዜም እፈልጋለሁ። በአስተያየቴ ኔፊ ከሁሉም በላይ የሆነ የጥሩነት ምሳሌ ነው። እንደእርሱ አይነት ሆኜ ከማደግ—ወይም እርሱ የተሻለ የሆነበትን ነገር አይነት በትንሽም ቢሆን ለማግኘት ከማስብበት በላይ የማልምበት ብዙም ነገሮች የሉም።

አንድ ቀን ብቁ ባለመሆን ስሜታ እጨነቅ ነበር። ታናቅ ፍላጎቶች እና ብዙ አላማዎች ነበሩኝ። ነገር ግን ምንም ለማከናወን እንደምችል የሚመስል አልነበረም። በተስፋ መቁረጥ እምባዎች እነዚህን ስሜታዎቼን ለአባቴ ገለፅኩኝ። እርሱም ወዲያው ተነሳ፣ ወደ መፅሀፍ መደርደሪያው ሄደ፣ እና አንዱን የመፅሀፈ ሞርሞኑን አወጣ። ምንም ሳይልም ወደ 2 ኔፊ 4 ከፈተው እና ቁጥር 17ን ማንበብ ጀመረ።

“እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ!” የሚሉትን እነዚህን ሀይለኛ ቃላቶች ሲያነብ ስሰማ በሰውነቴ ውስጥ ቀዝቃዛነት እንደ ኤሌክትሪክ ተሰማኝ። ሀሳቦቼም ተፋጠኑ። የእኔ ጀግና እና ምሳሌው ኔፊ እንዴት “ጎስቋላ” ነኝ ይላል? እርሱ ጎስቋላ ከሆነ፣ እኔ ምን ነኝ ማለት ነው?

እንደገና አባቴ ቁጥር 28ን ሲያነብ እንደ ኤሌክትሪክ በሰውነቴ ላይ ተሰማኝ፧ “ነፍሴ ሆይ፣ ንቂ! ከእንግዲህ በኃጢአት አትድከሚ” በአእምሮዬ ውስጥ ያለው ጭለማ እንደተበተነ እና ክፍት የሆነ ሰማያዊ ሰማይን እና ብሩህ ጸሀይን ለመግለፅ የተከፈተ እንደሆነም ተሰማኝ። እንዴት ይህ ቁጥር ነፍሴን እንዳብራራው ለመግለፅ አስቸጋሪ ነው። ይህ ቁጥር በብዙ ተስፋ፣ መነሳሳት፣ እና ደስታ እንደሞላኝ አይነት ሌሎች ያደረጉ ብዙዎችም የሉም።

በቁጥር 30 ውስጥ ኔፊ እኔ እንደማስብበት፣ ግን በጣም ልብ በሚነኩ ቃላቶች ነበር ያለው፧ “አምላኬ ነፍሴ በአንተ ደስ ይላታል፣ እንዲሁም አንተ የደህንነቴ አለት ነህ።” ይህ ቁጥር የሰላም እና በጌታ ምህረት እና ፍቅር ምስጋና ስሜታዎችን አመጣ።

አባቴ መፅሀፉን ዘጋ እና እነዚህ ቁጥሮች አንዳንዴ የኔፊ መዝሙር ተብለው እንደሚጠሩ ገለጸ። ከዛም በምድር ውስጥ ከሁሉም በላይ የሆኑ ሰዎችም ፍጹም እንዳልሆኑ፣ እና እነዚህ ሰዎች ፍጹም ያለመሆናቸውን ማወቅ እንዳለባቸው አለበለዚያም እነርሱ ኩራተኛ እንደሚሆኑ እና ስለዚህ ታላቅ እንደማይሆኑ በትግስት አስተማረኝ።

እኔም ገባኝ። ደካማነት ስላለኝ እንደ ኔፊ አይነት ለመሆን ችሎታ የለኝም ማለት አይደለም። ደካማነቴን ማወቄ እንደ ኔፊ ለመሆን ቅርብ እንድሆን አደረገኝ። ኔፊ፣ ታዛዥ እና ታማኝ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ታላቅ የነበረው ትሁት እና ስህተቶች እድዳደረገ ለመቀበል ፈቃደኛ ስለሆነ ነው።

ከእዚያ አጋጣሚ ጀምሮ፣ እነዚህን የኔፊን ቃላቶች እንደሀብት ይዤአቸዋለሁ። በማንባቸው ጊዜ ሁሉ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳነባቸው እንደተሰማኝ አይነት ደስታ እና መነሳሳት ያጋጥመኛል። ቁጥሮቹም እኔ ከማስብበት በላይ ላማከናወን ችሎታ ያለኝ፣ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ እንደሆንኩኝ ያውጅልኛል። ታማኝ ከሆንኩኝ እና ወደፊት ከገፋሁኝ፣ ተነግረው ያልነበሩ በረከቶች እንደሚኖርኝ አውቃለሁ።

አትም