2011 (እ.አ.አ)
ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም
ኤፕረል 2011


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሚያዝያ 2011 (እ.አ.አ)

ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም

ዛሬ በሀይቅ ዳርቻ የምትገኘው፣ በአዳኝ የጋለሊ አገልግሎች መሃከለኛ በነበረችው ከተማ በቅፍርናሆም የቀረው የፈረሱ ቤቶች ብቻ ናቸው። በምኩራብ ሰበከ፣ በባህር ዳር አስተማረ፣ እናም በቤቶች ውስጥ ፈወሰ።

በአገልግሎቱ መጀመሪያ፣ ኢየሱስ ከኢሳይያስ ጠቀሰ፧ “የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል” (ኢሳይያስ 61፧1፤ ደግሞም ሉቃስ 4፧18 ተመልከቱ)—ይህም የእግዚአብሔርን ወንዶችና ሴት ልጆች ለማዳን የተመደበ መለኮታዊ አላማን በግልፅ የታወጀበት ነበር።

ነገር ግን በገሊላ የኢየሱስ የሰበከው ገና የሁሉም መጀመሪያ ነበር። የሰው ልጅ በጎልጎታ ኮረብታ ላይ መጠበቅ ያለበት የሚያሰቅቅ ቀጠሮ ነበረው።

ከመጨረሻው እራት በኋላ በገትሰመኔ የአትክልት ስፍራ ተያዘ፣ በደቀ መዛሙርቱ ተካደ፣ ተተፋበት፣ በፍርድ ቤት ፊት ቀረበ፣ እና ተሳለቁበት፣ ኢየሱስም ከታላቅ መስቀሉ በታች ተንገዳገደ። ከድል ወደ ክህደት፣ ድብደባ፣ እና በመስቀል ላይ ወደመሰቀል ሄደ።

በ“ቅዱስ ከተማ” መዝሙሩ ቃላትም፧

ትእይንቱ ተቀየረ። …

ጠዋቱ የቀዘቀዘ እና ብርድ ነበር፣

የመስቀሉ ጥላ ሲነሳ

በብቸኛው ኮረብታ ላይ።1

ለእኛ የሰማይ አባት ልጁን አሳልፎ ሰጠ። ለእኛ ታላቁ ወንድማችን ህይወቱን ሰጠ።

በመጨረሻው ጊዜም መምህር ለመመለስ ይችል ነበር። ነገር ግን አልተመለሰም። ሁሉንም ነገሮች፣ የሰው ዘርን፣ ምድርን፣ እና በዚህ ይኖሩ የነበሩ ህይወቶችን በሙሉ ያድን ዘንድ ከሁሉም ነገሮች በታች አለፈ።

ለምታለቅሰው ለመግደላዊት ማርያም እና ለሌላዋ ማርያም የጌታቸውን አስካሬን ለመንከባከብ ወደ መቃብር በሚቀርቡበት ጊዜ መላእክቱ ከተናገራቸው ቃላት በላይ ለእኔ ታላቅ ትርጉም ያለው ቃል በክርስቲያን አለም የለም፧ “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም (ሉቃስ 24፧5–6)።

በዚህ አዋጅ፣ ኖረው የሞቱት፣ አሁን የሚኖሩት እና አንድ ቀን የሚሞቱት፣ እና ገና ያለተወለዱት እና ገና ያልሞቱት ድነው ነበር።

ክርስቶስ በመቃብር ላይ በነበረው ድል፣ እኛም ከሞት እንነሳለን። ይህም የነፍስ ደህንነት ነው። ጳውሎስ እንደጻፈው፧

“ደግሞ ሰማያዊ አካል አለ፥ ምድራዊም አካል አለ፤ ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር ልዩ ነው፥ የምድራዊም አካል ክብር ልዩ ነው።

“የፀሐይ ክብር አንድ ነው የጨረቃም ክብር ሌላ ነው የከዋክብትም ክብር ሌላ ነው፤ በክብር አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ ይለያልና።

“የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው” (1 ቆሮንቶስ 15፧40–42)።

የምንፈልገውም የሰለስቲያል ክብርን ነው። ለመኖር የምንፈልገውም በእግዚአብሔር ፊት ነው። አባል ለመሆን የምንፈልገውም በዘለአለማዊ ቤተሰብ ውስጥ ነው።

ሁላችንን ከዘለአለማዊ ሞት እያንዳንዳችንን ስላዳነን፣ እርሱ የእውነት አስተማሪ፣ ግን ከአስተማሪ በላይ እንደነበረ እመሰክራለሁ። እርሱ የፍጹም ህይወት ምሳሌ፣ ግን ከምሳሌ በላይ ነው። እርሱም ታላቁ ሀኪም፣ ግን ከሀኪም በላይ ነው። እርሱም “እኔ ፊተኛውና መጨረሻው ነኝ፤ እኔ ህያው ነኝ፣ የተገደልኩትም እኔ ነኝ፤ እኔም በአብ ዘንድ ጠበቃችሁ ነኝ” (D&C 110:4) ብሎ ያወጀው የአለም አዳኝ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የሰላም ልዑል፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እንዲሁም ከሞት የተነሳው ጌታ ነው።

“እንዴት ይህ አረፍተ ነገር ጣፋች ደስታ ይሰጣል፧ “ቤዛዬ ህያው እንደሆነ አውቃለሁ!’”2

ስለዚህ እመሰክራለሁ።

ማስታወሻዎች

  1. ፍሬድሪክ ኢ ወዘርሊ “The Holy City” (1892)።

  2. “I Know That My Redeemer Lives,” መዝሙሮች፣ ቁጥር 36።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

ጥሩ አስተማሪዎች ከሚያስተምሯቸው መካከል አንድነትን ያበረታታሉ። ሰዎች አስተያየታቸውን ሲካፈሉ እና አንዱ በሌላ በክብር ሲያዳምጡ፣ ለመማር ጥሩ የሆነውን አካባቢ ሊደሰቱበት ብቻ ሳይሆን አንድም ይሆናሉ (ደግሞም Teaching, No Greater Call [1999]፣ 63)። እናንተ እና እነርሱ በአምልኮት ስለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ ምስክር ስትሰጡ በምታስተምሯቸው መካከል አንድነት ያድጋል። እንደዚህ አይነት አንድነት ቤተሰቦች “የዘለአለም ቤተሰብ እንዲሆኑ” ፕሬዘደንት ሞንሰን የሰጡትን ምክር እንዲከተሉ ይረዳል።

አትም