የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሚያዝያ 2010 (እ.አ.አ)
የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማ
ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።
አመራራችን በመጀመሪያ ጊዜ በተጠሩበት ጊዜ፣ ስለየሴቶች መረዳጃ ማህበር ታሪክ አንዳንድ የምናጠናቸው ተሰጥተውን ነበር። የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማ ምን እንደሆነና ጌታ ምን እንድናደርግ እንደሚፈልገን ለማወቅ በጸሎት አጠናናቸው። በጌታ እንደተደራጀችው፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማ ሴት ልጆቹን ለዘለአለም ህይወት በረከቶች እንዲዘጋጁ ለማደራጀት፣ ለማስተማር እና ለማነሳሳት ነው።
ይህን የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማ ለማሟላት፣ ጌታ እያንዳንዷን እህት እና ድርጅቱን በሙሉ ሀላፊነት ሰጥቷል።
እምነትን እና የግል ጻድቅነትን ማሳደግ።
ቤተሰቦችንና ቤቶችን ማጠናከር።
ጌታን እና ልጆቹን በማገልገል እርዳታን መስጠት።
ይህን ስራ በጌታ መንገድ የምንሰራው የግል ራዕይን በመፈለግ፣ በመቀበል፣ እና በዚህም በመስራት ነው። ያለግል ራዕይ፣ ውጤታማ ለመሆን አንችልም። የግል ራዕይን ካዳመጥን፣ ልንወድቅ አንችልም። ነቢዩ ኔፊ መንፈስ ቅዱስ “ማድረግ የሚገባን ነገሮች ሁሉ” (2 ኔፊ32:5) እንደሚያሳየን አስተምሮናል። የመንፈስን ድምፅ ለመስማት እራሳችንን ጸጥተኛ መሆን ይገባናል።
እህቶች፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ለመርዳት እና ለጌታ መምጣት ለመዘጋጀት የምናደርጋቸው ዋና ስራዎች አሉን። በእርግጥም፣ የጌታ ስራ ያለሴት ልጆቹ እርዳታ ለመከናወን አይችልም። በዚህም ምክንያት፣ ጌታ ቁርባናችንን እንድንጨምርበት ይጠብቅብናል። የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማን እንድናሟላም ይጠብቅብናል።
ጁሊ ቤክ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት።
ከቅዱስ መጻህፍት
ከታሪካችን
በሰኔ 9 ቀን 1842 (እ.አ.አ) የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ላይ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለእህቶች ማህበሩ “ደሀዎችን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን ነፍሳትን ለማዳን ነው” ብሎ አስተምሯቸው ነበር። 1 ይህም የሴቶች መረዳጃ ማህበርን መንፈሳዊና ምድራዊ አላማን በታሪኳ ውስጥ አንጸባርቋል። በ1906 (እ.አ.አ) ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ (1838–1918) እንዳስተማሩት፧ “[የሴቶች መረዳጃ ማህበር] ደሀዎችን የታመሙትን እና እርዳታ ፈላጊዎችን መርዳታ ብቻ ሳይሆን፣ የዚህ ታላቅ የሆነው ሀላፊነት ለፅዮን እናቶችና እህቶች መንፈሳዊ ደህንነት እና መዳን መጠበቅ፤ ማንኛዋም ችላ እንዳትባል፣ ግን ሁሉም ከመጥፎ እድል፣ ከመአት፣ ከጭለማ ሀይል፣ እና አለም ከሚያስፈራሩ ጥፋቶች እንዲጠበቁ ማድረግ ነው።”2 በ2001 (እ.አ.አ) የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ካህን ኤም ራስል ባለርድ ደግመው እንደተናገሩት፣ “በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን የገባች እያንዳንዷ እህት እያንዳንዱን መንፈስ ለመርዳት፣ የአለም ሴቶችን ለመምራት፣ የፅዮን ቤቶችን ለማጠናከር፣ እና የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት መለኮታዊ ሀላፊነት አላት።”3
© 2011 በ Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/10 (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/10 (እ.አ.አ)። Visiting Teaching Message, April 2011 ትርጉም። Amharic። 09764 506