2010 (እ.አ.አ)
ቅዱስ ቤተመቅደስ
ኦክተውበር 2010


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ጥቅምት 2010 (እ.አ.አ)

ቅዱስ ቤተመቅደስ

በቤተመቅደሳት ውስጥ እራሳቸውን ብቁ የሚያደርጉ የቤተክርስትያኗ አባላት ለሰው ዘር በተገለጸው ከፍ በሚያደርግ አዳኝ ስነስርዓትውስጥ ተካፋይ ለመሆን ይችላሉ።

በቤተመቅደሳት ውስጥ ከፍ በሚያደርጉ አዳኝ ስንስርዓቶች ተካፋይ ለመሆን እንችላለን።

ሰው ወደቤተመቅደስ ለመሄድ የሚፈልግበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። የውጪ አመለካከቱም ጥልቅ መንፈሳዊ አላማውን የሚያመለክት ይመስላል። በግድግዳዎቹ ውስጥ ግልፅ የሆኑ ብዙ አሉ። በቤተመቅደሱ በር ላይ “ለጌታ ቅድስና” የሚል መታሰቢያ አለ። ወደተቀደሰ ቤተመቅደስ ስትገቡ፣ በጌታ ቤት ውስጥ ናችሁ።

በቤተመቅደሳት ውስጥ እራሳቸውን ብቁ የሚያደርጉ የቤተክርስትያኗ አባላት ለሰው ዘር በተገለጸው ከፍ በሚያደርግ አዳኝ ስነስርዓትውስጥ ተካፋይ ለመሆን ይችላሉ። በእዚያም በቅዱስ ስነስርዓት ሰው መታጠብ እና መቀባት እናም መማር እናም መንፈሳዊ ስጦታ መሰጠት እናም በተሳሰር ይችላል። እናም እነዚህን በረከቶች ለእራሳችን በምንቀበልበት ጊዜ፣ እንደዚህ አይነት እድል ከማግኘታቸው በፊት ለሞቱት ይህን እናከናውናለን። በቤተመቅደሳት ውስጥ ለህያው እና ለሙታን አንድ አይነት ስነስርዓቶች ይፈጸማሉ።

የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ያልተምታቱ፣ ወብታዊና ቅዱስ ናቸው።

ጌታ ሁሉንም ነገሮች ለሁሉም ህዝቦች እንዳልነገረ ቅዱስ መጻህፍትን በጥንቃቄ ማንበብ ይገልጻል። ቅዱስ መዝገቦችን ለመቀበል በፊት የሚያስፈልጉ አንዳንድ ብቁነት አሉ። የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ከዚህ ምድቦች ውስጥ ናቸው።

የቤተመቅደስ ስነስርዓቶችን ከቤተመቅደስ ውጪ አንወያይም። የቤተመቅደስ ስነስርዓቶ እውቀት ለተመረጡ አንዳንዶች ብቻ ተሰጥቶ እነርሱም ሌሎች ስለእነዚህ በምንም እንዳይማሩ ለማድረግ ማረጋገጥ እንደላባቸው አይነት አልደለም። በእርግጥ ይህም ከዚህ ተቃራኒ ነው። በታላቅ ጥረት እያንዳንዱ መንፈስ ለቤተመቅደስ አጋጣሚ ብቁ እንዲሆኑ እና እንዲዘጋጁ እናበረታታለን። ወደቤተመቅደስ የገቡት መሰረታዊ አመራርን ተምረዋል፧ የሚኖር የነበረ እያንዳንዱ ነፍስ ወንጌሉን ለመስማት እና ቤተመቅደስ የሚያቀርበውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል እድል ይኖረዋል። ይህን እድል የማይቀበሉም ከሆነ፣ ይህንም የማይቀበሉት ግለሰብ እራሳቸው ናቸው።

የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ያልተምታቱ ናቸው። ወብታዊም ናቸው። የተቀደሱም ናቸው። ላልተዘጋጁት እንዳይሰጡ ዘንድ በሚስጥር ይጠበቃሉ። ለማወቅ መጓጓት ዝግጅት አይደለም። ጥልቅ የእውቀት ፍላጎትም ዝግጅት አይደለም። ለስነስርዓቱ ለመዘጋጀት የመጀመሪያ ደረጃዎች አሉት፧ እምነት፣ ንስሀ መግባት፣ ጥምቀት፣ መረጋገጥ፣ ብቁነት፣ ወደጌታ ቤት እንደ እንግዳ ተጋብዞ እንደሚመጣ ሰው ጎልማሳነትና ብቁነት።

