ወጣቶች
ፍጹም የሆነ የገና ዋዜማ
በልጅነቴ፣ በየአመቱ የሚመጣ እጅግ የሚያረካ ድርጊት ቢኖር የገና ዋዜማ ነበር። ቤተሰቤ እና እኔ ፒዛ እንሰራለን፣ የገና ዘፈን ለመዝፈን እንሄዳለን፣ እና ከዚያም ለገና መለኮታዊ መልእክት እንሰበሰባለን። በሚንቀጠቀጥ አራት ክፍል ያለው መዝሙር እንዘምራለን እናም በተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎችም የገና መዝሙሮችን እንጫወታለን። አባታችንም የደስታ እምባ በሚያመጣብን የገና ሀሳብ ምሽቱን ሁልጊዜ ይፈጽም ነበር ህይወት ከገና ዋዜማ የሚሻል አልነበረም።
በእድሜ ትንሽ ስገፋም፣ እናቴ ኬሊ የምትባለውን ወጣት ጎረቤታችንን መርዳት ጀመረች። እናቷ ፓቲ ወደ ስራ ስትሄድ፣ ኬሊ ከትምህርት ቤት ስትመለስ ወደ እኛ ቤት በየቀኑ መምጣት ጀመረች። ኬሊ ልክ እንደሚጮህ እና እርዳታ እንደሚፈልግ ቡችላ ሁልጊዜ ትከተለኝ ነበር። ፓቲ መጥታ ልጇን ስትወስድ እና ቤቴን እና ቤተሰቤን በሰላም ስትተው ሁልጊዜም እረፍት ያመጣልኝ ነበር።
በአንድ ታህሳስ፣ እናቴ ፓቲን እና ኬሊን የገና ዋዜማን ከእኛ ጋር እኒያሳልፉ ስትጋብዥ በጣም ደንግጬ ነበር። የእኔ የገና ዋዜማ. እናቴ ፈገግ አለች እና “ይህ ምንም ነገርን አይቀይርም” በማለት ማረጋገጫ ሰጠችኝ። ነገር ግን እንዳለችው እንደማይሆን አውቄ ነበር። ፒዛችንን በሙሉ ይበሉብናል። ኬሊ ስንዘምር ትቀልድብናለች። ከሁሉም ይበልጥ መጥፎ ለሆነ የገና ዋዜማ እራሴን አዘጋጀሁ።
ምሽት ሲመጣ፣ ፓቲ እና ኬሊ መጡ፣ እናም እኛም ተነጋገርን እናም ሳቅን እናም ዘመርን። እናቴ ትክክል ነበረች። ይህም ፍጹም ነበር። በእኩል ሌሊት አመሰገኑን እናም በቸልተኝነት ተለያየን። ወደ መኝታ በሞላ ልብ ሄድኩኝ። በእውነት ውድ የሆኑት የገና ስጦታዎች ስንካፈላቸው እንደማይቀንሱ አወቅሁኝ። በምትኩ ስትሰጧቸው ጣፋጭ ያደርጓቸዋል እናም ያበዟቸዋል።