2011 (እ.አ.አ)
እርሱ ስለእናተ ያስባል
ኖቬምበር 2011


እርሱ ስለእናተ ያስባል

ጌታ ከአለም በጣም የተለየ መመዘኛ የነፍስን ዋጋ ለመመዘን ይጠቀማል።

አለም ታውቃቸው ከነበሩት ነቢያት ታላቅ የነበረው ሙሴ በነርዖን ሴት ልጅ ነበር ያደገው እናም የህይወቱን የመጀመሪያ 40 አመት በግብጽ ንጉሳዊ ቤት ውስጥ ነበር ያሳለፈው። የጥንት መንግስትን ግርማ እና ታላቅነት ለእራሱ ያውቅ ነበር።

ከአመቶች በኋላም፣ ከታላቋ ግብጽ ድምቀት እና አስደናቂነት በራቀበት በሩቅ ተራራ ላይ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ እናም ሰው ከጓደኛው ጋር እንደሚነጋገረው፣ እርሱም ፊት ለፊት ተነጋገረ።1 በእዚህ ግንኙነት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሙሴን የእጆቹን ስራ አሳየው፣ ስራውንና ግርማውን እንዲመለከትም ፈቀደለት። ራዕዩ ሲያልቅ፣ ሙሴ ለብዙ ሰዓት በምድር ላይ ወደቀ። ጥንካሬው ሲመለስለት፣ በፈርዖን ቤተመንግስት ውስጥ እያለ ያልገባው ነገር ገባው።

እንዲህም አለ፣ “ሰው ምንም እንዳልሆነ አወኩኝ።”2

እኛ ከምናስብበት በታች ነን

ስለሁለንተና በተጨማሪ ስንማር፣ በትንሽም ክፍል ቢሆን፣ ሙሴ ያወቀምን በተጨማሪ ለመገንዘብ እንችላለን። ሁለተና በጣም ትልቅ፣ ሚስጥራዊ፣ እና ግርማዊ ሆኖ የሰው አዕእምሮ ሊገነዘበው አይችልም። .እግዚአብሔርም ለሙሴ፣ “ለመቁጠር የማይቻል አለሞችንም ፈጠርኩኝ” አለው።3 የምሽት ሰማይ ድንቀቶች ስለእዚያ እውነት ምስክር ናቸው።

ባህሮችን እና ክፍለ አህጉሮችን በጭለማ በመሻገር እና ከአውሮፕላኑ መስኮት የሚልዮን ኮኮቦች መጨረሻ የሌለውን ግርማ በአውሮፕላን እየበረርኩኝ በምሄድበት ጊዜ የሚኖረኝ ትንፋሴን የሚያሳጥሩ አይነት ድንቀቶች ጥቂት ነበሩ።

የስነፈለክ መርማሪዎች በሁለንተና ውስጥ ያሉትን ኮኮቦች ለመቁጠር ሞክረዋል። አንድ የሳይንስ ቡድን አጉልቶ በሚያሳይ መነፅር በመጠቀም ለማየት የምንችላቸው ኮኮቦች በአለም ባህር ዳራት እና በባህሮች ውስጥ ከሚገኙት አሸዋዎች በሙሉ ቁጥር በላይ እንደሆኑ ገምተዋል።4

ይህም አዋጅ በጥንት ነቢይ ሔኖክ ከተገለጸው ጋር አንድነት አላቸው፥ “እና የዚህ ምድርን፣ አዎን፣ እንደዚህ አይነት ሚልዮን ምድሮችን፣ ታናሽ መጠንን ሰው ለመቁጠር የሚችሉ ቢሆንም፣ አንተ ለፈጠርካቸው የመቆጠሪያ መጀመሪያም አይሆንም።”5

የእግዚአብሔር ፍጥረት በጣም ብዙ ሆነው፣ ንጉስ ቢንያም ህዝቡን “የእግዚአብሔርን ታላቅነትና የራሳችሁን ከንቱነት እንዲያስታውሱ” መምከሩ የሚያስደንቅ አይደለም።6