ብቁ የሆኑት ወደቤተመቅደስ መግባት ይችላሉ።

በሁሉም ነገሮች ብቁ የሆኑት በሙሉ ከቅዱስ ስርዓተ-ሀይማኖትና ስነስርዓቶች ጋር ለመተዋወቅ ወደቤተመቅደስ ለመግባት ይችላሉ።

ስለቤተመቀድስ በረከቶች እና በቤተመቅደስ ውስጥ፡ስለሚከናወኑት ስነስርዓቶች ቅድስና አንዳንድ ስሜት ካገኘህ በኋላ፣ ወደቤተመቅደስ ለመግባት ጌታ የሰጠውን ከፍተኛ የብቁነት መመዘኛ ትክክለኝነት አትጠራጠሩም።

ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ ለመግባት የፈቃድ ወረቀት ያስፈልጋችኋል። ይህ የመግቢያ ፈቃድ ወረቀት በትክክለኛው የቤተክርስትያን ባለስልጣን መፈረም አለበት። ብቁ የሆኑት ብቻ ወደቤተመቅደስ መግባት ይገባቸዋል። የአካባቢያችሁ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዘደንት የቤተመቅደስ ስነስርዓቶቻችሁን ከመቀበላችሁ በፊት ስለግለሰብ ብቁነታችሁ ጥያቄዎችን የማቅረብ ሀላፊነት አለው። ይህ የቃል ጥያቄ በጣም አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ይህም ከተሾመ የጌታ አገልጋይ ጋር የህትወታችሁን ንድፍ ለመመልከት እድል ይሰጣልና። በህይወታችሁ ትክክል ያልሆነ ነግር ካለ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ይህን ለማስተካከል ሊረዳችሁ ይችላል። በዚህ መሰረት፣ ከጌታ ፈቃድ ጋር ብቁነታችሁን ለማረጋገጥ ወይም ለመመስረት ለመረዳት ትችላላችሁ።

ወደ ቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ የሚገኝበት የቃል ጥያቄ የሚከናወነው ከቤተክርስትያኗ አባል እና ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር መካከል ብቻ ነው። በዚህም አባል ስለእርሱ ወይም ስለእርሷ ድርገት፣ ብቁነት፣ እና ለቤተክርስትያኗ እና ለባለስልጣኖቿ ስላለው ታማኝነት የሚፈትሹ ጥያቄዎችን ይጠየቃል። ግለሰቡም እርሱ ወይም እርሷ በተግባረ ጥሩ እና የጥበብ ቃላትን የሚጠብቁ፣ አስራትን የሚከፍሉ፣ በቤተክርስትያኗ ትምህርት ጋር በመስማማት የሚኖሩ፣ እና ከጥፋተኝ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ወይም ድጋፌ የሌላቸው እንደሆኑ ማረጋገጥ አለባቸው። ኤጲስ ቆጶሱ ቃል ጥያቄ ከሚያደርጉባቸው ሰዎች ጋር እነዚህን ነገሮች በሚስጥር መጠበቅ እንዳለበት መመሪያ ተሰጥቶታል።

ለኤጲስ ቆጶሱ ጥያቄዎች በቂ መልስ መስጠት ግለሰብ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለማግኘት ብቁነትን ይመሰርታል። አመልካች ትእዛዛትን የማይጠብቅ ከሆነ ወይም መስተካከል ያለበት ነገር በህይወታቸው ውስጥ ካላቸው፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት እውነተኛ ንስሀ መግባትን ማሳየታቸው አስፈላጊ ነው።

ኤጲስ ቆጶስ የቃል ጥያቄውን ከፈጸመ በኋላ፣ የቤተመቅደስን ስነስርዓት ከመቀበልህ በፊት የስቴክ ፕሬዘደንትም የቃል ጥያቄ ያቀርብልሀል።

