2011 (እ.አ.አ)
በቅዱስ ቦታዎች ላይ ቁሙ
ኖቬምበር 2011


በቅዱስ ቦታዎች ላይ ቁሙ

እኛ ወደ እርሱ በምንጸልይበት እና እርሱ በሚያነሳሳን መንገድ ከሰማይ አባታችን ጋር መነጋገራችን የህይወትን ፈተናዎች ለመቋቋም እንድንችል አስፈላጊ ናቸው።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በእዚህ ጠዋት ጥሩ መልእክቶችን አዳምጠናል፣ እናም የተሳተፉትን አመሰግናለሁ። ሽማግሌ ሮበርት ዲ ሄልስ ተሽሏቸው ከእኛ ጋር በመገኘታቸው ተደስተናል። ቧብ፣ እንወድሀለን።

በዚህ ጠዋት ምን እንደምላችሁ ሳሰላስል፣ አስፈላጊ እና ጊዜአዊ የሆኑ ሀሳቦችንና ስሜታዎችን ከእናንተ ጋር ለመካፈል ተነሳስቼ ነበር። በንግግሬ እንድመራም እጸልያለሁ።

በዚህች ምድር ለ84 አመት ለመኖር ችያለሁ። አስተያየት እንዲኖራችሁ፣ የተወለድኩት ቻርልስ ሊንድበርግከኒው ዮርክ ወደ ፓሪስ ብቻውን በአውሮፕላን ለመብረር በተቻለበት አመት ነበር። ከእዚያ ጊዜ በሚቀጥሉት 84 አመታት ብዙ ነገሮች ተቀይረው ነበር። ሰው ወደ ጨረቃ ደርሰው ተመልሰዋል። በእርግጥም፣ የትላልትና የልብ እልም የአሁን እውነታ ሆኗል። ያም እውነት በቴክኖሎጂ ምክንያት በፍጥነት እየተቀየረ፣ ይህን ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል። የሚደወል ስልክ እና መተየቢያ መኪና ለምናስታውሰው፣ የአሁኑ ቴክኖሎግይ ከሚያስደንቅ በላይ ነው።

በፍጥነት በመቀየር ያለውም የህብረተሰብ ምግባረ ጥሩነት አመለካከት ነው። በፊት ትክክል ያልነበሩት እና ግብረገባዊ ያልሆኑት ነገሮች፣ አሁን ተቀባይነት ማግኘት ጀምረዋል።

በቅርብ የእንግሊዝ ዋና መምህር ጆናተን ሳክስ Wall Street Journal የጻፉትን አኝቀፅ አንብቤ ነበር። ከሌሎች በተጨማሪ ይህን ጽፏል፣ “በ1960 ዓ/ም በምስራቅ ህብረተሰቦች በሙሉ በባህል ጸባያቸውን የሚቆጣጠሩበትን የተዉበት የምግባረ ጥሩነት ለውጥ ነበረ። Beatles እንደዘፈኑት፣ የሚያስፈልገው ፍቅር ብቻ ነው።የአይሁድ-ክርስቲያን የምግባረ ጥሩነት ደንብ ተጣለ። በዚህም ቦታ “የሚጠቅምህን አድርጉ። አስራቱ ቃላት የተጻፉት እንደ አስሩ ሀሳቦች ነውና” የሚል አባባል መጣ።

መምህር ሳክስ በመቀጠል እንዲህ ጸጸታቸውን ገልጸዋል፥

“ገንዘባችንን እንዳባከንነው መሰረታዊ ምግባረ ጥሩነታችንን እናባክናቸዋለን። …

“ሀይማኖት የድሮ ነገር ብቻ የሆነበት የአለም ታላቅ ክፍሎች አሉ እናም ለዚህ ነገሮች ብቁ ስለሆንን ግዛው፣ ገንዘብ አውጣ፣ ልበሰው፣ እናም የሚንጸባረቀውን አሳዩ የሚለውን ባህን የሚቃወም ድምጽ የለም። መልእክትም ምግባረ ጥሩነት ጊዜው ያለፈበት ነው፣ ህሊና ለደካማዎች ነው፣ እና ከሁሉ አስፈላጊ የሆነው ትእዛዝ ‘አይታወቅብህም” የሚል ነው።’”1

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ አለማችንን የሚገልጽ ነው። መጨነቅ አለብን እናም በዚህ አለም እንዴት ለመኖር እንደምንችል በሀሳብ እንጥለቀለቃለን? አይደለም። በህይወታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አለን፣ እናም ምግባረ ጥሩነት ጊዜው ያለፈ ነገር እንዳልሆነ፣ ህሊና እንዳለን፣ እናም ለስራችን ሀላፊነት እንዳለን እናውቃለን።