እኛ ከምናስበው በላይ ታላቅ ነን

ምንም እንኳን ሰው ምንም ባይሆንም፣ “የነፍሶች ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ” መሆኑን ሳስብበት በድንቀትና በአክብሮት ስሜት እሞላለሁ።7

የሁለንተናን ትልቅነት በመመልከት “ሰው ከፍጥረት ግርማ ጋር ሲመዛዘን ምን ነው?” እንል ይሆናል። እግዚአብሔር እራሱ ሁለንተናን የፈጠረበት ምክንያት እኛ ነን ብሏል! ለእዚህ አስደናቂ ሁለንተና አላማ የሆነው ስራውና ግርማው የሰው ዘርን ከፍ ለማድረግ እና ዘለአለማዊ ለማድረግ ነው።8 በሌላ አባባል፣ የዘለአለም ታላቅነት፣ የሁለንተና እና የጊዜ መጨረሻ የሌላቸው ሚስጥሮች ሁሉ የተገነቡት እንደ እናንተ እና እኔ አይነት ለሆኑት የሰው ዘሮች ጥቅም ነው። የሰማይ አባታችን ሁለንተናን የፈጠረው እንደ ወንድ እና ሴት ልጆቹ ሙሉ ችሎታችንን ለማሟላት እንድንችል ነው።

ይህም ስለሰው የሚያምታታው ነገር ነው፥ ከእግዚአብሔር ጋር ሲመሳሰል፣ ሰው ምንም አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ለእግዚአብሔር ሁሉም ነገሮች ነን። ከዘለአለማ ፍጥረት ጋር ስንመዛዘን ምንም እንመስል ይሆናል፣ ነገር ግን የዘለአለም እሳት በልባችን እየነደደ ነው። በእጃችን አጠገብ ለመገንዘብ የማንችለው ከፍ የምንደረግበት— መጨረሻ የሌለው አለሞች— ቃል ኪዳን አለን። እና እግዚአብሔር ይህን እንድንደርስበት ሊረዳን ይፈልጋል።

የትምቢት ሞኝነት

ታላቁ አታላይ የእግዚአብሔርን ልጆች ለማሰናከል የሚችልበት ከመሳሪያዎቹ ሁሉ በላይ ውጤታማ የሆነው የሰው የሚያምታታ ሁኔታን በስሜት ማነሳሳት እንደሆነ ያውቃል። ለአንዳንዶች ኩራተኛ ስሜታቸውን በማነሳሳት፣ እንዲወጠሩና ስለእራሳቸው አስፈላጊነትና የማይሸነፉ እንደሆኑ እንዲያምኑ ያበረታታቸዋል። ተራ ከሆነው አልፈው እንዳደጉ እና በችሎታ፣ በበኩራት፣ ወይም በማህበራዊ ክብር ምክንያት ከሚከብቧቸው ተራ ነገሮች የተለዩ እንደሆኑ ይነግራቸዋል ስለዚህ እነርሱ በማንም አመራር ስር እንዳልሆኑ እና በሌሎች ሰዎች ችግር ምንም ማሰብ እንደማያስፈልጋቸው ውሳኔ እንዲያደርጉ ይመራቸዋል።

አብርሀም ሊንከን እንዲህ የሚለውን ግጥም ይወዳሉ ተብሎ ነበር፥

አቤቱ ለምን የስጋዊ መንፈስ ይኮራል?