የቤተመቅደስ ትምህርቶች ምሳሌአዊ ናቸው።

ወደቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሄድ በፊት፣ ወይም ክብዙ ጊዜዎች በኋላ፣ የቤተመቅደስ ትምህርቶች በምሳሌአዊ ሁኔታ እንደሚቀርቡ መረዳት ይረዳችኋል። መምህር አስተማሪ የሆነው ጌታ ብዙዎቹን ያስተማረውን በዚህ አይነት ነበር የሰጠው።

ቤተመቅደስ ታላቅ ትምህርት ቤት ነው። ይህም የመማሪያ ቤት ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ ሁኔታው ጥልቅ የሆኑ የመንፈስ ጉዳዮችን ለመማር የሚመች እንዲሆን ሆኖ ነው። የድሮው የአስራ ሑለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ካህን ጆን ኤ ውድሶው የታወቁ የዩንቨርስቲ ፕሬዘደንትና በአለም የታወቁ ምሁር ነበሩ። ለቤተመቅደስ ስራ ታላቅ አምልኮት ነበራቸው እና አንዳንዴ እንዲህ ይሉ ነበር፧

“የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች የቤተክርስትያኗ መሪዎች ሁልጊዜ የሚያስተምሩትን የደህንነት አላማ በሙሉ የሚያቅፍ ነው እና ለመረዳት አስቸጋሪ የሆኑትንም ያብራራል። የቤተመቅደስ ትምህርትን ከደህንነት ታላቅ አላማ ጋር ለማያያዝ ምንም ማዘባረቅ ወይም መጠማዘዝ የለም። የመንፈሳዊ ስጦታ የፍልስፍና ሙሉነት የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች እውነትነትን የሚያመለክት ነው። በተጨማሪም፣ ይህ የወንጌል አላማ በሙሉ መገምገም እና መብራራት የወንጌልን ሙሉ አካልን ለማስታወስ የሚያስችል ከሆኑ ውጤታማ ዘዴዎች የቤተመቅደስ አምልኮ አንዱ እንዲሆን ያደርገዋል። (“Temple Worship,” Utah Genealogical and Historical Magazine, መጋቢት 1921, 58)

ወደ ቤተመቅደስ ብትሄዱና በዚያ የምትማሩት መሳሌአዊ እንደሆነ ካስታወሳችሁ፣ በትክክለኛው አስተሳሰብ ገብታችሁ አስተያየታችሁ ሳይስፋፋ፣ ትንሽም ከፍ ከፍ ሳትሉ፣ ስለመንፈሳዊ ነገሮች እውቀታችሁ ሳያድግ ከዚያ መውጣት አትችሉም። የማስተማሪያው አላማ አስደናቂ ነው። ይህም የተነሳሳ ነው። አዋቂ አስተማሪው ጌታም እራሱ ደቀመዛሙርቱን ሁልጊዜም በምሳሌ ነው ያስተማረው—ይህም ለመረዳት አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮችን በምሳሌአዊ ቃላቶች ወክሎ መናገር ነው።

ቤተመቅደስ እራሱ ምሳሌአዊ ነው። ከቤተመቅደሶች አንዱን በሙሉ በመብራት ተሸፍኖ ካያችሁት፣ ምን ያህል አስደናቂ እንደሆነ ታውቃላችሁ። የጌታ ቤት በብርሀን ተሸፍኖ፣ ከጭለማ ብቅ ብሎ፣ ወደመንፈሳዊ ጭለማ ለመጥለቅ ለሚቀጥለው አለም ምልክት በመሆን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሀይል እና መነሳሻነት ምሳሌ ይሆናል።

ወደቤተመቅደስ ስትገቡ፣ በየመንገድ የምትለብሱትን ልብስ በቤተመቅደስ ነጭ ልብስ ትቀይሩታላችሁ። ልብስም የሚቀየረው እያንዳንዱ ሰው በብቻኛው ልብሳቸውን በሚቀይሩበት እና እቃዎቻቸውን በሚጠብቁበት በልብስ መቀየሪያ ውስጥ ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ መጠነኝነት በጥንቃቄ የሚጠበቅ ነው። ልብሶቻችሁን በማስቀመጫው ውስጥ ስታስቀምጡ፣ ከእነርሱም ጋር ሀሳባችሁን እና ጭንቀታችሁን ከእነርሱ ጋር ትተውታላችሁ። ነጭ ለብሳችሁ የብቻችሁ ከሆነው ልብስ መቀየሪያ ቦታ ትወጡ እና በአካባቢያችሁ እንደእናንተ ከለበሱት ጋር አንድነት እና የእኩልነት ስሜታ ይሰማችኋል።