ምንም እንኳን አለም ቢቀየርም፣ የእግዚአብሔር ህግጋት ቁም ናቸው። አልተቀየሩም፤ አይቀየሩም። አስራቱ ቃላት ትእዛዛት ናቸው። እንድናስብባቸው የተሰጡን አይደሉም። እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች በሰጣቸው ጊዜ አስፈላጊ እንደነበሩ፣ አሁንም አስፈላጊ ናቸው። ካዳመጥን፣ የእክዚአብሔር ድምፅ በእዚህ እና አሁን ሲያናግረን እንሰማለን፥

“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።

 … “የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።

“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ …

“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። …

“አባትህንና እናትህን አክብር፤ …

“አትግደል።

“አታመንዝር።

“አትስረቅ።

 “…በሐሰት አትመስክር።

“አትመኝ።”2

የተግባራችን የተወሰነ ነው፣ እናም የምንክራከርበት አይደለም። የሚገኘው በአስሩ ቃላት ብቻ ሳይሆን፣ አዳኝ በምድር በተራመደበት ጊዜ በተሰጠን በተራራ ስብከት ውስጥ የሚገኝ ነው። ባስተማራቸው ውስጥ ሁሉ ይገኛል። በአሁን ቀን ራዕይ ውስጥም ይገኛል።

የሰማይ አባታችን ትላንትናም፣ ዛሬም፣ እና ለዘለአለም አንድ ነው። ነቢዩ ሞርሞን እንደነገረን፣ እግዚአብሔር “ከዘለአለም እስከ ዘለዓለም የማይቀየር ነው።”3 ሁሉም ነገሮች የሚቀየሩ በሚመስሉበት በዚህ አለም ውስጥ፣ የማይቀየር መሆኑ ለመመካት የምንችልበት፣ አጥብቀን የምንይዘውና ደህና የምንሆንበት የመረጋጋት ምንጭ ነው፣ አለበለዚያም አደገኛ ወደሆነው ቦታ እንጠረጋለን።

አንዳንዴ በአለም ውስጥ ያሉት ከእናንተ በላይ ተደሳች የሚሆኑ ይመስላችሁ ይሆናል። አንዳንዶቻችሁ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ባሉት ተግባሮች የተገደባችሁ ይመስላችኋል። ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አዳኝን ስንከተል እና ትእዛዛትን ስናከብር ወደእኛ መምጣት ከሚችለው መንፈስ ከሚያመጣልን በላይ በህይወታችን ተጨማሪ ደስታና በነፍሳችን ውስጥ ተጨማሪ ሰላም ሊያመጣልን የሚችል ምንም እንደሌለ አውጅላችኋለሁ። አብዛኛዎቹ የአለም ሰዎች በሚሳተፉበት ነገሮች ውስጥ፡መንፈስ ሊገኝበት አይችልም። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ገልጿል “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።”4 “ፍጥረታዊ ሰው” ማንኛችንንም ሊጠቁም ይችላል።

መንፈሳዊ ከሆነው ነገሮች ፈቀቅ ካለው አለም ውስጥ በመኖር መንጠንቀቅ አለብን። ከመሰረታዊ መመሪያችን ጋር የማይስማማውን ማንኛውም ነገር ማስወገድ፣ በዚህም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የዘለአለም ህይወት የማግኘት ፍላጎታችንን ለማጣት እምቢ እንበል። በጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች ይኖሩብናል፣ ምክንያቱም በስጋዊ አጋጣሚ የማናመልጣቸው ናቸውና። ነገር ግን፣ በህይወታችን መሰረት ውስጥ ወንጌልን ካለ እና በልባችን ውስጥ የአዳኝ ፍቅር አከን፣ እነዚህን ለመቋቋም፣ ከእነዚህ ለመማር፣ እናም ለማሸነፍ በደንብ የተዘጋጀን ነን። ነቢዩ ኢሳይያስ እንደገለጸው፣ “የጽድቅም ሥራ ሰላም፥ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።”5

በአለም ውስጥ ብንሆንም የአለም ክፍል ላለመሆን፣ ከሰማይ አባታችን ጋረ በጸሎት መገናኘታችን አስፈላጊ ነው። ይህን እንድናደርግ ይፈልገናል፤ ጸሎታችንን መልስ ይሰጣቸዋል። በ3 ኔፊ 18 ውስጥ አዳኝ እንደገሰጸን፣ “ …እንዳትፈተኑ ዘወትር መንቃት እናም መፀለይ አለባችሁ፤ ምክንያቱም ሰይጣን … ይፈልጋችኋልና።