በፍጥነት እንደሚበር ተወርዋሪ ኮኮብ፣ እንደፈጣኝ በራሪ ዳመና፣

የመብረቅ ብልጭታ፣ የማእበል ምታት፣

ሰው ከህይወት አልፎ ወደ መቃብር ለማረፍ ይሄዳል።9

ከዘለአለም ጋር ሲመዛዘን፣ በእዚህ ስጋዊ አለም የእኛ ህይወት በሁለንተና እና በጊዜ “ትንሽ ቅፅበት” ብቻ እንደሆነ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ይገባቸዋል።10 የሰው እውነተኛ ዋጋ አለም በከፍተኛ ክብር ከምትመለከተው ጋር ትንሽ ብቻ የሆነ ግንኙነት እንዳለው ያውቃሉ። የአለም ሙሉ ገንዘቦችን ብታጠራቅም፣ በሰማይ ኢኮኖሚ ዳቦንም ለመግዛት እንደማይችል ያውቃሉ።

“የእግዚአብሔርን መንግስት የሚወርሱት”11 “እንደ ልጅ የዋህ፣ ትሁትና ትዕግስተኛ፣ በፍቅር [የተሞሉት]” ናቸው።12 “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”13 እንደዚህ አይነት ደቀመዛሙርቶች ደግሞም “[እነርሱ] ሰዎችን [በሚያገለግሉበት] ጊዜ እግዚአብሔርን ብቻ እንደሚያገለግሉ]” ይረዳሉ።14

አልተረሳንም

ሰይጣን የሚያታልልበት ሌላ መንገድ ተስፋ በማስቆረጥ ነው። ምን ያህል ዋጋ እንዳለን መጠራጠር እስከምንጀምር ድረስ፣ እኛ ምንም ባለመሆናችን ላይ እንድናተኩር ለማድረግ ይሞክራል። እኛ ማንም ኩረት ሊሰጠን እስከማይቻል ድረስ ትንሽ እንደሆንን፣ በልዩም በእግዚአብሔር እንደተረሳን ይነግረናል።

ትንሽ፣ የተረሱ፣ ወይም ብቸኛ ለሆኑት እርዳታ ሊሆን የሚችል የግል አጋጣሚን ልንገራችሁ።

ከብዙ አመት በፊት፣ በዩናይትድ ስቴትስ የአየር ሀይል ውስጥ የአውሮፕላን ለማብረር ለመሰልጠን ሄድኩኝ። ከቤት የራቅኩኝ፣ በቼኮስሎቫኪያ የተወለድኩ፣ በምስራቅ ጀርመን ያደግኩኝ፣ እና እንግሊዘኛ በችግር የምናገር የምዕራብ ጀርመን ወታደር ነበርኩኝ። በቴክሳስ ወደነበረው የማሰልጠኛ ቦታ ጉዞዬን በግልጽ አስታውሳለሁ። የአሜሪካ የደቡብ የንግግር ዘዬ ባለው ሌላ ተጋዥ አጠገብ በአውሮፕላን ውስጥ ተቀምጬ ነበር። የሚናገራቸውን ቃላት በደንብ ሊገባኝ አላልኩም ነበር። የተማርኩት ቋንቋ ስህተት እንደነበረም ማስብ ጀመርኩኝ። በአውሮፕላን አብራሪ ማሰልጠኛ ከፍተኛ ቦታ ለማግኘት እንግሊዘኛ በሚናገሩበት ከተወለዱ ሰዎች ጋር ለመፎካከር ስላለብኝ እያሰብኩኝ በጣም ፈርቼ ነበር።

ቢግ ስፕሪንግ፣ ቴክሳስ በሚባለው ትንሽ ከተማ ውስጥ ስደርስ፣ በጦር ሰፈር ውስጥ ክፍል ተከራይተው የሚሰበሰቡትን ቁጥራቸው ትንሽ የሆኑትን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቅርንጫፍን ፈልጌ አገኘሁ። አባላት እንደ ቤተክርስቲያኑ ቋሚ መሰብሰቢያ ቦታ የሚያገለግል የስብሰባ ቦታ እየገነቡ ነበሩ። በእነዚያ ጊዜ አባላት አዲስ ህንጻዎችን ለመገንባት አብዛኛውን ስራ እራሳቸው ይሰሩ ነበር።

