የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት ፣ መጋቢት 2010 (እ.አ.አ)
በእግዚአብሔር አብ እና በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን በግል ቅዱስ መጻህፍት ጥናት ማጠናከር
እነዚህን ቅዱስ መጻህፍትን እና ጥቅሶችን ወይም፣ አስፈላጊም ከሆነ፣ የምትጎበኗቸውን እህቶች ፍላጎት የሚያሟሉትን ሌሎች መሰረቶች አስተምሩ። ስለትምህርቱም ምስክራችሁን ስጡ። የምትጎብኟቸውንም የተማሩትን እና የሚሰማቸውን እንዲካፈሉ ጋብዟቸው።
“አዲስ ሙሽራ በነበርኩበት ጊዜ፣ …በዎርዴ መፅሐፈ ሞርሞንን ወይም አጭሩን የቤተክርስትያን ታሪክ መፅሀል ላነበቡት የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች ወደተሰጠው ምሳ ተጋብዤ ነበር። ቅዱስ መጻህፍትን ማንበቤ ችላ እያልኩኝ ነበር፣ ስለዚህ ወደ ምሳው ለመሄድ ብቁ የሆንኩት ቀላል እና ብዙ ጊዜ የማይፈጀውን አጭሩን መፅሐፍ በማንበብ ነበር። ምሳዬን እየበላሁ እያለሁ፣ ምንም እንኳን የታሪክ መፅሀፉ ጥሩ ቢሆንም፣ መፅሐፈ ሞርሞንን ማንበብ እንደነበረብኝ ስሜታ መጣብኝ። መንፈስ ቅዱስ የቅዱስ መጻህፍት ማንበብ ጸባዬን እንድቀይር እያነሳሳኝ ነበር። በእዚያም ቀን መፅሐፈ ሞርሞንን በየቀኑ ማንበብ ጀመርኩኝ፣ እና በምንም አላቆምኩም። …በየቀኑ ቅዱስ መጻህፍትን ስላነበብኩኝ፣ ስለሰማይ አባቴ፣ ስለልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና እነደእነርሱ አይነት ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ተማርኩኝ። …
“… እያንዳንዷ ሴት በቤቷ ውስጥ የወንጌል ትምህርት አስተማሪ መሆን ትችላለህ፣ እና በቤተክርስትያኗ ውስጥ ያለችው እያንዳንዷ እህት እንደ መሪ እና አስተማሪ የወንጌል እውቀት ያስፈልጋታል። በየቀኑ ቅዱስ መጻህፍት የማጥናት ጸባይ የማይኖራችሁ ከሆናችሁ፣ አሁን ጀምሩ እና በዚህ እና በዘለአለማዊ ህይወቶች ለሚኖራችሁ ሀላፊነት ለመዘጋጀት ዘንድ በማጥናት ቀጥሉ።”1
ጁሊ ቤክ፣ የሴኦትች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት።
“የቅዱስ መጻህፍት ጥናት ምስክራችንን እና የቤተሰቦቻችንን ምስክሮች ለማሳደግ ይረዱናል። በእነዚህ ቀናት ልጆቻችን ትክክል የሆነውን እንዲያስወግዱ እና በምትኩም የአለም ደስታዎችን እንዲፈልጉ በሚገፋፏቸው ድምጾች ተከብበው እያደጉ ናቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፣ በእውነት ምስክር፣ እና በጻድቅነት ለመኖር ውሳኔነት፣ ላይ ጽኑ የሆነ መመሪያ መሰረት ከሌላቸው በስተቀር፣ ለእነዚህ ተጽዕኖች በቀላል ለመማረክ የሚችሉ ይሆናሉ። እነርሱን መደገፍ እና መጠበቅ የእኛ ሀላፊነት ነው።”2
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።
“እህቶቻችን የቅዱስ መጻህፍት ምሁር እንዲሆኑ እንፈልጋቸዋለን። … ለእራሳችሁ ደህንናት እና የእራሳችሁን ልጆች እና ወደተፀኖአችሁ የሚመጡትን ሌሎች ለማስተማር አላማ ከእነዚህ ዘለአለማዊ እውነቶች ጋር የምትተዋወቁ እንድትሆኑ እንፈልጋችኋለን።”3
“ያገባችሁም ወይም ያላገባችሁ፣ ወጣት ወይም አሮጊት፣ ባል የሞተባቸው ወም ከቤተሰብ ጋር የምትኖሩ ቢሆንም፣ ቤቶቻችን ውዱስ መጻህፍት ምሁር በሆኑ እህቶች እንዲባረኩ እንፈልጋለን። የቅዱስ መጻህፍት ተማሪዎች ሁኑ—ሌሎችን ለመገሰፅ ሳይሆን፣ ሌሎችን ለማነሳሳት።”4
ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል (1895–1985)
© 2009 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/08 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/09 (እ.አ.አ) Visiting Teaching Message, March 2010 ትርጉም Amharic. 09363 506