ስለዚህ ዘወትር በስሜ ወደ አብ መፀለይ ይኖርባችኋል፤

“እናም በስሜ ትክክል የሆነውን ሀማንኛውንም ነገር በእምነት እናገኛለን በማለት አብን ከጠየቃችሁት፤ እነሆ ለእናንተ ይሰጣችኋልና።”6

ስለጸሎት ምስክሬን ያገኘሁት በ12 አመቴ አካባቢ ነበር። ገንዘብ ለማግኘት ጥረት አድርጌ ነበር፣ እናም አምስት ብር ለማከማቸት ችዬ ነበር። ይህም በጣም ችግር በነበረበት ጊዜ ስለነበረ፣ 5 ብር ለ12 አመት ልጅ በጣም ብዙ ገንዘብ ነበር። ሳንቲሞቼን በሙሉ ለአባቴ ሰጠሁት፣ እና እርሱም አምስት ብር ሰጠኝ። ምንም እንኳን ከእነዚህ አመታት በኋላ ምን እንደነበረ ባላስታውስም፣ በአምስት ብሩ ለመግዛት አላማ እንደነበረኝ አውቃለሁ። ለእኔ ገንዘቡ ምን ያህል አስፈላጊ እንደነበረ አስታውሳለሁ።

በእዚያ ጊዜ ልብስ የማጠቢያ መሺን አልነበረንም፣ ስለዚህ እናታችን በየሳምንቱ ልብሶቻችን እንዲታጠቡ ወደ ልብስ ማጠቢያ ትልካቸው ነበር። ከትንሽ ቀናት በኋላ፣ ውሀ ያለበት ይታጠበው ልብስ ወደ ቤታችን ይመለሳል፣ እናም እናታችን ልብሶቹ እንዲደርቁ ትሰቅላቸዋለች።

አምስት ብሬን በሱሪዬ ኪስ አስቀምጬ ነበር። እንደምትገምቱት፣ ገንዘቡ በኪሴ እያለች፣ ሱሪዬ ወደ ልብስ ማጠቢያው ተላከ። ምን እንደደረሰ ሳውቅ፣ በሀሳብ ተሰቃየሁ። ልብስ ከመታጠቡ በፉት ኪሱቹ እንደሚፈተሹ አውቅ ነበር። በዚህ ጊዜ ገንዘበ ካልተገኘ፣ በሚታጠብበት ጊዜ ገንዘቡ እንደሚወድቅ እናም ገንዘቡንም ሰራተኛው አግኝቶት ለመመለስ ፍላጎት የሚኖረ ቢሆንም ለማን ለመመለስ በማያውቀው የእራሱ እንደሚደረግ አውቅ ነበር። አምስት ብሬን መልሼ የማግኘቴ እድል ትንሽ ነበር፣ ይህንም ለእናቴ ገንዘቡን በኪሴ እንደተውኩት ስነግራት አረጋገጠችልኝ።

ያን ገንዘብ ፈልጌ ነበር፣ ያን ገንዘብ አስፍለጎኝም ነበር፤ ያን ገንዘብ ለማግኘት በሀይል ሰርቼ ነበር። ለማድረግ የምችለው አንድ ነገር ብቻ እንደሆነ አወቅኩኝ። በጭንቀት ወደሰማይ አባቴ ተመልስኩኝ፣ እናም ልብሳችን እስከሚመለስ ድረስ ገንዘቤን እንዲጠብቅልኝ ለመንኩት።

ከሁለት ቀናት በኋላ፣ የታጠበው ልብሳችን የሚመለስበት ቀን እንደቀረበ ሳውቅ፣ በመስኮት አጠገብ ቆሜ ጠበቅኩኝ። መኪናው ሲቆም፣ ልቤ በፍጥነት እየመታ ነበር። ልብሱ በቤት ሲደርስ፣ ሱሪዬን መንጭቄ አነሳሁትና ወደ መኝታ ቤቴ ረጥኩኝ። እጄ እየተንቀጠቀጠ ኪሴን ፈተሽሙት። ወዲያው ምንም ሳላገኝ ስቀር ጊዜ፣ ሁሉም የጠፋ መሰለኝ። ከእዚያም ጣቶቼ ውሀ ያዘለ አምስት ብርን ነኩ። ከኪሴ ሳወጣት፣ ሰላምታ ተሰማኝ። ለሰማይ አባቴ በልብ የተሰማኝን ምስጋና አቀረብኩለት፣ ምክንያቱም ጸሎቴን እንደመለሰልኝ አውቃለሁና።