በየቀኑ በአውሮፕላን አብራሪ ስልጣኔ ተሳተፍኩኝ፣ እስከምችለው ያህል በጣም አጠናሁ እና ከእዚያም የተረፈውን ጊዜዬን አዲሱን የስብሰባ ቤት ለመገንባት በመርዳት አሳለፍኩኝ። በእዚያም ሁለት-በአራት የዳንስ ዘዴ ሳይሆን እንጨት እንደሆነ ተማርኩኝ። ደግሞም ምስማርን ስመጣ ጣቴን የአለመምታት አስፈላጊነትንም ተማርኩኝ።

የስብሰባ ቦታውን በመገንባት በጣም ብዙ ጊዜ በማሳለፌ፣ የአውሮፕላን ማብረር አሰልጣኝ የነበረው የቅርንጫፍ ፕሬዘደንት ምናልባት ተጨማሪ ጊዜ በማጥናት ማሳለፍ እንደሚያስፈልገኝ ያለውን ሀሳብ ነገረኝ።

ጓደኞቼና ሌሎቹ የአውሮፕላን አብራሪዎች ጊዜአቸውን በFor the Strength of Youth ውስጥ ከሚገኙት ጋር የተስማማ ባልሆኑ ድርጊቶች ጊዜአቸን ያሳልፉ ነበር። እኔ የዚህች ትንሽ የቴክሳስ ቅርንጫፍ አባል በመሆን፣ አዲስ የተማርኩትን አናጺነትን በመለማመድ፣ እና በሽማግሌዎች ቡድን እና በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ በማስተማር እንግሊዘኛዬን በማሻሻል እደሰት ነበር።

በእዚያ ጊዜ፣ ብግ ስፕሪንግ ትንሽ፣ ትኩረት የማይሰጠው፣ እና የማይታወቅ ቦታ ነበር። ብዙም ጊዜ ስለእራሴ እንዲህ አይነት፣ እንዲሁም ትንሽ፣ ትኩረት የማይሰጠው፣ እና የማይታወቅ ስሜት ነበረኝ። ይህም ቢሆን፣ ጌታ እንደረሳኝ ወይም ሊያገኘኝ እንደሚችል አንዴም ቢሆን አልተጠራጠርኩም። የት እንደነበርኩኝ፣ በአውሮፕላን አብራሪ ማሰልጠኛ ክፍል ምን ደረጃ ላይ እንዳለሁ፣ ወይም በቤተክርስቲያኗ ምን ጥሪ እንዳለኝ ጌታ ምንም ችግር እንደሌለው አውቅ ነበር። እርሱ የሚያስብበት ቢኖር የምችለውን ያህል እንደማደርግ፣ ልቤ ወደ እርሱ የሚዘነብል እንደሆነ፣ እና በአካባቢዬ ያሉት ለመርዳት ፈቃደኛ እንደሆንኩኝ ነው። የምችለውን ያህል ካደረግኩኝ፣ ሁሉም መልካም እንደሚሆን አውቅ ነበር።

እና ሁሉም መልካም ነበር።15

ጌታ መጀመሪያ ይሆናል

ጌታ ቀናችንን በብይ በተሰራ ቤት ወይም በፈረስ ጋጥ ውስጥ በመስራታችን ላይ ምንም ሀሳብ የለውም። ሁነኢታችን ምንም የሚያሳዝን ቢሆን፣ የት እንዳለን ያውቃል። ልባጀውን ወደ እርሱ የሚያዘነብሉትን በእራሱ መንገድ እና ለእራሱ ቅዱስ አላማ ይጠቀማቸዋል።

ህይወት የነበራቸው ሁሉ ታላቅ ነፍሳት የሆኑት በታሪክ መፅሐፎች ውስጥ የማይገኙ እንደሆኑም ያውቃል። እነርሱን የአዳኝን ምሳሌ የሚከተሉና ህይወታቸውን መላክም በማድረግ የሚያሳልፉ የተባረኩ፣ ትሁት ነፍሶች ናቸው።16

