የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መጋቢት 2010
የምግባረ ጥሩነት ጉብዝና
የስጋዊ ህይወት አንድ አላማ ቢኖር ጉብዝና በሚያስፈልግበት ጊዜ ትእዛዛቱን እንደምናከብር ለእግዚአብሔር ማረጋገጫ መስጠት ነው። ይህን ፈተና በመንፈስ አለም ውስጥ አልፈን ነበር። ነገር ግን የመውደቅ አደጋ በሚኖርበት በስጋዊ ኑሮ እንዲፈተኑ የቀረበውን ሀሳብ እቅድ በመቃወም አንድ ሶስተኛው የሰማይ ሰራዊቶች አመጹ።
ከመወለዳችን በፊት፣ እግዚአብሔር አብን እና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በግል እናውቃቸው ነበር። ሲያስተምሩን እና ሲያበረታቱን ለማየት እና ለመስማት እንችል ነበር። አሁን በአዕምሮአችን እና በትዝታችን ላይ መጋረጃ አለባቸው። ሰውነቶቻችን ለስጋዊ ፈተና እና ለሰውነት ደካማነት ተገዚ እያደረጉን የማንነታችንን እውነት በእምነት አይኖች መመልከት ስላለብን፣ የሀሰት አባት ሰይጣን በእኛ ላይ ብልጫ ያለው ጥቅም አለው።
በዚህ ህይወት ጉብዝና የሚሰጡን ብዙ እርዳታዎች አሉን። ከእነዚህም ይበልጥ ታላቅ የሆነውም የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጥያት ክፍያ ነው። እርሱ ባደረገው ምክንያት፣ ኀጥያቶች በጥምቀት ውሀዎች ሊታጥቡ ይችላሉ። ቅዱስ ቁርባንን በእምነት እና ንስሀ በሚገባ ልብ ስንወስድ ይህን በረከት ለማደስ እንችላለን።
ሌላ እርዳታም የመንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው። የክርስቶስን መንፈስ በምንወለድበት ጊዜ እንቀበላለን። ያም በፊታችን ያለው ምርጫ ወደዘለአለም ህይወት እንደሚረዳ ለማወቅ ሀይል ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ ጓደኛችን ሆኖ በምናነባቸው ጊዜ ቅዱስ መጻህፍት የእርግጠኛ መመሪያችን ይሆናሉ።
መንፈስ ቅዱስ ምስጋና እንድናቀርብ እና ከሰማይ አባታችን ጋር በነበርንበት ጊዜ በተደሰትንበት እና ወደ እርሱም በምንመለስበት ጊዜ በሚኖረን ግልፅነት እና ልበ ሙሉነትበጸሎት እርዳታ እንድንጠይቅ ይፈቅድልናል። ያም ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገራችን ለሰማይ አባታችን እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት እና ፍቅር ሲገነባ ከልቦቻችን ፍርሀትን እንድናጠፋ ይረዳናል።
ቅዱስ የክህነት ስልጣን በአገልግሎታችን ጉብዝና ይሰጠናል። በስነስርዓቶቹም የእግዚአብሔርን ልጆች የምናገለግልበት እና የክፉን ተጽዕኖ የምንቋቋምበት ሀይል እንቀበላለን። እንድናገለግን ሲጠራን፣ ይህም የተስፋ ቃል አለን፧ “እናም የሚቀበሏችሁም፣ በእዚያም እገኛለሁ፣ በፊታችሁ እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል።” D&C 84:88
ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በአገልግሎቱ የሚፈራበት ምክንያት ነበረው። ነገር ግን እግዚአብሔር በመምህር ምሳሌ ማረጋገጫ ማበረታቻ ሰጥቶታል።
“እና ወደ ጉድጓድ ወይም ወደ ገዳዮች እጆች ከተጣልክ፣ እና የሞት ፍርድ ከተላለፈብህ፤ ወደ ጥልቁ ከተጣልክ፤ ወደፊይ እና ወደኋላ የሚገፋው ውሀ በአንተ ላይ ከአደመ፤ አደገኛው ነፋሶችም የአንተ ጠላት ከሆኑ፤ ሰማዮችም ጭለማን የሚሰበስቡ ከሆኑ፣ እና ንጥረ-ነገሮች ሁሉ መንገድህን ለማሰናከል ከተጣመሩ፤ እና ከሁሉም በላይ፣ የሲኦል መንጋጋም አፍዋን በሰፊ ከከፈተችብህ፣ ልጄ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም እንደሆኑም እወቅ።
“የሰው ልጅ ከሁሉም በታች ወርዷል። አንተ ከእርሱ ታልቅ ነህ?” (D&C 122:7–8)።
እግዚአብሔር፣ በህይወት ምንም ቢያጋጥመንም፣ ፍርሀትን እንድናጠፋ እና ጉብዝና እንዲሰጠን ከሚያስፈልገን በላይ እርዳታ ሰጥቶናል። የእርሱን እርዳታ ስንፈልግ፣ ወደምንፈልገው ዘለላለማዊ ህይወት ከፍ ሊያደርገን ይችላል።
© 2009 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ) First Presidency Message, March 2010 (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic. 09363 506