የቤተመቅደስ ጋብቻ ከቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ከፍተኛው ነው።

ወደቤተመቅደስ ጋብቻ በጉጉት ለምትጠብቁትም በዚህ ጊዜ ምን እንደሚደርስ ለማወቅ ትፈልጉ ይሆናል። የመተሳሰሩን (የጋብቻን) ስነስርዓት ቃላት ከቤተመቅደስ ውጪ ቃል በቃል አንጠቅስም፣ ነገር ግን የመተሳሰሪያውን ክፍል በአመለካከቱ ቆንጆ፣ በመንፈስ ጸጥተኛ እና ሰላማዊ፣ እና በእዚያ በሚከናወነው ቅዱስ ስራም የተቀደሰ እንደሆነ ለመግለፅ እንችላለን።

የሚጋቡት ለመተሳሰሪያው ስነስርዓት ወደ መሰዊያው ሲመጡ፣ የሚያጋባቸው ሰው ምክርን ለመስጠት እና የሚጋቡት ወጣቶች ምክርን ለመቀበል እድል አላቸው። የሚጋቡት ወጣቶች በእዚያ ጊዜ ከሚሰሙት ሀሳቦች መካከል የሚቀጥሉት አንዳንዶቹ ናቸው።

“ዛሬ የጋብቻችሁ ቀን ነው። በጋብቻ ተነሳሺ ስሜታዎች ተይዛችኋል። ቤተመቅደሳት የተገነቡት ለእንደዚህ አይነት ስነስርዓቶች መሸሸጊያ ነው። በአለም ውስጥ አይደለንም። የአለም ነገሮች በእዚህ ውስጥ እና በእዚህ ውስጥ በምናደርገው ተፅዕኖ የላቸውም። ከአለም ወጥተን ወደ ጌታ ቤተመቅደስ ገብተናል። ይህም በህይወታችሁ ከሁሉም ነገሮች በላይ አስፈላጊ ሆኗል።

“መንፈሳችሁ ስጋዊ ሰውነት እንዲኖረው ባዘጋጁት ወላጆቻችሁ ወደምድር ተጋብዛችሁ ተወልዳችሁ ነበር። እያንዳንዳችሁም ተጠምቃችኋል። ጥምቀት ቅዱስ ስነስርዓት፣ የፅዳት ምሳሌ፣ የሞትና ትንሳኤ ምሳሌ፣ በአዲስ ህይወት የመምጣት ምሳሌ ነው። ንስሀ መግባትን እና የኃጥያት ስርየትን የሚያሰላስል ነው። የጌታ እራት የሆነው ቅዱስ ቁርባን የጥምቀት ቃል ኪዳን ማሳደሻ ነው፣ እና የምንኖርለት ከሆነም የኃጥያት ስርየት ለማግኘት እንችላለን።

“አንተ ሙሽራም በክህነት ስልጣን ተሹመሀል። በመጀመሪያ የአሮናዊ የክህነት ስልጣን ተረጋግጦልህ ነበረ እና ምናልባት በዚህም ስልጣኖች—እንደ ዲያቆን፣ አስተማሪ፣ እና ቄስ በመሆን አልፈህ ነበር። ከዛም የመልከጼደቅ የክህነት ስልጣንን ለመቀበል ብቁ የሆንክበት ጊዜ መጣ። ከፍተኛው የክህነት ስልጣን የሆነው ያ የክህነት ስልጣን ከእግዚአብሔር ቅዱስ ስነስርዓት በኩል የሆነው የክህነት ስልጣን ወይም የእግዚአብሔር ልጅ ስርዓት ቅዱስ የክህነት ስልጣን ተብሎ ይገለጻል (አልማ 13፧18; ሔለማን 8፧18Doctrine and Covenants 107፧2–4 ተመልከቱ) ። በክህነት ስልጣን ውስጥ ሀላፊነት ተሰጥቶሀል። አሁን ካህን ነህ።