የጓደኛዬ ወላጆች የነበሩ እንደዚህ አይነት ባልና ሚስትም ይህን መሰረታዊ መርህ ለእኔ በምሳሌ አሳይተዋል። ባልየው በዩታ የብረት ፋብሪካ ውስጥ ይሰሩ ነበር። በምሳ ጊዜ ቅዱሳት መጻህፍትን እና የቤተክርስቲያን ገጼቶችን አውጥተው ያነቡ ነበር። ሌሎች ሰራተኞች ይህን ሲመለከቱ፣ ያሳልቁባቸው እና እምነታቸውን ይፈትኑባቸው ነበር። ይህን ሲያደርጉ፣ በደግነት እና በልበ ሙሉነት ያነጋሯቸው ነበር። የእነርሱ ክብር የለሽነት እንዲናደዱ እንዲያደርጋቸው አይፈቅዱም ነበር።

ከአመቶች በኋላ ከሌሎች በላይ አሳላቂ የነበረው በጣም ታመመ። ከመሞቱ በፊት፣ ይህ ትሁት ሰው በስርዓተ ቀብር ጊዜ ንግግር እንዲሰጡ ጠይቃቸው— እርሳቸውም ይህን አደረጉ።

ይህ ታማኝ የቤተክርስቲያኗ አባል በማህበረተሰብ ክብር ወይም ሀብት ብዙ አልነበራቸውም፣ ነገር ግን ተፅዕኖአቸው በሚያውቋቸው ሁሉ ላይ ታላቅ ነበሩ። በበረዶ ምክንያት ለመጓዝ ያልቻለን ሌላ ሰራተኛ በሚረዱበት ጊዜ በነበረ የኢንደስትሪ አደጋ ምክንያት ሞቱ።

ከእዚህ አንድ አመት ውስጥ የእርሳቸው መበለት የአንጎል ቀዶ ጥገና አደረጉ፣ ይህም ለመራመድ እንዳይችሉ አደረጋቸው። ነገር ግን በደንብ ስለሚያዳምጡ ሰዎች እርሳቸውን ለመጎብኘት መምጣትን ይወዱ ነበር። እርሳቸውም ያስታውሱ ነበር። እርሳቸውም ይጨነቁም ነበር። ለመጻፍ ስለማይችሉ፣ የልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ስልክ ቁጥሮች አገመገሙ። በፍቅርም ልደትን እና መታሰቢያ አመታዊ በአልን ያስታውሱ ነበር።

የሚጎበኟቸውም ስለህይወት እና ስለእራሳቸው ጥሩ ስሜት ኖሯቸው ይሄዱ ነበር። የእርሳቸውን ፍቅር ይሰማቸው ነበር። እንደሚያስቡላቸውም ያውቁ ነበር። ቅሬታን አይገልጹም ነበር፣ ነገር ግን ጊዜአቸውን የሌሎችን ህይወቶች በመባረክ ያሳልፉ ነበር። አንድ የእርሳቸው ጓደኛም ይህች ሴት ከምታውቃቸው የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እና ህይወት እውነተኛ ምሳሌ ከሚያሳዩ ሰዎች መካከል አንዷ ነች አሉ።

እነዚህ ባልና ሚስት በእዚህ አለም ውስጥ በጣም አስፈላጊ አይደለንም ለማለት የመጀመሪያ የሚሆኑት ናቸው። ነገር ግን ጌታ የነፍስን ዋጋ ለመመዘን ከአለም በጣም የተለየ መመዘኛ ይጠቀማል። እነዚህ ታማኝ ባልና ሚስት ያውቃል፤ ያፈቅራቸዋልም። ስራቸውም በእርሱ ስላላቸው ጠንካራ እምነት ህያው ምስክር ናቸው።

እርሱ ስለእናንተ ያስባል።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ሰው ከሁለንተና ጋር ሲመዛዘን ምንም አለመሆኑ እውነት ነው። አንዳንዴም ትርጉም የለሽ፣ የማይታይ፣ ብቸኛ፣ ወይም የተረሳን እንደሆንን ይሰማናል። ነገር ግን ሁልጊዜም እርሱ እንደሚያስብባችሁ አስታውሱ። ይህን የምትጠራጠሩ ከሆናችሁ፣ እነዚህን አራት መለኮታዊ መርሆችን አስቡባቸው።