ከእዚያ ጊዜ ጀምሮ መቆጠር የማይቻሉ ጸሎቶቼ መልስ አግኝተዋል። ከሰማይ አባቴ ጋር በጸሎት ያልተነጋገርኩበት ቀን የለም። የማከብረው ግንኙነት ነው፣ ያለዚያም እጠፋለሁና። ከሰማይ አባታችሁ ጋር እንደዚህ አይነት ግንኙነት ከሌላችሁ፣ ለዚህ አላማ እንድትጥሩ እገፋፋችኋለሁ። ይህን ስታደርጉ፣ በምድር ህይወታችን ጊዜ በመንፈስ ለመዳን የሚያስፈልጉትን ከእርሱ ለሚመጡት መነሳሻዎች እና ለህይወታችሁ መመሪያ መብት ያላችሁ ትሆናላችሁ። እንደ እነዚህ አይነት መነሳሻዎችና መምሪያዎች ከፈለግነው በነጻ የሚሰጠን ስጦታ ነው። እነዚህ ምን አይነት ሀብቶች ናቸው!

የሰማይ አባቴ በማነሳሻው ሲያነጋግረኝ ትህትና እና ምስጋና ይሰማኛል። ይህን ለማወቅ፣ ለማመን፣ እና ለመከተል ተምሬአለሁ። በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት መነሳሻን ተቀብያለሁ። አንዲ እንዲህ አይነት አጋጣሚ ያገኘሁት በነሀሴ 1987 ዓ/ም በፍራንክፈርት ጀርመን ቤተመቅደስ ቅደሳ ጊዜ ነበር። ፕሬዘደንት ቤንሰን ለቅደሳው የመጀመሪያ አንድ ወይም ኈት ቀን ከቆዩ በኋላ ወደ ቤት ተመለሱ፣ ስለዚህ የሚቀሩትን ስብሰባዎች የመምራት ሀላፊነት የእኔ ሆነ።

በቅዳሜ በፍራንክፈርት ቤተመቅደስ ዲስትሪክት ውስጥ ለሚገኙት ለደች አባላቶቻችን ስብሰባ ነበረን። በኔዘርላንድ ውስጥ ከሚኖሩት ከአንዱ ጥሩ መሪ ከሆኑት ከወንድም ፒተር ሞሪክ ጋር እተዋወቅ ነበር። ከስብሰባው በፊት ወንድም ሞሪክ እንድጠራውና ከደች አባላት ጋር እንዲነጋገር እንዳደርግና እርሱም የመጀመሪያው ተናጋሪ እንዲሆን የሚያነሳሳ ስሜታ ተሰማኝ። በቤተመቅደስ ውስጥ እርሱን ስላላየሁ፣ የክልል ፕሬዘደንት የነበረውን ሽማግሌ ካርሎስ ኢ አሴይን ፒተር ሞሪክ በስብሰባው ውስጥ እንደሚገኝ ጠየኩት። ተነስቼ ስብሰባውን ከመጀመሬ በፊት፣ ሽማግሌ አሴይ ወንድም ሞሪክ በስብሰባው እንዳልነበረ፣ በሌላ ቦታ እንዳለና፣ በሚቀጥለው ስብሰባ ለመሳተፍ አላማ እንዳለው መልእክት ሰጠኝ።

ሰዎችን ሰላምታ ለመስጠት እና የፕሮግራሙን ዝርዝር ለመንገር ወደ መስበኪያው ስሄድ፣ ፒተር ሞሪክስ እንደ መጀመሪያው ተናጋሪ እንዳስተዋውቅ የማይሳሳት የመነሳሻ ስሜት ተሰማኝ። ይህም ከማውቀው ሁሉ ልዩ ነበር፣ ምክንያቱም ሽማግሌ አሴይ ወንድም ሞሪክ በቤተመቅደስ ውስጥ እንዳልነበረ ነግሮኛልና። የተነሳሳሁበትን ሴታ በማመን፣ የዘማሪዎቹን መዝሙር፣ ጸሎቱን፣ እና ከዚያም የመጀመሪያው ተናጋሪ ወንድም ፒተር ሞሪክ እንደሚሆን አስተዋወቅኩኝ።

ወደ መቀመጫዬ ስመለስ፣ ወደ ሽማግሌ አሴይ ተመለከትኩኝ እናም በፊቱም ድንጋጤን ተመለከትኩኝ። በኋላም ወንድም ሞሪክን እንደ መጀመሪያ ተናጋሪ ሳስተዋውቅ ጆሮዎቹን እንዳላመነ ነገረኝ። መልእክቱን እንደተቀበልኩኝና እንዳነበብኩት እንዳወቀና፣ እርሱ በቤተመቅደስ ውስጥ እንደሌለ እያወቅኩኝ ለምን ወንድም ሞሪክ የመጀመሪያ ተናጋሪ እንደሚሆን እንዳስተዋወቅኩኝ እንዳልገባው ነገረኝ።