“እያንዳንዳችሁ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ተቀብላችኋል። በዚያም የመንፈሳዊ ስጦታ ለዘለአለማዊ ችሎታችሁ መብት ተሰጥቷችኋል። ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በሙሉ ወደዚህ መሰዊያ እንደ ባልና ሚስት ለጊዜ እና ለዘለአለም ለመተሳሰር ለመምጣታችሁ ቀዳሚ ድርጊት እና መዘጋጃ ነበሩ። አሁን ህይወትን ለመፍጠር ነጻ ሆናችሁ፣ በአምልኮት እና በመስዋዕት ልጆችን ወደአለም ለማምጣት እና ለማሳደግ እናም በስጋዊ ህይወታቸው በደህንነት ለመርዳት እድል ለማግኘት፣ እናም አንድ ቀን እናንተ እንዳደረጋችሁት እነርሱም በእነዚህ ቅዱስ የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ለምሳተፍ ሲመጡ ለማየት እንድትችሉ ዘንድ ቤተሰብ ሆናችኋል።

“በፈቃድ መጥታችኋል እና ብቁ ሆናችሁ ተገኝታችኋል። እናንተ እርስ በራስ በጋብቻ ቃል ኪዳን መቀበላችሁ መመዘን የማይቻል በረከቶችን የያዘ ታላቅ ሀላፊነት ነው።

የመተሳሰር ሀይል በምድር እና በሰማይ ሊያስር ይችላል።

የቤተመቅደስ ስራ ትምህርት እና ታሪክን ከተረዳን፣ የማሰር ሀይል ምን እንደሆነ ልንረዳ እንችላለን። ለምን የማሰር ሀይል ስልጣን ቁልፎችን መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ በአዕምሮአችን መመልከት ይገባናል።

“ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነይሉታል? ብሎ ጠየቀ።…

“ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፣ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።

“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።

“የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴዎስ 16፧13፣ 16–19)።

ጴጥሮስ ቁልፎችን ይዞ ነበር። በምድር ለማሰር ወይም ለማተም ወይም በምድር ለመፍታት እናም በሰማይ ላይም እንዲሁ እንዲሆን ሀይል ያለው ስልጣን የሆነውን የማተሚያ ሀይል ጴጥሮስ ይዞት ነበር። እነዚህም ቁልፎች ለቤተክርስትያኗ —ለነቢይ፣ ለገላጭ፣ እና ለባለራዕይ ተገቢ የሆኑ ናቸው። ያም ቅዱስ የሆነው የመተሳሰር ሀይል በቤተክርስትያኗ ውስጥ ነው። የዚህን ስልጣን ታላቅ ትርጉም የሚያውቁት በቅድስና የሚያሰላስሉት ከዚህ በላይ ምንም የለም። ከዚህ በላይ በቅርብ የሚይዙትም የለም። በአንድ ጊዜ በምድር ላይ ይህን የማስተሳሰር ሀይል እንዲኖራቸው ተሰጥቷቸው የሚገኙ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው—በእያንዳንዱ ቤተመቅደስ ውስጥ ይህን የማስተሳሰር ሀይል የተሰጣቸው ወንድሞች አሉ። ይህም ከነቢይ፣ ከባለራዕይ፣ እና ከገላጭ እና ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ፕሬዘደንት ካልሆነ በስተቀር ማንም ለማግኘት አይችልም።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ሁልጊዜ እንዲህ ይጠየቅ ነበር “‘እነዚህን ስነስርዓቶች በሙሉ ሳይከናወኑ ለመዳን ይቻላል?’ እኔም ለሙሉ ደህንነት አይቻልም ብዬ እመልሳለሁ። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፣ ‘በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፣… ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ።” [ዮሀንስ 14፧2 ተመልከቱ] በዚህ ውስጥ ቤት ተብሎ የተጠራው መንግስት ተብሎ መተርጎም ነበረበት፤ ከሁሉም በላይ ታላቅ በሆነው ቤት ከፍ የሚደረግ ሰው የሰለስቲያል ህግን፣ እና ህግን በሙሉ፣ መከተል ይገባዋል” (in History of the Church, 6:184)።

