2011 (እ.አ.አ)
የመፅሐፈ ሞርሞን ውድ ቃል ኪዳኖች
ኦክተውበር 2011


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥቅምት 2011 (እ.አ.አ)

የመፅሐፈ ሞርሞን ውድ ቃል ኪዳኖች

ከብዙ አመት በፊት በህይወት እና በሞት መካከል ባለ አንድ ወጣት አባት መኝታ አጠገብ ቆሜ ነበር። የምትጨነቀው ባለቤቱና ሁለቱ ልጆቻቸው በአጠገባችን ቆመው ነበር። እጄን ያዘ እናም በሚለምን አመለካከት፣ “ኤጲስ ቆጶስ፣ ለሞት እንደቀረብኩኝ አውቃለሁ። ስሞት ለመንፈሴ ምን እንደሚሆንበት ንገሩኝ” አለኝ።

ለሰማይ አመራር የጸጥታ ጸሎት አቀረብኩኝ እናም በመኝታው አጠገብ በጠረጴዛው ላይ ቅዱሳት መጻህፍትን አየሁ። መፅሐፉን አነሳሁና ገጾቹን ከፈትኩኝ። ወዲያውም፣ እኔ ምንም እጥረት ሳላደርግ፣ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በአልማ 40ኛው ምዕራፍ እንደከፈትኩት እንደቆምኩኝ ተመለከትኩኝ። እነዚህን ቃላት አነበብኩለት፥

“እንግዲህ፣ በሞትና በትንሣኤ መካከል የነፍስ ሁኔታን በተመለከተ — እነሆ፣ የሰዎች መንፈስ ሁሉ ከዚህ ሟች ከሆነው ሰውነታቸው እንደተለየ፣ አዎን፣ የሰዎች መንፈስ ሁሉ፣ … ህይወትን ወደ ሰጣቸው ወደ እግዚአብሔር እንደሚወሰድ በመልአኩ አማካኝነት እንዳውቀው ተደረገ።

እናም እንዲህ ሆነ የፃድቃኖች መንፈስ፣ ከሁሉም ችግር፣ ውጣ ውረድና ሀዘን ወደሚያርፉበት፣ ገነት ተብላ ወደምትጠራው፣ የእረፍት ቦታ፣ የሰላም ቦታ ውስጥ ወደ ደስታ ሁኔታ ይገባሉ” (Alma 40:11–12)።

ስለትንሳኤ ማንበብ ስቀጥል፣ የወጣቱ ሰው መብራት ጀመረ እናም ፈገግታ በከንፈሩ ላይ ታየ። ጉብኝቴን ስፈጽምም፣ ይህን አስደሳች ቤተሰብ ደህና ሁኑ አልኩኝ።

በሚቀጥለው ጊዜ ባለቤቱን እና ልጆቹን ያየኋቸው በመቃብሩ ጊዜ ነበር። ወጣቱ ሰው ስለእውነት ስለለመነበት እና ከመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ለጥያቀው መልስ ስላገኘበት ምሽት አሰብኩኝ።

ከመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ “የምድሪቷን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ካገለገልን” (ኤተር 2፥12) ድረስ ከሰላም፣ ከነጻነት፣ እና በረከቶች የተስፋ ቃላት በተጨማሪ ሌሎች ውድ የተስፋ ቃላት ይመጣሉ።

ከገጾቹም “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት [ለ]ሚጠብቁትም” “የማያልቅ ደስታ የተስፋ ቃል ይመጣል። እነሆም እነርሱ በሁሉም ነገሮች፣ ለጊዜያዊም ሆነ ለመንፈሳዊ፣ የተባረኩ ናቸውና” (ሞስያ 2፥41)።

ከገጾቹም ውድ ወንድ እና ሴት ልጆቹን ለማዳን “በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ” ለሚሆኑትም “ለማስተዋል የማይቻል ደስታ” ቃል ኪዳን ይመጣል (አልማ 28:8; 29:9)።

ከገጾቹም በታላቁ በአለም አቀፍ የሚስዮን ጥረታችን እያከናወንነው ባለው ስራ የተበተኑት እስራኤል እንደሚሰበሰቡ የተስፋ ቃል ይመጣል (3 ኔፊ 16፤ 21–22 ተመልከቱ)።

ከገጾቹም በተቀደሰው ኢየሱስ ክርስቶች ስም ወደ አብ ስንጸልይ፣ ቤተሰቦቻችን እንደሚባረኩ የተስፋ ቃል ይመጣል (3 ኔፊ 18:21 ተመልከቱ)።

ገጾቹንም በማጥናት ተጨማሪ የጌታ መንፈስ፣ ትእዛዛቱን በማክበር ለመሄድ የሚወሰንበት ጥንካሬ፣ እናም የእግዚአብሔር ልጅ ህያውነት ጠንካራ ምስክር “ወደ ህይወታችሁ እና ወደ ቤቶቻችሁ እንደሚመጣ” የተተነበየው የተስፋ ቃል መሟላት ይመጣል።1

ከመፅሐፈ ሞርሞን ገጾችም በጸሎት፣ በእውነተኛ ስሜታ፣ እና በክርስቶስ በማመን፣ “በመንፈስ ቅዱስ ሀይል” ስለእነዚህ የተስፋ ቃላት እምነታ ለማወቅ እንደምንችል የመሮኒ የተስፋ ቃል ይመጣል (Moroni 10:4–5 ተመልከቱ)።

ከሌሎች የኋለኛው ቀን ነቢያት ጋር፣ “በምድር ላይ ካሉት ማንኛውም መጽሀፎች በላይ ትክክል” ስለሆነው፣2 እንዲሁም ስለመፅሐፈ ሞርሞን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ተጨማሪ ምስክር፣ እውነትነት እመሰክራለሁ። መልእክቱ አለምን ያቅፋል እናም ለሚያነቡትን ስለእውነት እውቀት ያመጣል። መፅሐፈ ሞርሞን ህይወቶችን እንደሚቀይር ምስክርነቴ ነው። እያንዳንዳችን እናንበው እናም ደጋግመንም እናንበው። ስለውድ የተስፋ ቃላቱም ከእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ጋር ምስክራችንን በደስታ እንካፈል።

ማስታወሻዎች

  1. ጎርደን ቢ ሒንክሊ፣ “A Testimony Vibrant and True,” Liahona, ነሀሴ 2005፣ 6.

  2. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ስሚዝ [2007 (እ.አ.አ)]፣ 64

ከዚህ መልእክት ማስተማር

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ “የሰው ቤተሰብ የሚያጋጥማቸውን ሁሉንም የሚያምታቱ ነገሮችን እና ሁሉንም ችግሮች እና ሁሉንም ፈተናዎች መፍትሄ የሚሰጥ የእውነት መሰረታዊ መመሪያዎችን እናገኛለን” (Teaching, No Greater Call [1999]፣ 51)። የፕሬዘደንት ሞንሰንን መልእክት ከቤተሰብ ጋር ስትካፈሉ፣ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የጠኮሟቸውን “ውድ የተስፋ ቃላትን” እንዲያዳምጡ ጋብዟቸው። ለእናንተ ትርጉም ስላለው የመፅሐፈ ሞርሞን የተስፋ ቃል ለመካፈል ትችላላችሁ።

አትም