ይህ በሚደረግበት ጊዜ፣ ፒተርሞሪክ በፖርትስታርስ አካባቢ በስብሰባ ውስጥ ነበር። ስብሰባው ሲቀጥል፣ ወደ ሽማግሌ ሀክ ዞር ብሎ “ወደ ቤተመቅደሱ እንዴት በፍጥነት ልታደርሰኝ ትችላለህ?” ብሎ ጠየቀ።

በስፖርት መኪናው በፍጥነት እንደሚነዳ የሚታወቀው ሽማግሌ ሀክም “በ10 ደቂቃ ላደርስህ እችላለሁ! ነገር ግን ወደ ቤተመቅደስ ለምን መሄድ ትፈልጋለህ?” ብሎ መለሰለት።

ወንድም ሞሪክ ለምን ወደ ቤተመቅደሱ ለመሄድ እንዳለበት እንደማያውቅ፣ ግን እዚያ መሄድ እንዳለበት እንደሚያውቅ ነገረው። ወዲያው ሁለቱም ወደ ቤተመቅደስ ሄዱ።

ዘማሪዎቹ እየዘመሩ እያሉ፣ ፒተር ሞሪክን አየዋለሁ በማለት በማሰብ ዞር እል ነበር። አላየሁትም። በሚያስደንቅ ነገር ግን፣ አልፈራሁን ነበር። ሁሉም ደህና እንደሚሆን የማልክደው ማረጋገጫ ይሰማኝ ነበር።

ወንድም ሞሪክ አሁንም ለምን እዚህ እንዳለ ሳያውቅ የመጀመሪያው ጸሎት ሲፈጸም በቤተመቅደሱ በር ገባ። በፍጥነት ሲሄድም፣ “አሁን የወንድም ሞሪክ ንግግርን እናዳምጣለን” ብዬ ሳስተዋውቅ ሰማኝ።

ሽማግሌ አሴይን በማስደነቅ፣ ፒተር ሞሪክ ወዲያው ወደ ክፍሉ ገባና በመስበኪያው ፊት ቆመ።

ከስብሰባው በኋላ፣ ወንድም ሞሪክ እና እኔ ንግግር የማድረግ እድል ከማግኘቱ በፊት ምን እንደደረሰ ተነጋገርን። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለወንድም ፒተር ሞሪክ ስለመጣው መነሳሻ አስቤበታለሁ። ያም አስደናቂ አጋጣሚ እንዲህ አይነት አስፈላጊ መነሳሻ ለመቀበል ብቁ የመሆንና የማመን፣ እናም ሲመጣም የመከተል አስፈላጊነትን ምስክር ሰጥቶኛል። ጌታ በፍራንክፈርት ቤተመቅደስ ቅደሳ ውስጥ የነበሩት የአገልጋዩን የወንድም ፒተር ሞሪክ ሀይለኛና ልብን የሚነካ ምስክር እንዲሰሙ እንደፈለገ አውቃለሁ።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ እኛ ወደ እርሱ በምንጸልይበት እና እርሱ በሚያነሳሳን መንገድ ከሰማይ አባታችን ጋር መነጋገራችን የህይወትን ፈተናዎች ለመቋቋም እንድንችል አስፈላጊ ናቸው። ጌታ እንደሚጋብዘን፣ “ወደ እኔ ቅረቡ እና ወደእናንተ እኔም እቀርባለሁ፤ በትጋትም ፈልጉኝ እናም ታገኙኛላችሁ፤ ለምኑ፣ ትቀበላላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።”7ይህን ስናደርግ፣ መንፈሱ “በተቀደሱ ቦታዎች እንድንቆም፣ እናም አንዳንነቃነ” በጻድቅ በጥንካሬና በፅኑነት ለመቆም ፍላጎትና ማበረታቻ እየሰጠን በህይወታችን ይሰማናል።8

አለም በአካባቢያችን እየተቀየረ እያለ እናም የህብረተሰብ ምግባረ ጥሩነት ሲሰባበር ስንመለከት፣ ጌታ ለሚያምኑት የሰጠውን ውድ ቃል ኪዳን እናስታውስ፥ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።”9

እንዴት አስደናቂ የተስፋ ቃል ነው! ይህም በረከታችን ይሁን ብዬ የምጸልየው በጌታችንና በአዳኛችን፣ በኢየሱስ ክርስቶች ስም ነው፣ አሜን።

አትም