መጀመሪያ፣ እግዚአብሔር ትሁት እና የዋህን ይወዳል፣ እነርሱ “ከሁሉም በላይ የሚበልጡ” ናቸውና።17

ሁለተኛ፣ “ሀየወንጌሉ ሙላት በደካሞች እና በተራ ሰዎች …እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ይታወጅ ዘንድ” ሰጥቷል።18 “የአለም ደካማ ነገሮች ወደፊትም [እንዲመጡ] ብርቱን እና ጠንካራውን [ለመስበር]”19 እና “ብርቱንም ነገር” ለማሳፈር መርጧል።20

ሶስተኛ፣ የትም ብትኖሩ፣ ሁኔታችሁ እንዴት ትሁት ቢኖን፣ ስራችሁ በቂ ያልሆነ ቢሆን፣ ችሎታችሁ የተገደበ ቢሆን፣ መልካችሁ ምንም ቢመስል፣ ወይም የቤተክርስቲያን ጥሪአችሁ ታላቅ ባይሁንም፣ በሰማይ አባታችሁ የማትታዩ አይደላችሁም። ያፈቅራችኋል። ትሁት ልባችሁን እና የፍቅር እና የደግነት ስራችሁን ያውቃል። አብረውም፣ ለዘለአለም የሚቆይ ታማኝነትን እና እምነት ይሰራሉ።

አራተኛ እና በመጨረሻ፣ የምታዩት እና የሚያጋጥማችሁ ለዘላለም እንደዚህ እንዳልሆነ አባካችሁ ተረዱ። ብቸኛነት፣ ሀዘን፣ ህመም፣ ወይም ለዘለአለም የተስፋ መቁረጥ አይሰማችሁም። ከእግዚአብሔር ልባቸውን ወደ እርሱ የሚያዘናብሉን እንደማይረሳና እንደማይተው ታማኝ ቃል ኪዳን ሰጥቶናል።21 በእዚያ እምነት እና ቃል ኪዳን ተስፋ ይኑራችሁ። የሰማይ አባታችሁን ለማፍቀር እና በቃል እና በስራ የእርሱ ደቀ መዛሙርት መሆንን ተማሩ።

ከጸናችሁ፣ በእርሱ ካመናችሁ፣ እና ትእዛዛትንበማክበር ታማኝ ከሆናችሁ፣ አንድ ቀን ለሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ የተገለጹትን ቃል ኪዳኖች ለእራሳችሁ እንደሚያጋጥሟችሁ እርግጠኛ ሁኑ፥ “ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።”22

ወንድሞችና እህቶች፣ በሁለንተና ውስጥ ከሁሉም በላይ ሀይለኛ የሆነው የመንፈሳችሁ አባት ነው። ያውቃችኋል። በፍጹም ፍቅርም ያፈቅራችኋል።

እግዚአብሔር በትንሽ ፕላኔት ላይ ለትንሽ ጊዜ እንደሚር እንደ ሟች ሰው ብቻ አይደለም የሚያየን— የሚመለከትህ እንደ ልጁ ነው። ለመሆን እንደምትችል እና እንደተሰራኸው አይነት ሰው ነው የሚመለከትህ። እርሱ እንደሚያስብባችሁ እንድታውቁም ይፈልጋችኋል።

በእርሱ ሁልጊዜም እምነት ይኑረን፣ እናም የዘለአለም ዋጋችንን እና ችሎታችንን እንድንገነዘብ ህይወታችንን ከእርሱ ጋር አንድ እናድርግ። የሰማይ አባታችን ላዘጋጀልን ውድ በረከቶች ብቁ እንድንሆን የምጸልየው በልጁ፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶች ስም ነው፣ አሜን።

አትም