2011 (እ.አ.አ)
ካልተጠራጠርን
ኦክተውበር 2011


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ጥቅምት 2011 (እ.አ.አ)

ካልተጠራጠርን

ጁሊ ቤክ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት።

ይህን መልእክት አጥኑ፣ እና ትክክል በሆነውም ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩ። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ደፋር፣ ብርቱ፣ እና ጠንካራ ወጣት ወንዶች ምሳሌ እናንባለን። “አዎን የእውነት እና የጥሞና ሰዎች ነበሩ፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዲጠብቁና በፊቱም ሀበቅንነት እንደሚራመዱ ተምረዋልና” (አልማ 53፥21)። እነዚህ ታማኝ ወጣት ወንዶች ለምሳሌአቸው እና አስተማሪያቸው ለሆኑት እናቶቻቸው ድርጊት ምስጋና ሰጥተው ነበር።

የሔላማን ጀግናዎች እናቶች ከእኛ ዘመን በብዙ በማይለይ ዘመን ይኖሩ ነበር። ሁኔታቸው አስቸጋሩና አደገኛ ነበር፣ እናም ወጣቶቹም የስጋዊና መንፈሳዊ ነጻነትን ለመከራከር ተጠርተው ነበር። ዛሬ በምንኖርበት አለም “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” (Ephesians 6:12)።

አስቸጋሪ ጊዜዎች “ካልተጠራጠሩ፣ እግዚአብሔር ያድናቸዋል” (አልማ 56:47) የሚለውን የሔላማን ጀግናዎች እውነትን የሚያስተምሩ ጠንካራ ወላጆችን እና ምሳሌዎችን ይጠራል። ዛሬ ይህን እውነት ለማስተማር እና ምሳሌ መሆን ንቃት ያስፈልገዋል። ነገር ግን፣ መፍራት አያስፈልገንም። ማን እንደሆንን እና እግዚአብሔር ማን እንደሆነና ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንደገባን ስናውቅ፣ እንደ ጀግናዎቹ እናቶች እኛም ለመልካም ታላቅ ተፅዕኖ ይኖረናል።

እያንዳንዱ የሔላማን 2 ሺህ 60ጀግናዎች እናቶቻቸው ተፅዕኖ በእነርሱ ላይ ይኖራቸ ነበር። ነገር ግን እነዚህ እናቶች ብቻቸውን አልነበረም የሰሩት። ከሌሎች ጻድቅ ወንዶችና ሴቶች ጋር አብረው፣ እነዚህ እናቶች እምነታቸውን እና ምሳሌአቸውን የቃል ኪዳን ሀይልን ለማስተማር ተባብረዋል። እነዚህ የእዚያ ቀን ወጣቶች ወላጆቻቸው በጦርነት ላለመሳተፍ ስለገቡት ቃል ኪዳን ተረድተው ነበር። እናም የማይቻል ሲመስልም፣ አፍቃሪው የሰማይ አባት እነዚህ ወላጆች ቃል ኪዳናቸውን ለማክበር እና ነጻነታቸውን ለመጠበቅ የሚችሉበት መንገድ ከፈተላቸው (አልማ 56:5–9 ተመልከቱ)። የእኛ እና የዎርዳችን፣ የቅርንጫፎቻችን፣ የጎረቤቶቻችን፣ እና የህብረተሰቦቻችን ልጆች እና ወጣቶች ቃል ኪዳን ማክበርን እንዲገባቸውና እንዲደግፉ እኛም እንደዚህ ቃል ኪዳኖቻችንን ማክበር አለብን።

ቃል ኪዳኖቻችንን ስናከብር፣ የሰማይ አባት መንገድ ያዘጋጅልናል። ቃል ኪዳኖቻችንን በትክክል መኖር አለብን። ለምሳሌ በጸሎታችን፣ በቅዱሳት መጻህፍት ጥናታችን፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ መያዝ፣ በምግባረ ጥሩ አለባበስ፣ ሰንበትን በማክበር ትክክለኛ ለመሆን እንችላለን። ይህን ስናደርግ፣ ልጆቻችን “እናቶቻችን እንዳወቁት አንጠራጠርም” በማለት ለማወቅና ለማለት ይችላሉ (Alma 56:48)።

ጥንካሬአቸው ከጌታ የኃጢያት ክፍያ እንደሚመጣ የሚያውቁ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች በአስቸጋሪና ተስፋ በሚያስቆርጡ ጊዜዎች ተስፋ አይቆርጡም። እንደ ቃል ኪዳን ጠባቂዎች፣ አንድ ቀን ስለዚህ ትውልድ “እንዲህ ያለን ታላቅ ድፍረትን በጭራሽ መካከል አላየሁም” ለማለት እንድንችል ልጆችን እና ወጣቶችን ለመደገፍ፣ ለመንከባከብ፣ እና ለመጠበቅ የተለየ ችሎታ አለን” (Alma 56:45)።

ከቅዱሳት መጻህፍት

አልማ 53፤ 56–58

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. በሚያድጉትን ትውልዶች ላይ ተፅዕኖ እንዲኖራቸው ያላቸው ሀይል ለማወቅና ለመጠቀም እንዲችሉ እንዴት እህቶቼን ለመርዳት እችላለሁ?

  2. በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በዛሬ ለሚያጋጥሙኝ ፈተናዎች መልስ ለማግኘት ምን ማነሳሻ አገኛለሁ?

አትም