የቤተመቅደስ ስራ የመንፈሳዊ ሀይል መንጭ ነው።

ቤተመቅደሳት በቤተክርስትያኗ ውስጥ ዋና የመንፈሳዊ ጥንካሬ ናቸው። እንደቤተክርስትያን እና እንደ ግለሰብ በእነዚህ በተቀደሱ እና በተነሳሱ ስራዎች ለመሳተፍ ስንፈልግ ጠላት ሊያሰናክለን እንደሚጥር ጠብቁ። ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን እና ለቤተክርስትያኗ በሙሉ የብዙ መንፈሳዊ ሀይሎች ምንጭ ስለሆነ የቤተመቅደስ ስራ ብዙ ተቃዋሚነትን ያመጣል።

በሎገን ዩታ ቤተመቅደስ የመሰረት ድንጋይ መመረቂያ ላይ፣ በዚያ ጊዜ ፕሬዘደንት ጆየቀዳሚ አመራር አባል የነበሩት ርጅ ኪው ካነን ይህን አሉ?

“ለቤተመቅደስ የተቀመጠው እያንዳንዱ የመሰረት ድንጋይ፣ እና ለቅዱስ የክህነት ስልጣኑ በገለጸው ስርዓት መሰረት የተፈጸመው እያንዳንዱ ቤተመቅደስ በምድር ላይ ሰይጣን ያለውን ሀይል ይቀንሳል፣ እናም አምላክነትን እና የእግዚአብሔርን ሀይል ያሳድጋል፣ ለእኛም ጥቅም ሰማያትን በታላቅ ሀይል ያነቃንቃል፣ የዘለአለማዊ አምላኮችን እና ከእነርሱ ጋር የሚኖሩትን በረከቶችን ይለምናል እናም ይጠራል (“The Logan Temple,” ውስጥ Millennial Star, ህዳር 12, 1877, 743)።

የቤተክርስትያኗ አባላት በተቸገሩበት ጊዜ ወይም በአዕምሮአቸው ላይ ታላቅ አስፈላጊ ውሳኔዎች በሚጫኑባቸው ጊዜ፣ ወደቤተመቅደስ መሄዳቸው የተላመደ ነገር ነው። ሀሳቦቻችንን ለመውሰድ ጥሩ የሆነ ቦታ ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ መንፈሳዊ አስተያየትን ለመቀበል እንችላለን። በዚያም በቤተመቅደስ አገልግሎት ጊዜ “ከአለም ውጪ” የሆንን ነን።

አንዳንዴም አዕምሮአችን በችግሮች የተወረሩ ይሆናሉ እና በጣም ብዙ ነገሮች የእኛን ሀሳብ ለመያዝ ስለሚጣጣሩ በግልፅ ለማሰብ እና በግልፅ ለማየት አንችልም። በቤተመቅደስ ውስጥ በሀሳብ የሚስበን ነገሮች የሚረጋጉ፣ ጭጋግ እና ጉምም የሚነሱ ይመስላሉ፣ እናም ከዚህ በፊት ለማየት የማንችላቸው ነገሮችን ለማየት እንችላለን እናም ከዚህ በፊት የማናውቃቸው ከችግር የምንወጣባቸውን መንገዶችንም እናያለን።

በቤተመቅደሳት ቅዱስ ስነስርዓት ስራዎች ስንሳተፍም ጌታ ይባርከናል። በዚያ ያሉት በረከቶችም በቤተመቅደስ አገልግሎት ላይ ብቻ የተመደቡ አይደሉም። በምናደርጋቸው ነገሮች ላይ ሁሉ እንባረካለን።

የቤተመቅደስ አገልግሎታችን በጋሻ እና በመጠበቂያ ይሸፍኑናል።

በዚህች ቤተክርስትያን ውስጥ ከቤተመቅደስ ስራ እና ይህን ከሚረዳው የቤተሰብ ታሪክ ፍለጋ በላይ የሚጠብቅ ምንም ስራ የለም። ከዚህ ስራ በላይ በመንፈስ የሚያጣራ የለም። ከዚህ በላይ ሀይል የሚሰጠን ምንም የምንሰራው ስራ የለም። ከዚህ በላይ ታላቅ የሆነ የጻድቅነት መሰረት ያለው ምንም የምንሰራው ስራ የለም።

የቤተመቅደስ አገልግሎታችን፣ እንደግለሰብ እና እንደህዝብ፣ በጋሻ እና በመጠበቂያ ይሸፍኑናል።

ስለዚህ ወደቤተመቅደስ ኑ—ኑ እና በረከቶቻችሁን ተቀበሉ። ይህም የተቀደሰ ስራ ነው።

አትም